group-telegram.com/TIBEBnegni/2560
Last Update:
የእግዚአብሔር ጸጋ
የእግዚአብሔር ጸጋ ማንንም ሳያስቀር ሰዎችን ሁሉ ስለሚጎበኝ ኃጢአተኞች እንኳ ከዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ ጉብኝት ተቋዳሾች ናቸው። ስለ ጌታችን እንዲህ ተብሎ ትጽፏል “እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስ የተገዙትንም እየፈወሰ ዞረ” ሐዋ. 10፥38። እርሱ የጠፉት ነፍሳት ባለመታመናቸው በልበ ደንዳናነት ከእርሱ ርቀው ቢጠፉም እርሱ ግን መፈለጉን አላቋረጠም። የነበሩበት እጅግ ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም እንኳ መልሶ እስከሚያመጣቸው ድረስ ፍለጋው አልተቋረጠም።
ሰዎች ስለ ድኅነታቸው ተስፋ የሚቆርጡ ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ግን በሰዎች ላይ ተስፋ ማሳደሩን አያቋርጥም። እግዚአብሔር በመንፈሳቸው የደከሙትን ቀርቶ ሞቶ ሥጋው በመሽተት ላይ ያለውን ሰው እንኳ ሳያስቀር ለሁሉም ሁሉ ጊዜ በጎ ነገርን ይሰራል። (ዮሐ. 11፥39) ከዚህ በተጨማሪ እርሱ በሕይወቱ የመጨረሻ ህቅታ ለነበረው ወንበዴ፣ ለቀረጥ ሰብሳቢው ዘኪዎስና አምስት ባሎች ለነበርዋት ሳምራዊት ሴት ይሰራ ነበር። (ሉቃስ. 23፥43፣ ሉቃስ. 19፥9፣ ዮሐ. 4፥18)። እርሱ ያቺ ጠፍታ የነበረችው ሳምራዊት ሴት ወደ ንስሐ ሊመራት ያለችበት ድረስ ሄዶ ፈልጓታል።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእግዚእብሔርን ፍቅር በማስመልከት “እግዚአብሔር ለድኅነታችን ምክንያት ይሆን ዘንድ አንዲት ዘለላ እንባ እንኳ ትበቃዋለች። ይህች ዘለላ እንባ የከንቱ ደስታ ባለቤት በሆነው በዲያብሎስ ከመነጠቅዋ በፊት ለእኛ ለድኅነታችን ምክንያት እንድትሆን እግዚአብሔር ይቀበላታል” ብሎ ነበር።
በእርግጥ ከእኛ ልቦናዎች ይበልጥ እጅግ ርኅሩኅ ከሆነው ከአምላካችን ልብ የሚበልጥ የለም። ይህንን በማስመልከትም አምላካችን እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል “ቀኑን ሁሉ ወደማይታዘዝና ወደ ሚቃወም ሕዝብ እጆቼን ዘረጋሁ” (ሮሜ. 10፥21፣ ኢሳ. 65፥2)።
አምላካችን እግዚአብሔር ኃጢአት እንጂ ኃጥእ አይጸየፍምና ያለ አድልዎ ለሁሉም በእኩል ዓይን ይጎበኘዋል።
ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
BY ሰው መሆን...
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/TIBEBnegni/2560