Telegram Group Search
እኔም ያምረኛል!🤭!
ማሰብ ቅንጦት በሆነበት በዚህ በዘመነ ጡዘት የማንንም ሀሳብ ሳይሆን የራሴን ሀሳብ የማስብና ሀሳቤን የምኖር ሰው በመሆኔ ታድዬ!!

"እንዲህም ያምረኛል!!
የእራሴ ቀብር ቀን ጥሩንባ ማሰማት ፣
ለቀስተኛው መሀል አብሮ ደረት መምታት ፣
ማንበብ ህይወት ታሪክ ውሸት የሌለበት ፣
ከድንኳን ውስጥ ቆሜ እድርተኛ መጥራት ፣
በእራሴ ቀብር ላይ እንዲህ ይዳዳኛል ፣
ሞቴን ቆሞ ማየት አለቅጥ ያምረኛል ፣
አልቃሽ አሽሟጣጩን ካልታዘብክ ይለኛል ፣
ያሁኑ በሽታዬ እንዲህ ያሰኘኛል ፣
የማያምር ነገር በድንገት ያምረኛል።"
ደራሲ:-አይታወቅም!!

ተመስገን!!
ዋናው መተንፈስ ነው!!
#EnvironmentFirst
#ሰው_መሆን
#ይራስን_ሀሳብማሰብ
#እራስን_የራስንና_የሌላውንማክበር
#ይሉንታናትሁትነት_ቅንነትናአገልጋይነት
#ብሩህ_ዜጋ

#አጋዥ_እረጂና_ሸክምአቅላይ
#Borderless_Volunteerisም
#UBUNTU*
#ቀርክሀ_ወርቅናሐብት_ነው
#ባሕል_ሀብትና_ቅርስነው
#PanAfricanAID-A Renewed Vision
of Connecting The Dots for Convergence, Collaboration and Global Alliances to Serve Humanity and Mother Earth, Peace & Greening Africa as Our Priority!!
*እኔ ሰው የሆንኩት በናንተ ነውና ህመማችሁና ጭንቀታችሁ ህመሜና ጭንቀቴ እንዲሁም ብትብድሉኝና ብታስከፉኝም ደስታችሁና ስኬታችሁ ደስታዬና ስኬቴ-በአፍሪቃ የባንቱ ማሕበረሰብ "I Am Because We Are” ጥበብና እሳቤ!!
አንቺ "ጨው ለራስሽ ብለሽ ጣፍጭ ካልሆነም ድንጋይ ነች ብለው ይጥሉሻል"!!
አንተ ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ ካልሆነም ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሀል!!

ትሁት ፣ ቅንና አገልጋይ ከሆንኩ ለራሴ!!
ሰውን የሚያክል
(በዓምላክ አምሳል የተፈጠረና እኔ የመሰለ እራሴን የሆነ ሰው) የማጉላላ ፣ የማመናጭቅና የምበድል ከሆንኩ ለራሴ!!
ፍትሕ የማጏድልና በሙስና ከተጨማለኩ ለራሴ!!
ዋሾና ቀጣፊ ከሆንኩ ለራሴ!!
ባሴርና ባስመስል ለራሴ!!
ክፉና ንፉግ ከሆንኩ ለራሴ!!
ቂመኛ(ካንሰርና) ተንኮለኛ ከሆንኩ ለራሴ!!
ቅንና ግልፅ ብሆን ለራሴ!!
መልካምና በጎ ከሆንኩ ለራሴ!!
በትህትና የማገለግልና የማካፍል ፣ የማግዝና የማካፍል ከሆንኩ ለራሴ!!
የውስጥ ሰላሜን ፣
ደስታዬንና ፈገግታዬን የማካፍል ከሆነ ለራሴ ፣ ለበለጠ ለውስጥ ሰላሜ ፣ ለእርካታዬና ለጤንነቴ!!

በዚች ሰው ከሆንኩ 23 ዓመታት አጭር ዕድሜዬ ውስጥ የዘራሁትን ሳጭድ አይቻለሁና!!

“ሰው የዘራዉን ያጭዳል።
በአንድ ሀገር የሚኖር ንጉስ ነበር እናም ይህ ንጉስ የአገልጋዮቹን ታማኝነት መፈተን ፈለገ ሶስት አገልጋዮችን ካስጠራ በኋላ አንድ ትዕዛዝ ያዛቸዋል

ጫካ ሄዳችሁ በዚህ ሙሉ ጣፋጭ ፍራፍሬ ለቅማችሁ ይዛችሁ እንድትመጡ እፈልጋለሁ ብሎ ለሶስቱም አንዳንድ ሻንጣ ይሰጣቸዋል።

የመጀመሪያዉ አገልጋይ በጣም ቅን እና ታማኝ ሰዉ ነበረ በደንብ ተጠንቅቆ ምርጥ ምርጥ ፍራፍሬዎችን ለጌታዉ በሻንጣዉ ሙሉ ለቅሞ ይዞ ሄደ፡፡

ሁለተኛዉ አገልጋይ እሱ ደግሞ ቸልተኛ እና ግድ የለሽ ሰዉ ነበር ዝም ብሎ መሬት ላይ ወድቆ ያገኘዉን የተበላሸዉን ያልተበላሸዉን አግበስብሶ በሻንጣዉ ሞልቶ ይዞ ሄደ፡፡

ሶስተኛዉ አገልጋይ እሱ ደግሞ ተንኮለኛ እና አጭበርባሪ ሰዉ ነበር ንጉሱ ይሄን ሻንጣ ከፍቶ አያየዉም ቢያይ እንኩዋን ሻንጣዎቹ ተመሳሳይ ናቸዉ ዬትኛዉ የእኔ እንደሆነ ማንም አያዉቅም ብሎ በሻንጣዉ ሙሉ ቅጠል ሞልቶ ሄደ።

ንጉሱ ሶስቱ አገልጋዮች እስከሚመጡ ጠበቀ እና ሶስቱም ከመጡ በሁዋላ ፖሊሶች ጠራ እና "እነዚህን ሶስት አገልጋዮች ለ አንድ ወር ያህል እስር ቤት አቆዩዋቸዉ ምግብ እንዳሰጡዋቸዉ የሰበሰቡትን እየበሉ ይቆዩ" ብሎ በትዕዛዝ ሰጠ። ፖሊሶቹም እንደታዘዙት አደረጉ።

በታሰሩበት ወቅት ጥሩ ፍራፍሬ የለቀመዉ ጣፋጭ ሲመገብ ከረመ ያግበሰበሰዉ ደግሞ ያንኑ እየበላ ታሞ ከረመ ቅጠል የሰበሰበው ደግሞ ሰዉ ያንን መመገብ ስለማይችል ሞተ።

"ሁሉም ለሰዉ የምንሰጠዉ ነገር ሁሉ ለእራሳችን ነዉ"

ዛሬ ለሰዎች ምን አይነት አገልግሎት ምን አይነት ፍቅር እና ታማኝነት እየሰጠን ነዉ የኛ ነገ እሱ ነዉ።”

ሁላችንን የምናጭደው
የዘራነውን ነውና በየእለቱ የምናስበውን ፣ የምንናገረውንና የምንዘራውን ቃልም ይሁን ተግባር
እንምረጥ!!

ዋናው መተንፈስ ነው!!
#EnvironmentFirst
#ሰው_መሆን
#እራስን_የራስንና_የሌላውንማክበር
#ይሉንታናትሁትነት_ቅንነትናአገልጋይነት
#አጋዥ_እረጂና_ሸክምአቅላይ
#ብሩሕ_ዜጋ
#Borderless_Volunteerisም
#UBUNTU*
#ቀርክሀ_ወርቅናሐብት_ነው
#የግራር_የዝግባ_የወይራ_ከተሞች
#ባሕል_ሀብትና_ቅርስነው
#PanAfricanAID-A Renewed Vision
of Connecting The Dots for Convergence, Collaboration and Global Alliances to Serve Humanity and Mother Earth, Peace & Greening Africa as Our Priority!!
*እኔ ሰው የሆንኩት በናንተ ነውና ህመማችሁና ጭንቀታችሁ ህመሜና ጭንቀቴ እንዲሁም ብትብድሉኝና ብታስከፉኝም ደስታችሁና ስኬታችሁ ደስታዬና ስኬቴ-በአፍሪቃ የባንቱ ማሕበረሰብ "I Am Because We Are” ጥበብና እሳቤ!!
Forwarded from Gashe Tamiru
Forwarded from Gashe Tamiru
Forwarded from Gashe Tamiru
ዋ ያች አደዋ እንደገና መጣች!!
ኑ እንነሳ ጎበዝና ጎበዚት እከሌ ከእከሊት ሳንል እንደጀግኖቻችን
ታሪክ እንስራ ዳግማዊ አደዋን እንድገም ያፈሩብንንም አፍሪቃውያንን እንደገና አለን እኮ እንበላቸው!!
ለዚህ ለዳረጉን የአፍሪቃ ተቀራማቾችን ቂም እንደተያዘባቸው እንደአፄ ምኒሊክ ጥቁር ሰው እንደገና ቅስማቸውን እንስበር!!
ጦራችንና ሀይላችን ልዑል ፈጣሪ ፣
መልካምነትና በጎነት ፣ ዕሩህሩህነት ፣
ቅንነትና ትህትና ፣ ተስፋ ፣ ዕምነትና የመንፈስ ፅናታችን መሆኑን እናሳያቸው!!
ያላቸው ምላስ(ትርክት መፍጠር) ፣ ተቋማትና ጉልበት ብቻም እንደሆነ እናሳያቸው!!

ኑ እንነሳ!!
#መልካምነትንና_በጎነትን_እንዝራ
#ቫይራል_እናድርግ
#Lets_Go_VIRAL
#አለን
#እንችላለን
#መፍትሔው_እጃችን_ላይነው
#መፍትሔው_እኛነን
#መፍትሔው_አሁንና_አሁንነው

በሀገርም ይሁን በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ ኤርትራውያን ፣ ራስ ተፈሪያንና ሌሎች እንደኔው ጥቁር ሰው ቤተሰቤ እኛ አፍሪቃውያንን እየጎዳ ያለው እነሱ የሚያደርጉት ፣ የሚዘሩብን የመከፋፈልና የመጨራረስ ፣ የመናናቅና የመበቃቀልን ትርክት ፣ የራሳችንን ልጆች እራሳቸውን ፣ ማንነታቸውንና እኛን በቲክቶክ ተዋርደው ማዋረዳቸው ፣ እራሳችንና የራሳችንን ንቀን የነሱ ቁሳቁስ ፣ አልባሳት ፣ አኗኗር ፣ ባሕልና ዕምነት ናፋቂዎች ማድረጋቸው ፣ እንዳናመርትና እንዳንረጋጋ መሰረታችንና እሴቶቻችንን መነቅነቅና መገዝገዛቸው ፣ የምናመርተውን እንድንንቅና የማናመርተውን እንድንናፍቅ ያደረጉን ፣ ልጆቻችን ሲመረቁ የብሔር ብሔረሰብን ሹርባ ትተው የሞተ ሰው ፀጉር("ሁማን ሄር") እንዲያደጉ ፍላጎት እንዲኖረን ፣ የአንገት ልብሳችንን ትተን በከረባት እንድንታነቅ ፣ የተፈጥሮ ሳርን ትተን ፕላስቲክ ቀጤማ በዶላር እንድናመጣ ፣ የራሳችንን ባሕላዊ መጠጦችና ምግቦች ትተን የነሱ ናፋቂዎች እኛን ማድረጋቸው ፣ ግራ ተጋቢዎችና ግራ አጋቢዎች ተላላኪዎቻቸው ያደረጉን ሳይሆን እኛን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳን ያለው እኛ ለእኛ ከእኛ በእኛ የማናደርገው ብለን በልዩነታችን ውስጥ እንደአደዋ ጀግኖቻችን በመተባበርና በአንድነት ለጋራ መፍትሔ አለመቆማችንና በዋናነት ባሰመሩልን ቱቦና አደገኛ የዘርና የብሔር ፣ የቋንቋ ፣ የባሕልና የሀይማኖት እስር ቤት ውስጥ ከተውን እነሱና እኛ እንድንባባል ስላደረጉን ነው!!

እነሱ ምን ያድርጉ?!
ይህን የሚያደርጉት ለጥቅማቸው ሲሉ ነው!!
ችግሩ እነሱ ሳይሆኑ "ብልህ ከሆናችሁ ተባበሩ ፣ ተደራጁ ካልሆነም እንደሞኞቹ ትጠፋላችሁ" እንደተባለው እኛ ልዩነታችንን ወደጎን ትተን ለጋራ ህልምና ለጋራ ድል በአንድነት መቆም ያቃተን የትውልድና የታሪክ ማፈሪያዎች በተለይም ከ40 ዓመት በላይ የሆን ወንዶች ነን!!
ደግነቱ እኔ ገና የ23 ዓመት ጎልማሳ አዛውንት ነኝ!(:.:)!

እስቲ ይህንን መልዕክቴን የደረሳችሁ 100+ ለሚሆኑ ቤተሰባችሁና ወዳጆቻችሁ ዛሬውኑ ፣ አሁኑኑ!!
ይህንን ማድረግ ካልቻላችሁ ማን ያድርግልን?!
1. ተመስገን ፣ ተመስገን ፣ ተመስገን!!
2. ዋናው መተንፈስ ነው!!
3. መልካምነት ፣ በጎነት ፣ ትሁትነት ፣ ቀናነት ፣ አካፋይነት ፣ ድንበርና ወሰን የለሽ አገልጋይነት ፣ አፍሪቃዊ ኡቡንቱነት-ለሰው ፣ ለትውልድና ለእናት ምድራችን መኖር!!
4. የባሕል ልብሴ ፣ የባሕል ምግቤ ፣ የባሕል መጠጦቼ ፣ ማንነቴ ፣ ሰው መሆኔ ለዛውም የፍቅር ፣ የጥበብ ፣ የመልካምነት ፣ የበጎነት ፣ የትህትና ፣ የይሉንታ ፣ የደስታና የፈገግታ ምንጭ ኢትዮጵያዊነት ፣ አፍሪቃዊነት ፣ ጥቁር ብሔር(ሰው) መሆን)!!
ብላችሁ በስልካችሁና በሶሻል ሚዲያው ዓየሩን አጨናንቁ(VIRAL) አድርጉ/እናድርግ!!

ይህንን ለሚቀጥሉት 30 ቀናት በሚሊዮኖች ሥራዬ ብለን ብናደርግ ጨለማው በብርሐን ይሸነፋልና ውጤቱን አብረን እናያለን!!

ወደእኛ ስንመጣ ዋናው
መተንፈስ ነውና!!
#EnvironmentFirst
1. እንደቸርነቱ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን ጠዋት የካ ተራራ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ያሉ 250 የሚሆኑ የKG ተመራቂ ህፃናት ልጆቻችን የነገ መሪዎቻችንን ከአስተማሪዎቻቸውና ከ20 ታዳጊ ህፃናት የፅዳትና ውበት አጋሮቻችን ጋር በመተባበር በድፎ ዳቦ ፣ በቄጤማ ፣ ሻይ ፣ ቡናና እንዲሁም እፅዋትና በቀርክሀ ችግኝ ተከላ በማድረግ ይመረቃሉ!!
በዚህ አጋጣሚ የሁል ጊዜም የማሕበራዊ ግዴታችንን መወጣት CSR-Corporate Social Responsibility ምርኩዛችንና አጋራችን ELDINA Clinic#1 ELDINA Clinic#2 እና የቀርክሀ ችግኝ አምራች Bamboo World Plc.,ን የቀርክሀ ችግኝ ለጋሻችንና የጏሮ አትክልት ችግኞች አቅራቢያችንን የሁልጊዜም ምርኩዛችን ከቦሌ ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ በጎ ፈቃደኛ አምባሳደር ወ/ሮ ዕሌኒ ከልብ እናመሰግናለን!!

2. እንደቸርነቱ እሁድ ሰኔ 15 ቀን "ለአርጋውያን እሮጣለሁ" ከፒያሳ ከአደዋ አደባባይ ወደቴዎድሮስ አደባባይ አቅጣጫ ድጋፋችንን ለማሳየት ከጧቱ 1 ሰዓት ተግኝተን ዋናው መተንፈስ ነው እያልን እሩጫው ቀርቶብን በዝግታ እሯጮቹን እናጅባለን!! ለመሳተፍ ቲሸርት መግዛት ለምትሹ በ0911813834 ወይም በ0995222214 ይደውሉ!!

3. እንደቸርነቱ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን ደግሞ ለዓመታት የቦሌ መድሃኒአለም የሃያ አምስቱ ማሕበራት የጋራ ቤቶች ባለቤቶች ማህበር!!
The True Spirit of ዋናው መተንፈስ ነው በተግባር!! አመራሮች የደከሙበትና እኛም ማሕበረሰቡን በቆሻሻ ማንሳትና ችግኝ ተከላ እንዲሁም የተለያዩ ማሕበራዊና አካባቢ ጥበቃን ግንዛቤስ ስንሰጥበት የቆየው ዋናው መተንፈስ ነው!! #EnvironmentFirst የሰላምና አረንጏዴ ሚኒ ቀርክሀ ፓርክ ሞዴልን ከማሕበረሰቡ ጋር በመሆን ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ስለምናስመርቅ ሁላችሁም ከመላው ቤተሰብ ጋር ተጋብዛችሗል!!

ዋናው መተንፈስ ነው!!
#EnvironmentFirst
#ሰው_መሆን
#እራስን_የራስንና_የሌላውንማክበር
#ይሉንታናትሁትነት_ቅንነትናአገልጋይነት
#አጋዥ_እረጂና_ሸክምአቅላይ
#ብሩሕ_ዜጋ
#Borderless_Volunteerisም
#UBUNTU*
#ቀርክሀ_ወርቅናሐብት_ነው
#ባሕል_ሀብትና_ቅርስነው
#PanAfricanAID-A Renewed Vision
of Connecting The Dots for Convergence, Collaboration and Global Alliances to Serve Humanity and Mother Earth, Peace & Greening Africa as Our Priority!!
*እኔ ሰው የሆንኩት በናንተ ነውና ህመማችሁና ጭንቀታችሁ ህመሜና ጭንቀቴ እንዲሁም ብትብድሉኝና ብታስከፉኝም ደስታችሁና ስኬታችሁ ደስታዬና ስኬቴ-በአፍሪቃ የባንቱ ማሕበረሰብ "I Am Because We Are” ጥበብና እሳቤ!!
2025/06/29 20:32:14
Back to Top
HTML Embed Code: