Telegram Group Search
Water Color ማለት ከውሀ ጋር መቀላቀል ሚችል ቀለም ሆኖ እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት በ3 አይነት መልክ ይቀርባል,
1. ደረቅ / Solid
2. ጭቃ / Acrylic Paste
3. በእርሳስ / water color Pencil

1ኛው በተለምዶ ለህፃናት ምንገዛው ግን አጠቃቀሙ ከገባን ለኛም የሚሆን አብዛኛው Stationary ምናገኘው ነው:: አጠቃቀሙም በወረቀት or similar material ላይ ቀለሙን በውሀ በማራስ በስስ ብሩሽ...

2ኛው Acrylic 12 different colors each 12ml በእሽግ ይቀርባል:: እንዲሁም ነጠላ ቀለም በብልቃጥ ተቀምሞ በያንዳንዱ አይነት ይቀርባል:: የጥርስ ሳሙና አይነት ባህሪ አለው:: በአብዛኛው ሸራ ላይ የምንጠቀምበት ሲሆን ወረቀት ላይም አመቺ ነው:: በወረቀት ላይ አጠቃቀሙ ከ1ኛው ጋር ተመሳሳይ ሲሆን በሸራ ላይ ግን ብሩሻችንን እንቀይራለን:: የሚገኘውም ውስን Stationaryዎች ጋር ነው::

3ኛው የምናውቃቸው የእርሳስ ቀለም (Color Pencil) ሆነው ሚለዩት ከሰራንበት በኃላ በትንሽ ውሀ ስናረጥበው ወዲያው ተቀላቅሎ ሥዕሉን ማድመቁ ነው::
በዚች ሴኮንድ
በዚች ደቂቃ
በዚች ሰዐት 🕧
በዚች እለት 💧
አዲሱን አመት ስለ ተቀበልን ክብር እና ምስጋና ለምናመልከው አምላክ ይሁን መጪውን ዘመን አገራችን ወደ ተሻለ ደረጃ የምናደርስበት ሰላም እና ፍቅር የበዛበት የፍቅር ዘመን ያድርግልን 🙏
ሥነ-ጥበብ ምንድን ናት? ዓላማ ግቧና ጥቅም አገልግሎቷስ?

ብዙውን ጊዜ ሥነ-ኪን ወይም የጥበብ ሥራ፣ ነገረ-ጥበብ ማለት እንፈልግና ኪነ-ጥበብ የሚለውን ቃልና ሥነ-ጥበብ የሚለውን ቃል እያጣረስን ስንጠቀም እንስተዋላለን፡፡ ኪነ-ጥበብ ወይም ኪነ-ጥበባት የሚለው ቃል ራሱ ግራ የተጋባ ቃል ነው፡፡ ልንጠቀምበት ፈልገን በምንጠቀምበት ቦታ ሁሉ ሰዋስዉ የተሳሳተ (Grammatically wrong) በሆነ መንገድ ነው፡፡ ቃሉ የግዕዝ ቃል ቢሆንም እነኝህን ሁለት ቃላት ማጣመር ግን የሰዋስው ስሕተትን ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም ኪን የሚለው ቃል ትርጉም ራሱ ጥበብ ማለት ነውና፡፡ ስለዚህም ኪነ-ጥበባት ስንል ጥበበ ጥበባት ማለታችን ነው ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት የጥበቦች ጥበብ ወይም ከጥበቦች ሁሉ የበላይ ጥበብ የሚል ትርጉምን ይሰጣል እንጅ አጠቃላይ የጥበብ ሥራ ዘርፍ ማለት አይደለም፡፡ ንጉሠ ነገሥታት ማለት የነገሥታት ንጉሥ ማለት እንደ ሆነ ሁሉ ማለት ነው፡፡ ስሕተቱ ይሄ አይደለም ይሄንን ቃል ጠቅሰን ልንገልጽ የምንፈልገው ጉዳይ ቃሉን ስሕተት ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም ቃሉ የተሳሳተ ነው፡፡ እናም ይስተካከል ቢባል ሊሆን የሚችለው “ሥነ-ኪን” ወይም ሲተረጎም “ነገረ-ጥበብ፣ የጥበብ ሥራ ባጭሩ ደግሞ ኪነት” ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎቻችን “ኪነት” ሲባል የሚመስለን ቃሉ የሚያመለክተው ዜማንና ግጥሙን ወይም ዘፈንን ብቻ ይመስለናል፡፡ እንደተረዳሁት ብዙ ሰዎች እንዲህ ብለው እንዲያስቡ ያደረጋቸው ደርግ በተለይ በወጣቱ አቀጣጣይነት የተነሣውን የወቅቱን አቢዮት ወጣቱን ለመያዝ ወጣቱን በሚስብና በሚቀሰቅስ ብሎም ወደሚፈልገው አቅጣጫ ለመውሰድ ወጣቱን የሚያሳትፍ በየቦታው በየክፍላተ ሀገሩ የኪነት ማዕከል አቋቋመ፡፡ በእነዚህ የኪነት ማዕከላት ውስጥ በርከት ያሉ የሥነ-ኪን ወይም ሲተረጎም የጥበብ ሥራ ወይም ደግሞ በአጭሩ የኪነት ዘርፎች የሆኑ የጥበብ ሥራዎች እንዲከወኑ እንዲሠሩ ሙከራ አድርጓል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ለምሳሌ ያህል ብንጠቃቅስ ተውኔት ወይም ቴአትር፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ሥነ-ጥበብ (ሥዕልና ቅርጻቅርጽ)፣ ዘፈን ወይም ሙዚቃ (በነገራችን ላይ ሙዚቃ አማርኛ አይደለም ሚዩዚክ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል በአገርኛ ለዛ ሲጠራ ነው ሙዚቃ የተባለው ልክ school የሚለው ቃል አስኳላ እንደተባለው ሁሉ ማለት ነው) ነበሩ፡፡ ነገር ግን የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ ይሁን የሌላ አላውቅም ከእነኝህ ሁሉ ዘርፎች ዘፈን ወይም ሙዚቃ ገኖና ጎልቶ ሌሎቹን ውጦ በመውጣቱ ለአጠቃላይ ዘርፉ የሚያገለግለው ሥያሜ ማለትም ኪነት የሚለው ቃል ዘፈንንና ዘፋኝነትን የሚያመለክት ብቻ ተደርጎ በስሕተት ሊቆጠር ቻለ፡፡ ባለፈው ጊዜ የሥነ-ኪን ወይም የኪነት ባለሙያዎች ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር አድርገውት በነበረው ውይይት ላይ ይህ ስሕተት በጉልህ ተስተውሏል ሁሉም ይጠቀሙት የነበረው ቃል ስሕተት ነበር፡፡ የመገናኛ ብዙኃንም ሥነ-ጥበብን የተመለከተ ውይይት እያሉ ሲዘግቡ ዓይተናል ሰምተናል፡፡ ሥነ-ጥበብ የሚለው ቃል ግን የእንግሊዘኛውን fine Art እንዲወክል በየመዝገበ ቃላቶቻችን ጭምር የሰፈረ ቃል ነው፡፡ ብቸኛው መንግሥታዊ የfine art ወይም የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት የሚጠራውም በዚሁ ሥያሜ ነው የሚወክለውም ሥዕልና ቅርጻቅርጽን ብቻ ነው፡፡ በዚያ ውይይት ተጋብዘው የተገኙት ግን ሠዓልያንና ቀራጽያን ብቻ ሳይሆኑ ዘፋኞች ወይም ሙዚቀኞችም፣ በተውኔት ወይም በቴአትር ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ተዋንያንና ደራሲያን እና በሌሎች የሥነ-ኪን (የጥበብ ሥራዎች) ወይም የኪነት ዘርፎች የተሠማሩ ከያኔያን (Artists) በሙሉ ነበሩ፡፡ ይህ ጽሑፍ የተሳሳተውን “ኪነ-ጥበብ” የሚለውን ቃል በማረም የሥነ-ኪንን (የጥበብን ሥራዎችን) ወይም ደሞ ባጭሩ የኪነትን እና የሥነ-ጥበብን ልዩነትና አጠቃቀም የጥበቡንም አገልግሎትና መቸት ያብራራል።

በሠዓሊ - አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
"ኪን” ማለት ምን ማለት ነው?

ኪን ቃሉ ግዕዝ ነው። እንደሚታወቀው አማርኛ የግዕዝ የበኩር ልጅ ምናልባትም አባት እንደመሆኑ የግዕዝን ቃላት በባለቤትነት ሲጠቀም ይስተዋላል፡፡ “ለአማርኛ ግዕዝ ነው ዳኛ” እየተባለም ይተረታል፡፡

ኪን፡- ጥሬ ዘር ሲሆን ጥበብ፣ የጥበብ ሥራ፣ የጥበብ ሙያ ማለት ነው፡፡
ኬንያ፡- የሚለውም ቃል ስም ነው ጥሬ ዘሩ “ኪን” ሆኖ ማለት ነው፡፡ ትርጉሙም ጥበበኛ ማለት ነው “ዘኢገብራ እደ ኬንያ ዘሰብእ” እንዲል፡፡ ትርጉም የጥበበኛ ሰው እጅ ያልሠራት ወይም ያልተጠበበባት ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ሥነ-ኪን ማለት የጥበብ ሥራ የጥበብ ሞያ ማለት ይሆናል፡፡ በሌላም በኩል “ከያኔ” ለነጠላ፣ “ከያኔያን” ለብዙ አሁንም ስም ሲሆኑ ጥሬ ዘሩም “ኪን” ነው ትርጉሙም የጥበብ ሥራ ሠራተኛ ወይም ሙያተኛ ማለት ነው፡፡

ሥነ-ኪን ወይም ኪነት የተለያዩ ዘርፎች ሲኖሯት ከእነርሱ ዋና ዋናዎቹም፡-

1. ሥነ-ዜማ (Music or Song) መግለጽ ወይም ማለት የተፈለገን ነገር በጥዑመ ዜማ መግለጽን ይመለከታል፡፡
2. ሥነ-ጥበብ (Fine art) ሥዕልና ቅርጻቅርጽን ይመለከታል፡፡
3. ሥነ-ጽሑፍ (Literature) ግጥምን ጨምሮ አጭር ረጅም ልብ ወለድና ኢልብ ወለድ ድርሰቶችን ወግን የጽሑፍ ሥራዎችን ይመለከታል፡፡
4. ተውኔት ወይም ትውንተ-ድርሰት (Theatre or Drama) የተለያዩ ጭብጦችን ይዞ በሕዝብ ወይም በተመልካቶች (Audience) ፊት በመድረክ ላይ ወይም በብዙኃን መገናኛ የሚተወን ድርሰትን ይመለከታል፡፡
5. ምትርኢት (film or movie) በቴሌቪዥን (በምርዓየ-ኩነት) ወይም በማንኛውም ሰሌዳ (screen) ላይ የሚታይ የትውንተ ድርሰት (Drama) ሥራን ይመለከታል፡፡
6. ሥነ-ሕንፃ ወይም ኪነ-ሕንፃ (Architecture) የሕንፃዎችን ንድፎች ከነ መዋቅሩ የሚመለከት ነው።

የተውኩት የሥነ-ኪን ዘርፍ ያለ አይመስለኝም ነገር ግን በስራቸው የሚካተቱ የየራሳቸው ዘርፎች ይኖራሉ ለምሳሌ ጭፈራና ድንከራ ወይም ውዝዋዜ በሥነ-ዜማ ውስጥ፣ ሥነ-ውበት በሥዕልና ቅርጻ ቅርጽ ወዘተ...

በሠዓሊ - አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
2024/11/19 19:00:11
Back to Top
HTML Embed Code: