Telegram Group & Telegram Channel
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔን ዛሬ ይሁን ነገ አልቀበልም " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ አተኩሮ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። ይህንን ተከትሎ ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ቡድኑ…
#TPLF

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማዕከላዊ ዉጥጥር ኮሚሽን ፥ የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ትእዛዝ እና ውሳኔን አልቀበለውም / ተቀባይነት የለውም ብሏል።

" ቦርዱ ያሳተላለፈው ውሳኔ እና ትእዛዝ ህጋዊ መሰረት የሌለው ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የሚጣረስ ነው " ሲል የገለጸው ኮሚሽኑ " ቦርዱ ትዕዛዝ እና ውሳኔ ከመስጠት እንዲቆጠብ " ሲልም ገልጿል።

የቁጥጥር ኮሚሽኑ " የኢትየጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጥር 10/2013 ዓ.ም ህወሓትን ከህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር ሰርዞ ነበር ፤ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ግን ነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ህጋዊነቱ ተመልሶለታል " ብለዋል።

" ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አዲስ የፓለቲካ ፓርቲ መመዝገቡ ተቀባይነት እንደሌለው ፓርቲው ወድያውኑ ገልፀዋል " ሲልም ጠቁሞ " ይሁን እንጂ ቦርዱ ፓርቲው ያቀረበውን 'የአልቀበልም" ምላሽ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ 'ልክ አይደለም ' " ሲል አብራርተዋል።

" የህወሓት ህጋዊነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ (Reinstate) እንዲደረግ እንጠይቃለን " ያለው ኮሚሽኑ ፤ " ከዚህ ውጭ ያለው ውሳኔ እና ትእዛዝ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

ከቀናት በፊትም የነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ባወጣው መግለጫ " ለሁለትዮሽ ውይይት ዝግጁ ነኝ የምርጫ ቦርድን የተናጠል ውሳኔ ዛሬም ይሁን ነገ አልቀበልም " ማለቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በሕጉ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።

ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።

ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።

@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/93981
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/93981

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

On Feb. 27, however, he admitted from his Russian-language account that "Telegram channels are increasingly becoming a source of unverified information related to Ukrainian events." Sebi said data, emails and other documents are being retrieved from the seized devices and detailed investigation is in progress. Two days after Russia invaded Ukraine, an account on the Telegram messaging platform posing as President Volodymyr Zelenskiy urged his armed forces to surrender. In addition, Telegram now supports the use of third-party streaming tools like OBS Studio and XSplit to broadcast live video, allowing users to add overlays and multi-screen layouts for a more professional look. In 2018, Russia banned Telegram although it reversed the prohibition two years later.
from es

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American