Telegram Group Search
ቁርአን የልብ ወዳጅ
....

ከሰዎች ጋር ያለኽ ቀረቤታ ምንም ቢኾን የኾነ ቀን ያስቀይሙኻል።

ወዳጄ ኹሉም ሰዎች ሊያስደስቱህ አይችሉም።

እንዲያውም አንዳንዶች እንደ ቀጤማ ብትጎዘጎዝላቸው ዓላማቸው አንተን መውቀስ ብቻ ይኾናል።

ነብዩ ሉጥ (ዐለይሂ አሰላም) ያን ያህል የኾነላቸው ሕዝቦቹ በስተመጨረሻ እነዚህ መጥራራት የሚፈልጉ ስዎች ናቸውና አስወጧቸው በሚል ተገፍቷል ፦

قالوا أخرجوهم من قريتكم إنهم أناس يتطهرون

ከሰዎች ደግሞ በአንተ ስኬት ብቻ የሚጠሉኽና በምቀኛ ልቦቻቸው ውስጥ የሚያገኙት አንተን ብቻ የኾኑ አሉ።

ለነዚህ ደግሞ ከምቀኞች ተንኮል ጎህን በሚቀደው አላህ (ጀለት ከላሙሁ) ተጠበቅ፦

قل أعوذ برب الفلق....ومن شر حاسد إذا حسد

ከሰዎች በአንተ ተስፋ መቁረጥ የነርሱ ተስፋ የሚለመልም የሚመስላቸው አሉ።

ምናልባትም ከአንድ ሜዳ ተገናኝታችኹ ከኾነ፣ጨዋታውን ጥለኽ ብትወጣና እነርሱ ብቻ ከሜዳው እንዳሉ ቢነገርላቸዉም ይወዳሉ።

ለነዚህ ሰዎች ደግሞ ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ኸዲርን ፍለጋ ጉዞ በወጣበት የተናገረውና የሰነቀው ብርታት ኃይል ይኹንህ፦

وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِفَتَاهُ لَا أَبْرَحُ حَتَّىٰ أَبْلُغَ مَجْمَعَ الْبَحْرَيْنِ أَوْ أَمْضِيَ حُقُبًا

ሙሳም ለወጣቱ «የሁለቱን ባሕሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምኼድ ድረስ (ከመጓዝ) አልወገድም»

ሕይወት ምነኛ ብትከፋ በቀጣይ ምዕራፏ የተሻለች ናትና የመጨረሻው ፊሽካ እንደተነፋ አታስብ፦


وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ

ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

ወደ የት እንደምትኼድ ጨርሶ ከጠፋኽ ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ከኋላው ፊርዓውን ከነ ጦሩ ከፊት ለፊቱ ደግሞ ባሕሩ ሲያፋጥጠው ያለውን አስታውስ፦


قَالَ كَلَّا ۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ

(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡

ሕመም እያሰቃየኽ ከኾነ አዩብን (ዐለይሂ አሰላም) ከነበረበት ሕመም ያወጣውን አላህ በተስፋ ምሉዕነት ለምን፦


۞ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡


فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَكَشَفْنَا مَا بِهِ مِن ضُرٍّ ۖ وَآتَيْنَاهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَذِكْرَىٰ لِلْعَابِدِينَ

ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን፡፡ ቤተሰቦቹንም ከእነሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው፡፡"

ወዳጄ አላህ ለኛ የሚያስፈለገንን ኹሉ በቁርአን እንደጠቆመን ልብ ይሏል።

ታዲያ ቁርአንን የልባችን ወዳጅ ማድረጉና ሌት ከመዓልት ማንበቡና ማስተንተኑ እንደምን ከበደን??

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
https://vm.tiktok.com/ZMkk81rpR/
ስላሴ በኢስላም (12)
ምክንያት መስጠት
...

አንዳንዶቻችን ዱንያ ላይ ስንኖር ለራሳችን ኹሉንም ዓይነት ምክንያት ሰጥተን ሰዎች ያንን ምክንያት ያልነውን እንዲቀበሉን ስናስገድድ ይታያል።

ለሰዎች ደግሞ በአንጻሩ ምንም ምክንያት ሳንሰጥ መስጠትም ሳንፈልግ በእጃችን የምንቆጣጠራቸው ሮቦቶች እንደኾኑ ኹሉ በምንፈልጋቸው ሜዳ ላይ መገኘት አለባቸው የሚል አጓጉል ትምክኽትም አለን።

ወዳጄ በዚህች ዱንያ ላይ እኮ ኹሉም ማንም የማይሸከምለት የራሱ ጣጣ አለው።

ለመኾኑ እንዴት እንዴት ባስብ ነው የኾነን ሰው በየ አውጫጭኙና እህል በሚወቃበት አውድማ ኹሉ ካላገኘኹኽ የምለው?

ዕውነት ዕውነት እሎታለኹ ወዳጄ የገዛ ልጄም ቢኾን በዚህ ልክ ላሽከርክርኽ ብለው በጄ አይልም!!!

እኛ በፈለግነው ሜዳ የምንጋልበው ሌት ከቀን የገራነው ፈረሳችን ብቻ ነው። እሱም ቢኾን የኾነ ቀን መቆሙ አይቀርም።

ምን መሰሎት ወዳጄ? በዚህች ምድር ላይ እኔ የፈለግኹት ኹሉ ይኹንልኝ የማለት አባዜ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንዱና አደገኛው ምክንያት ግን ራስን እጅግ አግንኖ ማየት ነው።

የሰው ልጅ ከናለበት አሸር ባሸር ስብዕና ጋር በዚህ ልክ የተለጠጠ ራሰ-ቁልልነት በሂደት ሰዉ ኹሉ ዐይንኽን ለዐፈር ብሎ እንዲሸሸ ዐይነተኛ ምክንያት ነውና እነ አያ ነውጤ ይታሰብበት!

ሰዎች ከመሰል አጓጉል መልካም ስራን ከሚያበላሹ ባሕሪያት ለመላቀቅ ኢስላም ተዝኪየቱ አኑፉስ በሚል የሚያስተምረንን እጅግ ጥልቅ የስነ ልቦናና የነፍስ ሕክምናን መለማመድ የግድ ይላቸዋል።

ነገ አላህ ፊት አሸናፊ ኾነው የጀነት ባለቤት የሚኾኑ በተዝኪያ ትምህርት ቤት ውስጥ የተመላለሱና ልቦቻቸውን በሚችሉት ልክ መወልወል የቻሉ ብቻ ናቸው።

يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ

ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡


إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
🔰 እዚህ ቻናል ላይ የተለቀቁ ኦድዮዎች በጥቂቱ። በቀላሉ ለማግኘት 👇 ፅሁፉን ተጭነው መልሱን ያድምጡ። ኦድዮዎቹ አጫጭር ናቸው ፤ ባረከላሁ ፊኩም🔰

ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል አንድ
➸  ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል ሁለት
➸  ኢስላም በቀደምት ነቢያት ተሰብኳል። ክፍል ሶስት
አላህ በነብዩ ዒሳ አንደበት ለምን አሕመድ የሚለውን ስም ተጠቀመ?ክፍል አንድ
አላህ በነብዩ ዒሳ አንደበት ለምን አሕመድ የሚለውን ስም ተጠቀመ? ክፍል ሁለት
ከወገብና ከርግብግቢቶች መካከል ይወጣል ሲል
ጂኖች ነብይ ነበራቸውን?
ከብጤው አንዲት ምዕራፍ አያመጡም
ከብጤው አንድ አያመጡም ክፍል ሁለት
ግምታዊ አገላለፅ በቁርአን
የአላህ ፍላጎት በሰዎች ፍላጎት ላይ.
ከአላህ ውጭ ሌሎች አማልክት ቢኖሩስ?
ኢስላም ዘረኝነትን ያስተምራልን?
የነቢይነት ማህተም ወይስ እጢ
ሐዲሱል ቁድስና ሐዲስ አነበዊ ክፍል አንድ
ሐዲሱል ቁድስና ሐዲስ አነበዊ ክፍል ሁለት
ወሕይ ማለት ምን ማለት ነው?
ኣላህ ወደ መላኢካ ወሕይ እንዴት ነው የሚያደርገው?
እውን አላህ ይረሳልን?
ሰው ሰራሽ ዝናብ
ከአንድ በላይ ማግባት
የዘይነብና የመልእክተኛው ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋብቻ
ነቢያትና ዝሙት በመፅሐፍ ቅዱስ
ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡
በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤
የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከአራት በላይ ማግባትና ከአራት በላይ እንዳታገቡ የሚለው ቁርኣናዊ ሕግ
አጋንንት የሩቅ ምስጢር ያውቃሉን?
በጃሂሊያ አጠራር የታገዘውን የአባትህን…ብላችኹ አነውሩት
ሩህ ፍጡር ነው ወይስ ፈጣ
ወደ ዝንጀሮ፣ከርከሮ ስለተለወጡ ሰዎች
ወደ ግመል አይመለከቱምን እንዴት እንደተፈጠረች
ግመል ከሰይጣን ተፈጥራለች?
ኢስላማዊ የጥቢ ህግጋት
ኣላህ ለምን እኛን መፈተን አስፈለገው?

ይቀጥላል ኢንሻአላህ.......
ቀለበት በየትኛው ጣት ላይ ይጠለቃል?!
.....

نَهَانِي رَسولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عليه وَسَلَّمَ
أَنْ أَتَخَتَّمَ في إصْبَعِي هذِه، أَوْ هذِه، قالَ: فأوْمَأَ إلى الوُسْطَى وَالَّتي تَلِيهَا.

المزيد..
الراوي : علي بن أبي طالب | المحدث : مسلم | المصدر : صحيح مسلم
الصفحة أو الرقم :2095

ዓሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በሚያወራው በዚህ ሐዲስ መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጠቋሚና መሐከለኛው ጣቶች ላይ ቀለበት እንዳላጠልቅ ከለከሉኝ በማለት ተናግሯል።

ምክንያቱን ዐወቅነውም ዐላወቅነውም መልክተኝው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የከለከሉንን መከልከል ግዴታ ነው።

መረጃው ከደረሰን በኋላ ግን እምቢኝ ማለት በአላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ላይ ማመጽ ስለኾነ ወጣቶች ይታሰብበት።

ሴት ልጅ በኹሉም ጣቷ ላይ ቀለበት ማጥለቅ እንደምትችል ይሰመርበት።

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
‏صورة من Eliyah
Eliyah Mahmoud
‏صورة من Eliyah
ዕውቅና በሰለፎች ዘንድ ፈተና ነበር ዛሬ ግን የስኬት መገለጫ ኾነ።

በፈተናና በስኬት መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ። ይህ ልዩነት በሰለፍችና በዛሬው ትውልድ መካከል ያለውን ተጨባጩን የመረዳት አቅም ፍንትው አድረጎ የሚያሳይ ነው።
ከስነ-ልቦና ሰዎች ምክር


ከሰዎች ከአንተ በርካታ እንክብካቤን የሚፈልጉ አሉ፡፡ ኾኖም በተንከባከብካቸው ልክ አንተ ኹሌም ለነርሱ የሚገባውን እንዳላደረክ ስለሚያስቡ ለአንተ ቦታ ሊኖራቸው ይቅርና ይልቁንም አንተ ግዴታኽን እንደተወጣኽ አደርገው ያስቡታል፡፡

እንዚህን ሰዎች ስትሸሻቸው ስለሚፈልጉኽ ሳይኾን እነሱ ከሰዎች ያገኙት የነበረውን አጓጉል ክብርና ቦታ ያጡ ስለሚመስላቸው ብቻ ኪሳራቸው ስለሚያስፈራቸው ይፈልጉኻል፡፡

እነዚህ ሰዎች ከሚገለጡባቸው ምልክቶች አንዱ ትንሽንም ቢኾን መስዋዕትነት ወይም ውለታ መዋል በፍጹም አይፈልጉም፡፡

ቀረብኹት የሚሉት ሰው እጅግ አሳሳቢ ነገር እንኳን ቢያጋጥመው፣ምንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ አይደሉም፡፡

ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? ካሉ አቅም በፈቀደ ልክ ከነዚህ ሰዎች መሸሽ - ይህ ለውስጥ ሰላም ሲባል መወሰድ ያለበት እርምጃ ነው፡፡

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
Eliyah Mahmoud
https://vm.tiktok.com/ZMk5DFVkY/
ወራሪዋ የአይሁድ መንግስት በፍልሥጤም ላይ የጀመረችውን የግፍ ጭፍጨፋ መቀጠል አለባት።


አሻንጉሊት የኾነውን የባይደን መንግሥት መስማት አይገባትም...ወዘተ እያለ በሚገደሉ ፍልስጤማውያን ላይ የውስኪውን ዋንጫ ሲያነሳ የነበረው ጄምስ ውድስ እነሆ ውድ ቤቱ ሎስ አንጀለስ ላይ በተነሳው ሰደድ እሳት ዶጋ አመድ ኾነ።

በዚህ ሰቅጣጭ ክረምት በቅዝቃዜና ርሓብ እያለቁ ባሉ የፍልስጤም ሕጻናት እምባ ላይ የሳቀው ጄምስ በአደባባይ ባንክ ውስጥ ባለኝ ስባሪ ሳንቲም ደግሜ ቤቴን እገነባው ይኾናል ብሎ አንብቷል።


هل الجزاء الاحسان إلا الاحسان


በሙስሊሙ ደም ላይ የተሳለቀ ኹሉ ያለምንም ርሕራሔ በተሳለቀው ልክ፣ባሴረው ልክ አላህ የጥፋቱን መዓት ያውርድበት።

اللهم آمين

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብረሃማዊ ሃይማኖቶች በሚል ሶስቱን ማለትም ኢስላም፣ክርስትናና አይሁድን አጣምረው ኹሉም አንድ አምላክን ይሰብካሉ ስለኾነም አንድ ናቸዉ የሚል ሰበካና ጥምቀት እያየን ነው።

ይህ ሰበካ በየትኛውም ስሌት በአልቦ መረጃ የሚንቀሳቀስ ተራ ወሬ መኾኑ ግልጽ ቢኾንም ከጀርባው ግን ሰዎችን ሃይማኖት የለሽ የማድረግ ዕቅድ እንዳለው ቅቡል ነው።

ዛሬ ላይ ትልልቅ ኡማውን ሊጠቅሙ የሚችሉ ሐሳቦች ፈጽሞ ቦታ አጥተው መሰል የኩፍር አካሄዶች ግን ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው እየተቀጣጠሉ ይገኛሉ።

አንድ ከዐረቦች ጋር ግንኙነት ያለው በትምህርት ደረጃው የዶክትሬት ዲግሪ ያለው ወዳጄ እንዳጫወተኝ በኢብራሂሚያ ዙሪያ የትኛውም ዓይነት ደጋፊ ምክረ-ሐሳብ (ፕሮፖዛል) ካለ በቀላሉ ከዐረቦቹ በጀት ማግኘት እንደሚቻል፣ ከዛ ውጪ ግን ለተለመዱ ዓይነት ዳዕዋዎች የሚበጀት ቀርቶ የሚፈልጋቸውም እንደሌለ አስረግጦ አረዳኝ።

ወዳጄ ዛሬ ላይ ከመቼውም ጊዜ በባሰ መልኩ ኹላችንም በምልዓት ወደ ኢስላማዊ ዕውቀት የምናመጣበት ቤተሰቦቻችንንም ከዛ አኳያ የምንመክርበት ወቅት ነው።

ስንቱ ሚዲያ ላይ በዳዕዋው የምናውቀው በዚህ ኢብራሂሚያ የኩፍር ጥሪ ተሰናክሎ ዛሬ የኢብራሂሚያ ሃዋሪያና ዳዒ ኾኗል!?

اللهم يا مقلب القلوب ثبت قلوبنا على دينك
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
١٥ يناير ٢٠٢٥
https://youtube.com/watch?v=l7-boSsKgIE&feature=shared
በነብዩ ላይ የዋሸው ሰው መጨረሻ
Eliyah Mahmoud
إلى شرف الأمّة .. إلى غزّة https://youtube.com/watch?v=1z4t8MzkyGY&feature=shared
በርካታ በዙሪያቸው ያሉ ሐገራት እንኳ ትተዋቸው የምዕራቡ ነጻ ሕሊና የገዛው ማሕበረሰብ በአደባባይ ስለ ነርሱ ድምጹን ከፍ ሲያደርግ ቆይቶ እነሆ ከዓመት በላይ የቆየው የፍልስጤም የነጻነት ትግል በሰላም ስምምነት ሊቋጭ የተቃረበ ይመስላል።

ብቻቸውን ኹሉንም ነገር ኾነው፥ኹሉንም ዓይነት መከራ አይተው፣በርሃብና ቸነፈር ሕጻናት ሳይቀር አልቀው አኹንም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረና እንዳልኾነባቸው ኹሉ ሰንደቃቸውን ከፍ አድርገው በፍርሃት ለራደውና ተድላ ለገደለው የዐረብ ሕዝብ ምሳሌ የኾኑ ሕዝቦች ናቸው።

አላህ ሰላሙን ያዝልቅላቸው!!!
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ላለፉት ሳምንታት ስላሴ በኢስላም የሚል ርዕስ ይዤ ስላሴን አስመልክቶ በኢስላም ላይ የሚነሱትን ሹብሃዎች ለመዳሰስ ሞክሬአለኹ።

ስትከታተሉኝ የነበራችኹ ያልዳሰስኹት ሐሳብ አለ ብላችኹ ካሰባችኹ ልትጠቁሙኝ ትችላላችኹ።
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
٢٠ يناير ٢٠٢٥
https://youtube.com/watch?v=3wv8CFzh5kc&feature=shared
ነብያት ኃጢያት ይፈጽማሉን?
2025/02/22 17:30:49
Back to Top
HTML Embed Code: