Telegram Group Search
መቼም ቢሆን ብቻህን አይደለህም! - ዕሑድ፣ መጋቢት 01/2016 ዓ.ም

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ማርቆስ እንደፃፈው፤ ምዕራፍ 9፤ ቁጥር 8

ድንገትም ዞረው ሲመለከቱ ከእነርሱ ጋር ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።
ማርቆስ 9፡8

መቼም ቢሆን ብቻህን አይደለህም!

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ቅር ተሰኝተው ይሆናል። አንድ ጊዜ የሰማይን ጨረፍታ አዩ። ኢየሱስ ክብሩ እንደ እግዚአብሔር ክብር እንዲታይ ፈቀደ። ሙሴ እና ኤልያስ በተዓምራዊ መንገድ ተገለጡ። የእግዚአብሔር አብ ውዳሴም ከደመናው ውስጥ በግርማ ሞገስ አስተጋባ። ብዙም ሳይቆይ በቅፅበት፤ ሁሉም ነገር አለፈ፡፡ በዚያ ሥፍራና ሁኔታ የቀረው፤ የተለመደው የኢየሱስ ቅርፅ ብቻ ነበር።

ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞህ ይሆናል፡፡ ለአጭር ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ ሁሉም ነገር ድንቅ ይመስላል። በዚያ ድንቅ በሚመስል አጭር ጊዜ ችግሮች እና ግጭቶች ስለሌሉ፤ ሁሉም ነገር ትርጉም ያለው ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ እንተ ረክተሃል ወይም በቃኝ ብለሃል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር መልካም ነው፣ በረከቶቹም በግልፅ ታይተውሃል። ነገር ግን በድንገት፤ ሁሉም ነገር ሲለወጥ፤ ሕይወትህ በሁከት ይሞላል፣ እና በጣም ብቸኝነት ይሰማሃል።

ምንም እንኳን ብስጭት፣ ብቸኝነት እና ባዶነት ቢያሰቃዩህም፣ ከኢየሱስ ጋር ነህ፣ መቼም ቢሆን ብቻህን አይደለህም።
“ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ” ስላለ፤ በህይወትህ ስለመገኘቱ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ይህ እውነት፤ አንተ ብቻህን የምትሆንበት ጊዜ እንደሌለ ይነግርሃል። እርሱ ሁል ጊዜ በቃሉ ሊመራህ አብሮህ ነው። እርሱ ሁል ጊዜ በፍቅሩ ሊያጽናናህ አብሮህ ነው። በገባልህ የተሥፋ ቃል ሊያበረታታህ ሁል ጊዜ አብሮህ አለ።

ከዚህ የበለጠ አሳማኝ የሆነው “ከፍቅሩ የሚለይህ ምንም ነገር የለም ” በማለት ማረጋገጫ የሰጠህ ሥራ ነው። ሥራውም፤ ኢየሱስ አንተን፤ በኃጢአት ከተበከለ ሕይወት ነፃ ሊያወጣህ የአባቱን ማረጋገጫ አግኝቷል። እንተ ከእግዚአብሔር ተለይተህ እንዳትጠፋ እና ከቅጣት ፍርድ ነፃ እንዲያወጣህ፤ የአባቱን ፍትሐዊ ፍርድ ተቀብሏል። ኢየሱስ አንተን የእራሱ ለማድረግ፤ በዲያብሎስ ጥቃትና በአስፈሪ ሞትና መቀበር ዕውነታ ውስጥ ጨክኖ አልፏል፡፡

የኢየሱስን የታመኑ ተስፋዎች፣ ውድ ሥራውንና ላንተ የማይገባህን ፍቅሩን ስታስታውስ፤ በፍፁም እርግጠኝነት እና በሰላም መኖር ትችላለህ። ከኢየሱስ ጋር ስትሆን፣ መቼም ብቻህን አይደለህም።

ጸሎት፡ (የክርስቲያን አምልኮ፡ መዝሙር - 783)
ልትባርክኝ ከአንተ ጋር ካለሁ፤ ጠላትን አልፈራም፤ የሚያሳምሙ ነገሮችም አይከብዱኝም፤ በዕንባ ማፍሰስም ምሬት የለም።
የሞት መውጊያ የት አለ? መቃብር ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ? አንተ ከእኔ ጋር ከሆንህ፤ አሁንም ድል አደርጋለሁ።
መሥቀልህን በሚጨፈኑ ዐይኖቼ ፊት ያዝ፤ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ በማብራት ወደ ሰማያት አመልክተኝ።
የሰማይ አዲስነት ይቋረጣል፤ የምድርም ከንቱ ጥላዎች ይሸሻሉ፤ በሕይወት ፣ በሞትም፣ ጌታ ሆይ ፣ ከእኔ ጋር ሁን! አሜን።

Forwarded from Telegram channel of The Lutheran Church of Ethiopia
ኢየሱስን በግልፅ ተመልከት! - ሰኞ፣ መጋቢት 02/2016 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል-ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ማርቆስ እንደፃፈው፤ ምዕራፍ 9፤ ከቁጥር 2 እስከ ቁጥር 3


ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤ አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ።
ማርቆስ 9፡2-3

ኢየሱስን በግልፅ ተመልከት!

አንድ ሰውዬ ሶስተኛ ክፍል እያለ ችግር አጋጥሞት ነበር። ጨዋ ተማሪ ነበር፣ ነገር ግን የት/ት ውጤቶቹ ቀስ በቀስ እየቀነሱ ነበር። በጣም የማያመሰግነው፤ አስተማሪው አሳቢ እና አስተዋይ ስለነበረች፤ ችግሩን ለመረዳት ብዙ ጊዜ አልፈጀባትም። ተማሪው በጥቁር ሰሌዳው ላይ ቢያተኩርም፤ የዐይኑ ዕይታ ተለውጧልና ከዚያ በኋላ በጥቁር ሰሌዳው ላይ ያለውን በግልፅ ማየት አይችልም ነበር።

ይህ ሁኔታ ወደ ዐይን ሐኪም እንዲሄድ አስገደደው፡፡ የዐይን ሐኪሙ፤ ከሩቅ ሆኖ በግድግዳ ላይ ያሉ ፊደሎችን ለይቶ በማወቅ እንዲናገር ጠየቀው። ከዚያም በፊቱ የሚያስፈራ ማሽን አቆመ። ያ ማሽን ፎሮፕተር እንደሚባል አያውቅም ነበር፡፡ የዐይን ሐኪሙ፤ ሌንሶችን በማሽኑ ላይ አስገብቶ፤ የትኛው ሌንስ ለዕይታው የተሻለ እንደሆነ ጠየቀው፣ “አንድ ወይም ሁለት፣ ሶስት ወይም አራት?” ትክክለኛው ሌንስ ሲገጠምለት፤ በግድግዳው ላይ ያሉትን ፊደሎች በትክክል ማወቅ እንደሚችል አስተዋለ፡፡ በዚያን ጊዜ ፊደሎቹ ደብዛዛ ከመሆን ይልቅ ይበልጥ ግልፅና ግልፅ ሆኑለት። በመጨረሻም፣ ከትልልቆቹ ፊደላት በታች ያሉትን ትናንሽ ፊደላት ማንበብ ቻለ።

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፤ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ተራራው ወጣ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ በእርግጥ ማን እንደሆነ የበለጠ ሊያሳያቸው ፈልጎ ነበር። እርሱ ያደረጋቸውን ተዓምራት አይተዋል። ኢየሱስ በሥልጣን ሲሰብክና ሲያስተምር ሰምተዋል። ነገር ግን ኢየሱስ እስከዚያች ደቂቃ፤ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሰው ይመስላል። ከተናቀችው ከናዝሬት የሆነ አንድ የአናፂ ወንድ ልጅ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ሊያዩት በሚችሉት ነገር ሁሉ፤ ኢየሱስ ሰው ነበር።

ነገር ግን በተራራው ላይ እያሉ፤ ኢየሱስ በፊታቸው መልኩ ተለወጠ። በዚያች ቅፅበት ሲያዩት መለኮት እንጂ፤ እንደቀድሞው ሰው አይመስልም ነበር። በዚያች ቅፅበት፤ ደቀ መዛሙርቱ ስለ ኢየሱስ ያላቸው አመለካከት የደበዘዘ እና የተሳሳተ ሳይሆን ግልፅ እና ትክክለኛ ነበር። በፊታቸው የቆመው እግዚአብሔር እራሱ ነበር። በኢየሱስ ተዓምራትና ትምህርት፤ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ትንሽ ፍንጭ አይተው ነበር፣ አሁን ግን ኢየሱስ አምላክ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እራሱን ሲገልጥ፤ ከኢየሱስ ጋር ብዙ ጊዜ ባሳለፋችሁ መጠን፤ እርሱን የበለጠ በግልፅ ታያላችሁ። የዐይን ሐኪም ሌንስ እየቀያየረ፤ በግልፅ እንዲያይ የዕይታ ችግር ያለበትን ሰው እንደሚረዳ፤ ኢየሱስም እርሱ አዳኛችሁ ሆኖ ስለ እናንተ ለመሞት ብሎ ዕውነተኛ ሰው መሆኑን እና የእርሱ መሥዋዕትነት ለእናንተና ለሰው ልጆች ኃጢአት ብሎ ዕውነተኛ አምላክ መሆኑን፤ ኢየሱስ ስለ እራሱ የበለጠ ይገልጥላችኋል።

ጸሎት፡-
ውድ ኢየሱስ፣ እራስህን እንደ እውነተኛ ሰው እና እውነተኛ አምላክ ስለገለፅክ አመሰግንሃለሁ። እንደ አዳኜ በግልፅ እንዳይህ ዕርዳኝ።

Forwarded from Telegram channel of The Lutheran Church of Ethiopia
የሕያዋን አምላክ! - ማክሰኞ፣ መጋቢት 03/2016 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል-ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ማርቆስ እንደፃፈው፤ ምዕራፍ 9፤ ቁጥር 4


ኤልያስና ሙሴም ታዩአቸው፥ ከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር። ማርቆስ 9፡4

የሕያዋን አምላክ!

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፤ ኢየሱስ መልኩ በተለወጠበት ተራራ ላይ ምን እንደተሰማቸው መገመት አስቸጋሪ ነው። ኢየሱስ በዓይናቸው ፊት መለወጡ ብቻ ሳይሆን፣ ወዲያውኑ፣ ሙሴ እና ኤልያስ የሚባሉ ሌሎች ሁለት ሰዎች ከኢየሱስ ጋር ታዩ። እነዚህ ሁለት ሰዎች የቀድሞ የኃይማኖት መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በደቀ መዛሙርቱ ባሕል እና ሐገር ጀግኖችም ነበሩ። የእነዚህ ሁለት ሰዎች ምድራዊ ሕይወት፤ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አብቅቶ ነበር፣ አሁንም ግን እነርሱ ሕያዋን ሆነው፤ ከኢየሱስ ጋር ሲነጋገሩ ነበር። ለአሜሪካውያን ጆርጅ ዋሽንግተን እና አብርሃም ሊንከን ብቅ ብለው እንደማየት ሲሆን፤ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ፤ በጥንት ዘመን በጀግንነት የሞቱት፤ የሐገር መሪዎች ብቅ ብለው እንደማየት ነው።

ደቀ መዛሙርቱ በተመለከቷቸው ሰዎች እና ባዩት ነገር ደነገጡ፤ ተደነቁም። በዚያን ጊዜ እየሆነ ያለውን ነገር በሚገባ ባለማገናዘባቸው ልንወቅሳቸው አንችልም። እግዚአብሔር አብ፤ ልጁ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ሙሴና ኤልያስ የሚወክሉት ሁሉ ፍፃሜ መሆኑን እያረጋገጠ ነበር።

እግዚአብሔር ሕጉን በሙሴ በኩል በሲና ተራራ ላይ ለሕዝቡ ሰጠ፤ ኢየሱስ እነዚህን ሕጎች ሊፈጽም መጣ። ኢየሱስ አንድም ጊዜ ሳይሰናከል ወይም ሥህተት ሳይሠራ እያንዳንዱን ሕግ ፍፁም በሆነ መንገድ ጠብቋል። ኢየሱስ በሙሴ በኩል ለሕዝቡ የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ ሲጠብቅ፤ እኛ ከቶ የማንችለውን አድርጓል።

ኤልያስ ከታላላቅ የእግዚአብሔር ነቢያት አንዱ ነበር። በተራራው ላይ ነቢያትን ሁሉ ወክሎ እና ስለሚመጣው መሢህ የተናገሩትን ተናገረ። ስለ መሢሁ ከ300 የሚበልጡ ትንቢቶች የተነገሩ ሲሆን ኢየሱስ እያንዳንዳቸውን ፈፅሟል። ሁሉም የእግዚአብሔር ዕቅዶች እና ዓላማዎች፤ ሕዝቡን ለማዳን በኢየሱስ በአንድነት ዕውን ሆነዋል።

ደቀ መዛሙርቱ፤ ኤልያስንና ሙሴን ሕያው ሆነው አዩዋቸው። ያ አስደናቂ መሆን ነበረበት። ግን ብዙም ሳይቆይ፤ የበለጠ አስገራሚ ነገር ያያሉ። ኢየሱስ በጭካኔ ከተሰቀለ በኋላ ሕያው ሆነ፤ ከሞት ተነሣ። ኢየሱስ ፍፁም አዳኝ እና ይመጣል ተብሎ በተስፋ ሲጠበቅ የነበረው መሢህ ለመሆኑ የበለጠ ማስረጃ ነው።።

ፀሎት፡-
ውድ ኢየሱስ ሆይ፤ አንተ የሕያዋን አምላክ ነህ እንጂ፤ የሙታን አይደለህም። ሕይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ። አሜን።

Forwarded from Telegram channel of The Lutheran Church of Ethiopia

ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
"ከምግብ ርቀህ ነገር ግን ዓይኖችህ እና [ሀሳቦችህ] ወደ ዝሙትና ወደ [ከንቱ] መመራመር፤ ወደ ተደበቀ ክፋት እና ለስድብ ቃላትና ለክፉ ዘፈን፣ ለክፉም ሀሜት፣ እና የስሜት ህዋሳትህ ለሚጎዷቸው ነገሮች ሁሉ ክፍት ከሆነ ታዲያ የጾም ጥቅሙ ምንድን ነው?

–የቅዱስ ጎርጎርዮስ ፓላማስ ስብከቶች፣ ስብከት 9፣ በፀሎት እና ፆም ጊዜ፣ ገጽ. 62

For context, read "The Homilies of Saint Gregory Palamas, Homily 9 - In the Time of Prayer and Fasting, pp. 60-64".

ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ድነታችን በገዛ ራሳችን ብርታት ወይም ምክር ሳይሆን በእግዚአብሔር አሠራር ላይ ብቻ የተመሠረተ መሆኑ [የተረጋገጠ ነው]...

በእኛ ውስጥ ድነትን የሚሠራው እኛ ሳንሆን እግዚአብሔር ብቻ ከሆነ እርሱ በእኛ ከመሥራቱ በፊት እኛ የምናደርገው ማንኛውም ነገር አንዳችና ምንም የድነት ጠቀሜታ እንደሌለው የታወቀ ይሆናል።

እግዚአብሔር ከሞት የሚያስነሳው በመግደል ነው፤ ሲያጸድቅ በደለኛ መሆንን በመናገር ነው፤ ወደ ሰማይ የሚወስደው ወደ ሲኦል በማውረድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ...[እንደሚለው] “እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ያወጣል" (1ሳሙ 2፡6)።


–የቤተ ክርስቲያን አዳሹ ማርቲን ሉተር፣ የፈቃድ እስራት

ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
የአትናቴዎስ የእምነት መግለጫ

1. ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ ከሁሉም ነገር አስቀድሞ የሁሉ የሆነች የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት እውነተኛ አድርጎ ሊቀበል ያስፈልገዋል።
2. ንጹሕና ሙሉ አድርጎ ያልጠበቀው ሁሉ ያለ ጥርጥር የዘላለም ጥፋት ይደርስበታል።
ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
የአትናቴዎስ የእምነት መግለጫ 1. ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ ከሁሉም ነገር አስቀድሞ የሁሉ የሆነች የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት እውነተኛ አድርጎ ሊቀበል ያስፈልገዋል። 2. ንጹሕና ሙሉ አድርጎ ያልጠበቀው ሁሉ ያለ ጥርጥር የዘላለም ጥፋት ይደርስበታል።
3. በሦስትነቱ አንድነቱን፥ በአንድነቱም ሦስትነቱን አምነን አንድ አምላክን እናመልካለን። ይህም እውነተኛ የክርስትና ሃይማኖት ነው።
4. ይህንንም የምናደርገው አካላቱን ሳንደባልቅ መለኮታዊ ህልውናውንም ሳንከፍል ነው።
5. ምክንያቱም የአብ አካል ለብቻው የወልድ ለብቻው፥ የመንፈስ ቅዱስም ለብቻው ስለሆነ ነው።
6. ሆኖም፥ የአብ፥ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ መለኮት አንድ ነው፥ ክብሩ ሥልጣኑም እኩል ሆኖ ይኖራል።
7. ወልድ በህልውናው እንደ አብ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም እንደዚሁ ነው።
8. አብ አልተፈጠረም፥ ወልድ አልተፈጠረም፥ መንፈስ ቅዱስም አልተፈጠረም።
9. አብ ወሰን የለውም፥ ወልድ ወሰን የለውም፥ መንፈስ ቅዱም ወሰን የለውም።
10. አብ ዘላለማዊ የሚሆን አንድ እንጂ ሦስት አይደሉም።
11. ቢሆንም ዘላለማዊ የሚሆን አንድ እንጂ ሦስት አየደሉም።
12. ያልተፈጠና ወሰን የሌለው ሦስት እንዳልሆነ እንደዚሁም ያልተፈጠረና ወሰን የሌለው አንድ ነው።
13. እንዲሁም አብ ሁሉን የሚችል ነው፥ ወልድ ሁሉን የሚችል ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ሁሉን የሚችል ነው።
14. ቢሆንም፥ ሁሉን የሚችል አንድ አንጂ ሦስት አይደለም።
15. ስለዚህ አብ አምላክ ነው፥ ወልድ አምላክ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው።
16. ሆኖም አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይደሉም
17. ስለዚህ አብ ጌታ ነው፥ ወልድ ጌታ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ጌታ ነው።
18. ሆኖም አንድ ጌታ እንጂ ሦስት ጌቶች አይደሉም።
19. ምክንያቱም የክርስትና እምነት እውነተኛነት እያንዳንዱ አካል አምላክና ጌታ መሆኑን እንድናምን እንደሚያስገድደን ሁሉ የክርስትና ሃይማኖት ሦስት አማልክት ወይም ሦስት ጌቶች እንዳንል ይከለክለናል።

20. አብ በማንም አልተሠራም፥ አልተፈጠረም፥ አልተወለደምም።
21. ወልድ ከአብ ተወለደ እንጂ አልተሠራም አልተፈጠረምም።
22. መንፈስ ቅዱ አልተሠራም፥ አልተፈጠረም፥ አልተወለደምም፥ ነገር ግን ከአብና ከወልድ የሚሠርጽ ነው።
23. ስለዚህ አብ አንድ ስለሆነ ሦስት አብ አይደለም፥ ወልድም አንድ አንጂ ሦስት ወልድ አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስም አንድ እንጂ ሦስት አይደለም።
24. ከሦስቱ አካላት አንዱ ከሌለው ቀዳሚነት ወይም ደኃሪነት የለውም፥ አንዱም ከሌላው የሚበልጥ ወይም የሚያንስ አይደለም።
25. ስለሆነም፥ ሦስቱ አካላት በእኩልነትና በዘላለማዊነት አንድ ናቸው። ከዚህ የተነሣም ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው ሦስቱ አካላት በአንድ መለኮት አንድ አምላክም በሦስት አካላት ይመለካል።
26. ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ ስለ ሥላሤ እንደዚህ ማሰብ ይገባዋል።

27. ስለዚህ ሌላ የዘላለምን ደኅንነት ለማግኘት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ መገለጽ በእውነት ማመን አስፈላጊ ነው።
28. ምክንያቱም ትክክለኛው እምነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ አምላክም ሰውም መሆኑን ማመን አስፈላጊ ነው።
29. እርሱም ከዘመናት አስቀድሞ ከአብ የተወለደ አምላክ ከእናቱም በሥጋ በዓለም የተወለደ ሰው ነው።
30. የሚያስብ ነፍስ ያለችውና የሰውን ሥጋ የለበሰ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው።

31. በአምላክነቱ ከአብ ጋር የተካከለ፥ በሰውነቱም ከአብ ያነሰ ነው፡
32. አምላክም ሰውም ቢሆንም አንድ ክርስቶስ እንጂ ሁለት ክርስቶስ አይደለም።
33. አንድ ነው ስንል ግን የሰውን ሥጋ ለበሰ እንጂ መለኮት ወደ ሥጋ አልለወጠም።
34. በእርግጥ አንድ የሆነውም በባሕርያት መደባለቅ ሳይሆን በአካል አንድ በመሆኑ ነው።
35. ምክንያቱም የሚያስብ ነፍስና ሥጋ አንድ ሰው እንደሆኑ ሁሉ አምላክና ሰው በክርስቶስ አንድ ናቸው።
36. እርሱም ለደህንነታችን ሲል መከራ ተቀበለ፥ ወደ ሲኦል ወረደ፥ ከሙታን ተነሣ።
37. ወደ ሰማይ የወጣ፥ በአብ ቀኝ የተቀመጠ፥ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ከዚያ የሚመለስ፥
38. በመምጣቱ ጊዜም ሰዎች ሁሉ በሥጋ ተነስተው ስለ ሥራቸው መልስ ይሰጣሉ።
39. መልካም የሠሩ ወደ ዘላለም ሕይወት ክፉ የሠሩም ወደ ዘላለም እሳት ይገባሉ።
40. ይህ እውነተኛው የክርስትና እምነት ነው። ይህን የሚያምንና አጥብቆ የማይዝ ሊድን አይችልም።



///
የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ

ኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ
የካህን ቡራኬ

እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤
እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።
በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ።
----------------------

እግዚአብሔር ይባርካችሁ፥ ይጠብቃችሁም፤
እግዚአብሔር ፊቱን ያብራላችሁ፥ ይራራላችሁም፤
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ እናንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጣችሁ።
በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ።


ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
እዩት እየሱስን መስቀሉ ማማሩን [መዝሙር] https://youtu.be/xfoZBOC0LMQ
፩፡ አምላክ ለኛ ብሎ ቢያፈሰው ደሙን
ፀሐይ ከለከለች ደማቅ ብርሃንዋን።
የከበረው ሥጋ የከበረው ደም፥
በመስቀል ላይ ዋለ ኢየሩሳሌም።
እዩት ኢየሱስን፥ መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረው
ብዙ ነው ምሥጢሩ።
፪፡ ቢገርፉት ቢሰቅሉት ቢያላግጡበት
ምንም አላገኙም ከርሱ ዘንድ ስሕተት።
ፈጣሪ መሆኑን ምሥጢሩ ገብቷት፥
ጌታን አልይዝም አለች ግዑዟ መሬት።
እዩት . . .።
፫፡ ይኼ ታላቅ ንጉሥ ሲገለጥ ከሰማይ
የናቁት የወጉት ይሉለታል ዋይ ዋይ።
ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሲሸሹ
ወዴት ልግባ ይላል ትልቁ ትንሹ።
እዩት . . .።
፬፡ ወደ ላይ ያረገው የከበረው ሥጋው፥
ዳግመኛ መምጣቱን ሁላችን አንዘንጋው።
በሰማይ ለሚኖር ቅዱስ አባታችን፥
ምስጋና ይድረሰው ከኛ ከሁላችን።
እዩት . . .።


ደ. ጸጋዬ ሀብትህ ይመር
መዝሙር 55 ከስብሐት ለኣምላክ "እዩት ኢየሱስን"

Website: www.ZenaKristos.org


ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
የሕማማት ሳምንት ዛሬ ይጀምራል

ሁላችንም የጌታችንን እና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስቃይና መከራ እንዲሁም ደግሞ ለኃጢአታችን ስርየት ሲል የጠጣውን የሞት ጽዋ እያስብን ራሳችንን በመመርመርና ክርስቶስ የከፈለውን ታላቅ ዕዳ እያሰብን የምንቆይበት ጊዜ እንዲሆን እንመክራለን!

ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡
Https://zenakristos.org/images
የህማማት ሳምንት - ሰኞ

ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲነግዱ ያገኛቸውን አስወጣቸው

"ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው። "
ማቴዎስ 21:12-13

የእግዚአብሔር ቤት ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡበት፣ ከእርሱ የኃጢአት ይቅርታን እና በረከትን የሚያገኙበት፣ እንዲሁም ደግሞ በፀሎት ወደ እግዚአብሔር ፊት የሚቀርቡበት ቦታ እንጂ በተለያዩ ኢ-ፍትሐዊ በሆኑ መንገዶች ገንዘብን የሚሰበሰቡበት ቦታ አይደለም። ክርስቶስ በዚህ ሁኔታ እጅጉን ከመቆጣቱ የተነሳ ገበያቸውን በሙሉ በተነ። በዚያን ዘመን እንደነበረው ሁሉ በአሁኑም ዘመን ብዙዎች የክርስቶስን ስም ተጠቅመው እግዚአብሔርን በማያስከበር መልኩ ገንዘብና ሀብትን ያተርፋሉ። ክርስቶስ ዛሬ በሚታይ አካሉ አብሮን ቢኖር ኖሮ ምን ይላቸው ይሆን?

"ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት!"

ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡
Https://zenakristos.org/images
የሕማማት የሳምንት - ማክሰኞ

ፍሬ አልባ የሆነችው በለስ


"በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው፦ በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች? ብለው ተደነቁ። ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው። "
ማቴዎስ 21:18-22

ኢየሱስ ክርስቶስ ተርቦ ፍሬን ፍለጋ ወደዛች በለስ ቢቀርብም ፍሬ አላገኘባትም። ስለዚህም ረገማት። ደቀመዛሙርቱም ሲደነቁ፤ በስሙ ምንም ቢለምኑ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው። በስሙ መለመን ማለት ግን በእርሱ ላይ ብቻ መተማመን ነው። ስለእዚህ በስሙ የ10 ሚሊዮን ብር ሎተሪ እንዲደርሰኝ መለመን ማለት ነውን? አይደለም!
በእግዚአብሔር ላይ ብቻ የሚተማመን ሰው ምንጊዜም የሚፀልየው ፀሎት "ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን" ነው። ስለዚህ ክርስቲያኖች ለሰማያዊው ሆነ ለምድራዊው ህይወታቸው ምንም አይነት ፀሎት ሲፀልዪ "የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ" ይላሉ። ሁሉ ሊያደርግልን በሚችል በእግዚአብሔር ላይ ብቻ እምነታችንን እያደረግን ይህንን የሕማማት ጊዜ እናሳልፍ። ይህንንም ማድረግ እንድንችል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይርዳን፤ አሜን!

ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡
Https://zenakristos.org/images
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሕማማት የሳምንት - እሮብ

ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ተስማማ



"በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ። ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት። ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር። "
ማቴዎስ 26:14-16


ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ከጠራበት ጊዜ ጀምሮ የነበረው የአስቆሮቱ ይሁዳ፤ ብዙ ተአምራትን፤ ብዙ ድሎችን እንዲሁም ብዙ ትምህርቶችን በኢየሱስ ዘንድ ቢያገኝም፤ ለገንዘብ ያለው ጥልቅ ፍቅር የገዛ መምህሩም እንኳን እንዲከዳ አድርጎታል። ኢየሱስ ከዚህ በፊት ሲያስተምር የገንዘብ ፍቅር የኃጢያት ሁሉ ሥር ነው ብሏል። ያንን ትምህርት የአስቆሮቱ ይሁዳ ሰምቶ ነበር፤ ቢሆንም ግን ወደ ልቡ ገብቶ እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ስላላመጣ፤ በኋላ ላይ የገዛ መምህሩም፣ አምላኩን እና ጌታውን በሥላሳ ብር ሊሰጥ ተስማማ። በዚህም ዘመን ብዙዎች ክርስቶስን የወደዱ መስሏቸው የገንዘብ ፍቅራቸው ከክርስቶስ ጋር አጣልቷቸው ይገኛል። ወገኖች ሆይ የገንዘብ ፍቅር ከክርስቶስ እዳይለየን በዚህ የሕማማት ጊዜ በፀሎት እና በምልጃ በእግዚአብሔር ፊት እንቅረብ። እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን!

ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡
Https://zenakristos.org/images
የሕማማት ሳምንት: ጸሎተ ሐሙስ

ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ


"ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። "
ዮሐንስ 13:4-5

የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሰውን ስጋ ለብሶ መምጣት ብቻ ሳይሆን እራሱን ዝቅ አድርጎ የተከታዮቹን እግር አጠበ። ይህ በአለማዊ አስተሳሰብ እጅግ እራስን ማዋረድ ቢሆንም ኢየሱስ በሰማያዊ አስተሳሰብ ዝቅ ማለት የትህትና ምልክት እንደሆነ እርሱ ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ አሳየን። ለዚያም ነው ኢየሱስ ትሁቶች እንድንሆን የሚጠራን። ኢየሱስ አምላክ ሆኖ ሳለ የሰውን እግር እስከማጠብ ድረስ ትሁት ከሆነ፤ እኛ ደሞ ለባልንጀሮቻችን ምን ያህል ትሁታን መሆን ይገባናል?

ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡
Https://zenakristos.org/images
2025/02/11 14:22:32
Back to Top
HTML Embed Code: