TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” - ሙስሊም ተማሪዎች 🔵 “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” - ዲላ ዩኒቨርሲቲ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው…
#Update
🔴 " ዩኒቨርሲቲያችን እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
➡️ " ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " - ሙስሊም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት የእስልምና እምነት ተከታይ / ሙስሊም ተማሪዎች " በሃይማኖታዊ አለባበሳችን ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን አድርሰዋል።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ተማሪዎቹ መካከል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ እና ሰመራ ካምፓስ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " አትግቡ መባል ከጀመርን አንድ ወር ገደማ ሆኗል " ያሉን ሲሆን " በሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኮሚቴ አማካኝነት በፅሑፍ ቅሬታ አቅርበን ስንጠባበቅ ከሰኞ ጥር 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ ' ንቃብ ማድረግ አትችሉም ' ተብለን ግቢ እንዳንገባ በመከልከላችን በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለን እንገኛለን " ብለዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ተወካይ ኑሬዲን አብደላህ ፤ " ችግሩ ከተማሪዎች ባሻገር አንዲት የዩኒቨርስቲው መምህርትም ጭምር ያካተተ ስለነበር ለዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮች ቅሬታ በፅሑፍ አቅርበን በቂ ምላሽ ስላልተሰጠን ተማሪዎች በዚህ የፈተና ወቅት በመስጊዶች ዉስጥ ተጠልለዉ ይገኛሉ " ብሏል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ከማል ሀሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ በደቡብ ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኩል 150 ተማሪዎች ከእስላማዊ አለባበሱ ጋር በተያያዘ ክልከላ እንደተደረገባቸውና አብዛኞቹ የፈተና ወቅት በመሆኑ ኒቃብ አዉልቀዉ ማስክ እየተጠቀሙ ወደ ግቢ እንደገቡ ገልጸዋል።
ስራ አስኪያጁ ፥ 22 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች አሁንም በመስጊዶች ተጠልለው እንደሚገኙ መረጃዉ በጽሑፍ እንደደረሳቸው ገልፀዉ ጉዳዩን ለትምህርት ሚንስትር በፅሑፍ ማቅረባቸውንና " ባለድርሻ አካላት የቆዩ መመሪያዎችን ዳግም ማየት ይጠበቅባቸዋል " ብለዋል።
" ከሁለት ዓመታት በፊት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ችግር ተነስቶ እንዲረግብ ተደርጎ የነበረ ሲሆን አሁንም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ችግሩ ላለመነሳቱ ዋስተና የሌለ በመሆኑ እነዚህን አጋጣሚዎች ለሌሎች ፍላጎቶች በሚጠቀሙ አካላት ጉዳዩ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ዘላቂ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል " ብለዋል።
ቲክቫህ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)ን ስለ ጉዳዩ አነጋግሯቸዋል።
ዶክተር ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፥ " የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሁሉም የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነዉ " ብለዋል።
" በዩኒቨርሲቲው ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ አልተከለከለም ኒቃብ ደግሞ አስቀድሞም በዩኒቨርሲቲ አይደረግም ነበር " ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለዉም " በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ዩኒቨርሲቲዉ ' ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ሂጃብ መልበስ ከልክሏል ' በሚል የሚሰራጨዉ መረጃ ትክክል ያልሆነ ሀሰተኛ መረጃ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
በዚህ ምክንያት ወጪ አሉ ስለተባሉ ተማሪዎች እና ስላመለጣቸዉ ፈተናዎች እንዲሁም ስለዩኒቨርስቲው ቀጣይ አቋም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበዉ ጥያቄ የተለየ ዉሳኔ አለመኖሩን ዩኒቨርስቲው አስታዉቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94027
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94027