Telegram Group & Telegram Channel
🛑 ፃማ 🛑

ክፍል ዘጠኝ
ደብዳቤውን አንብባ እንደጨረሰች ራሷን ጉልበቶቿ መሀል ወሸቀቻቸው። ለምን ይሄን ሁሉ መስዋዕትነት? ለምን ይህን ያህል ለአንዲት ሴት ራስን አሳልፎ መስጠት? በምላሹ ታፍቅረው አታፍቅረው ሳያውቅ ለምን ራሱን ለእሷ ሰጠ? በህይወት ቢኖርና ይህንን ጥያቄዋን ቢመልስላት በወደደች ነበር ግን እዮብ አይመለስ አሸልቧል።

ተሳሳትክ እዮብ ብትነግረኝ ይሻል ነበር። ከጭንቅላቴ የማይሻር ጠባሳ ተውክብኝ! መቼም ከፊቴ የተዘረረውን ያንተን አካል መዘንጋት አልችልም ፣ከአእምሮዬ ሊጠፋ አይችልም። እዮብ ስህተት ሰርተኻል አዎ በጣም ተሳስተሃል! እጇ ላከ የነበረውን ወረቀት ጨመደደችው። ምን ልታስብ እንደሚገባት ማወቅ አልቻለችም። ብቻ ልትከፍለው የማትችለው የእዮብ ውለታ አለባት።

አፈቅረው ነበር? እራሷን ጠየቀች ልቧ የአዎንታም የአሉታም ምላሽ አልሰጣትም። ለረጅም ሰአት አነባች። አልአዛር ለማባበል አልሞከረም። ምክንያቱም የእሱም እምባ እየፈሰሰ ነበር። አንድ ብቸኛ ወንድሙን እንዳጣ ገብቶታል። በጀግንነት የሞተው የወንድሙ ወኔና ድፍረት ታወሰው። ለእዚች ከፊት ለፊቱ ለተቀመጠችው ሴት የነበረው የፍቅር ጥንካሬ የተለየ ነበር። ምን ያደርጋል? በህይወት ሳለ መፈቀሯን ሳታውቅ ከሞተ በኅላ ለፍቅሯ የከፈለውን መስዋዕትነት የተረዳችው ወጣት ላታገግም ቆስላለች። በምንም መንገድ ሊያፅናናት አይችልም።

ማን ያውቃል? ጊዜ የሚያመጣው አይታወቅም አለ ለራሱ እዮብን ልትዘነጋ የምትችልበት መንገድ ይኖራል።  በተቻለው መጠን ሀዘኗን ልትረሳ የምትችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሙሉ አቅሙ ቆርጧል። ከመንግስትም የደንነት አባላት ጋር በነበረው የጠበቀ ግንኙነት አንድ የውሸት መታወቂያ ሊያገኝላት ችሏል። የእሷን መምጣት ቀደም ብሎ እየጠበቀች ስለነበር ሁሉንም ነገር አስቀድሞ ዝግጁ አድርጓል።

መታወቂያውን ከኪሱ አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው። 'መአዛ አሸናፊ' ይላል። ምንድን ነው በሚል ሁኔታ ተመለከተችው። አዲሱ ስምሽ ነው ትንሽ ራስሽን መቀየር ይኖርብሻል አለና ትርምስምሱ የወጣውን ረጅም ፀጉሯን አየ። መቆረጥ ሳይኖርበት አይቀርም። በተወሰነ መልኩ የፊትሽን ገፅታ ሊቀይረው ይችላል። ግን ይህን የመሰለ ፀጉር ተቆርጦ ሲወድግ ያሳዝናል ሲል አሰበ።

ብሌን አላመነታችም። በህይወት መኖር እስካለባት ድረስ ራሷን መለወጧ የግድ ነው። ሻወር መውሰድ ፈልጋለች። አልአዛር ጭንቅላቷን ያነበበ ይመስል መታጠብ ከፈለግሽ ሻወር ቤቱን ላሳይሽ እችላለሁ።  ፀጉርሽን የምትቆርጪበት መቀስ በስተቀኝ ባለው ኮመዲኖ ላይ ይገኛል። አላት ጊዜ ሳታጠፋ ልብሷን አወላልቃ ውሀው ውስጥ ተነከረች። ውሀው እንደውጪው ቆሻሻዋ ልቧ ውስጥም ያለውን ሸክም መውሰድ ቢችል ምንኛ በተደሰተች ነበር። ዐይኗን ጨፍና ከላይ የሚወርደውን ውሀ ከጭንቅላቷ ጀምሮ ታች እስኪደርስ ድረስ ታዳምጠዋለች። ከውሀው አንድ መፍትሔ ታገኝ ይመስል አሁንም አሁንም ትነከራለች። ሰውነቷ ቢፀዳም መውጣቱን ጠላችው። በጣም ከምትወዳት  ምስኪን እናቷ ጋር እንደማትገናኝ ተረድታለች። ይሄኔ እማዬ ሞቴን ሰምታ ሀዘን ተቀምጣ ይሆናል ስትል አሰበች። በራ ሄዳ አይዞሽ በህይወት አለውልሽ ልትላት ተመኘች።

✍️✍️✍️✍️ይቀጥላል...
@yabsiratesfaye ለወዳጅ ለዘመዶ ያጋሩ

group-telegram.com/yabsiratesfaye/124
Create:
Last Update:

BY አርያም - ARYAM

Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260

Share with your friend now:
group-telegram.com/yabsiratesfaye/124

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Telegram was founded in 2013 by two Russian brothers, Nikolai and Pavel Durov. In the past, it was noticed that through bulk SMSes, investors were induced to invest in or purchase the stocks of certain listed companies. The fake Zelenskiy account reached 20,000 followers on Telegram before it was shut down, a remedial action that experts say is all too rare. Pavel Durov, a billionaire who embraces an all-black wardrobe and is often compared to the character Neo from "the Matrix," funds Telegram through his personal wealth and debt financing. And despite being one of the world's most popular tech companies, Telegram reportedly has only about 30 employees who defer to Durov for most major decisions about the platform. Telegram was co-founded by Pavel and Nikolai Durov, the brothers who had previously created VKontakte. VK is Russia’s equivalent of Facebook, a social network used for public and private messaging, audio and video sharing as well as online gaming. In January, SimpleWeb reported that VK was Russia’s fourth most-visited website, after Yandex, YouTube and Google’s Russian-language homepage. In 2016, Forbes’ Michael Solomon described Pavel Durov (pictured, below) as the “Mark Zuckerberg of Russia.”
from id

Telegram አርያም - ARYAM
FROM American