Telegram Group Search
TIKVAH-ETHIOPIA
#ስምረት “ አሁን የተሰጠን ጊዜያዊ እውቅና ነው። ይሄ ማለት ደግሞ በሦስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ አለብን ” - አቶ ጣዕመ ዓረዶም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለእነ አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ መስጠቱ ታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የምርጫ ቦርድ ፈቃድ ቦርዱ የተሰጠውን የስልጣን ዐዋጅ ጠቅሶ፣ “ ይህ የክልላዊ የፓለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ…
" የፓርቲያችን መስራች ጉባኤ ትግራይ ይደረጋል ፤ ስንመለስ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ የማድረግ ሃላፊነት ለጊዚያዊ አስተዳደሩና ለፀጥታ አካላት የሚተው ይሆናል " - አቶ ረዳኢ ሓለፎም

በእነ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ስምረት (ሶሊዳሪቲ) ፓርቲ ቅድመ እውቅና ካገኘ ቀናት ተቆጥረዋል።

ከህወሓት ተነጥለው የወጡ መስራች አባላት ፓርቲያቸው የማስተዋወቅ ስራ በስፋት ተያይዘውታል።

ሰኞ ግንቦት 18/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ማግኘቱ በምስክር ወረቀት አስደግፎ ያስታወቀው ፓርቲው በስፋት ራሱን እያስተዋወቀ ነው።

በክልሉ የሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ፣ ድምፂ ወያነና 104.4 የመቐለ ኤፍኤም ስለ ፓርቲው መመስረት እስካሁን የሰጡት ዜና ሽፋን እንደሌለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አረጋግጧል።

የትግራይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ (ከሁለት ወራት በላይ ከትግራይ ውጪ ቢሆኑም ከሃላፊነት ስለመነሳተቸው በይፋ የተገለፀ የለም) ረዳኢ ሓለፎም የስምረት (ሶሊዳሪቲ) ፓርቲ መስራች አባልና በፓርቲው የኮሙኒኬሽንና ሚድያ ተጠሪ ናቸው።

ተጠሪው ትናንት ግንቦት 20/2017 ዓ.ም መቐለ መሰረቱ ለሆነው ላዛ ትግርኛ ለተባለ ሚድያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

- የፓርቲው መስራቾች ከ90 በመቶ በላይ ለውጥ ፈላጊ የሆኑ በክልሉ የሚኖሩ ወጣቶች ፣ ሙሁራን በከተማና ገጠር እንዲሁም በውጭ አገር የሚኖሩ ትግራዎት ሲሆኑ የአስተባባሪነት ሚናው ከህወሓት ተለይተው የወጡት 15 የማእከላይ ኮሚቴ አባላት ናቸው።

- የፓለቲካ ፕሮግራማችን እንዲጎለብት ረቂቁን ለሚድያዎችና ለመስራች አባላት እንዲደርስ እናደርጋለን ፤ አስተያየት ታክሎበት የተሟላ ሰነድ ሆኖ በመስራች ጉባኤ ይፀድቃል።

- የዓለም የዲፕሎማሲ ፣ የፓለቲካ ፣ የቴክኖሎጂ  አሁናዊ ሁኔታ ያካተተ የፓለቲካ አይዲዮሎጂ እንከተላለን፤ ስለሆነም የአባላትና የሚድያ ባለሙያዎች አስተያየት እስኪታከልበት የፓለቲካ አይዲዮሎጂያችን ይህ ነው ማለት አይቻልም።

- ዋና የፓለቲካ ትግል መሰረታችን ትግራይ ላይ ቢሆንም ከሁሉም ብሄሮች ፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእኩልነትና አንድነት የተመሰረተ የትግል አጋርነት ይኖረናል።

- ህወሓት መለወጥ ያቆመ ወደ ሙዝየም መግባት ያለበት ድርጅት ነው። እኛ ከህወሓት በተሻለ ለትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንታገላለን።

- መሬት የህዝብና የመንግስት ነው የሚለው በድጋሜ እንዲጠና ማድረግ አንዱ የመታገያ የፓለቲካ አማራጫችን ነው።

- እኩልነት የተረጋገጠባት የበለፀገች ትግራይ እንድትኖር እንታገላለን ትግላችን በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳር የሚካሄድ ነው ፤ ከኤርትራ ከጎረቤት በዘለለ የሚያገናኘን ነገር የለም።

- ድርጅታችን መቋቋሙ በአገር ውስጥና በመላ ዓለም ላሉ ደስታንና መነቃቃትን ፈጥሯል። "ዘግይታቹሃል " የሚሉን አሉ ልክ ናቸው ከነበርንበት ህወሓት የተሻለ ፓርቲ ለመፍጠር ብዙ ማስብ ነበረብን።

- ከይፋዊ ምስረታ በኃላ ተከታታይ የአባላት ምልመላ ስራ እንሰራለን፤ አባሎቻችን ድሮ እንደነበርንበት ህወሓት በስብሰባና ጭቅጭቅ ሳይሆን በስራ ገበታቸው እንዲውሉ የሚያደርግ አቅጣጫ እንከተላለን።

- መስራች ጉባኤያችን ትግራይ ላይ ነው የሚሆነው አዲስ አበባ ያለነው ሁላችን እንሳተፋለን። ስንመለስ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ፀጥታ የማስከበሩ ጉዳይ ለጊዚያዊ አስተዳደሩና ለፀጥታ አካላት የሚተው ነው።

- እኛ ታጣቂ ሃይል የለንም፤ ቢሆንም በረሃ ላለው ታጋይና ያነገበው ዓለማ እንደግፋለን እውቅናና ክብር እንሰጣለን። ታጋዩ " ወደ ህዝቤ መተኮስ የለብኝም  የተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ልክ አይደለም " ብሎ የወጣ ነው። ስለሆነም ይህ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ እንጂ የእኛ የስምረት የፓለቲካ ፓርቲ ታጣቂ ሊሆን አይችልም።

#ላዛትግርኛ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ኮሌጆች ወደ ጠቅላላ ትምህርት ለመግባት ዝግጅት ላይ ናቸው " -አስተያየት ሰጪ የዘርፉ ተዋናዮች

➡️ " አብዛኞቹ ኮሌጆች በራሳቸው መንገድ መክሰማቸው አይቀርም "

አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መቀጠል ስላልቻሉ ትምህርት ቤት ከፍተው ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ስማችን አይጠቀስ ያሉና በዘርፉ የተሰማሩ ተዋናዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ተማሪዎች ስለማያገኙና መንግስት ያወጣውንም መመዘኛ ስለማያሟሉ፣ ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኞቹ በዘርፉ አይቀጥሉም ሲሉ ነው ያስረዱት።

አንድ የዘርፉ ተዋናይ አስተያየት ሰጪ፣ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ወደ ጠቅላላ ትምህርት ገብተው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ባለው ዘርፍ ለማስተማር ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሌላ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚሰሩ ሁለተኛ አስተያየት ሰጪም እንደዚሁ፥ " ተቋማቱ ተማሪ የማግኘት ፈተና ስለገጠማቸውና መንግስት ያወጣውንም አዲስ መመዘኛ ለማሟላት ከባድ ስለሆነ ወደ ጠቅላላ ትምህርት ለመዞር እንቅስቃሴ እንዳለ መረጃው አለኝ " ብለዋል፡፡ 
          
አንደኛው ባለሙያ ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ መጀመሪያ 84 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዲሱ መስፈርት መሰረት ዳግም ለመመዝገብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ እንደሚዘጉ ገልፆ ነበር፡፡ ሌሎች 9 ተቋማትም በተመሳሳይ አካሔድ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ሲል ነበር፡፡

በኋላ ላይ በመመሪያው መሰረት ዳግም ለመመዝገብ ያመለከቱት 287 ተቋማትም አንዳቸውም መስፈርቱን እንዳላሟሉ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሚድያ ገልጿል።

እነሱ በአዲሱ መመሪያ መሰረት መስፈርቱን እንዲያሟሉ የ45 ቀን ጊዜ ተሰጣቸው። ሆኖም የተሰጠው መስፈርት የሚሟላ አይነት ስላልሆነ 45 ቀን አልፎ ወደ ሶስት ወር እየሔደ ነው አሁን፡፡

ከዛም ሁላችንንም ጠሩንና ሁላችሁም ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ስለሆናችሁ ያሉዋችሁን ተማሪዎች አስጨርሱ አሉን፡፡ አሁን እኛ ያሉንን ተማሪዎች በ2018 አስጨርሰን እንዘጋለን፡፡ በመንግስት እስካሁን ምንም አይነት እርምጃም አልተወሰደም ቀጣዩን እርምጃ እየጠበቅን ነው፡፡

እዚህ ሀገር ከነበሩት የግል ኮሌጆች ከ90 ከመቶ በላይ የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ያስተምራሉ፡፡ አሁን አብዛኞቹ ተማሪዎች ስለማያገኙ በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማሩ አይደሉም፡፡

ከ12ኛ ክፍል 3 በመቶ ብቻ ማሳለፍ ሲጀመር የአብዛኞቹ የግል ኮሌጆች የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ቆሟል። የ12ኛ ክፍል ፈተናን እያለፉ ያሉት ተማሪዎች አይደለም ለግል ኮሌጆች ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችም አይዳረሱም፡፡ የማስተርስ ፕሮግራም ጀምረው የነበሩ የግል ተቋማትም ይህን ፕሮግራም አጥፈዋል አብዛኞቹ፡፡

መንግስት አዲስ መመሪያ ስላወጣ ብቻም ሳይሆን ተማሪ ስለማያገኙ ከገበያው ይወጣሉ አሁን አብዛኞቹ ስራ አቁመዋል፡፡ በሒደት ደግሞ በራሳቸው ጊዜ ይከስማሉ፡፡

በተለይም የተቀመጠው አዲስ መስፈርት ይሟላ ከተባለ ወደ 90 ከመቶ የሚሆኑት ኮሌጆች እንደሚዘጉ ግልፅ ነው፡፡ ምናልባት በጣም ጥቂቶች የራሳቸው ህንፃ ያላቸውና የተደራጁ ተቋማት ይቀጥሉ ይሆናል፡፡

አብዛኞቹ ተቋማት ወደ ጠቅላላ የትምህርት ዘርፍ ለመግባት ዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ አሁን ባለኝ መረጃና ግምት (የግል አስተያየት) ከ40 - 50 ከመቶ የሚሆኑት የግል ተቋማት ወደ ጠቅላላ ትምህርት ይገባሉ፡፡ ትምህርት ቤት ለመክፈት መስፈርቱና ቅድመ ዝግጅቱ ከበድ ስለሚል በ2018 ዓ.ም ሙሉ ዝግጅት አድርገው በ2019 ዓ.ም ስራ ለመጀመር እየተዘጋጁ ያሉ ተቋማት አውቃለሁ፡፡

ከመዋዕለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ለማስተማር በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ እኛ በአዲስ አበባም በክልልም ያለንን ኮሌጅ ዘግተን ትምህርት ቤት ለመክፈት እየተዘጋጀን ነው ያለነው " ብለዋል።

ሁለተኛው አስተያየት ሰጪ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የተማሪ እጥረትና አሁን የመጣው አዲስ መስፈርት የተወሰኑ ተቋማትን ያከስማል፡፡ አሁን በማስተርስ ዲግሪ ብቻ ሲያስተምሩ የነበሩ ተቋማት በተማሪ እጦት የተነሳ ይህን ፕሮግራም አጥፈዋል፡፡ ዳግም ምዝገባው ምክንያት ነው የሆነላቸው፡፡ ዳግም ተመዝግበው ምንድነው የሚያደርጉት ተማሪ ከሌለ፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪ የሚያስተምሩትም ተማሪ እያገኙ አይደሉም፡፡

በአጠቃላይ ኢንዱስትሪው ተመቷል፡፡ በጣም ተጎድቷል፡፡ ለዚህ ነው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወደ ጠቅላላ ትምህርት ዘርፍ ለመዞር እየተዘጋጁ ያሉት፡፡ ከተቋማቱ እንዲህ አይነት ፍላጎት መኖሩን አውቃለሁ እሰማለሁ፡፡

ቀድሞ የተዘጋጀ የትምህርት ቁሳቁሶች ስላሉዋቸው ለእነሱ ዘርፉ አዋጭ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች የሚያስከፍሉት ክፍያ አንድ የዲግሪ ተማሪ በወር ከሚከፍለው ያነሰ አይደለም፡፡ ለአስተማሪዎች የሚያወጡት የደመወዝ መጠንም እንደ ኮሌጅ ከፍተኛ ላይሆን ይችላል፡፡

አዲሱን መስፈርት ለማሟላት ከባድ ነው
በአዲሱ መመሪያ ተመዘገቡ ከተባሉት 287 ተቋማት አንዱ የእኛ ነው፡፡ ሐላፊዎቹ መጥተው ጉብኝት ካደረጉ በኋላ፣ የጎደለንን ነገር ነግረውን፣ አሟልተን ሰነዱን አስገብተናል፣ እስካሁን ምላሻቸውን እየጠበቅን ነው ያለነው፡፡

በሐላፊዎቹ ያልተጎበኙም ይኖራሉ ብቁ ያልሆኑትን አንጎበኝም ብለዋል፡፡ ሆኖም አንድም ተቋም መስፈርቱን አላሟላም ሲል ሰምተናል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፡፡

አንድም ተቋም መስፈርቱን ካላሟላ ይህን ሁሉ ተቋም በአንዴ ይዘጋሉ ብዬ አላምንም፡፡ ቁሳቁሱን ማሟላት ትችላለህ፣ የሰው ሀይል ግን እነሱ በጠየቁት መሰረት ከዬትም ልናመጣ አንችልም፡፡ የሰው ሀይል ለማሟላት ደግሞ የገንዘብ አቅም ፈተና ሆኗል ከዬት ይመጣል፡፡ ያላቸውንም ሰራተኛ ይዘው ለመቀጠል የሚቸገሩ ተቋማት አሉ " ብለዋል።
          
በዚህ ጉዳይ ዙርያ፣ ከኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ አስተያየትና ምላሽ ካገኘን በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን፡፡   

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ነጭ ውሽትና የሶሻል ሚድያ ተከታይ ቁጥር ለማብዛት የተፈበረከ ነው ፤ በመከላከያ የተሰጠኝ ኃላፊነት የለም " - ጄነራል ሳሞራ የኑስ

የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የነበሩትና በጡረታ የተሰናበቱት ጄነራል ሳሞራ የኑስ " ዳግም ወደ መከላከያ ሰራዊት ተመልሰዋል ፤ መከላከያ ውስጥ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ፤ ከጄነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል ጋር በመሆን አፋር የሚገኝ ጣቢያ አስተባባሪ ሆነው ተመድበዋል " የሚሉ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲሰራጭ ነበር።

በሌላ በኩል ደግሞ ከጤናቸው ጋር በተያያዘ ምንጫቸው ያልታወቀና ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጄነራሉን አግኝቶ አናግሯቸዋል።

ጄነራል ሳሞራ የኑስ ፥ " የተወራው ወሬ ነጭ ውሽት እና የሶሻል ሚድያ ተከታይ ቁጥር  (SUBSCRIBER ) ለማብዛት የተፈበረከ ነው " ብለዋል።

" በመከላከያ የተሰጠኝ ሃላፊነት የለም፤ ትግራይ ላይ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይፈጥር እንጂ እንዲፈጠር የሚሰራ ሞራል የለኝም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጀነራሉ የጤና ሁኔታቸውን በተመለከተም " ጤናዬ ሙሉ ነው ለማረጋገጥ  ከተፈለገ ሁሌ ስፓርት በማዘወትርበት ቦታ (አዲስ አበባ) መጥቶ ማረጋገጥ ይቻላል " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
🎁 የአካል ጉዳተኞች የሞባይል ጥቅል!!

ከመደበኛ ጥቅል እስከ 35% በሚደርስ ታላቅ ቅናሽ የቀረቡትን ልዩ ጥቅሎች በ *999# ወይም 999 በመደወል ይግዙ፡፡

👉 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ሲገዙ ተጨማሪ 10% ስጦታ ያገኛሉ!

ማንኛውም ሰው ጥቅሎቹን ለተመዘገበ የማኅበሩ አባል መግዛትና በስጦታ መላክ ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3GECypV


#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)

የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.group-telegram.com/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ " ‘ካምፓኒው ገቢ ስላላገኘ አካል ክፍላችንን እያወጡ ለመሸጥ እንደወሰኑ እየነገሩን ነው’ ብላኛለች። የዓይኑን ብሌን ያጣ ልጅ አለ " - እንባ የሚተናነቃቸው የታጋች ቤተሰቦች " ያለንበት ቦታ በጣም አስቸጋሪ ነው። በቃል የሚገለጽ አይደለም። በዛ ላይ ያመኛል። ልለምናችሁ ከዚህ አስወጡን " - ታጋች ኢትዮጵያዊት በማይናማር እስካሁን በተለያዩ ፓርኮች የታገቱ 42፣ ከእገታ ወጥተው…
“ ዜጎች ብዙ ወጪ ወጥቶ ከያሉበት ተሰባስበው ወደ ሀገር እንዲመጡ ጥረት ይደረጋል የዛኑ ያክል ደግሞ በተለያየ ቀዳዳ ሰዎች ሲወጡ ይታያል ” - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

በማይናማር ከእገታ ወጥተው በካምፓኒ የሚገኙ፣ አሁንም በእገታ ያሉ ወገኖች መንግስት ጓደኞቻቸውን እንደመለሰው ሁሉ እነርሱንም እንዲመልሳቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እየተማጸኑ ይገኛሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ትላንት በሰጡት ሰሞነኛ መግለጫ ስለ ማይናማሩንጉዳይም ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

አምባሳደር ነብያት ምን አሉ ?

“ በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ጥረት ባለፈውና ከዛ በፊት በነበረው ሳምንት ተጠናክሮ፣ እስካሁን ከ700 በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል።

ሌሎች አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለመመለስም ኒው ደልሂ ባለው ኤምባሲያችን ጥረት መድረጉ ቀጥሏል።

መንግስት በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉትን ዜጎች ለመመለስ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅትም በሚዲያ፣ በመንግስት የሚሰጡ መግለጫዎችን በቸልታ በመመልከት አሁንም ሕገ ወጥ ጉዞ ባለመቋረጡ ህብረተሰባችን ራሱንና ልጆቹን ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ውል ወዳልተፈረሙባቸው አገራት እንዳይሄዱ መከላከል አለበት።

በውጭ አገራት የሚደረጉ የሥራ ስምሪቶች፣ የነጻ ትምህርት እድሎች 'የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በሚኒስቴሩ የተሰጠ እውቅና አለኝ' በማለት በማጭበርበር ወንጀል የተሰማሩ ግለሰቦችና ሀሰተኛ ተቋማት እንዳሉ ተረድተናል፡፡ እነኝህንም በሚመለከተው የሕግ አካል ክትትል እንዲደረግበት እያደረግን ነው።

በተለይ በሕገ ወጥ ደላላ ኔቶርክ ከሀገር ውስጥ ተመልምለው ዜጎች ራሳቸውን ለአደጋ ወደ ሚያጋልጧቸው አካባቢዎች እንቅስቃሴዎች ያደርጋሉ፡፡

የኔቶርኩ ነገር፣ ከአገር ውስጥ ጀምሮ ወደ ምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ፣ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በሕገ ወጥ መንገድ የሰዎች ትራፊኪንግ ሰንሰለቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በየጊዜው ይህንን ሰንሰለት ለመቆራረጥ ሕጋዊ እርምጃዎች ሲወሰዱ ቆይተዋል።

ያም ሆኖ አሁንም ቢሆን ከእንደህ ያለው ኔቶርክ ከአገር ውስጥ ጀምሮ ተጋላጭ ናቸው፡፡ አሁንም ስላልቆመ በሕጋዊ መንገድ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል ይገባናል። ጎን ለጎንም ግንዛቤ የመፍጠሩም ሥራ ሳይታክት ቅስቀሳው መቀጠል ይኖርበታል እስከ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ድረስ፡፡ ምክንያቱም ችግሩ አንዳንዴ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ይሆናል፡፡

ብዙ ተለፍቶበት በ100ዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ብዙ ወጪ ወጥቶ ከያሉበት ተሰባስበው ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ጥረት ይደረጋል፣ የዛኑ ያክል ደግሞ በተለያየ ቀዳዳ ሰዎች ሲወጡ ይታያል።

ኢትዮጵያ ዜጎቿ ከተለያዬ ሀገር ተገደው ወደ ሀገራቸው እንዲሄዱ በሚገደዱበት ጊዜ በማናቸውም ሁኔታ ዜጎቿን ለመቀበል፣ ለማስተናገድ ዝግጁ ናት ” ብለዋል፡፡

የመጡት ዜጎችን እጣፋንታ ምንድነው ?

“ ዜጎች በሚመጡበት ጊዜ የስደተኛና ከስደት ተመላሾች ተቋማት፣ ዓለም አቀፉ የፍልሰጠኞች ድርጅቶች ጋር በመተባባር ለተወሰኑ ቀናት ህብረተሰቡ ጋር ኢንተግሬት ማድርግ የሚችሉበትን ሁኔታ ቀለል ሊያደርጉ የሚችሉ የተወሰኑ ድጋፎች ይደረጋሉ፡፡ የግንዛቤ መግለጫ መድረኮች ይደረጋሉ።

ከህብረተሰቡ ጋር በቀላላ ሊቀላቀሉ የሚችሉብትን አቅም በፈቀደ መጠን እንዲህ ያሉ አሰራሮች በተግባር ላይ እየዋሉ ይገኛሉ ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
የኢንቨስትመንት ባንኮች ስራቸው ምንድነው ?

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለሁለት የኢንቨስትመንት ባንኮች ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም በሶስት የአገልግሎት ዘርፎች ለሚንቀሳቀሱ ተቋማት ማለትም ለሁለት የኢንቨስትመንት ባንኮች፣ ለአንድ የሰነደ ሙዓለ ገበያ አከናዋኝ እና ለሁለት የኢንቨስትመንት አማካሪ ኩባንያዎች ፈቃድ መስጠቱን በወቅቱ ተገልጿል።

የኢንቨስትመንት ባንክ እንዲያቋቁሙ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ወጋገን ባንክ ናቸው፡፡

ለመሆኑ እነዚህ የኢንቨስትመንት ባንኮች ተግባራቸው ምንድነው ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን በተመለከተ ከአንድ የባንክ ባለሙያ ማብራሪያ ጠይቋል፡፡

ባለሙያው በሰጡን ማብራሪያ፣ ቀደም ሲል አንድ ግለሰብ/ተቋም አክሲዮን የሚገዛበትና የሚሸጥበት ገበያ አልነበረም ብለዋል፡፡ አሁን ግን የሰነደ ሙዓለ ገበያ/ የካፒታ ገበያ ተቋቁሟል፡፡

በዚህ ገበያ አክሲዮን/ሼር መሸጥና መግዛት የሚችሉት ሁሉም ግለሰቦች አለያም ተቋማት አይደሉም፡፡ ይልቁንም በአክስዮን ገበያው ውስጥ ገብተው ሼር ለመሸጥና ለመግዛት እንዲጫረቱ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት አሉ፡፡ የኢንቨስትመንት ባንኮች ከነሱ መካከል ናቸው፡፡

የኢንቨስትመንት ባንክ በአክስዮን ገበያ ገብቶ ሌሎች ግለሰቦችን/ተቋማትን ወክሎ የአክስዮን ድርሻ የሚሸጥና የሚገዛ ተቋም ነው ይላሉ ስሜ እንዳይጠቀስ ያሉን ባለሙያ፡፡

የባንክ ባለሙያው በዝርዝር ምን አሉ ?

" ለምሳሌ አዲስ የአክስዮን ካምፓኒ አቋቁማለሁ የሚል አካል የአክስዮን ድርሻ በኢንቨስትመንት ባንኮቹ በኩል ነው የሚሸጠው፡፡ አንድ ሰው ከዚህ ቀደም፣ ለምሳሌ ከአንድ የንግድ ባንክ የገዛውን ሼር/አክሲዮን መሸጥ ቢፈልግ ለኢንቨስትመንት ባንኮቹ ሽጡልኝ ብሎ ይሰጣቸዋል፡፡ ግለሰቡ ራሱ በካፒታል ገበያ ተጫርቶ ሊሸጥ አይችልም፣ መግዛትም አይችልም፡፡ ሁሉም ባለ አክስዮኖች ሼሩን መሸጥ መለወጥ የሚችሉት በኢንቨስትመንት ባንኮቹ በኩል ነው፡፡

የኢንቨስትመንት ባንኮቹ የግለሰቡን አክስዮን ወደ ካፒታል ገበያ ለጨረታ አቅርበው ይሸጡለታል፡፡ ወይም ራሳቸውም ሊገዙት ይችላሉ፡፡ የአክስዮን ገበያው ከፍ ሲል/ሲጨምር ደግሞ የሰበሰቡትን ሼር መልሰው አትርፈው ይሸጣሉ፡፡ ገበያ ሲወርድ ደግሞ ከካፒታል ገበያው ሼር ይገዛሉ/ይሰበስባሉ፡፡ ዋጋው ሲጨምር ደግሞ ገዝተው የሰበሰቡትን ሼር መልሰው በመሸጥ ትርፍ ያገኛሉ፡፡

ከሆነ ንግድ ባንክ ሼር መግዛት የፈለገ ግለሰብም/ተቋም ሼሩን መግዛት የሚችለው በኢንቨስትመንት ባንኮቹ አማካኝነት ነው፡፡ ግለሰቡን ወክለው ከካፒታል ገበያው ተጫርተው ይገዙለታል/ኢንቨስት ያደርጉለታል፡፡  ተቋማትም ቢሆኑ እንደዛ ነው፡፡

ለምሳሌ ፦ አንድ ትርፋማ ባንክ ሼር መሸጥ ቢፈልግ፣ እንደ በፊቱ ውስጥ ለውስጥ በድብቅ በራሱ መሸጥ አይችልም፡፡ ይልቁንም ወደ ካፒታል ገበያ አውጥቶ ይሸጣል፡፡ ሼሩን የሚሸጠው የሆነ የንግድ ባንክ ቢሆን፣ ይህን ያህል ሼር አለኝ ይላቸዋል፡፡ የያዘውን ሼር በኢንቨስትመንት ባንኮቹ አማካኝነት ለአክስዮን ገበያ ያወጣዋል/ያጫርቷል፡፡

የኢንቨስትመንት ባንኮቹ ደግሞ ሼሩን ወደ አክስዮን ገበያ አውጥተው ይሸጡለታል፡፡ ሼሩ ለጨረታ ሲቀርብ፣ የመነሻ ዋጋው 1000 ብር ቢሆንና፣ በገበያው ግን 1005 ብር እገዛለሁ የሚል ተጫራች ከመጣ በዚሁ ዋጋ ይሸጡለታል፡፡ የሼር ሽያጩ በኢንቨስትመንት ባንኮቹ በኩል ስላለፈ ኮሚሽን ያገኛሉ፡፡

ሼሩን ራሳቸው ገዝተው ሊይዙትም ይችላሉ፡፡ ከዛ ሌላ ጊዜ ዋጋው ከፍ ሲል መልሰው ሊሸጡት ይችላሉ፣ አትርፈው ማለት ነው፡፡ በካፒታል ገበያው የሼሩ ዋጋ ከፍተኛው 1005 ብር ከነበረ፣ በዚሁ ዋጋ ገዝተው ይይዙትና በሌላ ጊዜ በሚቀርብ ጨረታ በ 1010 ብር ሊሸጡት ይችላሉ፡፡ የአምስት ብር ትርፍ አገኙ ማለት ነው፡፡ በዳግም ጨረታ ሽያጭ የሚገኘው ትርፍ የኢንቨስትመንት ባንኮቹ ነው የሚሆነው፣ የባለ ሼሩ ባንክ አይደለም፡፡ እሱ አንዴ ሸጦዋል፡፡

ኢንቨስትመንት ባንኮቹ ከስቶክ ማርኬት ሼር በመግዛት አጠራቅመው፣ የሆነ ጊዜ ላይ አትርፈው ይሸጡታል፡፡ ይህን ማድረግ የሚችሉት የኢንቨስትመንት ባንኮቹና ህጋዊ ፈቃድ የተሰጣቸው ሌሎች ተቋማት ናው፡፡ ሼር ሰብስበው በስቶክ ማርኬት የመጫረት ስልጣን የተሰጣቸው (ለመሸጥም ለመግዛትም) እነዚህ አካላት ናቸው፡፡

የኢንቨስትመንት ባንክ ለመክፈት መነሻ ካፒታሉ 100 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ንግድ ባንክ ለመክፈት መነሻው ካፒታል 5 ቢሊዮን ብር እንደተደረገው ማለት ነው፡፡ ወጋገን ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ የመነሻ ካፒታል፣ የኢንቨስትመንት ባንክ ለመክፈት ተፈቅዶላቸዋል፡፡ የተለየ ስራ ያላቸው ባንኮች ናቸው እነዚህ፡፡ ከንግድ ባንኮች የተለየ ነው ስራቸው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!

100ሺ ብር
ትላንት የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ለቆረጡ 2 እድለኞች እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ተሸላሚ አድርገናል።

ዛሬ በhttps://ethiolottery.et  ላይ ተመዝግበው የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ለሚቆርጡ 10 ዕድለኞች ለእያንዳንዳቸው 10 ሺህ ብር ጉርሻ ተዘጋጅቷል! ውጤቱንም እዛው ሽልማቶን ይክፈቱ የሚለውን በመጫን ማየት ይችላሉ!

የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪን በወረቀት፣ በቴሌብር ሱፐር አፕ፣ እንዲሁም https://ethiolottery.et ላይ በመግባት አሁኑኑ ይቁረጡ!

ከወዳጅዎ ጋር ይጋሩ! የ50 ሚሊዮን ሎተሪን ስጦታ ይላኩ!

መልካም ዕድል!

8 ቀን ብቻ ቀረው!

ለተጨማሪ መረጃ በ +251977717272 ይደውሉ!
ኢትዮ ሄሌክስ ትሬዲንግ የጆሮ መስሚያ ማዕከል

የጆሮ ችግር ገጥሞዎታልን?

እንዳያስቡ መፍትሔውን ይዘንልዎት መተናል። ጥራት፣ ጥንካሬ እና ምቾት ያለቸው የቱርክ ምርት የሆነ የጆሮ ማዳመጫዎችን ፣ audiometry ልኬት ፣በልኬትዎ መሰረት ሊያቀርብልዎ ኢትዮ ሄሌክስ ትሬዲንግ ብቅ ብሏል፡፡

ይምጡ ሰምተው ይሄዳሉ
ቃል እንጠብቃለን ለጤና ቅድሚያ እንሰጣለን!

☎️ ፡- +251909090358 ወይም +251911454732 ላይ ይደውሉ

አድራሻ: ካዛንቺስ ኢሊሌ ሆቴል ጀርባ ህብረት ባንክ ያለበት ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6-1 ያገኙናል
TIKVAH-ETHIOPIA
" ያለ ቅድመ ሁኔታ ከስራ መስመር እንድንወጣ መደረጉ ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጎናል " - የኤሌክትሪክ ባጃጅ አሽከርካሪዎች " በመንግስት አበረታችነት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በብድርና በዋስትና ጭምር አዉጥተን በቅርቡ የገዛናቸዉ የኤሌክትሪክ ባጃጆች በአስፓልት መንገዶች እንዳሰሩ ተደርገዋል ፤ ይህም ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጎናል " ሲሉ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን…
" ወደ ስራ ተመልሰናል ፤ ድምፅ ስለሆናችሁን እናመሰግናለን " - አሽከርካሪዎች

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የኤሌትሪክ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ከአንድ ወር በፊት 1.2 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ አዉጥተዉ የገዟቸውና እያንዳንዳቸው ሰባት ሰዎች የመጫን አቅም ያላቸዉ የኤሌክትሪክ ባጃጆች ያለምንም ምክንያት ከስራ መስመር እንዲወጡ መደረጉ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እንደዳረጋቸዉ ቅሬታቸዉን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተው ነበር።

የሀዋሳ ከተማ የኤሌክትሪክ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ማህበርና አስመጪዉ ሳፊ ትሬዲንግ ከመንግስት አካላት ጋር ባደረጉት ተደጋጋሚ ዉይይት ከአንድ ወር 10 ቀናት በኋላ ዳግም ወደ ስራ መስመር እንዲመለሱ እንደተፈቀደላቸው አሽከርካሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

" አስቀድሞዉኑ መከልከሉ ተገቢነት የሌለው እና በግለሰቦች ተፅእኖ ምክንያት ብቻ የተወሰደ እርምጃ ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

" ድምፃችንን በማሰማት ወደ ስራ እንድንመለስ ተባብራችሁናል " ያሉት አሽከርካሪዎቹ ስራ በመጀመራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

" አሁንም ቢሆን የኤሌክትሪክ ባጃጆቹ በከፍተኛ ወጪ የተገዙ ከመሆናቸዉም በላይ ምቹ ተስማሚና መንግስት ለአየር ንብረት ለዉጥ ለሰጠዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አጋዥ እና የነዳጅ ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ስላላቸው ማበረታታት ያስፈልጋል " ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የጤና_ባለሙያዎች " የጤና ጉዳይ ለነገ የሚባል ስላልሆነ እንጂ በግል ጤና ተቋማት ክፍያዉ ከአቅማችን በላይ ነዉ " - ተገልጋዮች ከሰሞነኛዉ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ጋር ተያይዞ ሐኪሞች ስራ ካቁሙባቸዉ ተቋማት አንዱ የሆነዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አሁንም ድረስ ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው በመገኘት አረጋግጧል። በሆስፒታሉ አቅራቢያ…
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ምን አለ ?

" ጤና ባለሙያዎች ለዘመናት ሲያነሷቸዉ የቆዩ ጥያቄዎች በውይይትና በድርድር ይፈቱ " - ማኅበሩ

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፤ የጤና ባለሙያዎችን ሁኔታ በተመለከት መግለጫ ልኳል።

በዚህም መገለጫው ፤ ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ  የጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎችን በማስታወስና  አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ለመንግሥት እና ለተለያዩ አካላት ማቅረቡን አስታውሷል።

ጤና ባለሙያዎች ላነሷቸው ጥያቄዎች ምንም ተጨባጭ መፍትሄ ባለመሰጠቱ ምክንያት ባለሙያዎች በራሳቸው መንገድ መብታቸውን በህጋዊ  እና ሰላማዊ መንገድ ሲጠይቁ እንደቆዩ ገልጿል።

ለዚህም ፍትሃዊና ሰላማዊ ጥያቄ እንደ ማህበር እውቅናና ድጋፍ በመስጠት መንግስት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጣቸው ቀደም ሲል ማሳወቁን አስታውሷል።

ማኅበሩ ፥ ጤና ባለሙያዎች ያነሷቸዉ ጥያቄዎች በተገቢዉ መንገድ መፍትሄ ባለማግኘታቸዉ ወደ ስራ ማቆም አድማ እንደተሸጋገሩ አመልክቷል።

" አሁንም ጉዳዩ እልባት ሊበጅለት ይገባል " ብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሺን (ኢሰመኮ) ጤና ባለሙያዎችን ከመንግስት ጋር አቀራርቦ ለማደራደር፣ ለማወያየት እያደረገ ያለዉን ጥረት እንደሚያደንቅና እዉቅናም እንደሚሰጥ ገልጾ ማኅበሩ ከኢትዮጵያ ሰባዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር እያደረገ ያለዉን ዉይይት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

" ጥረቱ ቀጥሎ ችግሮች ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኙ እንሻለን " ብሏል።

ማኅበሩ የመፍትሄ አቅጣጫ ያለውንም አስቀምጧል።

ማኅበሩ ፦

1. በፈጠራ የወንጀል ክስ እና ምክንያታዊ ባልሆነ ጥርጣሬ በእስር የሚገኙ ጤና ባለሙያዎችና  ሰራተኞች ያለምንም ቅድሜ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ከእስር እንዲፈቱ፤

2. በጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሱ ያሉ ከስራ ማሰናበት፣ ጥያቄ እየጠየቁ ያሉ ባለሙያዎችን  ምክንያት ያደረገ አዲስ ቅጥር ማዉጣት፣ ዛቻና ማስፈራርያ በአስቸኳይ እንዲቆም፤

3. ከሁሉም ሙያ ማህበራት ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ አባላት፣ ከመንግስት ስራ ኃላፊዎች የተወጣጣ የድርድር አፈጻጸሙን የሚከታተል ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ  ስራ እንዲገባ፤

4. ማንኛውንም ሰራተኛ ኢትዮጵያ ፈርማ በተቀበለቻቸው አለምአቀፍ ህግጋት እንዲሁም በኢፌድሪ ህገመንስት ላይ በተደነገገው  መሰረት መብቱን የመጠየቅ ዋስትና /warranty/ እንዲሰጠዉ ሲል ጠይቋል።

ጤና ባለሙያዎች ለዘመናት ሲያነሷቸዉ የቆዩ ጥያቄዎች በውይይትና በድርድር እንዲፈቱ ሲል በአፅንኦት አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የኢንቨስትመንት ባንኮች የተቋማት ሀብት/ፈንድንም ያስተዳድራሉ " - የፋይናንስ ባለሙያ

የፋይናንስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ይርጋ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ ባደጉት ሀገራት ዘንድ የኢንቨስትመንት ባንኮች በአቅም በኩል ከንግድ ባንኮችም ይበልጣሉ ብለዋል፡፡

እንዲህ አይነት ባንኮች ለባለሙያዎች ከፍተኛ ክፍያ እንደሚከፍሉ ትላልቅ ሞያተኞችንም እንደሚቀጥሩ ገልፀዋል፡፡

“ ምክንያቱም ብዙ ሀብት/ፈንድ ነው የሚያስተዳድሩት፡፡ የአንድ ካምፓኒ/ተቋም ለምሳሌ የጡረታ መስሪያ ቤትን ሀብት/ፈንድ ሊያስተዳድሩለት ይችላሉ ” በማለት ተናግረዋል፡፡ 

ተቋሙ የሰበሰበውን የጡረታ ገንዘብ ዝም ብሎ ከሚያስቀምጠው፣ የሆነ የንግድ ኩባንያ ላይ ሼር በመግዛት ኢንቨስት ያደርጉለታል፡፡

የጡረታ ተቋሙ የሰበሰበውን ገንዘብ ዝም ብሎ ከሚያስቀምጠው፣ ኢንቨስት ላድርገው ቢል ይህን ስራ ለኢንቨስትመንት ባንኮች ይሰጣቸዋል፡፡ የኢንቨስትመንት ባንኮቹም የጡረታ መስሪያ ቤቱን ወክለው አክሲዮን ከሚሸጥ ኩባንያ ሼር ይገዙለታል፡፡

የፋይናንስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ይርጋ ተስፋዬ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የኢንቨስትመንት ባንኮች ይህን ለማድረግ አስተማማኝ የሆነ ጥናት ያደርጋሉ፡፡ ' እዚህ ቦታ ላይ ሼር ብትገዛ ያዋጣሀል ' ብለው በማማከር ተቋማትን አሳምነው ያላቸውን ሀብት/ፈንድ ኢንቨስት ያደርጉላቸዋል፡፡

ቀድመው አክስዮን የገዙ ሰዎች ካሉ ደግሞ የያዙትን አክስዮን በፈለጉት ጊዜ ሊሸጡት ስለሚችሉ በነዚህ ኢንቨስትመንት ባንኮች በኩል ይሸጡታል፡፡ አንዴ የተገዛ አክስዮን/ሼር የሚሸጥ የሚለወጥ ሸቀጥ ነው ወይም ትሬደብል ኮሞዲቲ ነው፡፡

ቀድሞ በነበረው አሰራር ከአንድ የንግድ ባንክ የገዛኸው አክስዮን መሸጥ ብትፈልግ ወይ አክስዮኑን ወደገዛህበት ባንክ ሔደህ ሽጥልኝ ትለዋለህ አለያም በደላላ በኩል ነው ገዢ የምትፈልገው፡፡ አሁን ግን እንደዛ የለም፡፡ ይህን የሚያደርጉት የኢንቨስትመንት ባንኮቹ ናቸው፡፡ አንተ የያዝከውን አክስዮን ሽጡልኝ ትላቸዋለህ፣ ወይም የምትፈልገውን አክስዮን ግዙልኝ ትላቸዋለህ፡፡

የሆነ መጠን ያለው ሀብት/ፈንድ አለኝ፣ ትርፋማ ነው በምትሉት ኩባንያ ሼር በመግዛት ኢንቨስት አድርጉልኝ ልትላቸው ትችላለህ፡፡

ለምሳሌ በአመት በትንሹ 20 በመቶ ትርፍ በሚያስገኝልኝ ኩባንያ ላይ መርጣችሁ ኢንቨስት አድርጉልኝ ትላቸዋለህ፡፡ የትም ኢንቨስት አድርጉት በአመት ይህንን ያህል ትርፍ እፈልጋለሁ ብለህ ከእነሱ ጋር መደራደር ትችላለህ፡፡

የንግድ ተቋሙን የመምረጥ ሐላፊነቱ ለኢንቨስትመንት ባንኮቹ ትተወዋለህ፡፡ እነሱ የዳሰሳ ጥናት አድርገው ትርፋማ በሚሉት ተቋም/ባንክ/ኢንሹራንስ/ቴሌኮም ወይም ሌላ ኩባንያ ላይ ሼር በመግዛት ኢንቨስት ያደርጉልሀል፡፡

በራሳቸው ሌላ ኢንቨስትመንት ላይ አይሰማሩም/ ለምሳሌ በራሳቸው ሪል እስቴት አይገነቡም፡፡ ቀድመው በተመሰረቱ የንግድ ኩባንያዎች ላይ ነው ሼር በመግዛት አንተን ወክለው ሀብትህን ኢንቨስት የሚያደርጉት፡፡ በተቋማቱ ውስጥ የአክስዮን ድርሻ ነው የሚገዙልህ፡፡

ዋና ስራቸው ሁለት ነው አንድ ገበያውን በማጥናት መረጃዎችን እየተነተኑ ለኢንቨስትመንት ማመቻቸት፣ ሁለተኛ ደግሞ የተቋማትን/ግለሰቦችን ሀብት ማስተዳደር ወይም ኢንቨስት ማድረግ ነው፡፡ አሴት ማናጅመንት የሚባለው ማለት ነው፡፡ የትኛው ተቋም ላይ ኢንቨስት ቢደረግ አትራፊ ይሆናል የሚለውን በደንብ አጥንተው ይደርሱበታል፡፡
 
የኢንቨስትመንት ባንኮቹ ሼር የሚሸጡት የሚገዙት በአክስዮን ገበያው ነው፡፡ አክሲዮን የሚገዙባቸውና የሚሸጡላቸው ካምፓኒዎች በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡

አንድ ኩባንያ እዚህ የአክስዮን ገበያ ውስጥ ለመመዝገብ/ለመግባት የራሱ የሆነ መስፈርት አለው፡፡ ሁሉም ኩባንያዎች አይደሉም በዚህ የሚገበያዩት/የሚሳተፉት፡፡ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን መስፈርት በማስቀመጥ ይቆጣጠራቸዋል፡፡ በአክሲዮን ገበያ እንዲሳተፉ እንዲፈቀድላቸው የተቀመጡ መስፈርቶች ይኖራሉ፡፡ የኢንቨስትመንት ባንኮቹ ተቋማትን/ግለሰቦችን ወክለው የሚሸጡትና የሚገዙት ሼር፣ በካፒታል ገበያ እንዲሳተፉ ለተመዘገቡ ኩባንያዎች ነው፡፡

አንተ ከሆነ ኩባንያ ሼር ስትገዛ፣ ኩባንያውን አምነህ አይደለም ሼር የምትገዛው፡፡ ከኪሳራ ይጠብቀኛል የምትለውን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ቁጥጥርና ስርዓት አምነህ ነው የምትገዛው፡፡ ባለስልጣኑ ነው ኩባንያውን የሚቆጣጠረው፡፡ አቅም አለው ወይ ? ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ወይ ? ባለ አክስዮኖችን ለኪሳራ ይዳርጋል ወይ ? የሚሉት ነገሮች በባለስልጣኑ ነው ቁጥጥር የሚደረግባቸው፡፡ ይህን ስራ የኢንቨስትመንት ባንኮች ብቻም ሳይሆኑ አሴት ማናጅመንት ካምፓኒዎችም አሉ ያከናውኑታል " ብለዋል።

ስለ ኢንቨስትመንት ባንክ ፦ https://www.group-telegram.com/tikvahethiopia.com/97234

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2025/05/31 00:08:17
Back to Top
HTML Embed Code: