group-telegram.com/ZenaKristos/295
Last Update:
የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት
በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት
ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት
አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት
ለአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ሱባኤ ፡ ተገብቶ
መሰደድም ፡ ቀረ ፡ ከላይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጥቶ
መግቢያ ፡ በሩ ፡ ሰፋ ፡ ሰው ፡ ተግተለተለ
እንክርዳዱ ፡ ስንዴ ፡ ተኩላው ፡ በግ ፡ መሰለ
የድል ፡ አጥቢያ ፡ አርበኛ ፡ ዘለቀ ፡ ሆ ፡ ብሎ
ውጪያዊ ፡ ምስሉን ፡ ወጉን ፡ አስተካክሎ
በየጓዳው ፡ ፈላ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሰሪ
ራሱ ፡ ፈላጭ ፡ ቆራጭ ፡ ባለሚኒስትሪ
ዶክትሪኑ ፡ በዛ ፡ መድረክ ፡ ጠበበ
ጥራት ፡ ሳይሆን ፡ ብዛት ፡ ስንቱን ፡ ሰበሰበ
ግርግር ፡ እንዳይሉት ፡ ወይ ፡ ዘመነ ፡ ጥፉ
የአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ብለውት ፡ አረፉ
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ
[አዝማች]...
መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ኮሌጅ ፡ አጠናቅቄያለሁ
ምስክር ፡ ወረቀት ፡ ቆቤንም ፡ ጭኛለሁ
አንግዲህ ፡ የቀረኝ ፡ ሀያ ፡ ሰው ፡ ሰብስቤ
ኪሳቸው ፡ ኪሴ ፡ ነው ፡ ለወጭ ፡ ለቀለቤ
እያሉ ፡ የሚያልሙ ፡ ወንጌል ፡ ተጡዋሪዎች
ዙሪያችን ፡ ፈልተዋል ፡ ሥራ ፡ ጠላቱዎች (፪x)
ቀላዋጮች ፡ ብዙ ፡ ተንባዮች ፡ ለእንጐቻ
መረቅ ፡ ላጠጣቸው ፡ ላበላቸው ፡ ብቻ
እንደ ፡ መተተኛ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ እያሉ
ቅልጥም ፡ ላገኙበት ፡ ይተነብያሉ
የነጻነት ፡ ውልዶች ፡ ስንቱን ፡ ያሞኛሉ
በግርግር ፡ መጥተው ፡ የተቀላቀሉ ፡ የተቀላቀሉ
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ
[አዝማች]...
ራሱን ፡ የሚያዳንቅ ፡ አገልጋይ ፡ሞልቶናል
ሥሙን ፡ ሲያስተዋውቅ ፡ ፎቶውን ፡ አይተናል
ስብከቴ ፡ ነክቶአቸው ፡ እልፍ ፡ ሰዎች ፡ ዳኑ
አጋንንቶች ፡ ወጡ ፡ ብሎ ፡ ማጋነኑ
ራሱ ፡ እንዳደረገው ፡ በኃይል ፡ በጥበቡ
እውቁልኝ ፡ ብሎ ፡ ሥሙን ፡ ማነብነቡ (፪x)
ባለድርጂቱስ ፡ በጐ ፡ አድራጊ ፡ መሳይ
በሙት ፡ ልጆች ፡ ነጋጅ ፡ ጫና ፡ ጫንቃቸው ፡ ላይ
በድሀ ፡ ሥም ፡ ዞሮ ፡ ባከማቸው ፡ ሁሉ
ፎቁን ፡ ገንብቶበት ፡ የሚታይ ፡ ለሁሉ
ምናልባት ፡ ሲተርፈው ፡ ከርሱን ፡ ካጠገበ
ትርፍራፊው ፡ ሲቀር ፡ ድሆቹን ፡ አሰበ
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x)
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x)
—የአምልኮ ፡ ነጻነት (Yeamleko Netsanet) - ደረጀ ፡ ከበደ
ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
BY ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
![](https://photo.group-telegram.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/YNvix5qUGSTQfSyu6GIjs-oIGPyUabShbOP4zIZXpimnr2S_1MrMZIj48E4AoOrLDqwnBg6ViW9AePraCnMKnCge2_dOSxRLomdaVFyt_GM0R_YAwuIJxMCo8uBrp3wztvIvxRzKdPWa58BhdDP6ECwHZwpvd6S4fwl3yJHnJqmNyCyqZTcs1kjFn5lb8SjN_vhgcoSUNhK0UlZdp5kQiwbDHuI_jwxHDYzRpViwvMjBICuqTgm2-WwOsXthtLI_FCmFjRG81Rxx1cHwvEt6Jy-I693Qir_9p9jIpL9Xzo7ns7EyFhG-CwOVXQzcAKDcHx_THenXwdvbftNmDLVfKg.jpg)
Share with your friend now:
group-telegram.com/ZenaKristos/295