Telegram Group Search
“ሃገራዊ መግባባት ለህብረ -ብሄራዊ አንድነት"
(ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን 19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ቀን “ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የባለስልጣኑ ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡

የፓናል ውይይቱ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመክፈቻ ንግግራቸው የተለያየ መልክ ማንነት ያለን የተቀደሰች ውድ ሀገር ያለን የማንደራደር ህዝቦች ነን፤አባቶቻችን የተከበረች ሀገር አስረክበውናል ስለዚህ ሀገራችንን በመውደድ ልዩነታችንን በማክበር እና ምቹ ሀገርን በመፍጠር የልጆቻችን መብት እንዲከበር የኛ አስተዋጽኦ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን በልዩነታችን እንነጋገር ለሀገራችን ዘብ እንቁም የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አቶ ጋትዌች ቱት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ራስን፣ባህልን፣ሀገርን መውደድ ያስፈልጋል እኔ ከሚል አስተሳሰብ እኛ የሚል አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል ማንም ዝቅ ማንም ደግሞ ከፍ ሳይል ሁሉም ዜጋ በእኩል ዐይን ሊኖር ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ህብረ ብሄራዊነታችንን በማክበር ልዩነታችንን አክብረን እንኑር ብለዋል፡፡


ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት የሚቻለው ጠንካራ ህብረ ብሄር ሲኖር ነው አንዳችን ሌላችንን አክብረን ስንኖር ነው በመከባበር ውስጥ አንድነት፣ፍቅር፣ቤተሰባዊነት ስሜት እንዲሁም በመከባበር ውስጥ ጥላቻን እንቀርፋለን ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ ጠንካራ አንድነት ያለው ሀይል ይመጣል፣ስለዚህ ሚዛኑን ጠብቆ በመሄድ ጠንካራ ሆኖ የተገነባ ህብረ-ብሄር በመፍጠር ጠንካራ ኢትዮጵያን እንፍጠር ብለዋል፡፡

አቶ ሰለሞን አለማየሁ የባለስልጣኑ አማካሪ ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች በሚል ርዕስ ለፓናል ውይይቱ የመነሻ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆኑ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ቅ/ጽ/ቤቱ በድንገተኛ ኢንስፔክሽን ምልከታ ከፍተኛ የስርአተ ትምህርት ጥሰት ከታየባቸው የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

(ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት በአጠ/ትምህርት ዘርፍ በድንገተኛ ኢንስፔክሽን ምልከታ ከፍተኛ የስርአተ ትምህርት ጥሰት የታየባቸውን ት/ቤቶች መድረክ በማዘጋጀት ውይይት አደረገ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት በ2017 በጀት አመት በእቅድ መሰረት የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ትግበራ በአጠቃላይ እቅድ 142 ሲሆን በክንውኑም 148 ቅድመ አንደኛ እና አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች መቆጣጠር ተችሏል፡፡
በዚህም ትግበራ የስርአተ ትምህርት ጥሰት ማለትም ያልተፈቀዱ የትምህርት አይነቶችን የሚያስተምሩ፣ከማስተማሪያው ቋንቋ በተጨማሪ የትምህርት አይነቶችን በመለየት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጡ እና የሌላ አካል የሆነና ያልተፈቀደ መጽሐፍ በራሳቸው ፍቃድ በማሳተም ለማስተማሪያነት የሚጠቀሙትን በመለየት መድረክ በማዘጋጀት የማወያየት ስራ ተሰርቷል፡፡ውይይቱን የመሩት የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ምትኩ የሰርአተ ትምህርት ጥሰት በዜጎች ላይ የሚፈጸም አስጸያፊ የሆነ ተግባር እና የመንግስትን አቅጣጫ አለመከተል መሆኑን አስረግጠው የገለጹ ሲሆን በእለቱ ተለይተው የተጠሩትን 35 የሚሆኑ ተቋማት የታየባቸውን የስርአተ ትምህርት ጥሰት ጉዳዮች በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ተ/ማሪያም በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ በአጠቃላይ 32 የሚሆኑ የት/ተቋማት ባለቤቶችና የት/አመራሮች ተገኝተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን በክፍተት የተገኙባቸውን ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ስህተት መሆናቸውን በማመንና በመቀበል ከተደረገው ምልከታ በኋላ ባለው ጊዜ ያስተካከሉ መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡በማጠቃለያውም በቀጣይ ምልከታው የሚቀጥልና ተቋማትም የጀመሩትን የእርምት እርምጃ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቅጣጫ በማስቀመጥና መተማመን ላይ በመድረስ የእለቱ ውይይት በሙሉ መግባባት ተጠናቋል፡፡
ምንጭ፡- የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም ድንገተኛ ኢንስፔክሽን የተሰራላቸውን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ግኝት ሪፖርት አቀረበ፡፡

(ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ተሰርቶላቸው የፖሊሲ እና የስርዓተ ትምህርት ጥሰት የተገኘባቸውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግኝት ሪፖርት አቀረበ፡፡

አቶ ዳኛው ገብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አንድ ተቋም እውቅና በሚወስድበት ወቅት ፖሊሲ እና ስርዓተ ትምህርቱን ሊያከብር ነው ያንን ደግሞ ባለስልጣኑ የማስከበር ስልጣን አለው የስርዓተ ትምህርት ፖሊሲ ያላከበረ ተቋም የማይቀጥል እና ቀጣዩን እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን በመግለፅ ልጆቻችንን በአንድ አስተሳሰብ እናሳድጋቸው ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት አንድ ተቋም እውቅና ሲወስድ የተጠያቂነት ሀላፊነት ይወሰዳል፤ስለዚህ ተጠያቂ እንደሚሆን በማሰብ የተፈጠረውን መድረክ በመጠቀም በመናበብ እና ያሉትን ክፍተቶች በማስተካከል ህግ እና ስርዓቱን ልናከብር ግድ ይላል ብለዋል፡፡
የባለስልጣኑ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዋር ሙላት ግኝቱን ያቀረቡ ሲሆን በ2017 ዓ.ም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 136 ተቋማት ድንገተኛ ኢንስፔክሽን የተሰራላቸው መሆኑን ገልፀው 33 ተቋማት የስርዓተ ትምህርት እና የፖሊሲ ጥሰት የተገኘባቸው መሆኑ ገልፀው የተሰጣቸውን የማስተካከያ ጊዜ እንደ መልካም እድል በመውሰድ ተቋማቸውን ማስተካከል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

በመደረኩም ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ተቋማቱ በተሰጣቸው ግብረ መልስ መሰረት በተሰጣቸው ጊዜ የሚያስተካክሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመድረኩ ዋና አላማ የስርዓተ ትምህርት እና የፖሊሲ ጥሰት የተገኘባቸው ተቋማት ጋር በመወያየት እና የተሰጣቸውን የማስተካከያ ጊዜ በመልካም አጋጣሚ ወስደው እንዲታረሙ ለመወያየት መሆኑ ታውቋል፡፡

#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
የአራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ቀን በዓልን ከመላው ሰራተኞች ጋር በመሆን አከበረ፡፡
(ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ″ሃገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት″ በሚል መሪ ቃል ከመላው ሰራተኞች ጋር በመሆን በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በፓናል ውይይት እና በልዩልዩ ዝግጅቶች በዛሬው እለት አከበረ፡፡

የአራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራስኪያጅ ወ/ሮ ምንታምር አዴማ በፓናል ውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልእክት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሁሉም በኢኮኖሚው፣በፖለቲካ፣በማህበራዊ ጉዳዮችና ባህላቸውን፣ወጋቸውን እና ታሪካቸውን በእኩልነት እንዲያሳድጉና እንዲያበልጽጉ እኩል መብት በህገመንግስቱ አላቸው ብለዋል፡፡አያይዘውም እንደገለጹት እኛ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በመኖር እርስ በእርስ መከባበርና በትብብር እና በጋራ ማደግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የመነሻ ሃሳቡን ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሰፋ ሲሆን ብዝሃነትን በማስተናገድ ሆነ አገራዊ አንድነትን ከማረጋገጥ አንፃር የበዓሉ መከበር ከፍ ያለ ፋይዳ ያለው ነው ብለዋል፡፡በተጨማሪም ሃገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ሃገራዊ መግባባት ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
2024/11/17 02:59:50
Back to Top
HTML Embed Code: