Telegram Group Search
ዓርብ ነሐሴ 7/2013 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች
1፤ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል መልሶ ለማደራጀት የገባችውን ወታደራዊ ስምምነት
እንደሰረዘች የፈረንሳዩ ዜና ወኪል የፈረንሳይ ባለሥልጣናትን በምንጭነት ጠቅሶ ዘግቧል።
ፈረንሳይ ወታደራዊ ትብብሯን ባለፈው ወር ያቋረጠችው በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት
ጋር በተያያዘ እንደሆነ መሆኑን ዘገባው ገልጧል። ፈረንሳይ ያቋረጠችው የትብብር
ስምምነት፣ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይልን ለማደራጀት እና ለማዘመን የ100 ሚሊዮን ዶላር ብድር
ለመስጠት ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት በፕሬዚዳንት ማክሮን እና በጠቅላይ ሚንስትር
ዐቢይ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ነው።
2፤ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጀፍሪ ፊልትማን በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ሊሄዱ
እንደሆነ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ፊልትማን
ከዕሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ለ10 ቀናት በሚያደርጉት
ጉብኝት፣ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ልታደርገው በምትችለው አስተዋጽዖ
ዙሪያ ከየሀገራቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ መግለጫው ጠቁሟል። ፊልትማን
በተለይ ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መፍትሄ ለማፈላለግ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ
ያዘዟቸው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እንደሆኑ የፕሬዝዳንቱ ብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን
በትዊተር ገጻቸው ገልጠዋል።
3፤ የሕወሃት ተዋጊዎች የተቆጣጠሯቸውን የአማራ እና አፋር ክልል ቦታዎች እንደማይለቁ
የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከቢቢሲ ሐርድ ቶክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ
ተናግረዋል። የሕወሃት ኃይሎች ለተኩስ አቁም ዝግጁ የሚሆኑት፣ ቢያንስ መንግሥት
ለትግራይ ክልል ያቋረጣቸውን መሠረተ ልማቶች እንደገና ሲያስጀምር እንደሆነ ጌታቸው
ጠቁመዋል። ትግራይን መገንጠል ቀዳሚ የሕወሃት አጀንዳ እንዳልሆነ የገለጡት ጌታቸው፣
የትግራይን ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብቱ ግን እንዲተገበር እናደርጋለን
ብለዋል። ከሳምንት በፊት በአፋር ክልል በበርካታ ተፈናቃዮች ላይ የሕወሃት ተዋጊዎች
ስለፈጸሙት ግድያ ጌታቸው ተጠይቀው፣ ክስተቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል።
ሕወሃት ከአማጺው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ሠራዊት ጋር ወታደራዊ ትብብር መመስረቱንም
ጌታቸው በቃለ ምልልሳቸው አረጋግጠዋል።
4፤ የሕወሃት ተዋጊዎች በአማራ ክልል ከሰሜን ወሎዋ ወልድያ ከተማ ወደ ደቡብ ጎንደሯ
ወረታ ከተማ በሚወስደው መስመር ላይ ሰሞኑን ባካሄዱት ወታደራዊ ዘመቻ አንዳንድ
ከተሞችን እንደተቆጣጠሩ የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሕወሃት ተዋጊዎች ከአማራ
ክልል ታጣቂዎች አስለቅቀናል ያሉት የታች ጋይንት ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ንፋስ
መውጫን፣ የሰሜን ወሎዋን ደብረ ዘቢጥን እና ጨጨሆ የተባሉ ሌሎች ከተሞችን ነው።
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የተጠቀሱት ከተሞች በሕወሃት ተዋጊዎች
ስለመያዛቸው የአማራ ክልል መንግሥት ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ አልሰጠም።
5፤ አፍሪካ ኅብረት ስለ ትግራዩ ጦርነት ዛሬ በኦፊሴላዊ ትዊተር ገጹ ላይ ተለጥፎ የነበረው
መልዕክት የኅብረቱን አቋም የማይወክል በመሆኑ ባስቸኳይ ማንሳቱን ኅብረቱ በትዊተር ገጹ
አስታውቋል። በኅብረቱ ኦፊሴላዊ ትዊተር ገጽ ላይ የወጣው መልዕክት፣ አሜሪካ
ከአፍጋኒስታኑ ታሊባን ጋር እንደተደራደረችው የኢትዮጵያ መንግሥትም ከአሸባሪው ሕወሃት
ጋር ይደራደር ማለት ከሆነ ያ ፈጽሞ አይደረግም የሚል ይዘት ያለው ነበር። የኅብረቱን
የሠራተኛ ስነ ምግባር ደንብ በጣሰ መልኩ የግል አስተያየቱን በኅብረቱ ትዊተር ገጽ ላይ
የጻፈው አንድ የኅብረቱ ባልደረባ ያለው ድርጅቱ፣ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ገልጧል።
6፤ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በትግራይ ክልል ከሚገኙት መቀሌ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ እና
ራያ ዩኒቨርስቲዎች ከ10 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎችን ወደ ቀያቸው መመለሱን የሳይንስና
ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ዛሬ በድረገጹ
ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። ከአክሱም እና አዲግራት ዩኒቨርስቲዎች ዘንድሮ
ለመመረቅ አንዳንድ ትምህርቶች የቀሯቸው ተማሪዎች ወደፊት ትምህርቶቹን
የሚያጠናቅቁበትን መርሃ ግብር በሂደት አሳውቃለሁ- ብሏል ሚንስቴሩ። የሁሉም ተቋማት
ተማሪዎች የክረምት ዕረፍት በጸጥታ ችግር ሳቢያ ላንድ ወር በመዘግየቱ የዕረፍት ጊዜው
እንደሚያራዝም ሚንስቴሩ አክሎ ገልጧል።
7፤ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር የሚወስደው ዋናው የእስፓልት መንገድ ዓባይ በረሃ ላይ
የመሬት መንሸራተት በመከሰቱ የየብስ መጓጓዣ እንደተቋረጠ የኢትዮጵያ መንገዶች
ባለሥልጣን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ትናንት ሌሊት የድንጋይ ናዳ መንገዱ ላይ
የተከሰተው ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ የተባለ ቦታ ላይ መሆኑን የገለጠው ባለሥልጣኑ፣ መንገዱን
በአስቸኳይ የሚጠግን ግብረ ኃይል ወደ ሥፍራው ተንቀሳቅሷል ብሏል።
8፤ ዓለማቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ከወራት በፊት በትግራይ ክልል በሦስት
ሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመው ግድያ እንዲጣራለት በትዊተር ገጹ ባሰፈረው ጥሪ በድጋሚ
ጠይቋል። እስካሁን የሦስቱ ባልደረቦቹን ገዳዮች ማንነት እንደማያውቅ የገለጠው ቡድኑ፣
በወቅቱ በትግራይ ክልል የነበሩ ሁሉም የግጭቱ አካላት ግድያውን ለማጣራት እንዲተባበሩ
ጥሪ አድርጓል። ሰላም ሚንስቴር ግድያውን እና የገዳዮቹን ማንነት ለማጣራት እያደረገው
ያለውን ምርመራ እንደሚያደንቅ ቡድኑ አክሎ ገልጧል።
@ETH724
@ETH724
በመቀሌ ለአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎችን ሲመለምል የነበረ ከፍተኛ አመራር ተገደለ

#Ethiopia : ከትግራይ እናቶች ህፃናትንና ወጣቶችን እየነጠቀና እያስገደደ በመመልመል ለአሸባሪው ህወሓት በታጣቂነት በማሳለፍ ለአስከፊ ስቃይና ሞት ሲዳርግ በነበረው ገ/ዮሃንስ የተባለ የሽብርተኛው ህዋሃት ከፍተኛ አመራር ላይ ትናንት ምሽት 3 ሰአት በመቀሌ ከተማ ደብሪ ተብሎ በሚጠራው ክፍለ ከተማ እንደተገደለ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች ገለጹ፡፡

ገ/ዩሐንስ የተባለው አሸባሪ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በመቀሌ ከተማ ደብሪ ከተባለው ክፍለ ከተማ እድሜአቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትንና ታዳጊዎችን ሽብርተኛው ህወሃት አሁን ላይ “የህዝብ ማዕበል ማሰለፍ” በሚል እየፈፀመ ላለው የወረራ እስትራቴጂ ማሳኪያ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀሰ የነበረ
መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የእነዚህ ህፃናትና ታዳጊ ቤተሰቦች ልጆቻችን የትደረሱ? በሚል በተደጋጋሚ ሲያነሱለት ለነበረው ጥያቄ ገና እናንተም ትሄዳላችሁ በሚል ትዕቢት ሲያሸማቅቃቸውና ሲዘልፋቸው ስለነበር የአካባቢው ማህበረሰብና ወጣቶች ዓላማ ለሌለው ነገር አንዘምትም በሚል ፊትለፊት ምላሻ ይሰጡት እንደነበርና ይህን ተከትሎም በግለሰቡ ላይ ግድያው መፈፀሙን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

በትግራይ ክልል ወላጆች ልጆቻችን አንሰጥም በሚል እምቢተኝነታቸውን በተግባር ጭምር ማሳየት
እንደጀመሩና አሁንም ልጆቻቸው በህይወት መኖር አለመኖራቸው እንቆቅልሽ እንደሆነባቸውና
የሚመለከተው አካል መልስ እንዲሰጠን እንፈልጋለን በሚል በግልፅ ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸውን
ምንጮቻችን ከስፍራው አሳውቀዋል።
@ETH724
@ETH724
ሰበር ዜና‼️

#Ethiopia : የምስራቅ ዕዝ 33ኛው ጋሻ ክፍለ-ጦር አምባላጌን እና ማይጨውን በቆረጣ በቁጥጥር ስር አድርጓል። የመቀሌን መንገድ በመዝጋት ወደ ኮረም አላማጣ ወልድያ እና ቆቦ በባዶ ሜዳ የሮጠውን የአሸባሪውን የህወሓት ኃይል ርዝራዥምንም ከጀርባ ቆርጦ አስቀርቶታል
@ETH724
@ETH724
ዜና ከ አፋር
#Ethiopia : ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በአፋር በኩል በያሎ ወረዳ በተደጋጋሚ
ሲዋጋ የነበረውን የጁንታውን ሀይል ቆርጦ የራያ አዘቦን ድንበር በጁ አስገቡቷል

Soure 👇👇
Afarovich Mohammed
@ETH724
@ETH724
የድል መረጃ

የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውሃ አካባቢ ተደመሰሰ- የመከላከያ ሰራዊት

በከሃዲው በቀድሞው የ31ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውሃ አካባቢ መደምሰሱን የመከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡ በዚህ ውጊያ ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሊደመሰስ ችሏል ፡፡
መረጃ ከ ፋና ቲቪ ነው
@ETH724
@ETH724
Channel photo updated
ቀናችሁ የሰላም የይሁን ፡ ሀገራችንም ፈተናዋን የምትጨርሰበት ይሁን ፡ የዛሬውን ቀን በተከታዩ አባባል ጀመረ ፡፡
@ETH724
@ETH724
ዜና ስፖርት

👉ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ጨዋታዎች

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ

08:30 | ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሊድስ
11:00 | ብርንሌይ ከ ብራይቶን
11:00 | ቼልሲ ከ ክርስታል ፓላስ
11:00 | ኤቨርተን ከ ሳውዛፕተን
11:00 | ሌስተር ሲቲ ከ ዎልቭስ
11:00 | ዋትፎርድ ከ አስቶን ቪላ
01:30 | ኖርዊች ከ ሊቨርፑል

🇫🇷 በፈረንሳይ ሊግ 1

12:00 | ሊል ከ ኒስ
04:00 | ፒኤስጂ ከ ስትራርቡርግ

🇪🇸በስፔን ላሊጋ

02:30 | ካርዲዝ ከ ሌቫንቴ
02:30 | ማሎርካ ከ ሪያል ቤቲስ
05:00 | አላቬስ ከ ሪያል ማድሪድ
05:00 | ኦሳሱና ከ ኢስፓኞል

🇩🇪 በጀርመን ቡንደስሊጋ

10:30 | አርሜኒያ ቢልፊልድ ከ ፍራይቡርግ
10:30 | ኦግስበርግ ከ ሆፈናየም
10:30 | ስቱትጋርት ከ ግሪሁውታር
10:30 | ዩኒየን በርሊን ከ ባየርን ሊቨርኩሰን
10:30 | ወልፍስበርግ ከ ቦኩም
01:30 | ዶርትመንድ ከ ፍራንክፈርት

@ETH724
@ETH724
ዳግም ያገረሸው የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ

የመቀነስ አዝማሚያ ታይቶበት የነበረው የኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ የስርጭት ሁኔታ በተለይ ከባለፉት 3 ሳምንታት ወዲህ ዳግም እያገረሸ ነው፡፡

የመረጃው ምንጭ ፡የአል አይን
@ETH724
@ETH724
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት 30 ከመቶ በውጪ ሙሁራን 70 ከመቶ ደግሞ በሀገር ውስጥ ሙሁራን ተዘጋጅቷል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት 30 ከመቶ በተለያዩ ሀገራት ሙሁራን 70 ከመቶ ደግሞ በሀገር ውስጥ ሙሁራን ጥራቱ ተረጋገጦ የተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት እንደሆነ ትምህርት ሚኒስተር የስርዓተ ትምሀርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዛፍ አብርሃ ገለጹ።

ከነሀሴ 5-7/2013 ዓ.ም ድረስ በአርባ ምንጭ ማዕከል የመማሪያ ማስተማሪያ መጽሓፍት ዝግጅት ላይ ሲሰጥ በነበረው ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዳይሬክተሯ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአለም አቀፍ ጨረታ የካብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተወዳድሮ በማሸነፍ የአዲሱን ስርዓተ ትምህርት ጥራት ያረጋገጠ ጥናት አካሂዶ ሰነድ ሰጥቶናል ሲሉም ነው በዚህ ወቅት የገለጹት።

ይህ ስርዓተ ትምህርት እንደባለፉት ጊዜያት ቀጥታ ከውጭ ሀገራት የተቀዳ ሳይሆን የሀገር በቀል እውቀቶች አካቶ የተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት ነው ሲሉ ወ/ሮ ዛፍ አብርሃ ጠቅሰዋል።

የደቡብ ክልል ትምሀርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማሄ ቦዳ በበኩላቸው በክልሉ ወደ 7,773 አዘጋጆች ስልጠና መውሰዳቸውንና 2,700 መጽሐፍትም እንደሚዘጋጅ ጠቅሰዋል። አክለውም ክልሉ በርካታ ህብረ ብሔራዊነት ያለበት ክልል በመሆኑ ይህን ታሳብ ባደረገ መልኩ ዝግጅት የሚደረግ ይሆናል ብለዋል።

መረጃው የደቡብ ክልል ት/ቢሮ ነው።

@ETH724
@ETH724
በሱዳን በኩል በመግባት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሽብር ለመፍጠር እና በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ከ170 በላይ ግለሰቦች መደምሰሳቸው ተገለፀ።

ፀረ ሰላም ኃይሎች ናቸው የተባሉት ግለሰቦች መተከል ዞን ጉባ ወረዳ "አልመሃል" አከባቢ ሽብር ለመፍጠር እና በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ለማድረሰ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የክልሉ ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ፥ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የሕወሃት ቡድን ከክልሉ እና ከክልሉ ወጪ ከሚንቀሳቀሱ ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት ለመፍጠር ሲሠራ ቆይቷል ያለ ሲሆን፣ በእነዚህ ኃይሎች ላይ ማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ገልጿል።

እስከ ትላንት ድረስም የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ ከክልሉ የጸጥታ አካላት እንዲሁም በክልሉ ከሚገኙት የደቡብ፣ የጋምቤላ እና የሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃይል አባላት ጋር በመቀናጀት በተወሰደ እርምጃ ከ170 በላይ የሚሆኑ የጸረ ሰላም ኃይሎች ተደምስሰዋል፣ የቆሰሉና የተማረኩም አሉ ብሏል።

እነዚህ ኃይሎች በሱዳን ድንበር በኩል በመግባት በመተከል ዞን የሕዳሴ ግድብ መገኛ ጉባ ወረዳ አልመሃል ቀበሌን እንደ ማዕከል ተጠቅመው ወደ ግድቡ የሚደረገውን የእንቅስቃሴ መስመር በመቁረጥ ሥራውን ለማስተጓጎል አላማ እንደነበራቸውም ተነግሯል።

የህዳሴ ግድብ ሥራውን ከማስጓጎል ባለፈ በክልሉ ሽብር በመፍጠር በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት የማድረስ ዓላማ እንደነበራቸውም እና አልማሃልን ማዕከል በማድረግ ወደ አማራ ክልል ለመንቀሳቀስ ዝግጅት እንደነበራቸው ቢሮው ገልጿል።

በተወሰደው እርምጃ ከተደመሰሱት የጸረ-ሠላም ኃይሎች ናቸው ከተባሉት ግለሰቦች መካከል ከ16 በላይ የሚሆኑት የሕወሃት አባላት መሆናቸውን ቢሮ አሳውቋል።

@ETH724
@ETH724
ዜና ህዳሴ ግድብ

የኳታሩ ሻሂል ሆልዲንግ ግሩፕ ለህዳሴ ግድብ የ10 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ግብፆችን እያነጋገረ ይገኛል!

በቅርብ አመታት ኳታር ላይ ዘርፈ ብዙ ማዕቀብ ጥለው ከነበሩ ሀገራት መሀል ግብፅ አንዷ እንደነበረች ይታወሳል፣ ታድያ አሁን ላይ አንድ የኳታር ኩባንያ ለህዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ የግብፅ ሚድያዎችን ጭምር ያነጋገረ ሆኗል፣ ለኢትዮጵያም ጥሩ እድል ተደርጎ ተወስዷል።

የኳታሩ ኩባንያ ደብረ ብርሀን ከተማ ላይ አገልግሎት ላይ የዋሉ ባትሪዎችን ወደ ምርትነት የሚቀይር ፋብሪካ እየገነባ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቦ ነበር።

እንዲህ አይነት የአጋርነት ድጋፎች የጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅምም ስላላቸው በደንብ መጠቀም ይገባል።

Via አልሀራም ኦልላይን
@ETH724
@ETH724
የሱዳን ውሸት ሲጋለጥ

የሱዳን ወታደሮች በቴክኒክ ምክኒያት የወደቀች የራሳቸውን መድሀኒት መርጫ ድሮን
ከወደቀችበት አንስተው የኢትዮጵያ ድሮን መተን ጣልን ብለው ቢቢሲን ጨምሮ አልጀዚራ
ዘግቦት ነበር።
ዛሬ ደሞ የሱዳን አቬሽን ባለስልጣናት የሱዳን ወታደሮች በድንበር አካባቢ መተን ጣልነው
ያሉት ድሮን ንብረትነቱ የተባበሩት መንግስት ድርጅት ሲሆን ለሱዳን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
በስጦታ ተሰቶት
ከክረምቱ ጋር ተያይዞ የሚመጣን ወረርሽኝ ለመቀነስ የሱዳን ጤና ጥበቂ ሚኒስቴ
በየ አመቱ የሚያደርገውን የመድሀኒት እርጭ ዘንድሮም በሰው አልባ አውሮፕላን በመርጭት
ላይ እያለ አንዲት ድሮን በቴክኒክ ምክኒያት ገዳሪፍ ግዛት ውስጥ መውደቋን የአቬሽን
ባለስጣናትና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል። የሱዳን መከላከያ ሀይል የወደቀችን
ድሮን አንስቶ ከኢትዮጵያ ለስለስ የመጣችን ድሮን ደብዳቤ ጣልኩ እያለ ሰበር ዜና ማሶራት
ከጀመረ ሁለተኛ ቀኑ ነው።
ራሳቸው በራሳቸው የሚያጀግኑ ወታደሮች አሁን ምን ሊሉ ይሆን! በራሷ ብልሽ የወደቀችን
ድሮን ከመሬት አንስተው የኢትዮጵያ ነው መተን ጥለነው ነው እያሉ ጀብዳቸውን በሚዲያ
ሲያሶሩት ነበር !

👍ሱሌማን አብደላ እንደተረጎመው ፡፡
@ETH724
@ETH724
የርዋንዳው መሪ እና አርሰናል ሽንፈት

የርዋንዳው ፕሬዝደንት እና የአርሰናል ክለብ ደጋፊ የሆኑት ፖል ካጋሜ የክለቡ የትናንት ሽንፈትን ተከትሎ ትዊተር ላይ ያሰፈሩት የብስጭት ፅሁፍ ብዙ አስተያየትን አስተናግዷል!

አርሰናል በዚህ የውድድር ዘመን ወደ ፕሪምየር ሊግ በተቀላቀለው ብሬንትፎርድ ክለብ በፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ቀን 2 ለምንም ተሸንፎ ነበር። ብሬንትፎርድ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ዘንድሮ የተቀላቀለው ከ74 አመታት በሗላ ነው።

በነገራችን ላይ ርዋንዳ ከአርሰናል እና ሌሎች የአውሮፓ ክለቦች ጋር የማስታወቂያ ስምምነት አላት። የርዋንዳ መንግስት የሀገሪቱን ቱሪዝም ለማሳደግ "Visit Rwanda" የሚል ፅሁፍ የአርሰናል ማልያ ላይ ለማኖር ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ከፍሏል፣ ሰሞኑንም ይህን ውል ያደሰ ሲሆን The East African የተባለው የኬንያ ጋዜጣ ለሚቀጥለው ሁለት አመት ርዋንዳ 100 ሚልዮን ዶላር ትከፍላለች ብሏል።

Via Elias Meseret
@ETH724
@ETH724
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ‼️

ጀግናው አየር ኃይላችን ጎብጎብ እና ሳሊ ላይ የሚዋጋውን አሸባሪ ጁንታ ሙሉ በሙሉ ደምስሶታል
Via natenael mekonene
@ETH724
@ETH724
ቅዳሜ ነሐሴ 8/2013 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች
1፤ የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን ኩባንያ ከሁለተኛው የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ጨረታ
ራሴን አግልያለሁ ማለቱን የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኩባንያው በጨረታው
እንደማይወዳደር የገለጸው፣ በኢትዮጵያ ያለው አሳሳቢ የጸጥታ ሁኔታ ስጋት ስለፈጠረበት እና
ኢትዮ ቴሌኮምና የኬንያው ሳፋሪኮም በያዙት ገበያ ውስጥ ሦስተኛ ተወዳዳሪ ሆኖ መግባት
አዋጭ እንደማይሆን በመጥቀስ ነው። በዚህ ወር ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው
ጨረታ የሞባይል ገንዘብ ግብይት አገልግሎት መስጠትን እንደሚጨምር እና በመጀመሪያው
ዙር ጨረታ ያሸነፈው የኬንያው ሳፋሪኮም በጨረታው እንዲሳተፍ እንደማይፈቀድለት
የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ገልጧል። ኤምቲኤን በመጀመሪያው ተሳትፎ ነበር።
2፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላልተወሰነ ጊዜ መሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶችን
ላለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል። አስተዳደሩ እገዳውን የጣለው፣ አንዳንድ ግለሰቦች
ወቅታዊውን ሀገራዊ ሁኔታ እንደ ጥሩ እድል ወስደው በአቋራጭ ለመክበር ሲሉ ትኩረታቸውን
ወደ ከተማዋ መሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶች በማዞራቸው እንደሆነ የአስተዳደሩ ፕሬስ
ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ገልጧል።
3፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሽብር ዓላማ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ላይ ከትናንት ጀምሮ
ርምጃ እንዲወሰድባቸው ትዕዛዝ እንደተሰጠ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በማኅበራዊ
ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በኃይል ርምጃው በክልሉ ሰፍረው የሚገኙት
የደቡብ፣ ሲዳማ እና ጋምቤላ ልዩ ኃይሎች እንዲሳተፉ ክልሉ ፈቅዷል። በክልሉ በተለይም
በመተከል፣ ካማሺ እና አሶሳ ዞኖች ኦነግ ሸኔ እና የጉሙዝ ታጣቂዎች ለሚፈጽሙት ጥቃት
ጀርባ ሕወሃት እንዳለ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ገልጧል።
4፤ የቱርኩ ፌቱላህ ጉለን ንቅናቄ በአዲስ አበባ ያቋቋማቸው 11 ትምህርት ቤቶች በፍርድ
ቤት ትዕዛዝ "ማሪፍ ፋውንዴሽን" ለተባለ የቱርክ መንግሥታዊ ተቋም ተላልፈው እንደተሰጡ
የቱርኩ አናዶሉ ዜና ወኪል ዘግቧል። ከ2 ሺህ በላይ ተማሪ ያላቸውን ትምህርት ቤቶቹን
ንቅናቄው ቀደም ሲል ጀርመናዊያን ባለሀብቶች ላቋቋሙት የግል ድርጅት ሽጧቸው ነበር።
ጀርመናዊያኑ ባለሃብቶች በሕጋዊ መንገድ የገዟቸውን ትምህርት ቤቶች ሊነጠቁ
እንደማይገባ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። ከ5 ዓመት በፊት
በፕሬዝዳንትነት ጣይብ ኤርዶጋን ላይ መፈንቅለ መንግሥት እንዳቀነባበሩ የሚጠረጠሩት
ቱርካዊው ቱጃር ፌቱላህ ጉለን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ያቋቋሟቸውን
ትምህርት ቤቶች የቱርክ መንግሥት እየወረሰ ያለው፣ የፌቱላህ ጉለን ንቅናቄን በአሸባሪነት
መፈረጁን ተከትሎ ነው።
5፤ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በጸጥታ ችግር ሳቢያ
የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን የአከባቢው ነዋሪዎች እና የአስተዳደር ሃላፊዎች
ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል። ደምቢዶሎ፣ ጊምቢ፣ ነጆ፣ ጊደሚ በተባሉ ከተማዎች
ትራንስፖርት የተስተጓጎለው በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሳቢያ ነው። የኦነግ ሸኔ
ታጣቂዎች በዋና ዋና መንገዶች ላይ ከሹፌሮች መኪና እንደሚቀሙ የተናገሩት የዞኖቹ
አስተዳዳሪዎች፣ የትራንስፖርት መስተጓጎል እንጅ ሙሉ በሙሉ የተዘጋ መንገድ እንደሌለ
ተናግረዋል። ኦነግ ሸኔ በሁለቱ ዞኖች በመንግሥት ወታደሮች ላይ ጥቃት እንደከፈተ ሰሞኑን
ተናግሯል።
6፤ በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረ ማርቆስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት
እላፊ ገደብ እንደጣለ የከተማዋ አስተዳደር በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።
ከጸጥታ ኃይሎች ውጭ በከተማዋ ማንኛውም ሰው እና ተሽከርካሪ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ
ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ እንዳይንቀሳቀስ አስተዳደሩ አግዷል። የሰዓት እላፊ ገደቡ የተጣለው፣
የአማጺው ሕወሃት ሰርጎገቦች ስውር መረብ እየዘረጉ እንደሆነ በመታወቁ እንደሆነ አስተዳደሩ
ገልጧል። ሰዓት እላፊውን የጣሰ ማንኛውም ሰው የጠላት ተባባሪ እንደሆነ ተቆጥሮ ርምጃ
ይወሰድበታል ተብሏል። በክልሉ ቀደም ሲል የባሕርዳር እና ደሴ ከተሞች ከምሽት ጀምሮ
እስከ ንጋት በተሽከርካሪዎች ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ እንደጣሉ ይታወሳል።
7፤ የተቃዋሚው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻር ምክትል ሄነሪ
ኤድዋር በፍቃዳቸው ከአንድነት ሽግግር መንግሥቱ በመልቀቅ በቅርቡ ማቻርን ከተቃወመው
የደቡብ ሱዳን ነጸነት ንቅናቄ ሊቀመንበርነት እና ከፓርቲው ወታደራዊ ክንፍ አዘዥነታቸው
አውርደናቸዋል ላለው የውስጥ ወታደራዊ አንጃ በይፋ ድጋፋቸውን እንደሰጡ ዘ ኢስት
አፍሪካን ጋዜጣ ዘግቧል። የከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አንጃ ማቻርን ከሁሉም ሃላፊነቶች
አንስቻለሁ ያለው፣ ደካማ አመራራቸው የተቃዋሚውን ንቅናቄ ጎድቶታል በማለት ነው። ማቻር
ግን አሁንም የንቅናቄው ሊቀመንበር እንደሆኑ ያስታወቁ ሲሆን፣ የማቻር እና ተቀናቃኞቻቸው
የሥልጣን ሽኩቻ የሀገሪቱን የሽግግር አንድነት መንግሥት እንዳያናጋው ተሰግቷል።


@ETH724
@ETH724
ሰበር መረጃ

ወደ ደቡብ ጎንደር መሳሪያና ገንዘብ በቀይ መስቀል መኪና ጭነው ሰርገው የገቡ የህወሀት
ተላላኪዎች ተደመሰሱ።
በአካባቢው በፀጥታ ስራ ላይ የነበሩ የመረጃ ምንጫችን በደቡብ ጎንደር ዞን ልጫ
በምትባል ከተማ 6 ስናይፐር፡ በርካታ ክላሽንኮፍ መሳሪያና ተተኳሽ ጥይት እንዲሁም
እስከዚህ ሰዓት ያልተቆጠረ ሁለት ኩንታል ብር በቀይ መስቀል መኪና ጭነው ሰርገው የገቡ
የህወሀት ተላላኪዎች አካባቢያቸውን ሲጠብቁ በነበሩ ታጣቂዎች ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት
አካባቢ ተደምሰዋል ብለዋል።
ሰርጎ ገቦቹ አቁሙ ሲባሉ መኪና ለማቆም ፈቃደኛ ባለመሆን ጥሰው ለማምለጥ ሲሞክሩ
እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመረጃ ምንጫችን ገልፀዋል።
ገንዘቡና መሳሪያው ገቢ መደረጉንም ምንጫችን አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጉና ተራራ አካባቢ የነበረው የህወሀት ታጣቂ ቡድን ዛሬ ሙሉ
በሙሉ መደምሰሱንም ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
በዚህም በደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪው በተኩስ ደስታውን ሲገልፅ አምሽቷል።

Via Esat
@ETH724
@ETH724
#Kabul

ጉደኛው የታሊባን ታጣቂዎች ካቡል ደጃፍ ማንኳኳትን ይዘዋል

ለመሆኑን ከሰሞኑ በአፍጋኒስታን ምን ሆነ ? በአጭሩ ...

- "ታሊባን" በአሜሪካ መራሹ ጦር እአአ ጥቅምት 2001 ነው ከስልጣን የወረደው ፤ ቡድኑ ኦሳማ ቢን ላደንን እና ሌሎች መስከረም 11 በአሜሪካ ላይ ከተፈፀመ ጥቃት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች ዒላማ ያደረገ ነበር።

- ታሊባን ከስልጣን የተገፋው አሜሪካ አፍጋኒስታን ላይ ባካሄደችው ወረራ ነው።

- የአሜሪካ እና ኔቶ ጦር ኃይሎች በአፍጋኒስታ ለ20 ዓመታት ያህል ቆይተዋል።

- የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን አፍጋኒስታን የነበሩትን የአሜሪካ ወታደሮች የማወጣት ውሳኔ አሳልፈው ወታደሮቻቸውን አስወጥተዋል።

- 20 ዓመታት በአፍጋኒስታን የነበሩት የአሜሪካ እና ሌሎች ኃይሎች /ኔቶ/ ከአፍጋኒስታን መውጣታቸው ተከትሎ ታሊባን የተለያዩ ከተሞችን ከአሁኑ መንግስት ማስለቀቅ ጀመረ።

- አሜሪካ በአፍጋን ያሉ ዜጎቿን ለማስወጣ 5 ሺህ የሚደርሱ ወታደሮችን ልካ በዛው ያሉ ዜጎቿን፣ በኤምባሲ የሚሰሩ ሰራተኞቿን እያስወጣች ነው።

- በአጭር ጊዜ ውስጥ ታሊባን በርካታ ከተሞችን ወሳኝ መስመሮችን ተቆጣጥሯ ፤ አሁን ደግሞ በመንግስት እጅ በብቸኝነት ቀርታለች የተባለችውን ካቡልን (ዋና ከተማ) ከቧል።

- ካቡል ዙሪያዋ በታሊባን ታጣቂዎች ተከባ ምጥ ላይ ነች። የታሊባን ታጣቂዎች በመዲናዋ መውጪያና መግቢያዎች ላይ ታጣቂዎቻቸው እንዲጠብቁ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

- የአፍጋኒስታን የሃገር ውሰጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይደረጋል ፥ ለሽግግር መንግሥቱም ስልጣን ይሰጣል ብለዋል።

- ታሊባን ካቡልን በኃይል እንደማይወስድ ገልጿል፤ ከመንግስት ጋር ድርድር ላይ መሆኑንም አሳውቋል።

(ከቢቢሲ እና AFP የተውጣጣ)
@ETH724
@ETH724
2025/03/01 10:50:35
Back to Top
HTML Embed Code: