TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።
የሲዳማ ክልል ከሰሞኑ በፀጥታዉ ዘርፍ እየወሰደ እንደሆነ በተገለፀዉ ተቋማዊ ሪፎርም ዛሬ የቀድሞ የክልሉ ኮሚሽነር የነበሩትን ሽመልስ ቶማስ በዛሬዉ ዕለት ከስልጣን ማንሳቱ የተሰማ ሲሆን ማምሻዉን ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟቸዋል።
አዲሱ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ ሲዳማ በዞን መዋቅር ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በልዩ ልዩ ፖሊሳዊ አመራሮች ተቋሙን ያገለገሉና በአሁኑም ወቅትም የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሆነዉ ሲሰሩ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጧል።
ይህ መረጃ በተዘጋጀበት ወቅት ስለ ቀድሞዉ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ከኃላፊነት መነሳት ዙሪያ ይፋ የተደረገ መግለጫ የሌለ ሲሆን የፖሊስ ኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የአዲሱን ኮምሽነር ሹመት ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጎታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያቀርብ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በነጻ ይመዝገቡ !
Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo
በኢትዮጵያ ትልቁ የኮንስትራክሽን እና የመሠረተ ልማት አውደ ርዕይ በዚህ ሰኔ ይመለሳል። Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo ከሰኔ 19–21፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
🔥 ምን ይጠብቁ፦
✅ ከ20 በላይ አገራት የተውጣጡ 180+ ተሳትፊ ኩባንያዎች
✅ በኢትዮጵያ አዲስ የሆኑ ምርቶች
✅ በነፃ የሚሰጡ 20+ የCPD ሰርተፊኬት ያላቸው መድረኮች
ይህ ልዩ የኔትዎርኪንግ እድል እንዳያመልጥዎ፤ አሁኑኑ በነፃ ይመዝገቡ።
👉 https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia

#Addis_Bank
የባንካችን አርማ ትርጓሜ !
አዲስ ባንክ አ.ማ.
ለስኬትዎ የታመነ
Follow us
Website | Telegram | LinkedIn | Facebook | Instagram
#Addisbank #logoconcept #WhereTrustMeetsSuccess

#ትግራይ
በትግራይ ክልል ከሁለት ወር በፊት የተሾሙ የቢሮ ሃላፊ ተሽረው በሌላ ሃላፊ ተተኩ። እንዲህ ያለው ሹመት ያልተለመደ ነው ተብሏል።
አስተያየት ሰጪዎች " ሹመቱ ህወሓት መካከል ቡድናዊ ሽኩቻ መፈጠሩ ያሳያል " ብለዋል።
ከሹመት የተሻሩና የተተኩ እነማን ናቸው ?
አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን ነባር የህወሓት ታጋይ ናቸው።
ባለፉት 34 ዓመታት ከትግራይ የተለያዩ የዞን አስተዳዳሪነት እስከ የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ፅሕፈት ቤት ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል።
በታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የሚመራ ጊዚያዊ አስተዳደር ወደ ሃላፊነት ሲመጣ በህወሓት እጩ አቅራቢነት ባይቶና በተባለ ተቃዋሚ ፓርቲ አባል ሲመራ የነበረውን ተክተው የክልሉ የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአቶ ተወልደ ሹመት በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር ለተቃዋሚ ፓርቲ ሰጥቶት የነበረው ሁለት የቢሮ የሃላፊነት ቦታ ወደ አንድ የሚያሳንስ በመሆኑ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር።
ከፓለቲካ እንቅስቃሴ በተሰረዘው ህወሓት መካከል " ቡድናዊ ሽኩቻ አለ " ከሚል አስተያየት ውጪ የቢሮ ሃላፊው በሁለት ወር ውስጥ በምን ምክንያት ከሃላፊነት እንደተሻሩ በይፋ የተገለፀ ነገር በሌለበት ተነሱ።
የቢሮ ሃላፊው አቶ ተኽላይ ገ/መድህን በተባሉ የህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል መተካታቸው ተገልጿል።
አቶ ተኽላይ ገ/መድህን የሹመት ደብዳቤያቸው ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እጅ መቀበላቸው የክልሉ የውሃ ሃብት ቢሮ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Ethiopia #USA
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ግንኙነታቸዉን አካሂደዋል።
አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ነጩ ቤተመንግስት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
" ይኸው ግንኙነት በቀጣይ ጊዜአት ለሚደረጉ በርካታ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል " ያለው ኤባሲው " ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ናቸው በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ ናቸው " ብሏል።
አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በውይይቱ ወቅት የተገኙትን ስቴት ሴክሬተሪ ማርኮ ሩቢዮ ጋርም ተገናኝተዋል።
Photo credit: The White House

#EthiopianAirlines🇪🇹
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይትራክስ ለስምንተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ክብርን ተቀዳጅቷል።
ከዚህም በተጨማሪ ፦
🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል
🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል እና
🏆 በአፍሪካ ቢዝነስ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ሽልማትን ተጎናጽፏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
የእስራኤል እና ኢራን ጦርነት 6ኛ ቀኑን ይዟል።
- ሁለቱም ወገኖች እርስ በርስ መታኮሳቸውን ቀጥለዋል።
- እስራኤል ትናንት ሌሊት በቴህራን የሚገኘውን የዩራኒየም ማብላያ እና ጦር መሣርያ ማምረቻ መምታቷን ገልጻለች።
- ኢራንም ማዕከላዊና ሰሜናዊ እስራኤልን በሚሳኤል ስትደበድብ ነበር። በዚህም ሰዎች ስለመጎዳታቸው ተሰምቷል።
- ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ብትገልጽም የጥቃቱ መጠን ግን እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል።
- ሁለቱ አገራት አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚሳዔል እና የአየር ጥቃት እየፈጸሙ ሲሆን ነዋሪዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ እየሰጡ ነው።
- እስራኤል ነዋሪዎች ከተለያዩ የቴህራን ክፍሎች ለቀው እንዲወጡ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። በዚህም ምክንያት ነዋሪዎች የቻሉትን ንብረት እየያዙ ከከተማዋ ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት በነዳጅ ማደያዎች እና በጎዳናዎች ላይ ረጃጅም ሰልፎች እና የትራፊክ መጨናነቆች እየታዩ ነው።
- ኢራን የቴላቪቭ እና ሃይፋ ነዋሪዎች የሚመጣው ከባድ ስለሆነ ለቃችሁ ውጡ የሚል መልዕክት እያስተላለፈች ነው።
- አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ለማበር እያጤነች መሆኑ ተሰምቷል። አሜሪካ ከእስራኤል ጎን ተሰልፋ በኢራን ላይ በሚካሄደው ጥቃት የምትሳተፍ ከሆነ ግጭቱን ወደ አልተጠበቀ አቅጣጫ ሊወስደው ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ " እኛ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒን አንገድልም ቢያንስ ለጊዜው አንገድላቸውም። አያቶላህ የት እንዳሉ በትክክል እናውቃለን ፤ ቀላል ዒላማ ነው፤ ግን እዚያ መልካም ነው " ብለዋል።
- የአሜሪካው መሪ ትራምፕ " ትዕግሥታችን እያለቀ ነው " ሲሉ አጠንቅቀው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ኢራን እጅ መስጠት እንዳለባት ተናግረዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ እና ቲአርቲ ነው።
ቪድዮ ፦ የተጨናነቀ የተሽከርካሪ ሰልፍ የሚታይበት ቪድዮ ቴህራን ውስጥ እንደሆነና ነዋሪዎች ዋና ከተማውን ለቀው ለመውጣት እያደረጉ ባለው እንቅስቃሴ የተፈጠረ መሆኑን AFP ዘግቧል።
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በቀጥታ ወደ ጦርነቱ ትገባ ይሁን ?
እስራኤል በኢራን ላይ እያካሄደችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ ስለምትሳተፍበት ሁኔታ ለመወያየት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር አድርገዋል።
አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ በቆየው ስብሰባ ላይ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማዕከላት ላይ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ መሳትፍ እንዳለባት ለመወሰን ነበር።
የትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች በተሳተፉበት በዚህ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ አሜሪካ በጥቃቱ ውስጥ ስለሚኖራት ተሳትፎ ሙሉ ስምምነት ላይ አለመደረሱ ተዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቀናት ኢራን ወደ ኒውክሌር ድርድር እንድትመለስ በተደጋጋሚ ሲወተውቱ ከቆዩ በኋላ ነው እስራኤል በኢራን ላይ በከፈተችው ጦርነት ውስጥ አገራቸው በቀጥታ መሳተፍ ሊኖርባት ይችል እንደሆነ ማጤን የጀመሩት።
በትላንት ማታው የአሜሪካ መንግሥት የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ትራምፕ እና አማካሪዎቻቸው የኢራንን የኒውክሌር ማዕከላትን ለማጥቃት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሪፖርት አቅርበዋል።
በዚህም ዋነኛ ዒላማ ሊሆን የሚችለው ከተራራ ስር ከመሬት በታች የሚገኘው ፎርዶ የተባለው የዩራኒያም ማበልጸጊያ መሆኑ ተነግሯል። ይህንን ከመሬት በታች የሚገኝን ማዕከል ለማውደም የሚያስችል ቦምብ ያላት አሜሪካ ብቻ ናት።
የፕሬዝዳንቱ አማካሪዎች አሜሪካን በጦርነቱ ውስጥ በሚኖራት ተሳትፎ ዙሪያ ከስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም።
የአሜሪካ እና የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ከአስቸኳይ ስብሰባው በኋላ ትራምፕ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የዘገቡ ሲሆን፣ ነገር ግን በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ አልታወቀም።
ባለፉት ሦስት ቀናት የአሜሪካ የጦር ጄቶች እና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ነዳጅ የሚሞሉ ቢያንስ 30 ነዳጅ ጫኝ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ወደ አውሮፓ እንዲጓዙ ተደርገዋል።
ከአስቸኳይ ስብሰባው በፊት ዶናልድ ትራምፕ በተከታታይ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ኢራን " ያለ ቅድመ ሁኔታ እጇን እንድትሰጥ " መልዕክት ሲያስተላልፉ ነበር።
ለዚህም ምላሽ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተከታታይ በሰጡት ምላሽ አገራቸው " ከጽዮናውያን ጋር ፈጽሞ እንደማይስማሙ " ገልጸዋል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
▶️ @thiqahEth @tikvahethmagazine

የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጨመረ። እስራኤል ኢራን ላይ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከ2020 በኋላ በቀን ውስጥ በዚህ ደረጃ ሲጨምር ከፍተኛው ነው ተብሏል። የአንድ በርሜል የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 78 ዶላር ገብቷል። አሁን ያለው ውጥረት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ መቆራረጥ እንዳይፈጥር ተሰግቷል። ተንታኞች ውጥረቱ…
በኢራን እና እስራኤል ጦርነት ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እንዳሻቀበ ነው።
ዛሬ ላይ አንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ 76.45 ዶላር እንዲሁም በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት አንድ በርሜል ነዳጅ 74.84 ዶላር እየተሸጠ ነው።
ጦርነቱ ከቀጠለ እና ሌሎችም ሀገራት የሚሳተፉበት ከሆነ የዓለም ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።