Telegram Group Search
" በ7 ወራት ውስጥ ብቻ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኃይል መሰረተ-ልማት ስርቆት ተፈጽሟል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ባለፉት 7 ወራት፣ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኃይል መሰረተ-ልማት ሰርቆት ተፈጽሞበታል።

በአዲስ አበባም ጭምር በጠራራ ፀሀይ፣ በመሰረተልማቶች ላይ የሚፈፀመው ስርቆት ለአገልግሎት መቋረጥ ምክንያት መሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።


የአገልግሎቱ ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ ለዶቸቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

የተቋማቸው ተግባር፣ የኤሌክትሪክ ሀይልን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በጅምላ ገዝቶ ለደንበኞች ማቅረብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሆኖም፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሀይል መሰረተልማቶች ላይ የሚፈፀመው ስርቆት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትልቅ ተግዳሮት እየፈጠረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውም ጉዳት እንደዚሁ እየከፋ መምጣቱንም አመልክተዋል፡፡

በተያዘው የበጀት አመት ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኃይል መሰረተ-ልማት ስርቆት መፈፀሙን አስታውቋል፡፡

በዋና ከተማ አዲስ አበባም ጭምር በጠራራ ፀሀይ፣ በመሰረተልማቶች ላይ የሚፈፀመው ስርቆት፣ በሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች፣ በትራንስፎርመር እና በሀይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ያያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል።

እነዚህ በውጭ ምንዛሪ የሚገቡ ሀብቶች በመሆናቸው የሚያስከትለው ጉዳት ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

የሰርቆት ድርጊቱ በአገልግሎት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ እንዳለውም አመልክተዋል፡፡ 

"/በመሰረተልማቶች ላይ በሚደርሰው ጉዳት ምክንያት የሀይል አቅርቦት ሲቋረጥ፣ ተጎጅዎቹ ደንበኞች ብቻ አይደሉም ’ተቋሙም ከፍተኛ ጉዳት ያስተናግዳል " ያሉ ሲሆን " ይህ ድርጊት ከደንበኞች የምናገኘውን ገቢ ያሳጣናል፣ የወደሙትን መሰረተልማቶች መልሰን ለመጠገን የምናወጣው ወጪም ከፍተኛ ነው " ሲሉ ገልፀዋል፡፡

" የስርቆት ድርጊቱን ከመከላከል አኳያ፣ በአሁኑ ጊዜ መጠነኛ መሻሻል አለ " ያሉ ሲሆን ሆኖም አሳሳቢነቱ በመቀጠሉ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ይህን ችግር ለማስቆምና እነዚህን የሀገር ሀብቶች ከውድመት ለመታደግ ሊተባበሩ ይገባል ብለዋል።

 የኤለኤክትሪክ መሰረተልማቱ እየተሰረቀ ያለው ተቀባዮች ስላሉ ነው፣ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ‘ የሚሉት አቶ መላኩ፣ መንግስትም አጥፊዎችን ለህግ በማቅረቡ በኩል እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

#DW

@tikvahethiopia
#የአርሶአደሮችድምጽ🔈

🔴 “ ለሦስት ዓመታት ምንም የካሳ ክፍያ አልተከፈለንም፡፡ የምንመገበው አጥተን ለልመና ተዳርገናል” - አርሶ አደሮች

➡️ “ ክፍያዎቹን በተገቢው በሚፈለገው አግባብ እየከፈልን አይደለም ” - የአማራ ክልል መንገዶች
ቢሮ

በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ከቸና እስከ መካነ ኢየሱስ ከተማ ባለው የመንገድ ፕሮጀክት መሬት የተወሰደባቸው ወደ 40  አርሶ አደሮች ለ3 ዓመታት የካሳ ባለመከፈሉ ለልመና መዳረጋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

አርሶ አደሮቹ ስለቅሬታቸው ምን አሉ?

“ ከቸና እስከ መካነ ኢየሱስ ከተማ ድረስ ባለው ፕሮጀክት ለተወሰደው መሬት 2014 ዓ/ም የካሳ ክፍያ ብናውቅም 40 አርሶ አደሮች ለ3 ዓመታት ካሳ አልተከፈለም፡፡

በአሰራሩ መሰረት የካሳ ክፍያ እንደወቅቱ ሁኔታ እየታዬ በየስድስት ወሩ ማሻሻያ ይደረግበታል ክፍያ ሳይፈጸም ከቆዬ። የኛ ግን ለ3 ዓመት ማሻሻያ አልተደረገበትም፡፡

ከዓመታት በፊት የተገመተው ካሳ አሁንም ባለበት ነው። ከ3 ዓመታት በፊት የነበረው የገንዘብ ዋጋ ከአሁኑ ጋር ሲነጻጸር ሰፊ ልዩነት አለው። ያም ሆኖ ግን ከዓመታት በፊት የነበረው ካሳም እየተከፈለን አይደለም፡፡

የመካነ ኢየሱስ ከተማ ነዋሪም ቤቱን ሽጦ እንዳይመገብ መስመር ዳር ሊፈርስ ምልክት ስለተደረገበት መሸጥ አይቻልም፡፡ የገጠሩ አርሶ አደርም የተወሰደብን መሬት የአትክልት ማምረቻ ጭምር ማሳ ነው፡፡

አርሶ አደሩ እስከ 3 ማሳ ነበረው በግራና ቀኝ መንገድ ፕሮጀክቱ የደረደበት፡፡ አርሶ አደሩ ወይ አርሶ አልተጠቀመ ወይ የካሳ ክፍያ አላገኘ፡፡ አትክልቱ እንኳ አድጎ ጥቅም እንዳይሰጥ በለጋው ተቀጭቷል ” ብለዋል።


በ2014 ዓ/ም በነበረው የካሳ ተመን መሰረት ከ200 ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተላቸው አርሶ አደሮች እንዳሉ ገልጸው፣ በአሁኑ የገንዘብ የመግዛት አቅም ዋጋ ተተምኖ በቶሎ ካሳው እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለምን የአርሶ አደሮቹ ካሳ በወቅቱ አልተከፈለም፣ መቼስ ይከፈላለቸዋል? ሲል የአማራ ክልል መንገዶች ባለስልጣንን ጠይቋል።

የአማራ ክልል መንገዶች ቢሮ ምን መሰለ?

“ የወሰን ማስከበር ክፍያዎች በመንግስት በጀት ከምንከፍላቸው ክፍያዎች አንዱ ነው። ግን ክፍያዎቹን በተገቢው በሚፈለገው አግባብ እየከፈልን አይደለም።

ይሄ ደግሞ የተፈጠረው ለመስሪያ ቤታችን ከመንግስት በሚለቀቀው በጀት ጋር ተያይዞ እየገጠመን ባለው የበጀት ችግር ነው።

ይሄን ችግር እናውቀዋለን። ለመፍታት እየታገልን ያለነው ነው። ስለዚህ የበጀት ችግሩ እንደተፈታልን፣ መፈታት ብቻም ሳይሆን እንደተቃለልን ቀሪ ክፍያዎችን ባለው ፕራዮሪቱ ኦርደር መሠረት እንከፍላለን ” ብሏል።

(ጉዳዩን እስከመጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል
)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል " - የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ

በአዲስ አበባ ወደ ተግባር የገባው የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብን መተላለፍ የሚያስከትለው ቅጣት ስንት ነው ?

➡️ በባህሪው አደጋኝነት የሆነ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በወንዝ ዳርቻ ያሰወገደ ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር ይቀጣል።

➡️ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል።

➡️ ፍቃድ የወሰዱም ሆነ ሳይወስዱ ፍሳሽን ቀጥታ በወንዞች ዳርቻ ሲያስወግዱ ቢገኙ 100 ሺህ ብር  ይቀጣሉ።

➡️ በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ የፈሳሽ ማጣሪያ ሳይኖር በወንዝ ዳርቻና አካባቢ ተሽከርካሪ ማጠብ 400 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ እንስሳትን ማሰማራት፣ ማስገባት ከተፈቀደው ውጪ ተሽከርካሪ ማሽከርከር 30 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ለመዝናኛ፣ ለመናፈሻና ለፖርክ ከተፈቀደ ውጪ ግንባታ መገንባት 200 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ከአምራችና አገልግሎት ሰጪ  ተቋማት ማንኛውም ያልታከመ ቆሻሻ መልቀቅ 300 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ኬሚካል ነክ ቆሻሻዎችን የማከሚያ ዘዴ ሳይጠቀም የለቀቀ ግለሰብ 50 ሺህ፤ ድርጅት 300 ሺህ ብር ይቀጣሉ።

➡️ ማንኛውም በካይ ቆሻሻ ከተፈቀደ የፈሳሽ ማጠራቀሚያ ውጪ ያፈሰስ ግለስብ 50 ሺህ ፤ ድርጅት 400 ሺህ ብር ይቀጣል።

➡️ የአትክልትና ፍራፍሬ ተረፈ ምርቶችን በወንዝ ዳርቻ ማስወገድ ግለሰብ 20 ሺህ፣ ድርጅት 100 ሺህ ይቀጣሉ።

➡️ ዘይት፣ ጨዋማ ፈሳሽ፣የሞተር ዘይት፣ ነዳጅ ሳሙና ነክ ነገሮችን በወንዝ ዳርቻ ያስወገደ 400 ሺህ ብር ይቀጣል።

➡️ ማንኛውም ያልተጣራ ቆሻሻ ወደ ወንዝ መልቀቅ ግለሰብ 150 ሺህ ድርጀት 300 ሺህ ይቀጣል።

➡️ ፍቃድ ሳይሰጠው ያልታከመ ቆሻሻን ወደ ወንዝ ያስወገደ ግለሰብ 15 ሺህ ብር ድርጅት 40 ሺህ ብር ይቀጣል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tikvahethiopia
#የሠራተኞችድምጽ🔈

🔴 “ የምናደርገው አጥተን ነው ተማረን በእንባ የወጣነው። 3 ልጆች አሉኝ  በ1,000 ብር ደመወዝ ነው የምተዳደረው፤ አሁን የት እንውደቅ ? ” - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

➡️ “ ፕሬዚዳንቱ ተስፋ አስቆረጠን። 'እናንተን ዩንቨርሲቲው እንጂ የቀጠራችሁ የመንግስት ሰራተኞች አይደላችሁም' አለን ” - የ1,100 ብር ደሞዝተኛ

እስከ 20 ዓመታት ' አገለገልን ' ያሉ ከ800 በላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምገባና የሌሎች ሠራተኞች " ዩኒቨርሲቲው ከሥራ ሊያሰናብተን ነው " ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ስሞታ አሰሙ።

ሠራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

አንድ አባት ፥ “ ከ2004 ዓ/ም ጀምሮ ከከተማው ተደራጅቼ በመስተንግዶና ሁለገብ ሥራ ግቢው እንደፈለገ ነው የምሰራው። የአባቶች እግራቸው ተሰብሯል፤ ጥርሳቸው ወልቋል፤ እጃቸው በእሳት ተቃጥሏል ” ብለዋል።

“ የዩኒቨርሲቲ ዋናው ፕሬዚዳንት ‘መንግስት መዋቅር እያስተካከለ ነው። ይህ ሂደት ካለቀ በኋላ ማኀበራትን ሁሉ ያሰናብታል። መንግስት ከዚህ ግቢ አያውቃችሁም’ ብሏል። እንደ አሮጌ እቃ ቆጥረውናልና መፍትሄ የሚሰጠን የህግ አካል መጥቶ ይመልከተን ” ሲሉም ተማጽነዋል።

ልላኛው አባት፣ “ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ16 ዓመታት በላይ ከባልደረቦቻችን ጋር እንጨት እየፈለጥን እየተሸከምን ብዙ የሥራ ጫና ነበረብን ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ወድቄ ከተሰበርኩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኖኛል፤ ነገር ግን ህክምና አላገኘሁም። ሦስት ልጆች አሉኝ በ1000 ብር ደመወዝ ነው የምንተዳደረው። አሁን የት እንውደቅ ? የት እንግባ ? ” ሲሉም ጠይቀዋል።

ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢም፣ “ 9 ቤተሰብ የቤት ኪራይ እየከፈልኩ አስተዳድራለሁ። እኔ ራሴ መማር እፈልጋለሁ። ግን በገንዘብ ማነስ ምክንያት አልቻልኩም። 1,100 ብር ነው የሚከፈለኝ። ይቺን 1100 ብር ታዲያ ወስጄ ምንድን ነው የማደርጋት ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ሌላኛዋ እናት፣ “ ለፍተን እየሰራን ቆይተን አሁን ሁለት ፀጉር አብቅለን በሽተኛ ከሆንን በኋላ ጅብ ይብላችሁ ጎዳና ውጡ ተብለናል።  አራት፣ አምስት ወራት የቆዩትን ቋሚ አድርጎ 20 ዓመት በላይ ቆይታ እያለን ምንም አንዳልጠቀምን ተደርገናል ” ብለዋል።

“ 7 ልጆች አሉኝ ደመወዜ 1000 ብር ነች ከሌሎቹ እኩል አድርጉን እኛም ኢትዮጵያዊ ነን፤ አዋጁ ይመለከተናል፤ ይጨምርልን ስላልን ነው ‘ውጡ’ የተባልነው አንዲያውም አረጋውያን ይደገፉ እንጂ ይጣሉ አይባልም ነበር ” ሲሉም ወቅሰዋል።

ሌላኛዋ ቅሬታ አቅራቢ፣ “ 17 ዓመት ከጅብ ጋር እየተጋፋን እንደ ሻማ ቀልጠን አገልግለናል። ደመወዝ ጭማሪ ስንጠይቅ ‘እንዲያውም እስካሁን አገልግላችኋል አንፈልጋችሁም’ ተባልን ” የሚል ወቀሳ አቅርበዋል።

አክለው፣ “ እኔስ ቆሜ በሚዲያ ተናገርሁ ስንቱ ነው እግሩ የተቀደደው! ስንቱ ነው ሰባራ ሆኖ በየቤቱ ያለው። ቋሚ ሰራተኛ አድርጉን አላልንም ደመወዝ ይጨመርልን ነው የኛ ጥያቄ ” ነው ያሉት።

ሌላኛዋ እናት፣ “ ሙሉ 30 ቀናት ነው አፈር ግጠን የምንሰራው። ስንቀጠር 330 ብር ነበር ትንሽ፣ ትንሽ እየተጨመረልን 1100 ደረሰ። በኋላ ይጨመረናል ብለን ስንጠብቅ አዲሱ ፕሬዚዳንት ጭራሽ ተስፋ አስቆረጠን። ‘እናንተን ዩንቨርስቲው ነው እንጂ የቀጠራችሁ የመንግስት ሠራተኞች አይደላችሁም’ አለን ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ዩኒቨርስቲው ትንሽ፣ ትንሽ እየጨመረ ቆይቷል፤ አሁንስ ለምን አይጨምርም? ኑሮ ውድነቱ በኛስ አልጨመረም ወይ? ብለን ስንጠይቅ፥ ‘እናንተን አናወቃችሁም። እንዲያውም ተንሳፋፊ ሰራተኛ ተመድቦ ይሰራል። እናንተን እናስወጣለን ብዙ ስላገለገላችሁ ይበቃችኋል’ አለን ” ብለዋል።

አክለው፣ “ የምናደርገው አጥተን ነው ተማረን በእንባ የወጣነው ” ያሉ ሲሆን፣ ልላኛው አባትም፣ “ ከ2002 ጀምሬ ነው ዩኒቨርሲቲ ላይ በመስተንግዶ የሰራሁት። በሳምንት፤ በሁለት ሳምንታት ህክምና ለልዩ ልዩ ነገሮች ይኖራሉ። ሁሉን ትተን እየሰራን ቆይተናል ” ብለዋል።

“ ልጆች እናስተምራለን፤ የቤት ኪራይ አንከፍላለን በወር 1,100 በቀን 33 ብር እየተከፈለው በዚህ ኑሮ ውድነት ሰው እንዴት ይኖራል? ብለን ጥያቄ ስናቀርብ ‘በኔ በኩል ጨርሻለሁ ወደ ሚመለከተው ሂዱ የምታመጡት ነገር የለም’ ነው ያለን ፕሬዝዳንቱ ” ሲሉም አማረዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ ለመጠየቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

(ጥረቱ ይቀጥላል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#USA

" ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው ፤ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር አነሳለሁ " - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ምሽት በአሜሪካ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገው ነበር።

በዚህም ንግግራቸው " አሜሪካ ተመልሳለች " ያሉ ሲሆን የሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች " ዩ ኤስ ኤ" በሚል ዝማሬ አጅበዋቸዋል።

ትረምፕ ንግግራቸውን ከጀመሩ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በምክር ቤቱ አዳራሽ ከተሰበሰቡ ሰዎች በተሰማ የስላቅ ድምፅ ንግግራቸው ተስተጓጎሎ ነበር።

የተወካዮች ምክርቤቱ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን የምክርቤቱ ሥነ ስርዐት አስከባሪዎች፣ በቴክሳስ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለምክርቤት አባልነት የተመረጡትን አል ግሪን ከምክርቤቱ እንዲያስወጧቸው አዘዋል።  ሌሎች የምክር ቤቱ አባላትም ሥነ-ስርዐት እንዲከተሉ አሳስበዋል።

ግሪን ከምክርቤቱ አዳራሽ ከወጡ በኋላ ትረምፕ ንግግራቸውን ቀጥለዋል።

ትረምፕ በዚሁ ንግግራቸው " የመጀመሪያው ወር የፕሬዝደንትነት ዘመኔ፣ በሀገራችን ታሪክ እጅግ ስኬታማው መሆኑን ብዙዎች ገልጸውታል " ብለዋል።

ገና በጥቂት ሳምንታት አሳካው ያሏቸውን ስኬቶች አብራርተዋል።

ከነዚህ አንዱ በህገወጥ ስደተኞች ላይ የወሰዱትን እምርጃ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የፌደራል ቅጥር ሂደቶች እና የውጭ ርዳታዎች ላይ እግድ መጣላቸውን ገልጸዋል።

የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ቁጥር እና ሠራተኞችን ለመቀነስ፣ በምፅሃረ ቃሉ 'ዶጅ' በመባል የሚጠራ በኢላን መስክ የሚመራ ተቋም መመስረታቸውን የተናገሩት ትረምፕ በቢሊየኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገንዘብ እያዳነ መሆኑንም አመልክተዋል።

ትረምፕ በንግግራቸው በ48 ዓመት ውስጥ ያልታየውን የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል ከወሰዷቸው ርምጃዎች መካከል " ወርቃማ ፈሳሽ " ሲሉ የጠሩትን የነዳጅ ጋዝ ቁፋሮ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።

" የወሳኝ እና ብርቅዬ ማዕድናት ምርት ይፋጠናል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው " ያሉት ትራምፕ፣ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር እንደሚያነሱ ተናግረዋል።

ትረምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ ያደረጉትን ኃይለቃል የተሞላበት ውይይት ተከትሎ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋርጣለች።

" አውሮፓውያን ዩክሬንን ከመደገፍ ይልቅ ከሩስያ ለሚገዙት ነዳጅ እና ዘይት የበለጠ አውጥተዋል " ያሉት ትራምፕ የዩክሬን ፕሬዝደንት ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደፃፉላቸው አመልክተዋል።

ትረምፕ አክለው " በተመሳሳይ ጊዜ ከሩሲያ ጋራ ጠንከር ያለ ውይይት አድርገን ለሰላም ዝግጁ መኾናቸውን የሚያሳይ ምልክቶች አግኝተናል " ብለዋል።

መረጃው የቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba 🚨" ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊየን 293 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ  ተቀጥተዋል !! " እንደ ሸገር ሬድዮ ዘገባ ፥ በአዲስ አበባ በየቀኑ በአማካይ 7,183 አሽከርካሪዎች በትራፊክ ደንብ መተላለፍ በትራፊክ ፖሊስ ብቻ ይቀጣሉ። ይህ በሌሎች የትራፊክ ደንብ ታላፊዎችን የሚቀጡትን አይጨምርም። ባለፉት በ6 ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ…
#AddisAbaba

በተደመሰሰ፣ በታጠፈ እና በማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር ሲገለገሉ የተገኙ ከ1,000 በላይ አሽከርከሪዎችን ቀጥቻለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አሽከርካሪዎች የተቀባ፣ የታጠፈ ፣ የተፋፋቀ፣ የተቆራረጠ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን በመጠቀም ደምብ ሲተላለፉ ቆይተዋል ሲል ፖሊስ አስታውሷል፡፡

አንዳንዶቹ እንደውም ወንጀል ሲፈፅሙ ተገኝተው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው ብሏል፡፡

ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገ  ቁጥጥር  1,587 ተሽከርካሪዎች  ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን ለጥፈው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

የተፋፋቀ፣ የደበዘዘ፣ የታጠፈ እና የማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር መጠቀም፣ ከሰሌዳ መብራት ውጪ ሌሎች ዓይነቶችን አብረቅራቂ መብራቶችን መጠቀም፣ ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ መለጠፍ እና ሆን ብለው ሰሌዳን አጥፎ መንቀሳቀስ በቁጥጥሩ ወቅት የተገኙ ጥፋቶች ናቸው ሲል ፖሊስ አስረድቷል፡፡

በጥፋት ውስጥ ከተገኙት ውስጥ ኮድ-1 ወይም ታክሲ 216፣ ኮድ-2 ወይም የቤት መኪና 320፣ ኮድ-3 የሆኑ 1,037 እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች 14 መሆናቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ጠቅሷል፡፡

ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል  አብዛኛዎቹ  የፊት ወይም የኋላ ሰሌዳ ሳይኖራቸው የተገኙ  ናቸው፡፡  ቀሪዎቹ 633ቱ ደግሞ  የተቆረጠ ወይም ለዕይታ ግልጽ ያልሆነ ሰሌዳ ሲጠቀሙ የተገኙና ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ ያሰሩ፣ የተሸፈኑና የተለያየ ቀለም የተቀቡ ሰሌዳዎች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

#AddisAbabaPolice #ShegerFM

@tikvahethiopia
አቢሲንያ ባንክ

4ኛ ዙር እችላለሁ!  ማርች 8 እየደረሰ ነው ! ዝግጁ !    
                                                                                                                                                                                               
         የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃና የቲክቶክ ቪዲዮ ውድድር !

ባንካችን በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ምክንያት በማድረግ እ.አ.አ ከማርች 3 ቀን እስከ ማርች 31 ቀን 2025 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡

1) የሙዚቃ ተሰጥዖ ውድድር
ባንካችን የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው ይሸልማል፡፡ አንደኛ ለምትወጣው የብር 100,000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 75,000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 50,000 ሽልማት አዘጋጅቷል።
በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦዬን ያሳያል የምትሉትን ከሶስት (3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያና የድምፅ ማዳመጫ (Earphone) ሳይደረግ በቪዲዮ ሰርታችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ቴሌግራም መላክ ይኖርባችኋል፡፡ የቴሌግራም አድራሻ------------ 0919857373

2) የቲክቶክ ቪዲዮ ተሰጥዖ ውድድር
እንዲሁም በተመረጡ ቲክቶከሮች መካከል ባንካችን ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጃቸውን አደይና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መንገድ የማስተዋወቅ ውድድር ይካሄዳል፡፡በዚህም ውድድር አንደኛ ለምትወጣው የብር 100,000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 75,000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 50,000 ሽልማት አዘጋጅቷል።

3) የሥራ ፈጠራ ውድድር
የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ባሉት ዲስትሪክቶች የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔን ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቶችን የምታሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 19 ቀን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth/ መወዳጀት ይኖርባችኋል፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ለመመልከት ከታች የሚገኘውን የቴሌግራም ሊንክ መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ https://www.group-telegram.com/BoAEth
#SafaricomEthiopia

🎁 ስድስት ወር ሙሉ ዳታ እንደልብ! ለረጅም ጊዜ የሚቆዩትን ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 1,000 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ሶሻል ሚዲያዉን ፏ ፏ እናድርግ! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም አስተማማኝ ኔትወርክ ጋር ወደፊት!⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 " ሙሉ ፓትሮል መኪና መጣብን፡፡ እኛ ሮጠን አመለጥን ሌሎች 5 ሰዎች ታስረዋል " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

➡️ " እየለፉ እስከሆነ ድረስ ቢጨመርላቸው ደስ ይለናል " - የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

⚫️ " የማውቀው ጉዳይ የለም " - የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን

ከማኀበራት ተውጣጥተው በሀዋሳ የኒቨርሲቲ በምገባና ሌሎች ስራዎች ለዓመታት ሰራን ያሉ ወደ 800 ሠራተኞች ደመወዝ እንዲጨመርና ቋሚ ቅጥረኛ እንዲሆኑ ጥያቄ በማቅረባቸው፣ ዩኒቨርሲቲው ከሥራ ሊያሰናብታቸው መሆኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለው ነበር።

ሠራተኞቹ ዛሬ በሰጡን ቃልስ ምን አሉ ?

“ ደመወዝን በተመለከተ ቅሬችንን ለመግለጥ ወደ ደቡብ ኤፍኤፍ እየሄድን በነበረበት የተወሰኑ ሰዎች ታስረዋል መብታቸውን ስለጠቁ ታስረዋል፡፡ አንዱ ታሳሪ ታሟል፡፡

ጠዋት ደቡብ ኤፍኤም ቀጥሮን ነበር፡፡ 2 ሰዓት ተኩል ወደ ጣቢያው ስንሄድ ሙሉ ፓትሮል መኪና መጣብን፡፡ እኛ ሮጠን አመለጥን ሌሎች 5 ሰዎች ታደስረዋል፡፡ ጠዋት ነው የታሰሩት አሁን ስንሄድ ቃላቸውን የሚቀበላቸው የለም። እኛንም እየፈለጉን ነው ካፓስ ውጪ ነን። 

ሰዎቹ የታሰሩት ሀዋሳ 01 ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡ ምንም አላጠፋንም፡፡ ‘ለምን ተሰባሰባችሁ’? ሲሉን የደመወዝ ጭማሪ አልደረሰንም፡፡ በ1,000 ብር ደመወዝ እየሰራን ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልንም፡፡ መንግስት እንዲመለከተን ለሚዲያ ቃላችንን ልንሰጥ ነው የመጣነው አልናቸው፡፡

ከዚያ በኋላ ‘እንዴት ስማችን ይጠፋል? ለምንድን ነው የምታስተላልፉት’? ብለው ነው ወንዶቹን አተኩረው ያሰሯቸው። የታሰሩት ሠራተኞች እንጨት ሲፈልጡ ለትርፍ አንጀት በሽታ ተጋልጠው ቀዶ ጥገና የተሰሩ ናቸው፡፡ አንዱ መኪና ላይ ሲወረውሩት ራሱን አያውቅም።

መንግስት ይየን፡፡ ፍትህ ይደረግልን፡፡ የኑሮ ውድነት እኛን አልነካም? እኛ ልጆች የሉንም? ለምንድን ነው መንግስት የማያየን? የኑሮ ወድነቱን አልቻልንም፡፡ ተንከራተን ነው የምንኖረው፡፡ ልጆቻችን እየተራቡ፣ እየተጠሙ ነው፡፡

24 ሰዓት ነው ግቢ ውስጥ የምንሰራው፡፡ ከግቢ ወጥተን ሌላ ሥራ ለመስራትም ጊዜ የለንም፡፡ ሁሉም በችግር ላይ ነው። በዛ ላይ ወጥ የተደፋባቸው፣ እጃቸውን ማሽን የቆረጣቸው አሉ። አካል ጉዳተኞቹንም ለማሳየት ነበር ወደ ሚዲያ የሄድነው፡፡ ግን መብታችን ተረግጧል፡፡ ዲሞክራሲም የለም፡፡

አካል ጉዳተኞች 50 በላይ ይሆናሉ፡፡ እናቶች መንቀሳቀስ ስለማይችሉ ቤት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ የሚያሰሩት ሰዎችን 600 ብር ቀጥረው ነው፡፡ መስራት ስላማችሉ፡፡ ከታሰረው እንዱ ራሱ ወጥ ተደፍቶበት እግሩ ተቃጥሏል፡፡

እንጨት ከጫካ ተሸክመን አምጥተን ፈልጠን በዬኩሽናው እናደርስ ነበር። እንደዚህ ደክሞን ውለን የምንታጠብበት ሳሙና አልነበረንም። ችግር ከትክሻችን አልወርድ አለ። 

ለሌሎች ደመወዝ ሲጨመር የኛስ ድካም ለምን አይታይም? ልጆች እናስተምራለን፣ የቤት ኪራይ አለብን። 'ደመወዝ ተጨምሯል' ሲባልም የቤት ኪራይ ተጨምሮብን 'ቅድሚያ ካልከፈላችሁ ውጡ’ እየተባልን ነው፤ ተጨንቀናል ” ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች አማረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሠራተኞችን ቅሬታ ይዞ ፤ ሰዎቹ የመብት ጥያቄ ስላነሱ ለምን ታሰሩ ? ይህን ማድረግ አግባብ ነው ? ሲል የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ጠይቋል።

አንድ የቢሮው አካል በሰጡት ምላሽ፣ የደመወዝ ጭማሬና ቋሚ ሰራተኛ መሆንን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው የራሱ መተዳደሪያ ደንብ እንዳለው፣ ጭማሬው ለቋሚ ሠራተኞች እንጅ ለጊዜያዊ እንደማይሆን ገልጸዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ለሰዎቹ ደመወዝ የመጨመርና ቋሚ ሠራተኛ ማድረግን የሚመለከተው ዩኒቨርሲቲው ሆኖ እያለ፣ ሠራተኞቹ የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው መታሰታቸው አግባብ ነው ? ሲል ለእኝሁ አካል በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

እሳቸው በምላሻቸው፣ ከክልል ይታሰሩ እንዳልተባለ ገልጸው፣ " አንተ እንዳልከው እኛ ደመወዝ ይጨመርላቸው፤ አይጨመርላቸው የመተዳደሪያ ደንብ ስላላቸው እነርሱ ናቸው የሚያስተካክሉት " ብለዋል፡፡

" ቢጨምሩላቸው እኛም ደስ ይለናል፡፡ እየለፉ እስከሆነ ድረስ ቢጨመርላቸው ደስ ይለናል፡፡ ግን እነዚህ ሰዎች ታስረዋል ? ማነው ያሰራቸው ? የሚለውን ለመጠየቅ እየሞከርኩኝ ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ናቸው፡፡ ሲወጡ እንዴት ታሰሩ ? የሚለውን አጣራለሁ " ብለዋል፡፡

በተጨማሪም፣ ሠራተኞችን ለምን እንደታሰሩ ማብራሪያ  የጠየቅናቸው የሲዳማ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጩቦ በሰጡን ቃል፣ " የማውቀው ነገር የለም " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
 
(የክልሉ ፓሊስና ጸጥታ ቢሮ ተጨማሪ አጥጋቢ ምላሽ  ከሰጡን የምናቀርብ ሲሆን፣ ጉዳዩንም እስከ ጥግ እንከታተለዋልን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያስፈፅሙ አሳሰበ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ * የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዋና ዓላማ መዘንጋት የለባቸውም " ሲሉ አሳሰቡ።

ሚኒስትሩ ይህን ማሳሰኒያ የሰጡት ዛሬ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

" ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅባቸዋል " ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ፥ ተቋማቱ በአካባቢ ሳይታጠሩ ለተመሠረቱበት ዓላማ መኖር አለባቸውም ብለዋል፡፡

- የሙስና መንሰራፋት፣
- ግብረ-ገብነት ማጣት
- ዕውቀት የመቀያየር ባሕል በምሁራን ዘንድ መቀዛቀዙን አንስተዋል

እነዚህ ችግሮች ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የዕውቀት ማዕከል እንዳይሆኑ አድርገዋል ብለዋል።

" ሀገራችን በዘርፈ-ብዙ ችግሮች ውስጥ በመሆኗ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት እና የእውነት ማዕከል እንዲሆኑየሪፎርም ሥራ እየተከናወነ ነው " ሲሉም አመልክተዋል።

ተቋማቱ፤ ጥራት ባለው ትምሕርት ትውልድን መቅረጽ እና የማሕበረሰቡን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ ምርምሮችን በማድረግ ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም በአጽንኦት አሳስበዋል።

Credit -
#FMC

@tikvahethiopia
2025/03/06 01:28:26
Back to Top
HTML Embed Code: