Telegram Group Search
ባለስልጣኑ በዛሬው ዕለት የማዕድ ማጋራት አደረገ፡፡
በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም የነገ ቀን በጋራ አክብረዋል፡፡በዕለቱም በባለስልጣኑ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮች እና በጡረታ ከባለስልጣኑ ለተገለሉ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት ተካሂዷል::
ዕለቱን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በመስጠታችን እናተርፍበታለን በመስጠታችን እንጠቀማለን ከሰጠነው በላይ ይጨመርልናል ያሉ ሲሆን እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳቹህ አደረስን አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የአብሮነት ይሁንልን በማለት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም የነገ ቀን
የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት!!
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ermja.pdf
1.2 MB
በድንገተኛ ኢንስፔክሽን የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃን ይመለከታል፡፡
(መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!
(መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መልካም በዓል!!
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
በምዘና ዘርፍ በመዛኝነት አገልግሎት የሚሰጡ መዛኞች ሕዝቡን በታማኝነት እና በጥሩ ስነ-ምግባር ማገልገል እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡
(መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የቴክኒክና ሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከተለያዩ ኢንደስትሪዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች የምዘና ስነ-ዘዴ ስልጠና ሰጠ፡፡
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የምዘና ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጋትዌች ቱት በስልጠናው ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ባለስልጣኑ በየዓመቱ አዳዲስ መዛኞች በማፍራት እና የመዛኞች ቁጥር በመጨመር ጥራት ያለው ምዘና ለመስጠት እቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በምዘና ሂደት ላይ የመዛኞች ቁጥር ከፍ ማለት የስነ-ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ለይቶ ለማውጣት እና በአግባቡ ምዘናውን የሚያከናውኑትን በምዘናው ስራ ላይ ለማስቀጠል የሚረዳ መሆኑን ገልጸው፤መዛኞች በትእግስት እና ለምዘና የሚመጡትን ተገልጋዩችን በአግባቡ በጥሩ አቀባበል በመቀበል ሊመዝኑ እንደሚገባ አሳውቀዋል፤ እንዲሁም በመዛኝነት የተመለመሉ እጩ መዛኞች ከስልጠናው በኋላ በምዘና ስራው ላይ በተገቢው አገልግሎት መስጠት የሚገባቸው ሲሆን ራሳቸውን ከብልሹ አሠራሮች በማራቅ በአግባቡ የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው አሳውቀዋል፡፡
አቶ አበራ አመንቴ የባለስልጠኑ የቴክኒክና ሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ በበኩላቸው የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአጠቃላይ የትምህርት እና በቴክኒክና ሙያ የምዘና ዘርፍ የተለያዩ አገልግሎት በመስጠት የትምህርት ስልጠና ጥራት እንዲረጋገጥ የሚሰራ ተቋም መሆኑን ጠቁመው፤
በምዘና አገልግሎትም የምዘና ጣቢያ በማዘጋጀት፣የምዘና ቱል/ፈተና በማዘጋጀት እንዲሁም ተመዛኞችን በመመዘን ተገቢውን ምዘና እንዲያገኙ በማድረግ ለኢንዱስትሪው ብቁ የሆነ የሰው ኃይል በማፍራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ እጩ መዛኝ በባለሙያዎች ሲመለመሉ ጥሩ ስራ በመስራት እውቀትን መሰረት በማድረግ ትክክለኛ ፍርድ ይሰጣሉ የሚል አመኔታ ተጥሎባቸው በመሆኑ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም እጩ መዛኞች በተቻለ መጠን ጥሩ እንደሚሰሩ ተስፋ የሚያደርግ ሲሆን በስልጠና እና በልምድ የሚያገኙትን ሙያ በማስመዘን ብቃታቸውን ለማረጋገጥ የሚመጡትን ተመዛኞችን በአግባቡ በመመዘን ስራቸውን በሃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የትምህርት ስልጠና ፖሊሲ፣ ምዘና ቱል/ፈተና እንዴት እንደሚዘጋጅ እንዲሁም ለእጩ መዛኞች አስፈላጊ የሆኑ ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዩች ለአምስት ቀናት በንድፈ ሃሳብና በተግባር ልምምድ የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ 21 እጩ መዛኞች ተሳትፈዋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ባለስልጣኑ የአብሮነት የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት በዓል የሆነውን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
(መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት በዓል የሆነውን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ውይይት አድርገዋል፡፡ስለ በዓላቱ ታሪካዊ ትውፊት መነሻ እና አከባበር ሰነድ የባለስልጣኑ አማካሪ በሆኑት አቶ ሰለሞን አለማየሁ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
አቶ ሰለሞን እንደገለጹት በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃይማኖታዊም ሆኑ ህዝባዊ በዓላት ትውፊታቸው ተጠብቆ ሃገራችንን በአለም አደባባይ በማስጠራት የሃገራችን ታላቅ ኩራት በመሆናቸው በዓላቱ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ባገናዘበ መልኩ በአብሮነት ስሜት ልናከብራቸው ይገባል ብለዋል፡፡ከዚህ ሌላ በዓላቱ በብዙ ህዝብ በአደባባይ የሚከበሩ በመሆናቸው ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲያከበሩ ሁሉም አመራር እና ሰራተኛ የሚጠበቅበትን ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ተሳታፊዎችም በበኩላቸው በዓሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ እና የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
2024/09/30 04:32:23
Back to Top
HTML Embed Code: