Telegram Group Search
Channel photo updated
መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርግሀል፡መሄድ የማታውቀውን ዕድል እንድትሞክር ይረዳሀል፡፡ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ ቆይቶም ትበሰብሳለህ፡፡ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ፡፡ባለቀ ትናንት አትታሰር በተበላ ዛሬ አትወስን ይልቅ ወደ ማይታወቀው ነገ ሂድ፡፡ነገ ወዳንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ፡፡አንድ ቦታ ላይ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ስር ይሰጠን ነበር፡፡
ዳኔል ክብረት
ዶክተር ምህረት ሌላ ሰው ላይ እንዲህ አለ

እያንዳንዷ ህፃን በውስጧ ,,,,ገና ያላደገች ሌላ ሴት ተሸክማለች፡፡በትንሿ ሰውነት ውስጥ መገለጧን የምትጠጠባበቀው ትልቋ ሌላ ሴት የስብዕና ዝንባሌዋንና እምቅ ችሎታዋን እንደተቀረፀችበት መንገድ ክፉ ወይም ደግ፡ትጉ ወይም ሰነፍ ፡ግፈኛ ወይም ሩህሩህ ትሆናለች፡፡ወላጅ ልጅን ቢወልድም፡ልጅ ደግሞ ሌላ ወላጅን ይወልዳል፡፡ከልጅ ውስጥ አዲሱን ወላጅ ማዋለድ በዋናነት የመጀመሪያው ወላጅ ስራ ነው፡፡

ወላጅ የልጁ መስታወት ነው፡፡ ህፃኗ በመስታወቱ ውስጥ ያየችውን አይነት ሰው ትሆናለች ሰባራ መስታወት ሰባራ ስብዕናን የተበላሸ መስታወትም የተዛነፈ ስብዕናን በልጆች ውስት ይፈጥራል፡፡

እያንዳንዱ ትልቅ ሰው በልጅ ውስጥ ይፀነሳል፡፡በዛው ልጅ ውስጥ አድጎ የስብዕናን የባህሪ ቅርፁን ይዞ የራሱ ሰው ይሆናል፡፡
አዘናግቶ በላት

ተኩላ በግ ቢበላ አይምሰልህ ወዶ
ቢርበው ነው እንጂ ሆዱ ቢሆን ባዶ፡፡
ለራሱ ቢያደላ ሰው ፍትህ ያዛባል
በግን የዋህ ብሎ ተኩላ ላይ ይፈርዳል፡፡
የዋህም ብትሆን በግስ አለላት ሳር
በተኩላ ግን የለም ካልገደሉ መኖር፡፡
ምን አግብቶት ነው ሰው በግን የዋህ ያላት
ሀሳብ ሳይቀበል በ
አዘናግቶ በላት

ተኩላ በግ ቢበላ አይምሰልህ ወዶ
ቢርበው ነው እንጂ ሆዱ ቢሆን ባዶ፡፡
ለራሱ ቢያደላ ሰው ፍትህ ያዛባል
በግን የዋህ ብሎ ተኩላ ላይ ይፈርዳል፡፡
የዋህም ብትሆን በግስ አለላት ሳር
በተኩላ ግን የለም ካልገደሉ መኖር፡፡
ምን አግብቶት ነው ሰው በግን የዋህ ያላት
ሀሳብ ሳይቀበል በሷ ግዞት ካሉት
የበግን ጭካኔ ይመስክሩ እፀዋት
በመጋዝ ጥርሶቿ የተጨፈጨፉት
ሰው አልደረሰበት ይህን ሁሉ ታዓምር
የመበላላት ህግ የተፈጥሮ ሚስጥር፡፡
ብቻ ሰው ከንቱ ነው እራሱን ይወዳል
ለበግ አዛኝ መስሎ ተኩላን ያሳድዳል፡፡
ያተረፋት መስሎ ከተኩላው ያስጣላት
አቤት ሰው ክፋቱ አዘናግቶ በላት፡፡

የረዲ ሽኩር(አቃቢ ህግ)
ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ መዝሙር ነው፡፡ሰርዓተ ትድድር ለመሆን ገና የአስተሳሰባችን ጥሬነት ይገዳደረዋል፡፡ዲሞክራሲ ፅንሰ ሀሳቡ በራሱ የከበደን ይመስለኛል፡፡ዲሞክራሲ በመሸነፍ ማሸነፍ ነው፡፡ዲሞክራሲ የሌላን ሀሳብ ማክበርና የራስንም የማስከበር ጥበብ ነው፡፡እኔ ብቻ ነኝ ትክክል የሚል አባት ኮትኩቶ ያሳደገው ትውልድ እንዴት ህዝብን ትክክል ነህ ብሎ ስልጣን ያስረክባል፡፡እኔ አውቅላቹኋለሁ በሚል ስርዓት ኮትኩቶ ያሳደገው ትውልድ እንደምንስ መንበሩን ለሚያውቁ አሳልፎ ይሰጣል?? ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል ...በሚል ገዳይ አባባል ተከቦ ያደገን ተተኪ እንደምን ሳይበላ ማውረድ ይቻላል፡፡
አሁን የሁሉም ችግራችን ቁልፍ መፍትሄ የአስተሳሰባችን ለውጥ እንጂ የስርዓት ለውጥ አይመስልም፡፡
ፍትህና ፍትሀዊነትን ልም አዕምሮ አጥብቆ ይወዳታል፡፡አንባገነኖች የለማ ከተማን መቆርቆር ቢችሉም የለማ ማህበረሰብን ግን ከቶ አይችሉም፡፡

ይሁኔ አወቀ (ወቃሽ ትውልድ)
ብሄርተኝነት በበውቀቱ ስዩም ሲገለፅ
ጃፈር አ/መጂድ

በዘመናችን ብሄርተኝነት ማለት ሳይደክሙ የሌሎችን የድካም ውጤት መቀማት መሆኑን አውቃለሁ፡፡አንድ ሰው በግሉ ስኬትን መቀዳጀት ሲያቅተው በጥረታቸው ብልጫ ያስመዘገቡ ግለሠቦችን ውጤት ወደ ብሄር ስኬት ለውጦ ባዶነቱን ለመሙላት ይሞክራል፡፡ሌላው እልም ያለ ፈሪ ሆኖ "የበላይ ዘር " እያለ ይፎክራል፡፡ ብብቱ ውስጥ ገብተው ካልገፉት በቀር አልጋ ላይ መውጣት ማይችለው ሰውዬ አበበ ቢቂላ በተነሳ ቁጥር "አበበ ኬኛ" እያለ ይኩራራል ፡፡ በላይና አበበ ያስመዘገቡት ውጤት በላብና በደም የተገኘ የግለሠብ ጥረት ውጤት ነው፡፡ ድል በዘር አይተላለፍም፡፡የአባቶች ታላቅነት በዘር ወደ ልጆች የሚተላለፍ ቢሆን ኖሮ ግሪኮች በዛሬይቱ አውሮፓ እግር ስር እንደ ጉድፍ ወድቀው ባልተገኙ ነበር ፡፡ ብሄርተኝነት የግለሰብ ጥረትን ሰርቆ የራስን ድክመት ለመሙላት የሚደረግ መሠሪ እንቅስቃሴ ነው ፡፡

በውቀቱ ስዩም (ከአሜን ባሻገር)
አውሎ ንፋስ
.አውሎ ንፋስ ሲነፍስ ሁለት መሆን አለህ
. የመጀመሪያው .
.ባህር ዛፉን ሆነህ
አቅምህን ሳታቅ ትገዳደርና
.ዳግም ላትነሳ ትገነደሳለህ ።
.ሁለተኛው መሆን.
.እንደ ሠንበሌጡ አቅምህን አውቀህ
ንፋሱ ሲመጣ
. ታሳልፈውና ለጥ ዝቅ ብለህ
.ተሸንፈህለት ታሸንፈዋለህ
ፍቅር: ሠውን በፍፁም እጣ ፈንታውን ከመከተል ገድቦ እንደማያውቅ መረዳት አለብህ።
ህልምህን መከተል ካቆምክ ሃቀኛ ፍቅር ባለመሆኑ ምክንያት ነው....የዐለምን ሁሉ ቋንቋ የሚናገረው
ፍቅር ነው።

እናም አንድ ነገር በምትፈልግበት ጊዜ :መላው ዩኒቨርስ ግብህን እንድትወጣ
ለመርዳት ያሴራል።
Forwarded from ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️ (ምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ)
💪💯 ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም!

💪💯 ህይወት የምልልስ መንገድ ነች ። የከፍታውና የዝቅታው መንገድ ምልልስ ፣ የመጎዳትና የመንፃት ምልልስ ፣ የመሰበርና የመጠገን ምልልስ ፣ የማዘንና የመደሰት ምልልስ ። ስለዚህም ነው የነዚህን ምልልስ አይቀሬነት ተገንዝቦ ችግሮችን ከማጉላትና በደስታም ጫፍ ከመንካት መቆጠብ አስፈላጊ የሆነው ። የዝቅታ ጊዜያት ፣ የመረበሽ ወቅቶች የሚባሉት የፍራቻ ፣ የሃዘን ፣ የመገለል ፣ የመጎዳት ፣ የመቸገር ፣ የመሰቃየትና አስጨናቂ ጊዜያት እንዲሁ መጥተው የሚሔዱና የተለመዱ (normal) የሚባሉ የህይወት ክስተቶች ናቸው ። ብቻህን መፍታት ያልቻልከው ችግር ካለ እርዳታ ጠይቅ ፣ እንቅልፍ የሚነሳህ አስጨናቂ ሃሳብ ካለብህ ለልብ ወዳጅህ ተንፈስ በል ፣ እንደ ከባድ ጭነት የከበደህ ሸክም ካለብህ ለአምላክ አዋየው ፣ ለእርሱ አስረክበው ፣ በእርሱ ላይ ጣለው ። ያንተን ችግር በማቅለሉ የሚመፃደቅ አምላክ እንዳልሆነም አስታውስ ።

💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! አንተን መርጦ አልመጣም! ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም ፣ አንተ ላይ ስለሆነ ብቻ ተዓምርና የማይሆን አይነት ነገር እንዳይመስልህ ። ማንኛውም ሰው እንደሚወድቀው ትውድቃለህ ፣ እንደማንኛው ሰው ትሰበራለህ ፣ ተስፋ ትቆርጣለህ ፣ ታዝናለህ ። ማንም እንደሚሆነው ትከዳለህ ፣ ትናቃለህ ፣ ትገፋለህ ። ይህ ሁሉ ግን አንተ ላይ ብቻ የተከሰተ እንዳልሆነ አስታውስ ። በሰወኛው ባህሪ ለብቻ ከፍ ማለት እንጂ ለብቻ መጎዳትን አንወድ ይሆናል ። ነገር ግን የሰውነት ማንነታችን ማለፍ የሚገባንን አስቸጋሪና አስከፊ ጊዜም እንድናልፍ ያደርገናል ። በውስጣችን የገነባነው ጠንካራው ስብዕና ወደፊት ያሻግረናል ።

💪💯 አዎ! የሆነብህ ፣ የደረሰብህ ፣ እየሆነብህ ያለው ሁሉ አዲስ አንዳልሆነ አስተውል ። አመጣጡ ያንተ መዳረሻ እርሱን አልፈህ ፣ እርሱን ተሻግረህ የምትደርስበት መሆኑን ለማስገንዘብ እንደሆነ እወቅ ። መጨነቅህ ፣ ማዘንህ ፣ ተስፋ ማጣትህ አዲስ አይደለም ፤ ሰው ነህና ከእነዚህ ከባድ ሁኔታዎች መንፃት አትችልም ። ከመጡ ቦሃላ ግን ማንፃትና ማስተካከል ትችላለህ ፤ ከእነርሱ ነፃ መውጣት ትችላለህ ። በነገሮች መበላሸት አትደነቅ ፣ በእቅድህ አለመሳካት እትረበሽ ፣ በሚያስጨንቁና በሚያናድዱ የህይወት አጋጣሚዎች የውድቀትና የበታችነት ስሜት አይሰማህ ፣ ብዙ እንቅልፍ አልባ ምሺቶችን ማሳለፍህ ፣ ረፍት አልባ ጊዜያት ውስጥ መገኘትህ የማይታመንና ይበልጥ ጫና ውስጥ ከከተተህ ማመንንና መቀበልን የመጀመሪያ አማራጭህ አድርገው ። ለብቻ የመብሰልሰልን ፣ በውስጥ የመያዝን ፣ በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር መፍራትን እንመፍትሔ መቁጠር አቁም ። ካንተ ችግር በላይ አሳልፈው ዛሬም ደስተኛ የሆኑ ሰዎች እንዳሉ አስታውስ ። እንዲያልፍ የፈቀድክለት የትኛውም ከባድና አስቸጋሪ ጊዜ ያልፋልና በማካበድና ብዙ በመጨነቅ ስሜትህንና ጊዜህን አታባክን ።
═════════❁✿❁ ═════════
💪💯 አንብባችሁ #ሼር አላደርግ ስትሉ #ብሞት እንኳን #የማትቀብሩኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ #ልሙትላችሁ  ሆሆ ፣ ለማንኛውም አሁንም #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇
https://www.group-telegram.com/joinchat-AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
Channel name was changed to «Hira media_ሂራ ሚዲያ»
መኖር ይሰለቻል

ሁሌ እንዲሁ መኖር ያሰለቻል። የትናንቱን ቀን ዛሬ መድገም ያሰለቻል። በቀናት መካከል ያደገ ነገር አለማሰብ፣ የተለየ ነገር አለመሥራት፣ የተለየ ነገር አለማውራት ያሰለቻል። ሁሌ በትናንቱ ላይ መቸከል ያሰለቻል። አለመለወጥ አለማደግ ያሰለቻል። ወሬው ሥራው አንድ ዓይነት መሆን ያሰለቻል።

ከሁሉ እዚህ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያደገ ሃሳብ አለማየት ያሰለቻል። አላዋቂውም (ደደቡም ላለማለት እየተኸተንኩ ነው።) (ተኸተነ = ትህትና) አዋቂውም እኩል ሲመላለስ ያሰለቻል። በሚጻፉ ሃሳቦች ላይ የሚሰጡ መልሶች ስሜት ሲሆኑ ቋቅ ችክ ሲል ያስጠላል። ተስፋ የጣልኩባቸው አሳቢዎች ወድቀው ሲከሰከሱ ሳይ ቅስም ይሰብራል።

እያደር ማነሳ፣ በሁሉም ነገር መውረድ የኑሮ መሰልቸትን ያመጣል። መፍትሔው ማንበብ ነው። ከዚህ የአሉባልታ መንደር መራቅ በመጽሐፍት ጉያ ውስጥ መወሸቅ።

ደግሞ የያዙትን ይዞ ማለፍም ይከነክናል ይቆጠቁጣል። ..... ቲሽ ደግሞ ማን ማወቅ ይፈልግና?! ይህን ማሰብ ስጀምር መኖር ስልችት ይለኛል። ለማወቅ መሮጥን ሩጬ ያወቅኩትን ካላካፈልኩ፣ በሥራ ላይ ካላዋልኩ የማወቄ ፋይዳ ምንድነው? ያወቅሁትን ላሳውቅ ብዬ ሊያውቅ የሚፈልግ ሳጣ...

" ሁለቱ ቀኑ አንድ የሆኑበት ከሠራ" ብለዋል ረሱል። ትናንትህም ዛሬህም እንዴት አንድ ይሆንብሃል? ቢያንስ ከትናንት በአንድ ነገር ተለወጥንጂ፣ እደግንጂ፣ ሃሳብህን አሳድግ፣ ንግግርህን አሳድግ፣ አንብብ.... አለበለዚያ ሁሉም ነገር ይሰለቸሃል።

ሁሴን ከድር
2025/03/09 01:05:25
Back to Top
HTML Embed Code: