Telegram Group & Telegram Channel
ዓርብ ነሐሴ 7/2013 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች
1፤ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል መልሶ ለማደራጀት የገባችውን ወታደራዊ ስምምነት
እንደሰረዘች የፈረንሳዩ ዜና ወኪል የፈረንሳይ ባለሥልጣናትን በምንጭነት ጠቅሶ ዘግቧል።
ፈረንሳይ ወታደራዊ ትብብሯን ባለፈው ወር ያቋረጠችው በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት
ጋር በተያያዘ እንደሆነ መሆኑን ዘገባው ገልጧል። ፈረንሳይ ያቋረጠችው የትብብር
ስምምነት፣ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይልን ለማደራጀት እና ለማዘመን የ100 ሚሊዮን ዶላር ብድር
ለመስጠት ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት በፕሬዚዳንት ማክሮን እና በጠቅላይ ሚንስትር
ዐቢይ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ነው።
2፤ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጀፍሪ ፊልትማን በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ሊሄዱ
እንደሆነ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ፊልትማን
ከዕሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ለ10 ቀናት በሚያደርጉት
ጉብኝት፣ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ልታደርገው በምትችለው አስተዋጽዖ
ዙሪያ ከየሀገራቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ መግለጫው ጠቁሟል። ፊልትማን
በተለይ ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መፍትሄ ለማፈላለግ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ
ያዘዟቸው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እንደሆኑ የፕሬዝዳንቱ ብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን
በትዊተር ገጻቸው ገልጠዋል።
3፤ የሕወሃት ተዋጊዎች የተቆጣጠሯቸውን የአማራ እና አፋር ክልል ቦታዎች እንደማይለቁ
የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከቢቢሲ ሐርድ ቶክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ
ተናግረዋል። የሕወሃት ኃይሎች ለተኩስ አቁም ዝግጁ የሚሆኑት፣ ቢያንስ መንግሥት
ለትግራይ ክልል ያቋረጣቸውን መሠረተ ልማቶች እንደገና ሲያስጀምር እንደሆነ ጌታቸው
ጠቁመዋል። ትግራይን መገንጠል ቀዳሚ የሕወሃት አጀንዳ እንዳልሆነ የገለጡት ጌታቸው፣
የትግራይን ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብቱ ግን እንዲተገበር እናደርጋለን
ብለዋል። ከሳምንት በፊት በአፋር ክልል በበርካታ ተፈናቃዮች ላይ የሕወሃት ተዋጊዎች
ስለፈጸሙት ግድያ ጌታቸው ተጠይቀው፣ ክስተቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል።
ሕወሃት ከአማጺው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ሠራዊት ጋር ወታደራዊ ትብብር መመስረቱንም
ጌታቸው በቃለ ምልልሳቸው አረጋግጠዋል።
4፤ የሕወሃት ተዋጊዎች በአማራ ክልል ከሰሜን ወሎዋ ወልድያ ከተማ ወደ ደቡብ ጎንደሯ
ወረታ ከተማ በሚወስደው መስመር ላይ ሰሞኑን ባካሄዱት ወታደራዊ ዘመቻ አንዳንድ
ከተሞችን እንደተቆጣጠሩ የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሕወሃት ተዋጊዎች ከአማራ
ክልል ታጣቂዎች አስለቅቀናል ያሉት የታች ጋይንት ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ንፋስ
መውጫን፣ የሰሜን ወሎዋን ደብረ ዘቢጥን እና ጨጨሆ የተባሉ ሌሎች ከተሞችን ነው።
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የተጠቀሱት ከተሞች በሕወሃት ተዋጊዎች
ስለመያዛቸው የአማራ ክልል መንግሥት ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ አልሰጠም።
5፤ አፍሪካ ኅብረት ስለ ትግራዩ ጦርነት ዛሬ በኦፊሴላዊ ትዊተር ገጹ ላይ ተለጥፎ የነበረው
መልዕክት የኅብረቱን አቋም የማይወክል በመሆኑ ባስቸኳይ ማንሳቱን ኅብረቱ በትዊተር ገጹ
አስታውቋል። በኅብረቱ ኦፊሴላዊ ትዊተር ገጽ ላይ የወጣው መልዕክት፣ አሜሪካ
ከአፍጋኒስታኑ ታሊባን ጋር እንደተደራደረችው የኢትዮጵያ መንግሥትም ከአሸባሪው ሕወሃት
ጋር ይደራደር ማለት ከሆነ ያ ፈጽሞ አይደረግም የሚል ይዘት ያለው ነበር። የኅብረቱን
የሠራተኛ ስነ ምግባር ደንብ በጣሰ መልኩ የግል አስተያየቱን በኅብረቱ ትዊተር ገጽ ላይ
የጻፈው አንድ የኅብረቱ ባልደረባ ያለው ድርጅቱ፣ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ገልጧል።
6፤ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በትግራይ ክልል ከሚገኙት መቀሌ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ እና
ራያ ዩኒቨርስቲዎች ከ10 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎችን ወደ ቀያቸው መመለሱን የሳይንስና
ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ዛሬ በድረገጹ
ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። ከአክሱም እና አዲግራት ዩኒቨርስቲዎች ዘንድሮ
ለመመረቅ አንዳንድ ትምህርቶች የቀሯቸው ተማሪዎች ወደፊት ትምህርቶቹን
የሚያጠናቅቁበትን መርሃ ግብር በሂደት አሳውቃለሁ- ብሏል ሚንስቴሩ። የሁሉም ተቋማት
ተማሪዎች የክረምት ዕረፍት በጸጥታ ችግር ሳቢያ ላንድ ወር በመዘግየቱ የዕረፍት ጊዜው
እንደሚያራዝም ሚንስቴሩ አክሎ ገልጧል።
7፤ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር የሚወስደው ዋናው የእስፓልት መንገድ ዓባይ በረሃ ላይ
የመሬት መንሸራተት በመከሰቱ የየብስ መጓጓዣ እንደተቋረጠ የኢትዮጵያ መንገዶች
ባለሥልጣን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ትናንት ሌሊት የድንጋይ ናዳ መንገዱ ላይ
የተከሰተው ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ የተባለ ቦታ ላይ መሆኑን የገለጠው ባለሥልጣኑ፣ መንገዱን
በአስቸኳይ የሚጠግን ግብረ ኃይል ወደ ሥፍራው ተንቀሳቅሷል ብሏል።
8፤ ዓለማቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ከወራት በፊት በትግራይ ክልል በሦስት
ሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመው ግድያ እንዲጣራለት በትዊተር ገጹ ባሰፈረው ጥሪ በድጋሚ
ጠይቋል። እስካሁን የሦስቱ ባልደረቦቹን ገዳዮች ማንነት እንደማያውቅ የገለጠው ቡድኑ፣
በወቅቱ በትግራይ ክልል የነበሩ ሁሉም የግጭቱ አካላት ግድያውን ለማጣራት እንዲተባበሩ
ጥሪ አድርጓል። ሰላም ሚንስቴር ግድያውን እና የገዳዮቹን ማንነት ለማጣራት እያደረገው
ያለውን ምርመራ እንደሚያደንቅ ቡድኑ አክሎ ገልጧል።
@ETH724
@ETH724

group-telegram.com/ETH724/2
Create:
Last Update:

BY ኢትዮ 7/24 መረጃ

Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260

Share with your friend now:
group-telegram.com/ETH724/2

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

At its heart, Telegram is little more than a messaging app like WhatsApp or Signal. But it also offers open channels that enable a single user, or a group of users, to communicate with large numbers in a method similar to a Twitter account. This has proven to be both a blessing and a curse for Telegram and its users, since these channels can be used for both good and ill. Right now, as Wired reports, the app is a key way for Ukrainians to receive updates from the government during the invasion. The regulator said it had received information that messages containing stock tips and other investment advice with respect to selected listed companies are being widely circulated through websites and social media platforms such as Telegram, Facebook, WhatsApp and Instagram. Pavel Durov, Telegram's CEO, is known as "the Russian Mark Zuckerberg," for co-founding VKontakte, which is Russian for "in touch," a Facebook imitator that became the country's most popular social networking site. In 2014, Pavel Durov fled the country after allies of the Kremlin took control of the social networking site most know just as VK. Russia's intelligence agency had asked Durov to turn over the data of anti-Kremlin protesters. Durov refused to do so. "He has kind of an old-school cyber-libertarian world view where technology is there to set you free," Maréchal said.
from us

Telegram ኢትዮ 7/24 መረጃ
FROM American