Telegram Group Search
ዋጋን ማወቅ

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከዕለታት በአንዱ ቀን መኳንንቱና ሊቃውንቱ በተሰበሰቡበት፡

“ለመሆኑ እኔ ብሸጥ ስንተ አወጣለሁ ?” በማለት ጥያቄ አቀረቡ ። ጥያቄው ድንገተኛ ፣ ለመመለስም አስቸጋሪ ነበር ። የሚወዷቸውና የሚያከብሯቸው ነበሩና ለእርሳቸው ዋጋ ለመተመን ሕሊናቸው ተጨነቀ ። ሁሉም መልስ መመለስ አቅቶት ዝምታን በመረጠበት ጊዜ አንድ የቆሎ ተማሪ “እኔ አለሁ” በሚል ስሜት መንቆራጠጥ ጀመረ ። መልስ አለኝ ብሎም ብድግ ብሎ ቆመ።

ምኒልክም “በል ተናገር” ብለው ዕድሉን ሰጡት ። ሊቃውንቱና መኳንንቱ ያቃታቸውን መልስ ተማሪው በድፍረት መለሰ ።

“ንጉሥ ሆይ ሃያ ዘጠኝ ብር ያወጣሉ” አላቸው ።

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክም ቆጣ ብለው፡- “እንዴት እኔን በሃያ ዘጠኝ ብር ገመትከኝ?” ቢሉት ተማሪውም፡-

“የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው ክርስቶስ የተሸጠው በሠላሳ ብር ነውና ምን ደግ ቢሆኑ ከክርስቶስ አይበልጡም ብዬ ነው በሃያ ዘጠኝ ብር የገመትክዎት” አላቸው ።

በተማሪውም መልስ ንጉሡና በዙሪያቸው የነበሩ መኳንንቱና ሊቃውንቱ ተደንቀው ሳቁ ።

በዚህ ዓለም ላይ የራሳችንን ዋጋ ማወቅ የምፈልግበት ቀን አለ ። ንጉሥም ሆነ ሎሌ “እኔ ስንት አወጣለሁ ?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል ፤ ዙሪያውንም መልስ ፍለጋ ያማትራል ። ምን ያህል ሕዝብ ይወደኛል ? ብሞት ማንን አጎዳለሁ ? ብኖርስ ማንን እጠቅማለሁ ? የሚሉ ጥያቄዎች በውስጣችን ተረግዘው ይወለዳሉ ። እነዚህ ጥያቄዎች ከጽንሰት እስከ ልደት ድረስ አስጨናቂ ናቸው ። አንዳንድ ሰው ራሱ በራሱ ፊት ዋጋው እያነሰበት “መኖር ትርጉም የለውም” ብሎ ይደመድማል ። ምክንያቱ ካለቀበት አንድ እርምጃ መጓዝ ሁሉም ሰው ሊከብደው ይችላል ። ወደ እግዚአብሔር “አቤት” ብሎ “ጌታዬ ሆይ ዋጋ ሁነኝ” ካላለ ውስጡን መገሠጽ ፣ ማዕበሉን መቅዘፍ ይቸገራል ።

“እኔ ብሞት ምን ትላላችሁ ?” ብለን ልጆቻችንን እንጠይቃለን ። የምትሄደው ወይም የምትሄጅው ክርስቶስ ጋ ነውና ጥሩ ነው ካሉን ፣ “የዛሬ ልጅ ጨካኝ ነው” እንላለን ። የጠየቅነው የምንፈልገውን መልስ ለመስማት ነው ። ራሳችን ጠይቀን ራሳችን እንታዘባለን ። የዚህ ሁሉ አሰሳ ምክንያቱ ዋጋችንን ለማወቅ ነው ። ጓደኞቻችንን “ፎቶዬን ላሳድግ ፎቶ ቤት እየሄድኩ ነው” እንላለን ። ለምን ? ሲሉን “ብሞት እንኳ ማስለቀሻ ይሆናል” በማለት እንመልሳለን ። ሲደነግጡና “አይባልም” ሲሉን ደስ ይለናል ። ምክንያቱም በእነርሱ ዘንድ ያለንን ዋጋ አውቀናልና ። የአገር መሪዎች ሰልፍ የሚያስወጡት ዋጋቸውን ለማወቅም ነው ። ይጠፉና ታመሙ የሚባል ወሬ ያስወሩና ሁሉም ለፍልፎ ሲደክመው ብቅ ይላሉ ። የፎከረና ዙፋን ያማረው ያፍራል ። ያዘነና ያለቀሰም ይደሰታል ። አመመኝ የሚሉ ሚስቶች ፣ የሚያጉረመርሙ ባሎች አንዱ ችግራቸው ዋጋቸውን ስንት መሆኑን ማወቅ ስለሚፈልጉ ነው ። ኑሮ በዘዴ እንጂ በጉልበት አይደለም ። ዘዴውን ያወቁ መንገዱ ጥርጊያ ሲሆንላቸው ፣ ያላወቁት ደግሞ ፊት ለፊት ከሚጋረጥ ተራራ ጋር ይጋጠማሉ ።

ሕፃናትም ዋጋቸውን ማወቅ ይፈልጋሉ ። በድንገት ውድቅ በማለት “ልጄን” ሲባሉ ይደሰታሉ ፣ ይስቃሉ ። የሚደነግጥላቸው ፣ በአካል ሲወድቁ በአሳብ አብሮ የሚወድቅላቸውን ማወቅ ይሻሉ ። ወንድም በወንድሙ ዘንድ ያለውን ዋጋ ለማወቅ “እንዲህ ያለ ወንጀል ሠርቼ ልታሰር ነው” ይለዋል ። ወንድሙም ሐሰተኛ ዜና መሆኑን ሳያውቅ ይደነግጥና መላ ማቅረብ ይጀምራል ። ያን ቀን ጠያቂው ወንድም ፣ ተጠያቂ ወንድሙን በወርቅ ቀለም ይጽፈዋል ። መምህራን ዋጋቸውን ለማወቅ፡- “ጉባዔውን በትኜ አንድ ገዳም እገባለሁ” ይላሉ ። ተማሪውና ሕዝቡም፡- “ምን በደልን ይቅር ይበሉን” ሲላቸው ዋጋቸውን ያገኙትና ደስ ይላቸዋል ።

ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ነው ። ምንም ትሑት ብንሆን ከእርሱ አንበልጥም ። እርሱ ሊያጠፋን አቅም እያለው ችሎናል ። ምክንያቱም ትሑት ነውና ። እኛ ግን አቅም ስላነሰን ዝቅ ማለታችን ትሕትና ተብሎ ይጠራል ።

እርሱ ቢገድለንም ቢያድነንም ሁሉም በፊቱ ነው ። ትዕግሥተኛ ነውና ለመግደል በቂ ምክንያት እያለው ያድነናል ። ጥፋታችንን ሳይሆን ራሱን እያየ ይጋርደናል ። ምንም ትዕግሥተኛ ብንሆን የእርሱን ያህል ታጋሽ አይደለንም ። ምንም መከረኛ ብንሆን የእርሱን ያህል መከራ አልተቀበልንም ። እርሱ በጌትነቱ ብቻ ሳይሆን አርአያ ገብርን በመንሣቱም ልክ የለም ፣ አይደረስበትም ።

እርሱ በበረት ተወልዷል ። ከበረት ያነሰ ቦታ መፈለግ ይገባናል ። እርሱ እኛን ሀብታም ሊያደርግ እንደ ደኸየ ከማሰብ እርሱ በመንፈስ ሊያበለጥገን ምንም የሌለው ምስኪን እንደሆነ ማመን የተሻለ ነው ። እርሱ በግብጽ በረሃ ተሰድዷል ። እኛ ግን ተሰደድን የምንለው ከእርሱ ስደት ጋር የማይነጻጸር ነው ። እርሱ ቤት የለሽ ሁኖ ኑሯል ። እኛ ግን በኪራይ ቤት ስለምንኖር እንበሳጫለን ። በኪራይ ዓለም ተቀምጠን ፣ በኮንትራት ዕድሜ እየኖርን ቋሚ ቤት እንፈልጋለን ። እርሱ በተውሶ ጀልባ ተንቀሳቅሷል ፣ እኛ ግን የራሳችን መኪና ስለሌለን ፣ በታክሲ ስለምንንቀሳቀስ እንበሳጫለን ። እርሱ በባሪያው እጅ ተጠምቋል ፣ እኛ በዕድሜም በጸጋም በክህነትም ለሚበልጡን አባቶች ዝቅ ማለት አንሻም ። እርሱ ጋኔን አለበት ተብሏል ። እኛ ግን ባነሰ ስድብ ደንብረናል ። እርሱ እብድ ነው ተብሏል ። እኛ ግን መናፍቅ መባል ያሰጋናል ። እርሱ አናጢነትን ሙያው አድርጓል ። እኛ ግን ሥራ እናማርጣለን ፣ በምንሠራው ሥራም ትልቅነት አይሰማንም ። እርሱ በጲላጦስ አደባባይ ያለ ወንጀሉ ተከስሷል ። እኛ ግን በገዛ ወንጀላችን ስንከሰስ ይከፋናል ። እርሱ በጴጥሮስ ተክዷል ። እኛ ግን በልባችን የከዳናቸው በአካል ሲከዱን ተቀደምኩ ብለን እናዝናለን ። እርሱ በይሁዳ ተሽጧል ። እኛ ግን ብዙዎችን ሸጠን ፣ አንድ ጊዜ ስንሸጥ ይቆረቁረናል ።

በጣም ትሑት ሆነን ዝቅተኛውን ስፍራ በረትን ከመረጥን እርሱንም ክርስቶስ ይዞብናል ። በሲና በረሃ መንከራተትን ብንመርጥ እርሱ ተሰዶበታል ። ቤት የለሽ መሆንን ብንፈልግ እርሱ በተራራ ያድር ነበረ ። የገዛ ወንድሞቻችን ስለናቁን ትልቅ ማዕረግ እንዳለን ከቆጠርን እርሱ ይበልጥ በእናቱ ዘመዶች ተንቋል ። ከበረት ያነሰውን ቦታ ፣ ከባሪያ ያነሰውን አገልጋይ ፣ ከሲና በረሃ የባሰውን መንገድ ፣ ከሠላሳ ብር ያነሰውን ዋጋ መፈለግ አለብን ። እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ይህን ካገኘ እኛማ ገና ይቀረናል ።

ስለ መከራችን ለማውራት መከራው ይገሥጸናል ። ስለ ስደታችን ለመተረክ ስደቱ ገና ነው ይለናል ። የሚሊየን ብር ዋጋ ለራሳችን ስናወጣ ክርስቶስ የተሸጠበት ሠላሳ ብሩ ተዉ ይለናል ። በመከራው ፊት መከራችን ፣ በአገልግሎቱ ፊት አገልግሎታችን ፣ በመሥዋዕትነቱ ፊት የከፈልነው ዋጋ ትንሽ ነው ።

ጌታ ሆይ ዋጋችንን ካንተ ዋጋ እንዳናስበልጥ እርዳን ።@THESECRETKNOWITFIRST
@THESECRETKNOEITFIRST
...አንድ ግዜ የሆነ ልጅ ነው። የሚበላ ዳቦ ፈልጎ በዙሪያው ካሉት ህፃናቶች ውስጥ ገለል ብሎ የገረጣውን ይጠራውና ዳቦውን ገዝቶለት እንዲመጣ ይልከዋል። ህፃኑም የተባለበት ቦታ በደስታ እንዲሁም በፍጥነት ደርሶ የታዘዘውን ዳቦ ገዝቶ ይመጣል።

...ቅድም ከጨዋታ የተገለለው እቤት ቁርስ ስላልበላና ስለራበው ነበር። ትድያ ይህ የላከኝ ግለሰብ አንድ ፍሬ ይሰጠኛል ብሎ በተስፋ አይን አይኑን እያየ ሲጠባበቅ የላከው ልጅ "አንተ...ሂድ እንጂ!! ከጓደኞችህ ጋር ተጫወት በሜለት በግልምጫ ያባረዋል። ህፃኑም እየራበውም ቢሆን ስለፈራ ደንግጦ ከአጠገቡ ዞር አለ።

.....ትንሽ ቆይቶ አንድ የዝህ የህፃኑ ላኪ ግለሰብ #ጓደኛ ይመጣል። ሰላም ከተባባሉም በኋላ የያዘውን ዳቦ አብረው እንዲበሉ ይጋብዘዋል። ጓደኛው አሁን በቅርብ ቁርስ እንደበላና ሆዱ በጣም እንደጠገበ ይነግረዋል። ሰውየው ግን በግድ ጓደኛውን ካልበላህ ብሎ በመለመን ከያዘው ዳቦ ግማሽ የሚሆነውን አካፍሎት አብረው ተመገቡ። የቅድሙ #ህፃን ድርጊቱን ተመልክቶ በጣም አዘነ። እሱ እየተራበ ሳይሰጠው ለጠገበና አልፈልግም ላለ በመሰጠቱ በጣም አስከፋው። ውሎውንም በትካዜ ተሞልቶ አሳለፈ።


... ከዚህ ታሪክ የምንማረው ሁላችንም ያሉንን ነገራቶች ለሚገባቸው አካላት በመለገስ አምላካችን የሚወደውን ስራ አንስራ። ብዙ ግዜ ሰርግ ይዘጋጃል፤ተዝካር እንደዛው ነገር ግን እነዚህ ዝግጅቶች ላይ የሚጠሩት በረሃብ የተመቱ ደካሞች ሳይሆን ቤት የተረፋቸው ቦርጫምና የጠገቡ ሃብታሞች ናቸው። ይህ መሆን የለበትም። ህፃናትንም ቢሆን ልከን ለላክናቸው እንዲደሰቱ ሌላም ቀን በደስታ እሺ እንዲሉን ስሜታቸውን በመረዳት እናስደስታቸው።


ሼር ሼር ሼር ሼር!!
www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
+ ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር +

እመቤታችን ጌታን ጸንሳ ከወለደችው በኋላ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ እንደ ልጅነቱ እያገለገላት ፣ እንደ አምላክነቱ እያገለገለችው አብራው በአንድ ቤት ውስጥ ኖራለች፡፡

ሌላውን እንተወውና ይኼ ነገር ብቻ ለማሰብ ያስጨንቃል! ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ አንድ ቤት ውስጥ መኖር እንዴት ያለ ነገር ነው? ልብ በሉ ድንግል ማርያም ጠዋት ከእንቅልፍዋ ስትነቃ "እንዴት አደርህ?" የምትለው ፈጣሪዋን ነበር:: ማታ ስትተኛ "ደህና እደሪ" የሚላትም አምላክዋ ነበር:: የማይተኛው ትጉሕ እረኛ በተኛች ጊዜ ሕፃን ሆኖ ከአጠገብዋ ያደረ ከእመቤታችን በቀር ማን አለ?

ኪሩቤልና ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ የሚሉትን አምላክ እንደ እናት "እሹሩሩ" ብላ ያስተኛች እርስዋ ነበረች:: ምድርን በአበባ ልብስ የሚያስጌጠውን ጌታ በተኛበት ያለበሰችውም እርስዋ ነበረች:: ዓለምን በእጆቹ የያዘውን ጌታ ክንዶችዋን ያንተራሰችው እርስዋ ነበረች:: እነዚያን ሌሊቶች ድንግል ማርያም እንዴት አሳልፋ ይሆን? በሕልምም በእውንም ከፈጣሪ ጋር ማሳለፍ እንዴት ያለ ጸጋ ነው?

ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፡፡ እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ለሠላሳ ዓመታት አብራ በአንድ ቤት ስትኖር የነበራቸው ንግግር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደመሆኑ ጸሎትም ጭምር ነበር፡፡

የጠዋትና ማታ ጸሎትሽ ከልጅሽ ጋር ማውራት የሆነልሽ : ልጅሽ የሚሠጥሽ መልስ የፈጣሪ መልስ የሆነልሽ እመቤቴ ሆይ ስላንቺ ክብር ማሰብ ምንኛ ያስጨንቃል?

እስቲ ረጋ ብላችሁ አስቡት! እመቤታችን እና ጌታችን በእነዚያ ሁሉ ዓመታት ምን ሊነጋገሩ ይችሉ ነበር? ከእርስዋ በቀር ማን ይነግረናል? ድንግል ሆይ አንቺ ካልነገርሽን ማን ይነግረናል? ለማዕድ ስትቀመጡ ምን ብሎ ጸልዮ ይሆን? እንደ ሐዋርያቱ ቆርሶ ሠጥቶሽ ይሆን? ውኃን እንዲጠጣ ሞልተሽ ስትሠጪው ውቅያኖስን እንዴት በውኃ እንደሞላ ነግሮሽ ይሆን?

በእርግጥ በእነዚያ ዓመታት ክርስቶስ ለእናቱ ምን ምን ሲነግራትስ ኖሮ ይሆን? ስለየትኛውስ ምሥጢር ሲገልጥላት ነበር? ገና የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያነጋገሩት የአይሁድ መምህራን ‹በማስተዋሉና በመልሱ ሲገረሙ ነበር› እመቤታችን ከሕጻንነቱ ጀምሮ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ አብራው ስትኖር በስንቱ ነገር ስትደነቅ ኖራ ይሆን? /ሉቃ. ፪፥፵፯/

እንደ መንፈሳዊት እናት ድንግል ማርያም ለልጅዋ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እየነገረች አሳድጋው ይሆን? ሙሴ ስላያት ዕፀ ጳጦስ ታሪክ አልነገረችው ይሆን? ታሪኩን ሰምቶ "ያቺ ዕፅ አንቺ ነሽ እሳቱ ደግሞ እኔ ነኝ"ብሏት ይሆን? ውኃ ስለፈለቀበትና እስራኤል ስለጠጡበት ዓለት ነግራው ይሆን? እርሱስ "ያ ዓለት እኮ እኔ ነበርሁ" ብሎአት ይሆን?

ብሉይን ስታነብ ሐዲስን እየተረጎመ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ልብዋን አቃጥሎት ይሆን? ሉቃ. ፳፬፥፴፪/ ጠቢበ ጠቢባን ሊቀ ሊቃውንት ኢየሱስ ክርስቶስ በቤትሽ ጉባኤ የዘረጋብሽና ያስተማረሽ ድንግል ሆይ አንቺ እንደሆንሽ በልብሽ ከመጠበቅ ውጪ ብዙ አትናገሪም:: ሆኖም ልጅሽ ምን ምሥጢር ነግሮሽ ይሆን?

ኤልሳቤጥ እንኳን ዮሐንስን ጸንሳ ስለጽንሱ የምትለው ብዙ ነገር ነበራት:: ፈጣሪ በአንቺ ዘንድ ያደረ ድንግል ሆይ አንቺስ ምን ትነግሪን ይሆን? "የመለኮት እሳት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት ነው:: እንደምን አላቃጠለሽም? የኪሩቤል ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘረጋ? በግራ ነው ወይንስ በቀኝ? ታናሽ አካል ስትሆኚ ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን ይችላል?" እያልን ከአባ ሕርያቆስ ጋር እንጠይቅሻለን::

እንዳንቺ ፈጣሪውን የሚያውቅ ፍጡር የለምና የዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት : የነገረ መለኮት ምሁራን : የወንጌሉ ተንታኞች ሁሉ ከአንቺ እግር ወድቀው እንደ አዲስ ስለ ክርስቶስ ሊማሩ ይገባቸዋል:: ልህቅተ ሊቃውንት እመቤታችን ሆይ ሊቃውንት ሁሉ ያንቺ ተማሪዎች ናቸው:: ባለ ቅኔዎች ሁሉ ባንቺ ፊት ገና ፊደል አልቆጠሩም:: ሰውና መላእክት አንድ ላይ ተሰልፈው "ብርቱ የሚሆን በአንቺ ያደረገውን ታላቅ ነገር" ሊሰሙ ይጠባበቃሉ:: ወዳጄ ጥቅስ ፍለጋህን ትተህ እግዚአብሔርን በእቅፍዋ ከያዘችው ቃሉን በሹክሹክታ በጆሮዋ ከሰማችው ድንግል እግር ሥር እንደ እኔ ብትደፋ ይሻልሃል:: የእግዚአብሔርን እጆች ይዛ የመጀመሪያዎቹን የሕፃንነት እርምጃዎቹን እንዲራመድ የመራችውን ድንግል መቆም ያቃተንን ደካሞች እንድትመራን አብረን ደጅ ብንጠናት ይሻላል::

እነ ጴጥሮስ በቅዱሱ የታቦር ተራራ ከጌታ ጋር ነበሩ ፊቱ ሲያበራ አይተው በዚህ ካልኖርን ብለው ተመኝተው : ኤልያስና ሙሴን አግኝተው ነበር:: ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር የኖርሽው እመቤታችን ሆይ የልጅሽ ልብሱ ስንት ቀን አብርቶ ይሆን? ከነቢያትስ እነማንን አምጥቶ አሳይቶሽ ይሆን? እንደ ጴጥሮስ "ሦስት ዳስ እንሥራ" የማትይዋ የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ሆይ ቤትሽ ደብረ ታቦር ሆኖልሻልና ልጅሽ ምን አሳይቶሽ ይሆን? ከእግዚአብሔር አብ "ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሚው" የሚል ድምፅ መስማት የማያስፈልግሽ "ለእኔም ልጄ ነው" ማለት የምትችይዋ እናት ሆይ እንደ እግዚአብሔር አብ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" ለማለት ሥልጣን የተሠጠሽ ሆይ ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር መኖርሽን ባሰብሁ ጊዜ ጠባብዋ ሕሊናዬ ኃጢአት ያደቀቃት ሰውነቴ እጅግ ተጨነቀች::

ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት ብዙ ራእይ አይቶ "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኩ" ብሎ ጻፈ:: ሠላሳ ዓመታት የጌታ ቀን የሆነላት በመንፈስ የነበረች ድንግልስ ስንት ራእይ አይታ ይሆን?
መላ የሰውነታችን አካል ሁሉ አፍ ቢሆን የእርስዋን ክብርና ምስጋና ተናግረን መፈጸም አንችልም::

@THESECRETKNOWITFIRST
ኢሚኔም
ከእነዚህ መካከል አንዱ ታዋቂው የራፕ አቀንቃኝ የሆነው ኢሚኔም ሲሆን በ 2006 እኤአ በመኪና አደጋ እንደሞተ ወይም እንዲሞት እንደተደረገና ከዛ በኋላ ያለው ኢሚኔም በኢሉሚናቲዎች የተፈጠረው እንደሆነ ይነገራል። በተጨማሪም ኢሚኔም የመኪና አደጋ ከደረሰበት በፊት እና በኋላ ያለውን የፀጉር ቅርፅ፣ ድምፅና የጆሮ ቅርፅ ልዩነት ለማስረጃነት ይቀርባል። በዚህም ሌላኛው ካናዳዊው ዝነኛ ራፐር ቶም ማክዶናልድ እኤአ በ 2019 "Cloned Rapers" በተሰኘው ሙዚቃው የምስጢር ማህበረሰቡ መቆጣጠር ያልቻሉትን ሰው መንትያን በመፍጠር እንደሚያጠፉት ይናገራል።
[Verse 1]
The Illuminati knows the answers
Taking bone samples to clone rappers
Put the artists in prison to silence their vision
Genetic copies going home after
They look different, eyes shifted
Smile missing, skin lifted, it's scientific
If they can't contgrol you, they erase the old you
Get your duplication to enforce their message
They cloned Gucci, cloned Kodak
Cloned Eminem, he ain't rapped since Encore, know that
Cloning rappers when they overdose
To keep making money from producing more tracks
The game is a sham
Turning the artists who challenged to sacrificial lambs
The labels and devils are shaking hands
Creating our artists in labs
[Pre-Chorus]
The executions have been televised, oh
They're on TMZ like every night
They take our heroes, give us weaponized clones
The revolution won't be televised
[Chorus]
I can't be replicated
Copy the attitude and the chains
But no one will ever do me the same
I can't be replicated
Try to control me? Then guess again
Rebellion lives in my DNA
I can't be replicated
Duplicated, imitated, fabricated, eliminated
No, I can't be replicated
The system designed me to be a slave
I'm the glitch in their Matrix they can't escape
I can't be replicated
[Verse 2]
If they killed the rappers who were spitting truth
They wouldn't have a messenger to reach the youth
So they duplicate physically, implant abilities
Replicate tattoos in cloning facilities
Indie contracts say "Worldwide"
Label contracts say "Universal"
For all of time and all forms
They own all your music, your image, your name, and your
person
Huh, weird right? I know you don't think that it's facts
But for fifty thousand and a hair sample you can clone your
dog or your dying cat
It's another way for them to win the war by weaponizing
important celebrities
Don't kill your foes, just clone their Gods, then you'll control
all of your enemies
[Pre-Chorus]
The executions have been televised, oh
They're on TMZ like every night
They take our heroes, give us weaponized clones
The revolution won't be televised
[Chorus]
I can't be replicated
Copy the attitude and the chains
But no one will ever do me the same
I can't be replicated
Try to control me? Then guess again
Rebellion lives in my DNA
I can't be replicated
Duplicated, imitated, fabricated, eliminated
No, I can't be replicated
The system designed me to be a slave
I'm the glitch in their Matrix they can't escape
I can't be replicated
[Bridge]
You can see the difference in their face now
Casualties of money and of fame
Posing for the cameras with their fake smile
A clone of someone who they used to be
[Chorus]
I can't be replicated
Copy the attitude and the chains
But no one will ever do me the same
I can't be replicated
Try to control me? Then guess again
Rebellion lives in my DNA
I can't be replicated
Duplicated, imitated, fabricated, eliminated
No, I can't be replicated
The system designed me to be a slave
I'm the glitch in their Matrix they can't escape
I can't be replicated

ማይሊ ሳይረስ
ሌላኛዋ የመንትያ ፈጠራ ተጠቂ እንደሆነች የምትታሰበው ታዋቂዋ ድምፃዊ ማይሊ ሳይረስ ናት። በካሊፎርንያ በዲዝኒ እንደተገደለችና በሌላ ተመሳሳይ እንደተተካችም ይታሰባል። 'ጨዋ' የሚባል አይነት የግል ህይወት የነበራት ማይሊ ሳይረስ እኤአ ከ 2013 በኋላ ከድሮ ህይወቷ ያፈነገጡና ልቅ የሆኑ ድርጊቶችን እያከናወነች በመምጣቷ ነው። በተጨማሪም ከአደጋው በኋላ አካላዊ ልዩነት እየተስተዋለባትም ስለመጣ ነው...
ይቀጥላል .......
www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
🤔..አስቲ እናስተውል!😂

🌷ከበሮ ለምን ይጮኻል..??🌷

የኔታ ለተማሪዎቻቸው አንድ ጥያቄ አቀረቡ 🗣 "ከበሮ ለምን ይጮኻል?"

የኔታ የኔታ አሉ ተማሪዎቻቸው እየተሽቀዳደሙ። አንዱ ዕድሉ እንደተሰጠው "በቆዳ ስለተወጠረ ነው!" አለ አንድ ተማሪ የዳዊት መኻደሩን በእጁ አንጠልጥሎ ለመመለስ እየቸኮለ።

የኔታም "አይደለም!" አሉ። ሌላኛው ተማሪም "የኔታ ከእንጨት ስለተሠራ ነው" አለ የለበሰውን ለምድ ከፍ ከፍ እያደረገ። የኔታም ትንሽ ዝም ካሉ በኋላ "አይደለም" አሉ።

ተማሪው ኹላ ማውጣት ማውረድ ጀመረ በሐሳብ ተወጠረ። ኹሉም የመጣለትን እና የገመተውን መናገር ቀጠለ ግን የሚመልስ ጠፋ።

በስተመጨረሻ አንድ የኹሉንም ምላሽ በእርጋታ ይሰማ የነበረ ተማሪ እጁን አወጣ። " እሽ ልጄ" አሉ የኔታ። ድምፁን ከፍ አደረገና "የኔታ እድሉን ስለ ሰጡኝ አመሰግናለኹ" ብሎ እጅ ነሣ! ቀጥሎም "ከበሮ የሚጮኸው ባዶ ስለኾነ ነው!" አለ።

የኔታም የልጁን ምላሽ በማድነቅ ከወንበራቸው በመነሣት ልጄ ተባረክ አሉ። ተማሪዎቹም በጭብጨባ አጀቡት።

የኔታም ቀጠል አደረጉና "ልጆች ባዶ የኾነ ነገር ኹላ ይጮኻል። በውስጡ የኾነ ነገር ያለው ዕቃ ግን አይጮኽም። የተማረም ሰው እንዲኹ ነው። እውቀት ያለው አይጮኽም - ጥበብ ያለው አይጮኽም! ምንጊዜም ባዶ የኾነ ሰው ሲጮኽ - ጥበብ የሌለው ሲፎክር - ዕውቀት የሌለው ሲያቅራራ ይታያል። እና ልጆቼ እናንተ ባዶ እንዳትኾኑ ዕውቀትን ጨምሩ! በዕውቀት ላይ ጥበብን፣ በጥበብ ላይ እግዚአብሔርን መፍራት ጨምሩ። ምድራችንን በማስተማር እና በመስበክ የሞሉ ግን ባዶ የኾኑ - ምድሪቱን በዝማሬ የሞሉ በሃይማኖት እና በምግባር ግን ባዶ የኾኑ - እንደ ሰው ተፈጥረው እንደ እንስሳ በደመ ነፍስ የሚኖሩ ሰዎች በዝተዋልና!" ብለው ቁጭ አሉ። ተማሪዎቹም የኔታን አመስግነው ትምህርታቸውን ቀጠሉ።
www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
አኛ ማን ነን⁉️



👉ሰውዬው ድንኳን ሰባሪ ነው፡፡ ሁለት ቦታ የአቡዬ ድግስ እንዳለ ይሰማል፡፡ ሰዓቱ ሲደርስ እንደ ተጠራ ሰው የክት ልብሱን ለብሶ ይወጣል፡፡ የሁለቱም ድግስ የተለያየ ቦታ ነበር፡፡ ወደ አንደኛው እየሄደ ሳለ የዚያኛው ድግስ ቢበልጥስ ብሎ ተመለሰ፡፡ ወደዚያም ጉዞ እንደ ጀመረ የዚህኛው ምስር ሆኖ ያኛው ቁርጥ ቢሆንስ ብሎ እንደገና ተመለሰ፡፡ እንዲህ ሲያመነታ ሰዓቱ እያለፈበት ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ በመካከለኛ መንገድ ላይ ቆመና በጭንቀት ‹‹አቡዬ የዛሬን ብቻ ለሁለት ይሰንጥቁኝ›› ብሎ ጸለየ ይባላል፡፡
😁😁😁

🔵ዓለምንም እግዚአብሔርንም መያዝ አይቻልም፡፡ ሁለት አባሮም አንድ መያዝ አይቻልም፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎም ሁለት ዛፍ አይወጣም፡፡ አንዷ ብትጠፋ አንዷ ትዳን የምትባል ሁለት ነፍስም የያዘ የለም፡፡ ከካደው ይልቅ መሐል ሰፋሪው የመመለስ ዕድሉ የመነመነ ነው፡፡ ዛሬ አብያተ ክርስቲያናትን ያጣበቡ ‹‹ምንም ይሁን ሰላም ይስጠኝ እንጂ›› ብለው የመጡ ናቸው፡፡ ዛሬን እንቅልፍ መተኛት እንጂ ዘላለማዊ ሕይወት ማግኘት አይፈልጉም፡፡ ተባብረው ያድኗቸው እንጂ ፍጡርና ፈጣሪን፣ እግዚአብሔርንና ጠንቋይን አይለዩም፡፡ የሚያሳስባቸው ጉዳያቸው እንጂ የእግዚአብሔር ፍቅር አይደለም፡፡ ማዕዱን ትተው በፍርፋሪ ለመጥገብ የሚመኙ ሚና አጥተው ሁሉ ቦታ አሉ፡፡ ከቤታቸው ወጥተው ያሰቡበት አይደርሱም፡፡ ሁሉ ይጎትታቸዋል፡፡ የሚያዩት የሚሰሙት አፍዞ ያስቀራቸዋል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ክርስትና አቋም ሳይሆን ፋሽን ነው፡፡ ክርስትና ቃል ኪዳናቸው ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ሊተውት የሚችሉት ነገር ነው፡፡ የንስሓ ዝማሬ፣ ጸሎትና የተሰበረ ሕይወት ‹‹አይመቸንም›› ይላሉ፡፡ መቆዘም የማይፈልጉ ሁልጊዜ የግርግር ደስታን ከ‹‹ሃሌ ሉያ›› የተራቡ ናቸው፡፡

🔴ጌታ ስለ ጠፉት ሦስት ወገኖች ሲናገር አንደኛው ጠፊ ድሪሙ (ገንዘቡ) እቤት ውስጥ የጠፋ ነበር (ሉቃ 15÷8)፡፡ ዛሬም በቤቱ የጠፉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሳይድኑ ለማዳን የሚሰብኩ፣ መመራትን ሳያውቁ የሚመሩ፣ ግጥም ገዝተው የሚዘምሩ፣ የገዛ ድምፃቸው አስለቅሷቸው የሚወርዱ ብዙ የጠፉ ወገኖች ዛሬም በቤቱ አሉ፡፡

⚫️በድንበር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ቋንቋቸው የተደባለቀ ነው፡፡ የንግድ ልውውጡም የደራ ነው፡፡ ሁለት አገር መሆናቸውን የሚያውቁት ፖሊስ ሲያዩ ነው፡፡ ዛሬም የድንበር ክርስትናን የሚገፉ፣ አንድ እግራቸው ዓለም፣ አንድ እግራቸው ቤተ ክርስቲያን የሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ በሰማበት ጣዱኝ የሚሉ፣ ቋንቋቸው የተደባለቀ ሕዝቦች ዛሬም በቤቱ አሉ፡፡ ክርስትናቸውን የሚያስታውሱት ሰባኪ ሲያዩ ነው፡፡ ግን እኛ ማን ነን

🔶ከእስራኤል ልጆች የሮቤልና የጋድ ነገድ ዮርዳኖስን ተሻግረው መውረስን አልፈለጉም፡፡ ከሚወርድ ጅረት ጋር መታገልን፣ ኢያሪኮን ማፍረስን፣ ጠላትን መደምሰስን አልፈለጉም፡፡ በከነዓን ትይዩ መቀመጥን ፈለጉ (ዘኁ.32)፡፡ ውጤታቸው ግን ያለ ወንድሞቻቸው በበረሃ ተጠቅተው ቀሩ፡ ዛሬም ከክርስትናው ትይዩ አቅጣጫቸውን እያስተካከሉ የሚኖሩ፣ ዳር ዳር እየተጓዙ የሚቃርሙ ብዙዎች ናቸው፡፡ ውጤታቸው ግን እንዲሁ መና ሆነው መቅረት ነው፡፡ ላመኑበት ዋጋ ለመክፈል የሚፈሩ ለመኖርም ብቁ አይደሉም፡፡

🔻ጌታ፡- ‹‹ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ÷ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ፦ እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል ...›› (ማቴ. 11÷16-19) ብሏል፡፡

🔹ወንጌል ሲሰበክለት የእኔ አይደለም የሚል፣ ፍርድ ሲሰበክለት እግዚአብሔር አይጨክንም የሚል ትውልድ ምሳሌው ምንድነው? ቃሉን እንደ ኪኒን፣ መዝሙርን እንደ ዘፈን መለወጫ የሚጠቀም ትውልድ ምን ዓይነት ትውልድ ነው? እና ማን ነን? ማን እንደ ሆንን የምንጠየቀው ከውስጥ ነው፡፡ ደጁን ስናንኳኳ ማን ነው? ስንባል ‹‹እኔ ነኝ›› ካላልን የሚከፍትልን የለም፡፡ ‹‹እኔ ነኝ›› ማለት ካልቻልንም ሕይወት ደጇን አትከፍትልንም፡፡ ሰዎች ማን እንደሆኑ እናውቃለን እንላለን፡፡

ግን እኛ ማን ነን

https://www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
+ ያደረግሽው ምንድር ነው ? +

አዳም ዕፀ በለስን በበላና ክብሩን ባጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሲጠይቀው እንዲህ አለ :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ::

ከዚያ በኁዋላ ግን እግዚአብሔር ለሔዋን :- ለምን ዛፉን ብላ ብለሽ ሠጠሽው? አላላትም:: "ያደረግሽው ምንድነው" ብቻ አላት::

እርሱ በሰዎች አስተያየት አይፈርድም:: ሌላው ስለ አንተ የሚለውን ትቶ አንተን ለብቻህ ይጠይቅሃል:: የሰዎችን ግምገማ አይሰማም:: እንደ ሃናንያ "ኸረ ጌታ ሆይ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ነበረኮ" ቢሉትም ቸል ብሎ ምርጥ ዕቃው ያደርግሃል:: በድንጋይ ልትወገር ይገባታል ሲሉት ክሱን ትቶ ከሳሾቹን ሊከስስ መሬት ላይ ይጽፋል::
ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጻፉ ጣቶቹ ዘማዊትዋን ሴት ነጻ ሊያወጣ አፈር ይጭራል::

ሰው ጨካኝ ፈራጅ እንደሆነ ያውቃልና በአዳም አስተያየት ሔዋን ላይ አይፈርድም:: "ያደረግሽው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቃት::

እግዚአብሔር ዛሬም ነፍሳችንን ይጠይቃታል::

ያደረግሽው ምንድር ነው? የአዳምን ክስ ሰምቻለሁ! ሰዎች ስለ አንቺ የሚሉትን አዳምጫለሁ:: አንቺ ግን ንገሪኝ:: ግራውን ሰምቼ አልፈርድም:: ምናልባት ቀኙን ብሰማ ይሻላል የሚል ርኅሩኅ አምላክ ነው::
እኛ የምንፈርድባቸው ሰዎች ሁሉ ቢጠየቁ የሚናገሩት የየራሳቸው የታሪክ ማዕዘን (side of the story) አላቸው::
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ሰምቶ አልፈረደም ሔዋንን ጠርቶ ጠየቃት
"ያደረግሽው ምንድር ነው
@THESECRETKNOWITFIRST
"ሰይጣን የማይነካው ዕቃ "

በአንድ ሐገር ድንገት የአንድ" ጠንቋይ ዝና ከዳር ዳር ተሰማ ። ሰውዬው የማያሳየው ምትሐት የለም። አንበሳ ላለ አንበሳ፣ ነብር ላለ ነብር፣ የሞተ ዘመዴን ላለ የሞተ ዘመዱን፣ የጠፋብኝን ዕቃ
ከቤት ፈልገህ አምጣልኝ ላለ ዕቃውን ያመጣለታል። እንደሚታወቀው አጋንንት ከክብራቸው የተዋረዱ መላእክት ናቸው። መላእክት ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ መገለጥ ይችላሉ። ይህ ጠንቋይ የሚሰጣቸውን ገጸ ባሕርይ ተቀብለው አንዴ አንበሳ፣ አንዴ ነብር፣ አንዴ ሰው እየሆኑ የሚተውኑት እንግዲህ አጋንንቱ ነበሩ። የበዚህ ጠንቋይ ዝና ወደ ንጉሱ ደረሰ። ንጉሱ ደግሞ ክርስቲያን
ቢሆንም ከመጸሐፍ ቅዱስ ይልቅ እንዲህ ያለ ተአምር እዚህ ቦታ ተፈጸመ ሲባል ለማየተት የሚሮጥ ሰው ነበር። ተአምር የሚወድ ሰው ደግሞ ክርስቲያንም ቢሆን ሰይጣን በሚሰራው ምትሐት
መታለሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ይህ ንጉስ የተማረውን መጽሐፍ ቅዱስ ዘንግቶ በጠንቋዩ ምትሐት አመነ።
ይህንን የሰሙ የንጉሱ ንስሐ አባት ነገሩን ሰምተው ወደ ቤተ መንግሥት ሲሮጡ ደረሱ። ሲደርሱ ንጉሡ ከቁም ነገር
አልቆጠራቸውም። እሱ የጠንቋይ ትርዒት ማየት ቀጠለ። "እስቲ አሁን ደግሞ እእእ ነጭ ፈረስ አምጣልኝ" ማለቱን ቀጠለ በነገሩ ያዘኑት "ኧረ ንጉሥ ሆይ ይተዉ፡ ይህ እኮ የሰይጣን ምትሐት ነው " ብለው ሊያስረዱት ሲሉ በቁጣ አስቆማቸው። ተአምር የሚከተል ሰው መቼስ ቢነግሩት አይሰማም። ጭራሽ
እንዲያው ለንስሐ አባቱ እንዲህ አላቸው። " የሰይጣን ስራ ነው አትበሉ፤ ቅናት ነው ይኼማ,,,, ይልቅ እርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ይጠይቁት ያምጣልዎት!"አላቸው። ጠንቋዩ «የፈለጉትን ላምጣልውት,,,,,ምን ይፈልጋሉ,,,, " የሞተ ዘመድ አለዎት,,,,, ወይስ ከቤትዎ,,,, » አላቸው በኩራት። ካህኑ ውስጣቸው በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጠለ። « እንግዲያውስ የፈለኩትን ማምጣት ከቻልህ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደህ ልብሰ ተክህኖዬ ውስጥ መስቀል አለ እርሱን ይዘህልኝ ና » አሉት።
ይህን ግዜ ጠንቋዩ ገና ድግምቱን ሲጀምር አጋንንቱ እላዩ ላይ ሰፍረው ጣሉት። በካህኑ ፊት ወደቀ። ሰይጣን ምንም ነገር ማምጣት ይችል ይሆናል። መስቀሉን ግን ማምጣት አይችልም።
አባቶቻችን ሰይጣን እንኳን መስቀል ቀርቶ መስቀለኛ መንገድም
አይወድም ይላሉ።

www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
አልወጣም ከቤቴ ቁ.፪

ክፍል ፩(1) ምንጭ 👉 የእግዚአብሔር ቃል

"መስታውት ለሰው ልጅ በጣም ከሚጠቅሙ ነገሮች ውስጥ አንዱና ትልቁ ነገር ነው..... ለማየት ለውበት ሳይሆን ለማንነት.... ነገሮችን እንደ አቀባበላችን ነው የሚለውንም ቃል በተግባር ያሳየኛል ለምሳሌ መስታውቱን ሳየው ምስቅ ከሆነ በመስታውት ማያትም አብራኝ ትስቃለች ማለቅስም ከሆነ እንደዛው... ይህ ከአቀባበሌ የሚጀምር ይመስለኛል ቀና አድርጌ ከተቀበልኳት ነገር ሁሉ በጎ ይሆንልኛል መጥፎ ካደረግኩትም እንዲሁ... ሀሳቤ ተበታተነ... ? "

ዘሀራ(የፈዲላ እናት) ፡- ፈዲላ ፈዲላ.....

ፈዲላ፡- አቤት እማ

ዘሀራ፡- ብቻሽን እያወራሽ ነው ደህና ነሽ??

ፈዲላ፡- አዎ እማ ደህና ነኝ አታስቢ ዝም ብዬ ከራሴ ጋር እያወራሁ ነው

ዘሀራ፡- እሺ ልጄ መልካም ነይ ለማንኛውም ምሳ ቀርቧል

ፈዲላ፡- እሺ መጣሁ እማ ትንሽ ልቆይ

ዘሀራ፡- የለም! ይህ ሳሙኤል የሚባለው ልጅ አንቺን ከማሳመም አልፎ የምግብ ፍላጎትሽንም ዘጋው?

ፈዲላ፡- አይደለም ስለበቃኝ እኮ ነው

ዘሀራ፡- ምን በልተሽ ነው ሚበቃሽ ልጄ ትናንት ቀን ሶስት ማንኪያ ሩዝ የቀመስሽ ኮ ነሽ! ኧረ ተይ ልጄ ራስሽን አትጉጂ

ፈዲላ፡- እሺ እማ መጣሁ

አለችና እምባዋን ጠራረገች ስለ ሳሙኤል ማሰብና ማሰላሰል ማቆም ያልቻለችው ፈዲላ እስከ ዛሬ ድረስ በልቧ አስቀምጣው በሱ ፍቅር ትሰቃያለች ምክንያቱም በጣም ወዳው ነበር።

ወደ ሳሎንም ገባች

ጀማል(የፈዲላ ወንድም)፡- ይህች ልጅ እስኳሁን ሳሙኤል ላይ ነች እማ? ፊቷ ያስታውቃል

ዘሀራ፡- ተው ጀማል! ዝም በይውና ነይ ተቀመጪ ልጄ

ፈዲላ፡- እሺ እማ ትቸዋለሁ

ዘሀራ፡- ይሄው ቆንጆ አድርጌ ነው ነው የሰራሁት ብይ ልጄ

ፈዲላ፡- እሺ አመሰግናለሁ

ጀማል፡- ፈዲላ እኔ ላንቺ አስቤ እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም ..... እንድታውቂው ብዬ ነው።

ፈዲላ፡- እሺ

ጀማል፡- ደሞ ከዚህ ካፊር...

እንዳለ ዘሀራ ከአፉ ቀማችና

ዘሀራ፡- ጀማል ስርአት ይኑርህ ደህና መብላት የጀመረችውን ልጅ አትረብሻት እንደውም እስክትጨርስ መኝታ ቤትህ ሁን ተነስ

ፈዲላ፡- ተይው እማ ሁሌ እንዲህ ስለሆነ ችግር የለውም ለምጄዋለሁ

ዘሀራ፡- ምን እየጠበቅክ ነው...... ተነስ እንጂ???

ጀማል፡- እሺ እሺ ተረጋጉ...ጉድ ኮ ነው ለአንዲት ቃል ወደ መኝታ ቤት መጠለዝ ስልችት ነው ያለኝ! " በማለት እያጉረመረመ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ። ፈዲላም ምሳውን ለመብላት እየሞከረች ቢሆንም ብዙ ሊገባላት አልቻለም።

በዚህ ሁኔታ ልቧ የተሰበረው የፈዲላ እናት ሁኔታዋን እያየች እጅጉን ታዝን ነበር።

ፈዲላ፡- ይጣፍጣል እማ በቃኝ

ዘሀራ፡- እንዴ ልጄ ምኑን በላሽ

ፈዲላ፡- እያየሽኝ እማ?

ዘሀራ፡- እሺ ልጄ አልጫንሽም ግን መኝታ ቤትሽ ከመግባትሽ በፊት ስለሆነ ነገር ላናግርሽ እፈልጋለሁ

ፈዲላ፡- እሺ እማ መልካም ታጥቤ መጣሁ" አለችና ወደ መታጠቢያ ቤት ገብታ ወዲያው ታጥባ መጣች።

ዘሀራ፡- እሺ ልጄ ላናግርሽ ያሰብኩት ነገር እዚህ ቤት ላንቺ ዝም ብሎ መቀመጥ ጥሩ አይደለም ስለዚህ ስራ ነገር ፈልገሽ ቢያንስ አይምሮሽን በሆነ ነገር ላይ ብታጠምጂው መልካም ነው ብዬ አስባለሁ

ፈዲላ፡- ይሻላል እማ እኔ መስራት አልፈልግም " ይህንን ያለችበት ምክንያት ስራውን ጠልታው ሳይሆን አሁን ካለችበት ሁኔታ የተነሳ የመስራትም ሆነ ነቃ የማለት ፍላጎቱ ስላልነበራት ነው።

ዘሀራ፡- አዎን ልጄ ብትወጪ ላንቺ መልካም ነው ደህናና ጥሩ ሁኔታ ላይ እንድትሆኙ ይጠቅምሻል ብትሰሪ ጥሩ ነው ባትፈልጊም ሞክሪው

ፈዲላ፡- እሺ

ዘሀራ፡- በእውነት ልጄ...... እሺ አልሽ

ፈዲላ፡- አዎ እማ ካልሽ እሞክረዋለሁ

ወዲያው ዘሀራ ስልክ አንስታ መደወል ጀመረች

ፈዲላ፡- እ... እማ ማን ጋር ነው ምትደውይው

ዘሀራ፡- አባትሽ ጋር ነ..... ሄሎ ሄሎ

መሀመድ፡- ሄሎ

ዘሀራ፡- ፈዲላ በትላትናው ጉዳይ ተስማምታለች አሁን መፈለግ ጀምር

መሀመድ፡- በእውነት. ..? ማሽ አላህ ማሽ አላህ አሁሁ አግኝላታለሁ ኢንሻላህ

ዘሀራ፡- እሺ መልካም ሰላም ዋል

ፈዲላ፡- ይሄን ያህል አሳስቤያችሁ ነበር ማለት ነው? በጣም ይቅርታ

ዘሀራ፡- ምን ማለትሽ ነው ልጄ ቤተሰቦችሽ ነን

ፈዲላ፡- አይ እንደሱ ለማለት አይደለም ይቅርታ በድጋሚ

ዘሀራ፡- አይ የኔ ልጅ መጥፎ ነገር እንዲነካሽ አልፈልግም አንቺ ሁሉ ነገሬ ነሽ በረካ ሁኚ" አለችና የበሉበትን ሰሀን ማነሳሳት ጀመረች።

ይቀጥላል............
http://www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
​​አልወጣም ከቤቴ ቁ. ፪

ክፍል ፪(2)

ፈዲላም ተነስታ ወደ መኝታ ቤቷ ተመልሳ ገባች። ወዲያው ተኛች

ከምሽቱ 2፡00 ሲሆን የልጇን ደህንነት እንደ ምጥ ምትጠባበቅ እናት በድጋሚ መኝታ ቤቷን እያንኳኳች "ፈዲላ ተነሽ እራት ቀመስ አድርጊና ትተኛለሽ" ትል ጀመር። ፈዲላም ነቅታ ስለነበር "እሺ" አለቻት

ወደ ሻውር ቤት ገብታ ከተጣጠበች በኋላ ወደ ሳሎን ገባች

መሀመድ፡- ልጄ እንደምን አመሸሽ ነይ አጠገቤ

ፈዲላ፡- አባ አለሁ" እያለች አጠገቡ ቁጭ አለች

መሀመድ፡- ጥሩ ዜና አለኝ

ፈዲላ፡- ምንድን?

መሀመድ፡- ስራ አግኝቼልሻለሁ! ከአሁን በኋላ ራስን መጉዳት ቀን መተኛትና በድብርት መዋል የለም ስራ ትሰሪያለሽ አይምሮሽም ይመለሳል

ፈዲላ፡- እሺ" ከማለት ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ አልነበራትም

ዘሀራም እራት አቀረበች ከወንድሞችና ከእህቶቿ ጋር እራቷን በላችና ተኛች። በነጋታውም መሀመድ ፈዲላን ቀሰቀሳትና "ዛሬ መስሪያ ቦታሽን አሳይሻለሁ ስራም ትጀምሪያለሽ ቶሎ ቶሎ ተዘጋጂ እንዳይረፍድብን" አላት።

ከተዘገጃጁም በኋላ አብረው ወደ ስራ ቦታ ሄዱ መሀመድም ስለ ፈዲላ በጣም ያስብ ነበርና ከድብርት እንድትወጣ የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳት ያዋራት ያወያያትም ነበር። በመጨረሻም ስለ ሀይማኖት አንድ ጥያቄ ጠየቃት

መሀመድ፡- ልጄ ግን ቁርአን አንብበሽ ታውቂያለሽ?

ፈዲላ፡- አዋ አባ ለምን አላነብም አነባለሁ

መሀመድ፡- እና በሀይማኖትሽ ትክክለኝነት እርግጠኛ ነሽ?

ፈዲላ፡- ይህን መመለስ ምችለው ሁሉም ሀይማኖቶች ውስጥ ያለውን ነገር መርምሬ ነው ስለዚህ አሁን የኢስላምን ትክክለኝነት በእርግጠኝነት አላቅም

መሀመድ፡- ወይ ልጄ እኔ አባትሽ ኡስታዝ ሆኜ አንቺ በኢስላም ሀይማኖት እርግጠኛ አይደለሁም ትያለሽ?
ስለ እስልምና መፅሀፉን አንብበሽ ተፍሲሩን ተረድተሽ ልትደርሺበት ትችያለሽ አንዲትም ስህተት የለውም! ነገር ግን ስለ ክርስትናና ስለ መፅሀፍ ቅዱስ ትክክል አለመሆን እኔ አባትሽ በደንብ አድርጌ አስተምርሻለሁ ኢንሻላህ።

በነገራችን ላይ ተወዳጆች ይህ ስልት ብዙዎች ወደ ክርስትናው አለም እንዳይመጡና ክርስትናና መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የተለየ አመለካከት እንዲኖራቸው ከሚደረጉባቸው መነገዶች አንዱ ሲሆን የብዙ ሙስሊሞች ነፍስ መጥፋት ምክንያት ከሆኑት ዋነኛው ነው። ከኡስታዝ መፅሀፍ ቅዱስንንና ክርስትናን መማር"

ፈዲላ፡- እሺ አባ መልካም

መሀመድ፡- ጥሩ ልጄ ከዛን ኢስላም በፈጣሪ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሀይማኖት እንደሆነ ሌሎቹ በጠቅላላ ከንቱ እንደሆኑ ትረጃለሽ

ፈዲላ፡- እሺ

ብዙ ከተጓዙ በኋላ ስራ ቦታ ደረሱ ወደውስጥም ከገቡ በኋላ በአንድ ክርስቲያን ጓደኛው ጋር የምትሰራበትን ቦታ ምን እንደምትሰራና ምትገባበት የምትወጣበትን ሰአት በሙሉ እንዲያብራራላት አደረገ። ፈዲላም ስራውን ስትገምተው የምትወጣበትም የምትገባበትም ሰአት እንዲሁ ምቹ ስለሆነ በሀሳቡ ደስ ተሰኘች

ፍቃዱ(የመሀመድ ጓደኛ)፡- ዛሬዉኑ ስራሽን መጀመር ትችያለሽ እኔ ቀጥሎ ያለው ቢሮ ስለሆንኩ የፈለግሽውን ነገር ልትጠይቂኝ ትችያለሽ

ፈዲላ፡- እሺ አመሰግናለሁ " አለችና ወደ ተጠቆመችበት ቢሮ ገባች አራት ሴቶችም ነበሩ። ሰላምታም ከተቀባበሉ በኋላ የተዘጋጀላት ቦታ ላይ ተቀመጠች።

ማህተምን በመምታት ሌሎች ስሮችንም በመሰራራት እንዲሁ እስከ 10 ሰአት ድረስ ቆየች በዛን ቀን ስራው ትንሽ አይምሮዋን ጠምዶት ስለነበር ስለ ሳሙኤል ብዙ አላሰበችም ነበር።

የሚወጡበት ሰአት በደረሰ ጊዜ ወደ ኋላ ቀረት ያለችውን ሰራተኛዋን ልትግባባት ፈልጋ ነበርና

ፈዲላ፡- ይቅርታ ሁሌ በዚህ ሰአት ነው የምንወጣው?

ኤልሳቤጥ ፡- አዎን እህት በዚህ ሰአት ነው ሁሌ የምንወጣው

ፈዲላ፡- መልካም እንተዋወቅ ፈዲላ እባላለሁ ፈዱ በይኝ ክክክክ

ኤልሳቤጥ ፡- ክክክክ እሺ ፈዱ እኔ ደግሞ ኤልሳቤጥ እባላለሁ

ፈዲላ፡- መልካም ስለተዋወቅኩሽ ደስ ብሎኛል

ኤልሳቤጥ፡- እኔም

ፈዲላ፡- እሺ ንገሪኝ ምን አይነት ሰው ነሽ ምን ትወጃለሽ ምን ትጠያለሽ" እያወሩና እየተግባቡ ወደ ታክሲ መያዣ ደረሱ። ፈዲላም መኪና አልያዘችም ነበርና ታክሲ የግድ መሳፈር ነበረባት።

ከተለያዩም በኋላ ፈዲላ ወደ ቤቷ እንደገባች እጅጉን ተደሰተች ቀኑን መልካም ና ጥሩ በሆነ ሁኔታ ስላሳለፈች እንዲሁም አንዲስ ጓደኛ ስለተዋወቀች ስሜቷ አሪፍ ነበር።

ይህንን ሁኔታ የተመለከተችው የፈዲላ እናት ዘሀራ እጅጉን ደስ አላት ልጄ ተመለሰችልኝ በማለት ፈጠረኝ ብላ ምታስበውን አካለ እጅጉን አመሰገነች። መሀመድም ተጨንቆ ነበርና ይህንን ሁኔታ ሲያይ ይህንኑ አደረገ ።

መሀመድ፡- ፈዲላ ደክሞሻል እንዴ

ፈዲላ፡- አይ አባ ምነው

መሀመድ፡- ስለ ጠዋቱ ውይይት ከዛሬ እንድንጀምር ብዬ ነው ሀይማኖታዊ ጥናት

ፈዲላ፡- አይ አልደከመኝም እሺ ተታጥቤ መጣሁ

መሀመድ፡- እሺ የኔ ልጅ "አለና ወደ ሳሎን ተመልሶ መፅሀፍቶቹን ማዘገጃጀት ጀመረ። እንደጨረሰችም ወደ ሳሎን ዘለቀች መሀመድም "መጣሽ ልጄ ቁጭ በይ" አላት ቁጭም አለች።


መሀመድ፡- እንግዲህ አሁን የምታያቸው መፅሀፍት ባይብልና ቅዱስ ቁርአን ናቸው ሁለቱም የአላህ ቃል ናቸው ነገር ግን ባይብል በአይሁድና በክርስቲያኖች ስለተበረዘ የምንቀበለው ነገር በጣም ትንሹን ነው።

ፈዲላ፡- እሺ አባ ለምን ተበረዘ

መሀመድ፡- እነሱ የሚፈልጉትንና ከኑሯቸው ጋር ሊስማማ ሚችለውን ነገር መጨመር ስለኖረባቸው ነው።

ፈዲላ፡- እሺ

ይቀጥላል...........
@THESECRETKNOWITFIRST
አልወጣም ከቤቴ

ክፍል 3(፫)

መሀመድ፡- እሺ እንቀጥል

ፈዲላ፡- አዎ

መሀመድ፡- መልካም አሁን በማሳይሽ መፅሀፍቶች ላይ እንደምናየው አላህ ከአደም ጀምሮ እጅግ ብዙ ነብያትን ወደ ምድር ልኳል ኢሳንም ጨምሮ

ፈዲላ፡- ኢሳ ና ኢየሱስ አንድ ናቸው ግን?

መሀመድ፡- አዎ ልጄ

ፈዲላ፡- ታዲያ ለምን መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ኢሳ አምላክ እንደሆነ ተናገረ?

መሀመድ፡- የት ነው የተናገረው? አንድም ቦታ ላይ ኢሳ አምላክነቱን የተናገረበት ቦታ የለም!

ፈዲላ፡- ኧረ አለ አባ እኔ መፅሀፍ ቅዱስን ብዙ ባላነብም ከሳሚ ጋር በነበርኩበት ሰአት ይህንን ነገር አንብቢያለሁ

መሀመድ፡- እሺ የታል?

ፈዲላ፡- የት እንዳለ አላቅም ግን መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ሀሳብ እንዳለ አውቃለሁ!

መሀመድ፡- አትሳቺ መስሎሽ ነው ኢሳ ራሱን አምላክ ያደረገበት አንድም ቦታ ላይ የለም!

ፈዲላ፡- እሺ ታዲያ መፅሀፍ ቅዱስ እንደዛ ካላለ ክርስቲያኖች ለምን ያመልኩታል?

መሀመድ፡-....... ልጄ እነሱ የኢሳን ማንነት በደንብ ስላላወቁ ነው

ፈዲላ፡- እሺ

መሀመድ፡- ኢሳ በመፅሀፍ ቅዱስም ሆነ በቁርአን እራሱን አምላክ አድርጎ አያውቅም ክርስቲያኖች ኢሳን የሚያመልኩት እሱ አምላክ ነኝ ስላለ ሳይሆን ተአምራቱንና የሚያደርጋቸውን ድንቅ ስራዎች ስለሰራ ነው እንጂ አላህን ተገዙ እሱን አምልኩ ሊል ነው ወደ እስራኤል የተላከው

ፈዲላ፡- እሺ አባ

መሀመድ፡- እሺ ማወቅ ምትፈልጊው ነገር ምን እንደሆነ ጠይቂኝና እንወያይበት

ፈዲላ፡- ስለ ኢሳ ማንነት በደንብ ብትነግረኝ ደስ ይለኛል

መሀመድ፡- እሺ ኢሳ አንድ በእስራኤል የተወለደ የአላህ ባሪያ የሆነ ክቡር መልእክተኛ ነው። አላህም ኢሳን የላከበት ምክንያት አይሁድን ወደ አላህ ተመለሱ የኔም የእናንተም ጌታ የሆነውን አምልኩ ሊል ነው። ግን ክርስቲያኖች እንደ አምላክ ተቀበሉት አይሁዶችም ይህንን ቃል ሲሰሙ በሱ ላይ አደሙ አላህን ተገዙ ስላላቸው ሊገድሉት ፈለጉ.... ከዛም ጌታችን የኢሳን መልክ ለአንዱ ደቀ መዝሙር ሰጠው አይሁድም እሱን አጊንተው ሰቀሉት ኢሳ ግን አልሞተም አላህ ነጥቆታል አይሁድም ኢሳን እንደሰቀሉት ያምናሉ ለዚህም አላህ ረግሟቸዋል ቁርአን 4፡157 የኢሳ ማንነት በአጭሩ ይህ ነው ልጄ በመጨረሻም መጥቶ መስቀሎችን ይሰባብራል ብዙ ነገሮችም ያደርጋል ነብያችን በሀዲሳት ይህንን በደምንብ ያስረዳናል ልጄ "

ይህንን ሁሉ ሲነገራት ማስታወሻ እየያዘች ነበረና ቃሉን ለመረዳት ብዙ አልከበዳትም ነበር ማወቅ የፈለገችውን ሁሉ ያወቀች ስለመሰላት

ፈዲላ፡- እሺ አባ አመሰግናለሁ ሳነብ ያልገባኝ ነገር ካለ እጠይቅሀለሁ

መሀመድ፡- እሺ ልጄ በደንብ ቁርአንን ሀዲሳትን ማንበብ ጥሩ ስለሆነ አንብቢና ያልገቡሽ ነገሮች ካሉ ትጠይቂኛለሽ

ፈዲላ፡- እሺ ኢንሻላህ .....

ዘሀራ፡- ጨረሳችሁ እናንተን ነበር እየጠበቅን የነበረው

መሀመድ፡- ጨርሰናል አሁን መብላት እንችላለን

ዘሀራ፡- መልካም ኑ እንደምታዩት አቀራርቤዋለሁ

ፈዲላ፡- እሺ ኡሚ መጣን

እራታቸውንም ተሰባስበው በፍቅር መንፈስ እየተጫወቱ ከበሉ በኋላ የሀይማኖይ ስርአታቸውን ፈፅመው ተኙ

በማግስቱም ፈዲላ ተነቃቅታ ነበረና በጠዋት ተነስታ መኝታ ቤቷን አፀዳድታ ሻውር ወስዳና ቁርሷን በልታ በመኪናዋ ወደ ስራ ቦታ ሄደች። እንዲህ በተነቃቃት ሰላም ባለው መንፈስ ስራ ቦታ እየዋለች ሁለት ሳምንታትን አሳለፈች።

ከእለታትም በአንዱ ቀን ወደ ስራ ቦታ ስትሄድ "ጊዜ ካለኝ አነበዋለሁ" ብላ መሀመድ ሲያስተምራት የነበረውን ትምህርት የፃፈችበትንም ማስታወሻም ይዛው ወደ ስራ ቦታ ሄደች።

እንደ ገባችም ማንም የለም ነበር ቦታዋ ቁጭ ብላ አንዳንድ ዶክመንቶችን ማስተካከል ጀመረች ቀስ እያሉ ባልደረቦች መምጣት ጀምሩ። በመጨረሻም ኤልሳቤጥ መጣች መቀመጫዋ ጋር ከመሄዷ በፊት ፈዲላን ሰላም ልትል ወደ እሷ ሄደች። ፈዲላም አላየቻትም ነበር ያንን ማስታወሻ በእጇ ይዛ እያነበበች እንዳለ

ኤልሳቤጥ፡- ፈዱ እንዴት አደርሽ

ፈዲላ፡- እ... ሰላም ነው ኤልሲ

ኤልሳቤጥ፡- እግዚአብሔር ይመስገን ምነው ደነገጥሽ ክክክ

ፈዲላ፡- ክክ አይ አላየሁሽም ነበር ለዛ ነው አስደነገጥሽኝ

ኤልሳቤጥ፡- መልካም ፈዱ" አለችና ወደ ቦታዋ ሄዳ ተቀመጠች

ከብዙ ስራ ና መላላክ በኋላ ምሳ ሰአት ደረሰ ፈዲላም ወደ ኤልሳቤጥ ጋር ሄዳ "ምሳ ሰአት ስለደረደረሰ ወጣ ብለን እንብላ" አለቻት። ኤልሳቤጥ ትንሽ የሚቀራት ስራ ነበረና አቆየቻት እንደጨረሰችም አብረው ወደ ሆነ ካፌ ገቡ።

ምሳቸውንም ከአጠናቀቁ በኋላ ኤልሳቤጥ ፈዲላ ጠዋት ታበነበው ስለነበረው ወረቀት ጠየቀቻት። ምክንያቱም የፈዲላ ድንጋጤ ሳታያት ቀርታ ስለነበረ ሳይሆን ስለ ወረቀቱ እንደሆነ እያወሩ እንዳለ ወረቀቱን ለመሸፈን ስታሳይ በነበረውን እንቅስቃሴ ተረድታው ነበር።

ፈዲላ፡- ዝም ምሎ ግጥም ነው ምነው?

ኤልሳቤጥ፡- አይ እንዳየው የፈለግሽ አልመሰለኝም ያን አስቤ ነው

ይቀጥላል.......
www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
🕯🕯የደግነት ጫፍ🕯🕯

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል... ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል።

አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል ...ከመስኮት አጠገብ ነው።ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል።

እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት
እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል።

".....በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ .. ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ "
በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ ይተርክለታል! ... በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።

አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው የተቀመጠው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ።
ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን ጠርታ አዘዘቻቸቸው ...

ያ ብቻውን የቀረው በጀርባው የተኛው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ እንዲወስዱለት ጠየቀ ወሰዱለት።

ሟች የነገርውን በሙሉ በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ
ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!

"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ። "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች
ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት። "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል #አይነስውር ነበር
አለችው።"

ልብ የሚነካ ነገር.... ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።
**
አንዱን ለማጠንከር ወይም ለማበርታት የኛ ጥንካሬና ብርታት አስፈላጊ ነው።
ለሰወች ደግ ነገር በማድርግ
የተጨነቀ አምሮአቸውን ዘና
እናድርግ

@THESECRETKNOWITFIRST
አልወጣም ከቤቴ

ክፍል ፬(4)

ፈዲላም ኤልሳቤጥ ያን ነገር ስትላት ደነገጠች። ልትዋሻትም ስላልፈለገች ስለ ኢሳ አባቴ ያስተማረኝን ትምህርት እያነበብኩ ነበር አንቺ ኢሳን ስለምታመልኪው ማስታወሻው ላይ የፃፍኩትን ነገር ብታነቢው ብዙም ደስ አይልሽም ብዬ ነው ለዛ ነው።

ኤልሳቤጥ፡- ኢሳ ማን ነው?

ፈዲላ፡- ኢየሱስ ነዋ

ኤልሳቤጥ፡- መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ኢየሱስ እያልሽ ባልሆነ

ፈዲላ፡- አዎ ነው

ኤልሳቤጥ፡- አትሳሳቺ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ኢየሱስ ኢሳ አይወክልም ስለ ኢየሱስ በቁርአናችሁ የተፃፈው ነገር በሙሉ ስህተት ነው ስለዚህም ኢሳ ኢየሱስ አይደለም

ፈዲላ፡- መፅሀፍ ቅዱሳችሁ ስለተበረዘ ነው እንዲህ ያልሽው እንጂ ቁርአን ስለ ኢሳ ማንነት በተሳሳተ መንገድ አልመዘገበም

ኤልሳቤጥ፡- ፈዱዬ መፅሀፍ ቅዱስ አልተበረዘም ይህ የእናንተ አስሳሰብ ነው እኔ መከራከር አልፈልግም ግን አንቺ የውይይት ፍላጎት ካለሽ እንማማራለን

ፈዲላ፡- እኔም አልወድም ግን ብንማማር ጥሩ ይመስለኛል

ኤልሳቤጥ፡- እሺ ፈዱ መልካም ሰአቱ ስለደረሰ ወደ ስራ ቦታ እንመለስ

ፈዲላ፡- ጥሩ ነገ ግማሽ ቀን ስለሆንን ለምን ከሰአት በኋላ አንቺም ባይብልሽን እኔም ቁርአኔን ይዤ እውነትን አንፈልግም

ኤልሳቤጥ፡- መልካም ይቻላል እንሂድ

ወደ ስራ ቦታም ተመልሰው ስራዎቻቸውን ከጨረሱ በኋላ የመውጫው ሰአት በደረሰ ሰአት ፈዲላ ኤልሳቤጥን ቤቷ ድረስ ሸኘቻትና እሷም አምሽታ ገባች ራቷን በልታ ተኛች።

በጠዋትም እንደለመደችው መኝታ ቤቷን አፀዳድታና ሻውር ወስዳ ቁርሷንም በልታ ዝግጅቷን ጨረሰች። ቁርአንንም በቦርሳዋ ይዛ ወደ ስራ ቦታ ሄደች። ቀኑም ቅዳሜ ስራ ሚጨርሱት ከሰአት ነው ።

እንደጨረሱም ከኤልሳቤጥ ጋር እንደተቀጣጠሩት ወደ ካፌ ገብተው ምሳቸውን በልተው ውይይታቸውን ጀመሩ።

ፈዲላ፡- እሺ ስለ ኢየሱስ ነበር እንወያያለን የተባባልነው

ኤልሳቤጥ፡- አዎ ነገሮችን በብዙ አቅጣጫና መስመር በመመልከት ሁለታችንም ትክክለኛውን ነገር እንድንረዳ የእዚህ አለም ፈጣሪ ይርዳን ራሱን ይግለጥልን

ፈዲላ፡- አሚን

ኤልሳቤጥ፡- አሁን በምሰጥሽ ሀሳብ ኢየሱስን መመልከት ያለብን ይመስለኛል ሀሳቤን ከነገርኩሽ በኋላ ማትስማሚበት ከሆነ ትነግሪኛለሽ

ፈዲላ፡- እሽ

ኤልሳቤጥ፡- ጥሩ ስለአንድ ሰው ታሪክ ለማወቅ ለምሳሌ በአንድ ወቅት በሀገራችን ላይ ንጉስ በነበረ ሰው ላሊበላ እንመልከት ካልን ስለ ላሊበላ ታሪካውያንን ብዙ ነገሮች ሊፅፉ ይችላሉ። ከላሊበላ ጋር አብረውት የዋሉት አብረው ያደሩት ሰዎች ማንነቱንና ተግባራቱን የሚያውቁ ሰዎች ስለሱ አንድ ነገር ፃፉ ታሪኩንም ስለማንነቱም ማንነቱ እንዲህ ነው ብለው ፃፉ ከዚያም ከብዙ አመታት በኋላ አንድ ሰው ተነስቶ ላሊበላ እንዲህ ሳይሆን እንዲህ ነው ብሎ ፃፈ ማለትም ከላሊበላ ባለንጀሮች ጋር የሚጣረስና እነሱ ነው ያሉትን የሚያፈርስ ማንነት ና ተግባራት ፃፈ ስለዚህ የትኛውን ነው ማመን ያለብን? ሀሳብሽን ንገሪኝ

ፈዲላ፡- የላሊበላ ባለንጀሮች የፃፉትን ነው

ኤልሳቤጥ፡- ትክክል ብለሻል ፈዲላ ከዚህ ሀሳብና አመለካከት ሳትወጪ የክርስቶስንም ማንነት ማን በትክክል እንደተናገረ እንየው

ፈዲላ፡- እሺ መልካም" አለችና የምትላትን ለማዳመጥ ዝግጁ ሆነች። ፈዲላ እንደ አባቷ ውሸትን ማሳመንና ህሊናን መሸጥ አታቅም እውነት የሆነውን ነገር ማወቅ ስለምትፈልግ ሁሉን በቀና አመለካከት በመመልከት ትክክል ከሆነ መቀበል ካልሆነ አለመቀበል ነው አላማዋ ። ስለዚህም ኤልሳቤጥ ምትላትን ነገር ለመስማት ጆሮዋን ሰጠቻት

ኤልሳቤጥ፡- እሺ ስለ ኢየሱስ ውይይታችንን ስንጀምር ኢየሱስ ከ፪ሺ አመት በፊት በእስራኤል ይመላለስ የነበረ አንድ አይሁድ ነበር። ከሀይማኖት ነጠል ብለን ሁሉንም በሌሎች አቅጣጫዎች እንድናይ ብዬ ነው

ፈዲላ፡- አዎ ገብቶኛል

ኤልሳቤጥ፡- መልካም ስለዚህ ስለ ኢየሱስ ማንነት ለማወቅ ኢየሱስ በነበረበት ዘመን የነበሩትን ሰዎች መጠየቅ አለብን

ፈዲላ፡- ልክ ነሽ

ኤልሳቤጥ፡- ጥሩ ስለዚህ እሱ በነበረበት ሰአት ምን ያደርግ እንደነበርም ማንነቱስ ማን እንደነበር እራሱን ማን ብሎ ይጠራ እንደነበር ከሱ ጋር ሲበሉ ሲጠጡ የነበሩ ሀዋርያት ስለሱ በዘመናቸው ብዙ ነገሮችን ፅፈዋል ስለሱ እነዚህን ሀዋአያት መቀበል አለንብን ።

ፈዲላ፡- አዎ ባለንጀሮቹ ከሆኑና እሱ በነበረበት ዘመን ስለራሱ ያለውንና ያመኑትን ነገር ከፃፉ

ኤልሳቤጥ፡- በጣም ጎበዝ አዎን ከዛን ከ600 አመት በኋላ በአረብ ምድር የተወለደ አንድ መሀመድ የተባለ ሰው ስለ ኢየሱስ በተቃራኒው መንገድ እና ከኢየሱስ ጋር አብረውት ሲበሉና ሲጠጡ የነበሩት ሰዎች ከመዘገቡት በሚፋለስ መልኩ ስለሱ ተናገረ ስለዚህ ፈዲላ ንገሪኝ እኔም አንቺም ስለ ኢየሱስ ለማወቅ የቱን ማመን አለብን??

ፈዲላም ይህንን ኤልሳቤጥ ስትጠይቃት ልቧ ደነገጠ ነገሩ እውነት ቢሆንም ይህንን እውነት ብትመልስ ቁርአንን ውሸት ማድረጓ ነው በሌላኛው መንገድ ደግሞ ብትወሽ በወሸት መንገድ እውነተኛውን ፈጣሪ ማግኘት እንደማይቻል ስለምታውቅ በህሊናዋ ተመርታ ትክክለኛውን መልስ መለሰችላት

ፈዲላ፡- የቀደሙትን

ኤልሳቤጥም በውስጧ በጣም ደስ አላት ይህች ልጅም ልትድን የምትችል እግዚአብሔር የጠራት ምስኪን ነፍስ ናት ከአሁኑ በህሊናዋ ምትመራና ማትዋሽ እውነትን ፈላጊ ከሆነች እግዚአብሔር ቢረዳት ትድናለች" አለች።

ኤልሳቤጥ፡- በጣም ጥሩ ፈዲላ አንድ ነጥብ እንጨምር ሀዋርያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የፃፉት ሙሉ ታሪኩን የገባበትን የወጣበትን ከአንድ 4 ሰዎች ፅፈውለታል ግን ቁርአን ላይ ይህንን አይናገርም ስለ ክርስቶስ ታሪክ የገባበትንና የወጣበትን አይናገርም በመርየም ትንሽ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ እነሱም ከየት እንደመጡ እናያለን ግን እንድታውቂ ምፈልገው ቀዳሚው መፅሀፍት ሙሉ ታሪኩ የሚገኝበትንም መፅሀፍ እንደሆነ ነው።

ፈዲላ፡- እሺ አምኛለሁ ካልሽው ነገር ላይ አንድም ስህተት የለም

ኤልሳቤጥ፡- መልካም ተባረኪ ስለዚህ ስለ ኢየሱስ ለማወቅ መፅሀፍ ቅዱስን ነው ቁርአንን መጠየቅ ያለብን

ፈዲላ፡- መፅሀፍ ቅዱስን

ኤልሳቤጥ፡- በትክክል መልካም ከሀይማኖት ወጣ ብለን ነገሮችን በተለያዩ መንገዶች ስንመለከት የምንግባባቸው ሀሳቦች ይከፈቱልናል አየሽ ስለዚህ አሁን በመፅሀፍ ቅዱስ ሀሳብ ኢየሱስ ማን ነው የሚለውን ነገር እንወያያለን።

ይቀጥላል..........
@THESECRETKNOWITFIRST
አልወጣም ከቤቴ

ክፍል ፭(5)

ፈዲላም በሀሳቧ ተስማማች ። ኤልሳቤጥም ታሪኮችን ከቁርአንና ከመፅሀፍ ቅዱስ ወጥተው መመርመር እንዳለባቸው ሀሳብ አነሳች። ከታሪክ ጋር የሚፋለስ ሀሳብ ይኑር አይኑር የራሷን መፅሀፍ እንድትመረምርም ለፈዲላ ነገረቻት ሁለቱም በዚህ ሀሳብ ተስማሙ።

ከዚያም በመጨረሻ ኤልሳቤጥ "የኢየሱስን ማንነት ምንጠይቀው መፅሀፍ ቅዱስን እንደሆነ ስለተስማማን ፈዲላ በተቻለሽ መጠን ወንጌልን አንብቢውና ቀጣይ ውይይታችን በወንጌላት ላይ ይሆናል።

ፈዲላም በድጋሚ በሀሳቡ መስማማቷን ከገለፀችላት በኋላ ቻው ተባብለው ወደየቤታቸው ሄዱ።

ዘሀራ፡- መጣሽ ልጄ ግቢ ደክሞሻል መሰለኝ

ፈዲላ፡- አዎ እማ ትንሽ

ዘሀራ፡- ዛሬ ከሌላው ቀን በተለየ ዘገየሽ በሰላም ነው?

ፈዲላ፡- አዎ ኡሚ ከጓደኛዬ ጋር ስለሆነ ጉዳይ እየተወያየን ነበር

ዘሀራ፡- መልካም የሚበላ ላምጣልሽ ቆይ....

ፈዲላ፡- አይ አይ ቆይ እማ ጥግብ ብያለሁ ባይሆን መክሰስ ወደ በኋላ እበላለሁ

ዘሀራ፡- እሺ ልጄ እንዳልሽ

ፈዲላም ወደ መኝታ ቤቷ ገብታ ለብዙ ደቂቃዎች አረፈችና ሻውር ወስዳ ከአባቷ ቢሮ ውስጥ መፅሀፍ ቅዱስ ወሰደች።

መኝታ ቤቷ በሚገኘው ማብበቢያ ቦታ ቁጭ ብላ የዮሀንስ ወንጌል የት እንዳለ ማውጫ ላይ ትመለከት ነበር።

ገልጣም ካገኘችው በኋላ መጀመሪያ ላይ ያነበበችው ምንም ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም ነበር ከዛን ሌላ ወንጌል ለማንበብ አሰበች። የሉቃስ ወንጌልን ሳሚ ቤት እያለች የጌታን ትምህርት መርጣ ታነብ ስለነበር በጣም ትወደዋለች ስለዚህም እሱን ለማንበብ አስባ ሉቃስ ወንጌል ላይ ገባች ።

እስከ ምእራፍ ሶስት ድረስ ስታበበው የክርስቶስን ክብር በጣም ተረዳች ከዚህ በፊት የሉቃስ ወንጌል ላይ የክርስቶስን ትምህርት መርጣ ታነብ ስለነበር ስለ ማንነቱ አንብባም አስተውላም አታቅም ነበር።

የክርስቶስን ክብር የሚገልጥበት ጥቅስ በምታነብበት ሰአት ልቧ በጣም ይደነግጥ ነበር። ያ ሁሉ ክብርንና የተወለደበት አላማ የሰው ልጅን ለማዳን እንደሆነ ትንሽ ምልክት ሰጥቷት ነበር ።

እንዲህ እያለች ብዙ አነበበች ከዚያም መሽቶ ስለነበር ራቷን በልታ ተኛች።

ከአንድ ቀን በኋላም ከስራ በኋላ ከጓደኛዋ ኤልሳቤጥ ጋር ካፌ ቁጭ ብለው ስለዚሁ ጉዳይ ያወሩ ነበር።

ኤልሳቤጥ፡- እሺ ፈዱ ወንጌል ላይ ስለ ኢየሱስ ምን አወቅሽ

ፈዲላ፡- ኤልሲ ልዋሽሽ አልፈልግም ከዚህ በፊት መፅሀፍ ቅዱስ ተበርዟል ተከልሷል ተብለን ስለምንመከር ምንም ያህል ስለ ኢሳ ክብር ቢናገር ቢያወራ ክርስቲያኖች እንዲያነቡ የፈለጉትን የጨመሩበት እና ማይፈልጉትን የቀነሱት ነው ብዬ አስብ ስለነበር ምንም አይመስለኝም ነበር ነገር ግን ኢየሱስ በመፅሀፍ ቅዱስ ትልቅ ክብር እንዳለው ከሉቃስ ወንጌል 3 ምእራፉ ብቻ ይናገራል ይህም በጣም እረፍት እየሰጠኝ አይደለም ልቤ ድንጋጤ ውስጥ ነው። ንገሪኝ ኢየሱስ ማን ነው ማንነቱን ማወቅ እፈልጋለሁ

ኤልሳቤጥ፡- እሺ በጣም ጥሩ ፈዲላ ኢየሱስ አለምን የፈጠረ አምላክ ነው አሁን ውይይታችንን በቀላል መንገድ እንጀምረውና አንቺ አንድ አካል አምላክ ለመባል ማሟላት ያለበትን ነጥቦች ትነግሪኛለሽ እኔ ደግሞ ያን ነገር ኢየሱስ ያሟላል አያሟላም የሚለውም ነገር ቀጥዬ አሳይሻለሁ።

ፈዲላ፡- እሺ በመጀመሪያ አምላክ ሰማይና ምድርን መፍጠሩ ነው አምላክ የሚያስብለው ኢየሱስ ሰማይና ምድርን ፈጥሯል?

ኤልሳቤጥ፡- አዎን ሰማይና ምድርን የፈጠረው ኢየሱስ በስጋ ማርያም ተገልጧል ዮሀ 1፡1-14

ፈዲላ፡- ይህ ቃል ባለፈው ሳነበው አልገባኝም ነበር

ኤልሳቤጥ፡- አዎን ልክ ነሽ እንዲሁ ስናነበው ቶሎ ሊገባን ስለማይችል ነው ቁጥር አንድን ካብራራሁልሽ ከዛ በኋላ ያለው ይገባሻል
❝በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።❞
—ዮሐንስ 1: 1
በመጀመሪያ ቃል ነበር ሲል አለም ከመፈጠሩ ዘመን ከመቆጠሩ በፊት ከሁሉ አስቀድሞ ቃል ነበር ማለት ነው
ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ማለት ያ አለም ሳይፈጠር ዘመን ሳቆጠር የነበረው ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ከእግዚአብሔር ጋር ነበር ይለናል
ቃልም እግዚአብሔር ነበር ማለት ያ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል በመጀመሪያ የነበረው ቃል ራሱ እግዚአብሔር ነበር ማለት ነው። ከዛን ሁሉም በእርሱ ሆነ ብሎ ይቀጥላል አለም በሱ እንደተፈጠረ የሚናገር ነው ስለዚህም በእዚህ ቃል በተባለው አካል አለም ተፈጠረ ይለንና 14 ቁጥር ላይ ቃል ስጋ ሆነ ይላል ስለዚህም በስጋ ማርያም የተገለጠው ክርስቶስ በቃልነት ሳለ አለምን መፍጠሩን ያሳያል።

ፈዲላ፡- ይገርማል በጣም ስለዚህ ኢየሱስ አለምን ፈጥሯል ማለት ነው? ጅማሬው ከመርየም ሲወለድ አይደለም?

ኤልሳቤጥ፡- አይደለም ቅድም የሰጠሁሽ ማስረጃ መረጃ ኢየሱስ አለምን መፍጠሩን ያሳያል እና እሱ ጅማሬው ከድንግል ማርያም ሲወለድ እንዳልሆነ በራሱ አንደበት ሲናገር መፅሀፍ ቅዱስ ላይ እናየዋልውን። አብረሀምን ወይንም በእናንተ ኢብራሂምን የምታውቂው ይመስለኛል አይደል

ፈዲላ፡- አዎን የአላህ ሰላም ይውረድበት አውቀዋለሁ

ኤልሳቤጥ፡- መልካም በስንተኛው ክፍለ ዘመን ነበሩ እና ከኢየሱስና ከአብረሀም ማን ነው ቀድሞ የተወለደው?

ፈዲላ፡- እንዴ ኢብራሂም በጣም ቆይተዋል

ኤልሳቤጥ፡- መልካም ስለዚህ አብረሀም ከኢየሱስ ይቀድማል አብረሀም በተወለደበት ሰአት ኢየሱስ አልነበረም ማለት ነው ጅማሬው ከድንግል ከሆነ

ፈዲላ፡- አዎን

ኤልሳቤጥ፡- ጥሩ ፈዱ ይህንን ቃል እንዴት ታይዋለሽ
ዮሐንስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝⁵⁷ አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት።
⁵⁸ ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።❞

ክርስቶስ ኢየሱስ አብረሀም ሳይውለድ እኔ አለሁ ብሏል ስለዚህ ጅማሬው ከድንግል ሲወለድ እንዳልሆነ ይናገራል እና 1፥1 ላይ እንዳየነውም በመጀመሪያ ብሎ ቃሉን ሲገልፅ ኢየሱስ አምላክ ስለሆነ ጅማሬ የሌለው መጀመሪያ እንደሆነ እና ቀንና ጊዜ የተገደበለት ጅማሬ የሌለው እደሆነ ይነግረናል።
ስለዚህ ኢየሱስ ጅማሬ የሌለው ዘላለማዊ አምላክ ነው።"

እንዲህ እንዲህ እያሉ ስለ ብዙ ነገር እየተወያዩና ኤልሳም ስለ ክርስቶስ አምላክነት የሚገልፁ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች እያቀረበች አመሹ።

ይቀጥላል...........
https://www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
ኤቭሪል ላቪኝ
ካናዳዊዋ ኤቭሪል ላቪኝ በ 2003 እንደሞተችና በተመሳሳይ መንትያ እንደተተካች የተለያዩ መረጃዎች ይቀርባሉ። ድምፃዊዋ ከአደጋው በፊትና በኋላ ከነበራት ገፅታ መለያየት በተጨማሪ እኤአ በ2002 እና በ 2004 የሙዚቃ አልበም ያወጣች ሲሆን በሁለቱም አልበም ድምጿ አለመመሳሰሉ፥ እንዲሁም "The day you slipped away" በተሰኘው ሙዚቃዋ ፍንጭ ለመስጠት እንደሞከረች ይነገራል።
Na, na, na, na, na, na, na
I miss you, miss you so bad
I don't forget you, oh, it's so sad
I hope you can hear me
I remember it clearly
The day you slipped away
Was the day I found it won't be the same, oh
Na, na, na, na, na, na, na
I didn't get around to kiss you
Goodbye on the hand
I wish that I could see you again
I know that I can't
Oh, I hope you can hear me, 'cause I remember it clearly
The day you slipped away
Was the day I found it won't be the same, oh
I've had my wake up
Won't you wake up
I keep asking why (I keep asking why)
And I can't take it
It wasn't fake
It happened, you passed by
Now you're gone, now you're gone
There you go, there you go
Somewhere I can't bring you back
Now you're gone, now you're gone
There you go, there you go
Somewhere, you're not coming back
The day you slipped away
Was the day I found it won't be the same, no
The day you slipped away
Was the day that I found it won't be the same, oh
Na, na, na, na, na, na, na
I miss you
She called her second album ‘Under My Skin’
The theory alleges that Lavigne “died” in 2003 at the age of 19, a year after the release of her debut album ‘Let Go’. Her second album ‘Under My Skin’ was released in 2004 and the blogger insists that the title “is very suggestive” of the truth. Is it?
They also claim that the album’s title means that the ‘new’ Lavigne is living “under the skin” of the actual Avril Lavigne. “Note that the name ‘Avril Lavigne’ is written in black, representing mourning the singer, and the ‘new’ Lavigne is in black with a red cross on his shoulder. The name ‘Under My Skin’ is red. The colors on the cover seem to suggest mourning and blood. [sic]” I mean, I’m not
entirely convinced that a colour scheme proves an artist is dead.
#የአልበምን_ፎቶውን_ታች_አልካለው
Here lyrics become Dark
you know what, they’re kind of on the money here. First, on ‘My Happy Ending’ she sings these dark words:
“In a city so dead/So high hanging/In such a fragile rope“. Then she follows that up with this line on ‘Together’: “The truth comes to me and I’m living a lie “. When you compare to first album lyrics, such as ‘SK8r Boi’s “ He was a skater boi/I said see ya later boy“, they are admittedly far “moodier”.
@THESECRETKNOWITFERST
Avril Lavigne The second album poster
"Under My Skin"
https://www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com
THE SECRET KNOW IT FIRST pinned «⁣Avril Lavigne The second album poster "Under My Skin" https://www.group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST.com»
2024/10/05 11:13:00
Back to Top
HTML Embed Code: