Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/tikvahethiopia/-94115-94116-94117-): Failed to open stream: No space left on device in /var/www/group-telegram/post.php on line 50
TIKVAH-ETHIOPIA | Telegram Webview: tikvahethiopia/94115 -
Telegram Group & Telegram Channel
" እግዚአብሔር ያለዉ ይሆናል ብዬ አይዞ ! አይዞ ! እያልኩ ነበር ወደ ወንዝ ዉስጥ የገባነዉ፤ በፈጣሪ እርዳታ ነው እንጂ በህይወት መትረፍ የማይታሰብ ነበር " - ከአደገኛ የመኪና አደጋ በህይወት የተረፈው ረዳት

በቅርቡ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ ገላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ከባድ የትራፊክ አደጋ ተከስቶ የ71 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፎ እንደነበር አይዘነጋም።

በትናንትናው ዕለት ምሽት ይኸው ቦታ ሌላ የትራፊክ አደጋ አስተናግዷል።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ- 3 - 85774 ኢት የሆነ ሲኖትራክ መኪና በትናንትናው ዕለት ምሽት 5:30 ገደማ ዶንጎራ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ የግንባታ አሸዋ ጭኖ ወደ በንሳ ወረዳ እየሄደ በነበረበት ወቅት ቦና ዙሪያ ወረዳ ገላና ወንዝ ሲደርስ ከሳምንታት በፊት የ71 ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈዉ ቦታ አደጋ ደርሶበታል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ አደጋዎች መከላከል ዳይሬክቶረት ዳይሬክተር ዋና ኢ/ር ዳንኤል ሹንኩራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ በመኪናዉ ዉስጥ ሹፌሩ እና ረዳቱ ብቻ ነበሩ።

" ከቦታዉ አደገኝነትና ከጫነዉ ሙሉ አሸዋ ክብደት አንፃር በሕይወት ይተርፋሉ ተብሎ ባይታሰብም በፈጣሪ እርዳታ መኪናዉ ተገልብጦ በአራቱም ጎማ ዉሃ ዉስጥ ማረፉን ተከትሎ በሕይወት መትረፋቸዉን " ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሲኖትራክ ሹፌሩን አቶ ቴዎድሮስ ተስፋዬን እና ረዳቱን ወጣት ሲሳይ አንዴቦ በስልክ አግኝቶ አነጋግሯቸዋል።

" ምሽት 5:30 ገላና ወንዘ አከባቢ ስንደርስ ፍሬን እምቢ አለኝ " ያለው ሹፌሩ " አሸዋ ጭነን ስለነበር በድንጋጤ ዘለህ ዉረድ...እያልኩ ረዳቱን ብማፀንም ግራ በተጋባንበት ሁኔታ እያየኝ መኪናዉ ከቁጥጥሬ ዉጪ ሆኖ ወደ ገደል ገባ " ሲል ስለሁኔታው አስረድቷል።

ረዳቱ ወጣት ሲሳይ አንዴቦ በበኩሉ " ከቦታዉ ቁልቁለታማነት እና መኪናዉ ከነበረበት ፍጥነት አንፃር እሱ ' ዝለል ' እያለኝ የነበረ ቢሆንም መዝለሉ የባሰ አደጋ ስለነበረዉ እግዚአብሔር ያለዉ ይሆናል ብዬ አይዞ ! አይዞ ! እያልኩ ነበር ወደ ወንዝ ዉስጥ የገባነዉ " ሲል ስለሁኔታው አክሏል።

" በፈጣሪ እርዳታ እንጂ ከቦታዉ አደገኝነት አንፃር በሕይወት መትረፍ የማይታሰብ ነዉ " የሚሉት ሹፌርና ረዳቱ " ሰዎች እየደወሉ ' ሞልታችኋል ተብሎ በየፌስቡኩ እየተሰራጬ አይደል!? ' እያሉ ይጠይቁናል " ብለዋል።

" በወቅቱ መኪናዉ ወደታች ሲወድቅ በጎማ ዉሃ ዉስጥ በማረፉ በኛ ላይ የከፋ አደጋ አልደረሰም " ያሉን ሲሆን " በአካባቢዉ ሰዎች እርዳታ ወዲያዉኑ ወደ ቦና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተወስደን መጠነኛ ሕክምና ከተደረገልን በኋላ በትራንስፖርት መኪና ተሳፍረን ወደ ሀዋሳ መጥተናል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ይህ ቦታ ካስከተለዉና እያስከተለ ካለዉ አደጋ አንፃር ምን ታስቦበታል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሲዳማ ክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመንገድ ደህንነት ዘርፍ ኃላፊ ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ ጥያቄ አቅርቧል እሳቸውም ጉዳዩን ለፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ማቅረባቸውንና ዘላቂ መፍትሔ እንዲበጅለት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94115
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94115

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Ukrainian President Volodymyr Zelensky said in a video message on Tuesday that Ukrainian forces "destroy the invaders wherever we can." Again, in contrast to Facebook, Google and Twitter, Telegram's founder Pavel Durov runs his company in relative secrecy from Dubai. Individual messages can be fully encrypted. But the user has to turn on that function. It's not automatic, as it is on Signal and WhatsApp. Unlike Silicon Valley giants such as Facebook and Twitter, which run very public anti-disinformation programs, Brooking said: "Telegram is famously lax or absent in its content moderation policy." It is unclear who runs the account, although Russia's official Ministry of Foreign Affairs Twitter account promoted the Telegram channel on Saturday and claimed it was operated by "a group of experts & journalists."
from es

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American