Telegram Group Search
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሚዘጋጀው የኢትዮጵያ ታምርት ሩጫ እና ኤክስፖ ተጋብዘዋል

📱 ሩጫው መቼ ነው ?

የኢትዮጵያ ታምርት  የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ መነሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ መስቀል አደባባይ የሚጠናቀቅ ሲሆን #ሚያዚያ_19 /2017 ዓ.ም ይከናወናል።

በዚህ ሩጫ ውድድር ፦
1ኛ ለሚወጡ 300,000 ሺህ ብር
2ኛ ለሚወጡ 200,000 ሺህ ብር
3ኛ ለሚወጡ 100,000 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

በሁለቱም ፆታ እስከ 10ኛ የሚወጡ አሸናፊዎችም #በሽልማት ይንበሸበሻሉ!

🎽 ቲሸርቱን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኙታል
📞 ለበለጠ መረጃ 0975070707

⚙️ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ መቼ ነው ?

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዝያ 25 እስከ 29/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።

ማንኛዉም ልዩ፤ ጥራትና ተወዳዳሪ ምርት ያላቸው አምራቾችና ኢንዱስትሪዎች በ #ኢትዮጵያ_ታምርት ኤክስፖ 2017 ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

📞 ለበለጠ መረጃ በ 0906555552 ወይም 0988080808 ይደውሉ

#ኢትዮጵያታምርት   #ኢንዱስትሪሚኒስቴር
አቢሲንያ ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ

ገደቡም ክፍያውም ተነስቷል!

ውድ ደንበኛችን! የባንካችንን አዲሱን የሞባይል መተግበሪያ ተጠቅመዉ ከሂሳብዎ ወደ ሌላ የባንካችን ሂሳብ ገንዘብ ያለ ገደብ እንዲሁም ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይችላሉ። #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
" የበዓል ገበያዉ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ መሸመት ከአቅማችን በለይ ሆኗል " - የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች

➡️ " በዓሉን ታሳቢ በማድረግ  በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል " - የከተማዉ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ


መጪዉን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም ምርቶችና ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ማስተዋላቸዉን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ " በቀናት ልዩነት ዉስጥ በእያንዳንዱ የሸቀጥና ሌሎች ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል " ብለዋል።

ለአብነትም ፦
- እንቁላል ከ13 እና 15 ወደ 20 ብር
- ሽንኩርት በኪሎ ከ45 ወደ 70 እና 80
- ቅቤ በኪሎ ከ800 ወደ 1000 ብር
- ቲማቲም በኪሎ ከ40 ወደ 65
- ዶሮ አንዱ ከ500-650 ወደ 850-1000
- ስኳር በኪሎ ከ110 ብር ወደ 650 ብር
- በርበሬ በኪሎ ከ600 ወደ  800 ብር
- ዘይት የሚረጋ የሚባለው
             ° 20 ሊትር ከ4500 ወደ 6200
             ° 5 ሊትር ከ1200 ወደ 1600
             ° 3 ሊትር ከ800 ወደ 1050
- ዘይት ባለ ሃይላንድ
             ° 5 ሊትር ከ1400 ወደ 1750
እየተሸጡ መሆኑንና የጤፍ እና የምስር ዋጋ በአንፃሩ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ ማሳየቱን ገልፀዋል።

አስፈላጊዉ ቁጥጥር ካልተደረገ እስከ በዓሉ መዳረሻ ቀናት የዋጋ ጭማሪዉ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል የሚናገሩት ሸማቾቹ በበዓሉ ዋዜማ ቀናት ዋጋ ለመጨመር ምርት የሚሰዉሩና እያሉ " የለም " የሚባሉ ሸቀጦችና ምርቶች ስለመኖራቸዉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ልዩ ልዩ የጥራጥሬ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሸቀጥና ቅመማ ቅመሞች እጥረት እንዳይኖር በማህበራት ዩኒየኖች አማካኝነት በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል " ያለ ሲሆን " የዋጋ ጭማሪዎች እንዳይኖር አስፈላጊውን የቁጥጥር ስራ እያከናወንኩ ነዉ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ አንዳንድ ጅምላ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት የተወሰኑ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ምርት የማሸሽና በየመደበቅ ስራ እየሰሩ መሆኑንና ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ብቻ መሸጥ የሚገባቸዉ ማህበራትም ለቸርቻሪ ነጋዴዎች እያሰራጩ መሆኑን ገልፀው ቁጥጥር እና ክትትሉ ካልተጠናረ የበዓል ገበያዉ ከዚህም በላይ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ጭማሪ ሊታይበት ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

@tikvahethiopia
" በስህተት ወደ አካውንቴ የገባልኝን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ መልሻለሁ " - አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስህተት ወደ አካዉንቱ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ተመላሽ ያደረገ ግለሰብ ምስጋና እየተቸረው ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ በስም ተጠቃሹን ግለሰብ አግኝቶ ያነጋገራቸው ሲሆን የባንክ ባለሙያ አስተያየት እና ምክርም ጠይቋል።

በስህተት የገባላቸዉን 3.5 ሚሊዮን ብር የመለሱት አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል ምን አሉ ?

" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት በተፈጠረ ስህተት ከሌላ ግለሰብ ወደ አካዉንቴ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ ተመላሽ አድርጊያለሁ።

እኔም የስራ ሰዉ ነኝ እንደዚህ አይነት ክስተት ልያጋጥመኝ ይችላል፤ ስለዚህ ገንዘቡ የኔ ስላልሆነና ለባለቤቱ መመለስ ስላለብኝ ሳላቅማማ መልሻለሁ " ሲሉ ጉዳዩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

አቶ በህጉ አክለዉም " ብዙ ሰዎች ሞኝ እንደሆንኩ፣ መመለስ እንዳልነበረብኝና ብመልስም ከላዩ ቀንሼ መሆን እንደነበረበት አስተያየት ሲሰጡ ሰምቻለሁ፤ ዳሩ ግን ቅድም እንዳልኩት የኔ ያልሆነ ነገር የኔ አይደለም፤ በተለይም እኔም በቢዝነስ አለም ዉስጥ እንዳለ ሰዉ ነግ በኔ እንደሆነ በመረዳት ማድረግ ያለብኝ ነዉ ያደረኩት "ብለዋል።

የአዋሽ ባንክ ባለሙያ ስለሁኔታዉ ምን አሉ ?

የአዋሽ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ኦፕሬሽንናል ማናጀር አቶ ፉፋ አሰፋ ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር አቶ ቦንሳ ታደለ የተባሉ የባንካችን ደንበኛ ከአንዱ ባንክ አካዉንት ወደ ሌላ ባንክ አካዉንት በአካል ተገኝተዉ በማንዋል ፅፈዉ ሂሳብ ሲያስተላልፉ አንድ ቀጥር ተሳስተዉ ፅፈዉ በመስጠታቸዉ 3.5 ሚሊዮን ብር ወደ አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል አካዉንንት ተላልፏል " ሲሉ ገልፀዋል።

ባንኩ ለአቶ በህጉ በመደወል ሁኔታውን ማስረዳቱንና አቶ በህጉም ተባባሪ በመሆን ለባለቤቱ ገንዘቡን ተመላሽ ማድረጋቸውን አስታውቋል።

ለሁሉም የባንክ ተጠቃሚዎች የባንክ ባለሙያዉ ምን አሉ ?

" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ የመፈጠር ዕድሉ ሰፊ ነዉ። ሁሉም ሰዉ በብር ዝዉዉርና አጠቃላይ በባንክ አጠቃቀም ወቅት ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት የሆኑትን ፦
➡️ ከበሮ፣
➡️ ጸናጽል፣
➡️ መቋሚያና እንዲሁም ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች መመዝገባቸውን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዜማ ንዋያተ ቅዱሳቱ እና ቅዱሳት መጻሕፍቱ ተመዝግበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆናቸው ከባለሥጣኑ በወጣው ደብዳቤ መረጋገጡን ገልጻለች።

መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወስኗን።

በትግራይ መምህራን ማህበር ጠበቆች የቀረበውና በጦርነቱ ጊዜ ያልተከፈለ የ17 ወራት የመምህራን ደመወዝ ሲመለከት የቆየው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ውሳኔውን ሰጥቷል።

ተከሳሾቹ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ፣ የፋይናንስ  ቢሮ ፣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም የገንዘብ/ የፋይናንስ ሚንስቴር ሲሆኑ ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ ቆይቷል።

ፍርድ ቤቱ የቀረበለት ክስ መርምሮ የመምህራኑ የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወስኖ ፋይሉ ወደ መዝገብ ቤት መልሶታል። 

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደሚቀበሉትና እንዳረካቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪ መምህራን ውሳኔው ቶሎ በመተግበር በከፋ ሁኔታ የሚመገኙ መምህራን መታደግ ይገባል ብለዋል።

ተከሳሾቹ ውሳኔው በማስመልከት እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

መምህራን ያካተተ የ17 ወራት ያልተከፈለ የመንግስት ሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ የመከፈል ጥያቄ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት የጀመረ ነው።

በቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዳይታይ የሚከልክል መምሪያ እስከማውጣት ደርሶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ፎቶ፦ Tigrai TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ አስከሬኑን ይዘው ትላንት ምሽት 11 ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል። ዛሬ ቀጨኔ ተቀበሩ ” - የረዳቱ የቅርብ ሰው ➡️ " የኔ ቤተሰቦች ሦስት ናቸው። ከሦስቱ አንዷ ሞታለች። ትላንት ተቀበረች " - ቤተሰብ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ ነበር የተባሉ የአንድ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎች ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ/ም ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ “ጎሃ ፅዮን” እና “ ቱሉ ሚልኪ ” የተሰኘ…
" አሽከርካሪ እንደ ቢሮ ሠራተኛ ጠዋት ወጥቶ አመሻሽ ከ11፡00 ሰዓት በኋላ እንዳይቀሳቀስ እየተገደበ ነው " - የጣና አሸከርካሪዎች ማኅበር

በሀገሪቱ የተለያዩ ሥፍራዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ዕገታዎችና ግድያዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሽከርካሪዎችና የታጋቾች ቤተሰቦች ጥያቄ አቅርበዋል።

ባለፈው ወር መጋቢት 8/ 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ልዩ ስሙ " አሊዶሮ " በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል ሲጓዝ በነበረ " ፈለገ ግዮን " የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ እገታ መፈፀማቸውና አብዛቹ ተጓዦች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል።

ታፍነው ከተወሰዱበት ዕገታ፣ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍለው ስለተመለሱ አክስታቸው  የተናገሩ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደጀን ከተማ ነዋሪ፣ " ዕገታ ዜጎችን እያማረረ ነው " ብለዋል።

ታጣቂዎቹ አክስታቸው እንዲለቀቁ 1.5 ሚሊየን ብር ጠይቀው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ዕገታው መፈጸሙን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከደጀን ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አጽፈው ገንዘብ በማሰባሰብ 1 ሚሊየን ብር አዘጋጅተው ለታጣቂዎች በባንክ አስገብተው አክስታቸው ከታገቱ ሁለት ሳምንት በኋላ እንደተለቀቁላቸው ገልጸዋል።

ሁለት ወንድሞቹ የታገቱበት የክልሉ ነዋሪ ደግሞ እስካሁን እንዳልተለቀቁ ተናግሯል።

ታጣቂዎች ለወንድማማቾቹ ከ2.5 ሚሊየን ብር በላይ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

እስካሁን 450,000 ብር ተሰብስቦ ለታጣቂዎቹ እንዲደርስ ቢደረግም፣ ቀሪውን ክፍያ ካልከፈሉ እንደማይለቀቁ ተነግሯቸው እንደገና እየሰበሰቡና ሁኔታውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አስረድቷል።

ሆኖም የኑሮ ሁኔታው አስቸጋሪ መሆንና የታጋቾች መብዛት ገንዘብ ለመሰብሰብ መሰላቸት እንደፈጠረ አክሏል።

" አሁን ማንም ሰው ምን ማድረግ ይችላል ? የዕገታ ሁኔታ አስቸጋሪ ሆኗል " ብሏል፡፡


የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ ምን አሉ (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

" የሚያሠጉ ቦታዎች በምንላቸው በተለይ በኦሮሚያ ክልል የወለንጭቲ መስመር እኛም ክትትል ስናደርግ በፀጥታ አካላት በፓትሮል ሲጠበቅ አይተናል፡፡ ነገር ግን በሆነ ቅጽበት ችግሩ እየተፈጠረ ነው።

ለአብነት በቅርቡ ወለንጪቲ ማደያ ላይ አንድ አሽከርካሪ በታጣቂዎቸ ተገድሏል።

በተመሳሳይ በቅርቡ ከሱሉልታ ወደ ፍቼ በሚወስደው መስመር ሁለት አሽከርካሪዎች ታግተውብናል።

ሆኖም ከ2015 ዓ.ም በፊት ይፈጸም ከነበረው ዕገታና ግድያ አንፃር አሁን ድርጊቱ በመጠን እየቀነሰ መጥቷል።

ለአብነት ያህል መሳቀቅ ይበዛባቸው በነበሩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ድርጊቶች ቀንሰዋል ፤ ማህበሩም ይሄን ያምናል " ብለዋል።

ጋዜጣው ድርጊቱ መቀነሱን ገምግማችኋል ወይ? ባለፉት 2 ዓመታት እየቀነሰ መጥቷል ስትሉስ በምን ዓይነት ንፅፅር ላይ ተመሥርታችሁ ነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር።

አቶ ሰለሞን " ከ2015 ዓ.ም. በፊት በቀን 20 እና 30 የሚደርሱ አሽከርካሪዎች ይታገቱ ነበር፣ አሁን ግን ድርጊቱ እየቆየ እንደሚፈጸም እያየን ነው " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

" በአጠቃላይ ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ የተረጋገጠ ከ120 በላይ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ተገድለዋል፡፡ ከሁሉም አካባቢዎች የተረጋገጠ መረጃ ስለማይመጣልን እንጂ፣ ቁጥሩ ከዚህ ከፍ የሚልበት ዕድል አለ " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ማኅበሩ ፤ " የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኦሮሚያ ክልልና የፀጥታ አካላትን ስንጠይቅ ምላሽ ይሰጡናል። ነገር ግን ችግሩ ያለው የከተማ አስተዳደሮች ላይ ነው፡፡ ከቀናት በፊትም ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በድጋሚ ደብዳቤ አስገብተናል " ሲል ገልጿል።

" በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ ግን አስቸጋሪ ስለሆነ በክልሉ ድንገተኛ ክስተቶች ይፈጠራሉ፡፡ ይኼ ነው ብለን ሐሳብ የማንሰጥበት ችግር ነው ያለው " ብሏል፡፡

የጣና አሸከርካሪዎች ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ ሰጡ ብርሃን ምን አሉ  (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

" የእገታ ድርጊቱ እየቀነሰ ሳይሆን እየጨመረ ነው። ድርጊቱ ቀነሰ የሚባል ሳይሆን እየጨመረ ነው፡፡ በተለይ ዕገታ እየተለመደና ጭካኔዎች እየበዙ ናቸው።

ከዚህ በፊት ለ24 ሰዓት በነፃነት እንጓዝ ነበር፣ አሁን ግን እንቅስቃሴያችን የተገደበ ሆኗል፡፡ አሽከርካሪ እንደ ቢሮ ሠራተኛ ጠዋት ወጥቶ አመሻሽ ከ11፡00 ሰዓት በኋላ እንዳይቀሳቀስ እየተገደበ ነው፡፡

የትራንስፖርት ዘርፉ ግን በዚህ ሁኔታ መሥራት አይችልም፡፡ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የራሱ የሆነ ተዕፅኖም ይኖረዋልም

የችግሩን ጥልቀትና አሳሳቢነት በተመለከተ ለፌዴራል፣ ለአማራ፣ ለኦሮሚያና ለአፋር ክልሎች ደብዳቤ አስገብተናል፤ ተነጋግረናል። ዘላቂ መፍትሔ ግን አለመገኘቱን አልተገኘም " ብለዋል።


የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ምን አሉ (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ ዋና ዋና መንገዶችን ተከትሎ በትራንስፖርት ተጠቃሚ ዜጎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የዕገታ እና የግድያ ድርጊቶች ቁጥጥርን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ጄይላን አብዲ ፦

" ዕገታ የተለመደ ወቅታዊ ድርጊት (ፋሽን) እየሆነ መጥቷል፡፡ ለኅብረተሰቡ እንግዳ ነበር፣ አሁን ግን ሚዲያው እያስፋፋው ይገኛል፣ ስለዚህ በልኩ ነው መገለጽ ያለበት።

' ዕገታ እዚህ ቦታ ላይ ተፈጸመ፣ ተፈጠረ ማለት አይጠቅምም ' በአጋቾች ላይ ምን ዓይነት ዕርምጃ ተወሰደ የሚለው ነው ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት፡፡

ዕርምጃ ሲኖር ለሕዝብ እናሳውቃለን " ብለዋል።


ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት አዲስ አበባ በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች አንድ አቅጣጫ ብቻ ሆነው ለዛሬና ለነገ እንዲያገለግሉ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል። የትኞቹ መንገዶች ናቸው ? 🛣  ከጥይት ቤት እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት 🛣 ከቤተመንግስት ፖርኪንግ እስከ ጥይት ቤት 🛣 ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ሳይንስ ሙዝየም ያሉ መንገዶች ናቸው። በእነዚህ…
#እንድታውቁት

" 4 ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች ከዚህ በኋላ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አገልግሎት ይሰጣሉ " - የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

ከዚህ በኋላ 4 ኪሎ ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች በአንድ አቅጣጫ ብቻ አገልግሎት እንደሚሰጡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

በመሆኑም ፦
- ከጥይት ቤት  እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት፣
- ከቤተመንግስት ፖርክንግ እስከ ጥይት ቤት
- ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ሳይንስ ሙዝየም ድረስ ያሉ መንገዶች ቀድሞ ከነበረው ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ወደ አንድ አቅጣጫ መንገድ ተቀይረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳን መስመሮቹ እንደ ቀድሞው ባለ ሁለት አቅጣጫ ሆነው አገልግሎት መስጠታቸውን መቼ ይጀምራሉ ? ሲል ጠይቋል።

በምላሻቸው በአንድ አቅጣጫ እንጂ ወደበፊቱ ተመልሶ በሁለት አቅጣጫ አገልግሎት እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አስቀድመው " ለሁለት ቀን ወደ አንድ አቅጣጫ (One way) ተደርገው አገልግሎት ይሰጣሉ " በሚል ለቲክቫህ  ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ሆኖም  " ለሁለት ቀን ያልኩት በአንድ አቅጣጫ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች እና የጎደሉትን የማሟላት ስራ ለመስራት ነው " ሲሉ መንገዶቹ በቀጣይነትም ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ ሆነው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

አክለውም " የትራፊክ ስራ ዳይናሚክ ነው፣ እንደ የአስፈላጊነቱ  በየጊዜው የማሻሻል ስራዎች ሊኖሩ ይችላሉ " በማለት ጠቁመዋል።

ከዚህ በኃላ ግን መንገዶቹ ባለ አንድ አቅጣጫ ብቻ እንደሆኑ አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

Via @Tikvahethmagazine
2025/04/16 00:00:20
Back to Top
HTML Embed Code: