Telegram Group Search
በስመአብ ወወልድ ወመፈሥቅዱሥ አሀዶ አምላክ አሜን!
የእገዛ ጥሪ
በ58 የሚገኘው ቅዱሥ ገብርኤ ቤተክርቲያን ችግር ደርሶበታል ችግሩም ከቤተከርሥቲያኑ ጎን የጴንጤዎች ቸርች ሊሠሩ ነው ሠውም ቤተክርሥቲያን በጠራችው ጥሪ አሠሩም ብሎ ያጠሩትን ቢያፈርሡም ፖሊሶች አባቶቻችንን እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን አስረዋቸዋል እስካሁንም አልተለቀቁም ይሄ ጉዳይ ዝም ሊባል አይገባም ከሀይማኖት በላይ ምንም የለም ሁላችንም ግዴታችንን መወጣት አለብን ቤተክርሥቲያችን ልጆቾ ያሥፈልጎታል እኛም አለንልሽ ልንል ያስፈልጋል ቢያንስ እኮ ሼር እድታረጉ እድታረጉ በልዑል እግዚአብሔር እለምናቹሀለው፡፡
Forwarded from TWICE ART🎨🎨 via @like
ከህሊና ጋር መጋጨት ከምንም በላይ ከባድ ነው!
መጋቢት 1985 ዓም "ኬቨን ካርተር" የተባለ ደቡብ አፍሪካዊ
የፎቶግራፍ ባለሙያ ሱዳን ውስጥ ተከስቶ በነበረው ርሀብ
ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ልኡክ ጋር ለደግነት ወደ ደቡብ
ሱዳን ያመራል ፡፡
በአንዷ መከረኛ እለትም ራሱን ለሞት ያበቃዉን ምስል በካሜራው
አስቀረ፡፡
"ርሀብ አድቅቆት የገዛ ራሱን መሸከም ያቃተው ህፃን ልጅ እና
ይህን ገላ ለመግመጥ የቋመጠ ጥንብ አንሳ"
የረሀብን ክፉ ገፅታ፣ የድርቅን አሰቃቂ ሁነት፣ የምስኪኖችን እልቂት
፣ቃላት ሊገልፁ ከሚችሉበት አቅም በላይ በሆነ መንገድ በድንቅ
ካሜራው ለአለም አስቃኘ።
"ቀጫጫ እጆች፣ እንኳን ለመሮጥ፣ ለመቦረቅ ይቅርና የገዛ አካሉን
ለመሸከም ያዳገተው እግር፣ መቆም የከበደው ገላ እና በርሀብ
በሞቱ ሰዎች የደለበ ፈርጣማ አሞራ።"
ይህን ፎቶ ከወራት በኋላ በ 1985 ዓም ለኒውዮርክ ታይምስ
ጋዜጣ ተሸጦ ታተመ፡፡ ምስሉ በመላው አለም ታየ። ፎቶግራፈሩ
ክብር እና ዝናን አተረፈ፡፡ ተሸለመ፣ ተሞገሰ፤ ዓለም ስለፎቶግራፈሩ
አወራ፡፡
ከዚህ ሽልማት በኃላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአንድ
ጋዜጠኛ የተወረወረች ያልተጠበቀች ጥያቄ ግን የህይወቱን
አቅጣጫ እስከወዲያኛው ቀየረችው፤ አመሳቀለችው፡፡
"ህፃኗ ልጅ እንዴት ሆነች? ታደካት?" አይኖቹ ፈጠጡ፤ ላብ
አጠመቀው፤ ቃላት ከአንደበቱ ጠፋ፡፡
በምናብ ወደ ደቡብ ሱዳንዋ የርሃብ መንደር ተሰደደ፡፡ ጠያቂው
ግን ድጋሚ በጩኸት ጠየቀ "ህፃንዋን ልጅ ታደግካት? ነው
ፎቶዋን ብቻ ነው ይዘኸው የመጣህ?"
ካርተር ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጦ ወጣ፡፡ ከወዳጅ ከዘመድ
ሁሉ ተሰወረ፡፡ ከራሱ ጋር ተጣልቶ ለብቻው ውሳኔ አልባ ዶሴ
ከፈተ፡፡
በገዳይዋ ፊት ጥሏት የሄደው የጎስቋላዋ ህፃን ነፍስ ለወራት
እንቅልፍ ነሳው፡፡
ካርተር ራሱን ወነጀለ፡፡ የፎቶግራፍ ሽልማቱን ባሸነፈ በሦስት ወሩ
በልጅነቱ ሲቦርቅ ባደገባት "ፓርክሞር በተባለች ለምለም መንደር
ሀምሌ/19/1986 በ33 ዓመቱ እራሱን ገድሎ ተገኘ፡፡ ራሱን
የሞት ፍርድ ፈረደበት ፡፡
በሞቱ ዋዜማ ላይ ሆኖ ለወዳጅ ዘመዶቹ ባስቀረው ማስታወሻ
የሚከተለውን ፀፀት አሰፈረ፡፡
"ካለኝ ነገር ቀንሼ አልሰጠሁም፡፡ እኔን ለማኖር ስራየን ብቻ
ሰራሁ፡፡ ሚጡ ከርሀብ ጋር ስትታገል ጥንብ አንሳው በእሷ ጠግቦ
ይሆናል፡፡ ሚጡዋ፣ የአሞራው እራት ስትሆን፣ በሚጡ ርሀብ እኔ
ተሸለምኩ፡፡ ይህም እኔን ሚጡ ወዳለችበት የሞት ጎዳና እንዲሄድ
ፀፀቱ አስገደደኝ፡፡ ደህና ሁኑ ዘመዶቸ፡፡ ሰው ሲራብ፣ ሲቸገር አትዩ፡፡
ካያችሁም ከሌላችሁ ቀንሳችሁም ቢሆን እርዱ፡፡
የህሌና ቁስል መፈወሻ የለውም፡፡ ራሳችሁን ከህሌና ቁስለት
ታደጉ፡፡"
አዎ ሰው ላያይ ይችላል፤ ነገር ግን ሁሌም ቢሆን የማያዳላ ህሊና
የሚባል ዳኛ በሁላችንም አእምሮ ውስጥ አለና አንበድል፤ ክፋ
አንስራ፡፡
የበደልነው ሰው ካለ ይቅርታ እንጠይቅ!
ሳይገባኝ_አጣሁሽ

ፍቅረኛው፡- “ነገን ምንም ሳንገናኝ፣ ሳንጻጻፍና ሳንደዋወል እንውላለን” ይህን ማድረግ ከቻለ ለዘላለም እንደምትወደው ነግራው ይስማማል፡፡ በጊዜው ልጅቷ ለመሞት 24 ሰዓት እንደቀራትና ካንሰር እንዳለባት አላወቀም ነበርና እንደተባለው ምንም ሳያደርግ አድሮ በነጋታው ወደ ቤቷ ይሄዳል። “ፍቅሬ አደረኩት፤ ፈተናውን አለፍኩ” ብሎ ወደክፍሏ ሲገባ በሬሳ ሳጥን ውስጥ ተጋድማ ያያል። አምርሮ እያለቀሰ ከላይ የተቀመጠውን ማስታወሻ አነበበው “የኔ ውድ ያለኔ ለአንድ ቀን መኖር ችለሃል፡፡ እንድትጎዳብኝ ሳላልፈለኩ ነው ይህን ያደረኩት፤ ትላትን እንደቻልከው እባክህን ሁልጊዜ ቻልበት፡፡ እኔን በሞት በማጣትህ እንድትጎዳብኝ አልፈልግም፡፡”

ፍቅር ማለት አብረው እንደማይሆኑ እያወቁ እንኳን ለሚያፈቅሩት ሰው ደስታን መመኘት ነው፡፡

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
🌹 ፍቅር ነው መንገዴ 🌹
ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ
እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ
ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ።
በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን
ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና
ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው
ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም
ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ። በእንግሊዛዊው ድርጊት
በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ
ወለሉ አመራሁ። እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን
ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ
አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው
የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር፦ "ኢትዮጵያዊ_ነህ?" የሚል።
__________
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
Forwarded from TWICE ART🎨🎨 via @like
ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች በረሃ ውስጥ እየተጓዙ እያሉ ድንገት
አለመግባባት ተፈጠረና አንደኛው አንደኛውን በጥፊ ይመታዋል
የተመታው ጥፊው ቢያመውም ምንም ሳይናገር ዝም አለና
አሸዋው ላይ ዛሬ የምወደው ጓደኛየ በጥፊ መታኝ ብሎ ፃፈ ከዛም
እየተጓዙ እያሉ ትልቅ ባህር ያለበት ወንዝ ያገኙና መታጠብ
ፈልገው ይገባሉ እየዋኙ እያሉ ያ በጥፊ የተመታው ልጅ
ይሰምጣል በዚህ ስዓት ጓደኛው እንደምንም ብሎ ሂወቱን
ያተርፈዋል ከሞት የተረፈው ልጅ ቋጥኝ ድንጋይ ፈልጎ ድንጋዩ
ላይ እየፈለፈለ ዛሬ የምወደው ጓደኛዬ ሂወቴን አተረፈኝ ብሎ ፃፈ
ጓደኛውም ገርሞት ቅድም በጥፊ ስመታህ አሸዋ ላይ ፃፍክ አሁን
ከሞት ሳተርፍህ ደግሞ ድንጋይ ላይ ለምን እንደዚህ አደረክ
አለው
ጓደኛውም እንዲህ አለው የምንወዳቸው ሰዎች ሲበድሉን
በደላችንን የይቅርታ እና የምህረት ንፋስ እንዲያጠፋው አሸዋ ላይ
መፃፍ አለብን ጡሩ ነገር ሲያደርጉልን ግን ውለታቸውን እንዳንረሳ
ሁሌም እንድናስታውሰው ድንጋይ ላይ መፃፍ አለብን አለው!
ዝግ ዓለም

ከትራሴ ግድም ፤በተደፋው ሰማይ
ኮከብ እያበራ ፤በመከዳየ ላይ
ምንም አላነበብኩ ፤ከህዋው ግድግዳ
እውነትና ንጋት፤ እያደር እንግዳ፡፡
(ከስብስብ ግጥሞች)
በዕውቀቱ ስዩም
ዛሬ - ነሐሴ 10 - ብላቴን ጌታ ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን የተወለደበት ቀን ነው፤ 1928 ዓ.ም።

ብላቴን ጌታ ፀጋዬ በተወለደበት ዕለት አባቱ ኦቦ ገብረመድኅን ሮባ ቀዌሳ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጎን ተሰልፈው ማይጨው ላይ ከፋሽስት የጣሊያን ጦር ጋር እየተዋጉ ነበር። ኦቦ ገብረመድኅን ሮባ የሜጫ ኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን እናት ወይዘሮ ፈለቀች ዳኜ ኃይሉ ደግሞ የአንኮበር አማራ ተወላጅ።

የኦቦ ገብረመድኅን ሮባን ልጅ - ጸጋየ ገብረመድኅንን - ግዕዝና ዜማ ያስተማሩት፣ ቅኔ ያስቀፀሉት ... የአንኮበር አማራ ተወላጅ የነበሩት የእናቱ ዘመዶች ናቸው። ጸጋየ ለአባቱ ከተማ ለአምቦ፣ ለእናቱ ቅየ ለአንኮበር፣ ለወይጦ ባላገር፣ ለሐረር፣ ለአሥመራ፣ ለማይጨው፣ ለአዘቦ ... በእኩል ስሜት ተቀኝቷል።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን እና ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የተወለዱት በአንድ ቅየ ነው። ከአምቦ ከተማ ሠላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ "ቦዳ" ተብላ በምትጠራ መንደር።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን Pan-Africanist ነው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲቋቋም ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን በሥፍራው ተገኝቶ ታሪካዊ ክስተቱን ተጋርቷል። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መዝሙር የተደረሰውም በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅንና በኬንያዊው የሙዚቃ ሊቅ ዶክተር አርተር ኬሞሊ ነው። የአፍሪካ ህብረት አሁን ድረስ በዚህ መዝሙር ይገለገልበታል። ኬንያ ነጻነቷን ስታውጅ ወደ ኬንያ የተላከው የኢትዮጵያ ልዑክ የተመራው በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን ነበር።

ሎሬት ፀጋዬ "አድባር" በሚል ርዕስ በጻፈው ግጥም እንዲህ ይላል፦

በቄጤማ በለምለም ሣር
አትባራ አድባር
በጤና ዓዳም በጥሞና
የዋርካ አድባር የጀበና፡፡
ከታአካ እስከ ልደታ
ከአስተርዮ እስከ ባዕታ
አድባር አትሆር፣ አድባር አታ፡፡
በግንቦት እለት በዓልሽ ደጃፍሽን ተማፅነናል
ዛፍ ጽላትሽን ቀብተናል
ጠበልሽን ጠጥተናል
ጽዋሽን ግምጃ አልብሰናል፡፡
የአማልክቶች እናት አርማ
የመጀመሪያ ከተማ
የዓለም ሥልጣኔ ማማ፡፡
ልጆችሽ ስለረሳንሽ፣ አንችም መልሰሽ ረሳሽን
እኛ ስለራቅንሽ ራቅሽን
ስለረገምንሽ ረገምሽን፡፡
እማማ አድባር ማን ያስታርቀን?
ከተሰቀልንበት ዕብሪት በትህትና ማ ያውርደን
ርቀታችንን በድልድይ ገንብቶ ማን ያቀራርበን?

ከተሰቀልንበት እብሪት በትህትና የሚያወርደን... ርቀታችንን በድልድይ ገንብቶ የሚያቀራርበን... ይበርክት!

ጽሑፍ :- እሱባለው አማረ ::
እንዴት ናችሁ ቤተሰብ 👇👇👇👇👇ተጋበዙልኝ

ማነው ላገር ያላት አለሁሽ የሚላት
እቅፍ ድግፍ አርጎ የሚንከባከባት።
መዋረድን ጠልቶ ኩራቷን ተጠምቶ
ጥቅሙን ወዲያ ጥሎ ድምጹን አሰምቶ
ህብረትን ሰንቆ ባንድነቱ ፀንቶ
የሚታደግ ማነው? ህይወቱን ሰውቶ ።
ግጥሙ ከተመቻችሁ ሼር አድርጉ መልካም ምሽት። ኅዳር ፳፯ ፳፻፲፫ዓ.ም
Forwarded from TWICE ART🎨🎨 via @like
2025/01/13 05:06:35
Back to Top
HTML Embed Code: