Telegram Group Search
#AddisAbaba

የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ !

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ሚገኙ 1,227 የግል ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን እስከ 65 በመቶ ድረስ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ እንደተፈቀደለቸው ተሰምቷል።

የጭማሪውን ጣሪያ 65 በመቶ መጨመር እንዲችል የተፈቀደለት ግን አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ነው ተብሏል።

የከተማው ካቢኔ ባፀደቀው፣ " የግል ትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሠራር ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ቁጥር 194/2017 " መሠረት በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ከ1,585 የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1,227 ያህሉ እስከ 65 በመቶ ብቻ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዘዲን ሙስባህ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።

በ2018 ዓ.ም. ጭማሪ ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁ 1,227 ትምህርት ቤቶች አስቀድሞ የክፍያ ጭማሪ መነሻ ሐሳባችሁን አቅርቡ ሲባሉ " የዋጋ ግሽበት (Inflation) ጨምሯል " በሚል ያቀረቡት ጭማሪ አስደንጋጭ ነበር ብለዋል።

ከትምህርት ቤቶቹ ውስጥ 10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እስከ 50 በመቶ የጭማሪ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን፣ ቀሪ 90 በመቶ ያህሉ ከ75 እስከ 263 በመቶ ጭማሪ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ሆኖም ትምህርት ቤቶች ፣ ወላጆች፣ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ቢሮ፣ የንግድ ቢሮ፣ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የፍትሕ ቢሮና የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በተሳተፉበት ጥናት፣ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችልና በሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚኖር የዋጋ ማሪ ጣሪያ ይፋ መደረጉን አስረድተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የክፍያ ጭማሪ ጣሪያውን ሲያስቀምጥ አንዱ መሠረት ያደረገበት ነጥብ የትምህርት ቤቶች ጥራት እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህም ት/ቤቶች ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አራት ተብለው በመሥፈርት መለየታቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህም ውስጥ ጥራቱ የተሻለ የሚባለው ደረጃ አራት ትምህርት ቤት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

" ደረጃ አራት የተሻለ ጥራት ያለው ትምህርት ቤት ነው፤ ጭማሪ ሲደረግም ከደረጃ ሁለት ጋር እኩል መሆን የለበትም፡፡ ስለዚህ ጭማሪውን በፐርሰንት (በመቶኛ) አለያይተነዋል " ብለዋል።

በዚህም ቅድመ መደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉት እስከ 45 በመቶ ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል። " 45 በመቶ ጨምሩ ማለት ሳይሆን ከዜሮ ጀምሮ 10 301 45 በመቶ ብቻ መጨመር ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በላይ ማለፍ አይችሉም " ብለዋል።

- አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ 40 በመቶ
- መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ 45 በመቶ፣
- ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ 55 በመቶ ዋጋ መጨመር ይችላሉ ተብሏል።

በጣሪያው መሠረት ፦
° 144 ትምህርት ቤቶች እስከ 40 በመቶ፣
° 591 ትምህርት ቤቶች እስከ 45 በመቶ
° 378 ትምህርት ቤቶች እስከ 50 በመቶ፣
° 47 ትምህርት ቤቶች እስከ 55 በመቶ፣
° 66 ትምህርቶች እስከ 60 በመቶ ሊጨምሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ የመጨረሻውን ጣሪያ ማለትም እስከ 65 በመቶ ክፍያ መጨመር እንደሚችል አቶ ኢዘዲን አመላከተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 1,585 ትምህርት ቤቶች መካከል 358 ያህሉ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የጨመሩ ስለሆኑ በቀጣዩ ዓመት እንደማይጨምሩ ገልጸዋል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ክፍያ መጨመር የሚችሉት በ2019 ዓ.ም. እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
#UoG አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ 4 ቢሊዮን ብር ወጥቶባቸው የተሰሩ 22 ፕሮጀክቶችን እንዳስመረቀ አሳውቋል።

ከነዚህም አንዱ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኘው 510 ሚሊዮን ብር የወጣበት የካንሰር ጨረር ህክምና ማዕከል ሲሆን ማዕከሉ በይፋ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለካንሰር ታማሚዎች የኬሞ ቴራፒ የሚሰጥ ቢሆንም የጨረር ህክምና አገልግሎት ባለመኖሩ ታካሚዎች ወደ ሌሎች ቦታዎች እየሄዱ እየተቸገሩ ሲታከሙ ነበር።

የካንሰር ጨረር ህክምና ማዕከሉ ፦
- ለክልሉ
- ከቤኒሻንጉል ጉምዝ፣
- ከትግራይ እና ከሌሎች አጎራባች ክልሎች ለሚመጡ ታካሚዎች እንዲሁም ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ማዕከሉ ከጅማ፣ ሀረር፣ አዲስ አበባ እና ሀዋሳ በመቀጠል በሀገሪቱ 5ኛው ማዕከል ነው።

ከዚህ ባለፈ የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ ፕላትም መመረቁ ተገልጿል።

አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክቶቹን ያስቅመረቀው ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፣ ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው።

#UoG #AmharaCommu.

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Kenya ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ…
#Ethiopia #Kenya

ሊተገበር መመርያ እየተዘጋጀለት ያለው የኢትዮ ኬንያ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ ጥያቄ ተነሳ። 

ሊተገበር መመርያ እየተዘጋጀለት ያለው የኢትዮ ኬንያ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ " ጉድለቶች አሉት " ሲሉ ነጋዴዎችና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሞያሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የስምምነቱ ይዘቶች ማሻሸያ እንዲደረግባቸዉ የንግዱ ማኅበረሰብ እየጠየቀ እንደሆነ አስረድተዋል።

የኢትዮ - ኬንያ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት በኬንያዋ የዉቅያኖስ ዳርቻ ከተማ ሞምባሳ፣ በኢትዮጵያዉ ንግድ ና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ፒኤችዲ) እና በኬንያዉ አቻቸዉ ሊ ክኛንጁይ መካከል ነበር ባለፈዉ ሚያዚያ ወር ነበር ስምምነቱ የተፈረመዉ።

ይህ ‘ታሪካዊ’ የተባለዉና የአፍሪካ የነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት አካል መሆኑ የተነገረዉ ስምምነት የሁለቱ ሀገራትን የንግድ ግንኙነትን በይበልጥ ያሳልጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ነው።

ሆኖም የስምምነቱ ፊርማ ከተፈፀመ ወደ ሁለት ወር ቢጠጋም እስካሁን ግን ተግባራዊ አለመሆኑን የሞያሌ አካባቢ ነጋዴዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

አቶ አዲሱ ንግሴ የሞያሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ " በሚያዝያ ወር ኬንያ ና ኢትዮጵያ የተፈራረሙት ስምምነት የአካባቢዉ የረዥም ዓመት ጥያቄ ነዉ " ያሉ ሲሆን ሆኖም እስካሁን አለመተግበሩን ጠቁመዋል።

ፕረዚዳንቱ የስምምነቱ ይዘቶች ማሻሸያ የሚያስፈልጋቸው ናቸዉ በሚል ያነሳሉ። በዚህም ስምምነቱ ያጎደላቸዉ የሚሏቸውን አራት ነገሮች ዘርዝረዋል።

ፕረዚዳንቱ ያነሷቸው ማሻሻያ ነጥቦች ምንድን ናቸው ?

" አንደኛው፣ በስምምነቱ ነፃ የንግድ ቀጠና ስፋቱ፣ በኬንያ በኩል 100 ኪሎ ሜትር  ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በኩል ግን 50 ኪሎሜትር ብቻ መሆኑ፣ በእኛ በኩል ቅሬታን ፈጥሯል።

ምክንያቱም አርብቶአደር የሆነዉ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ተጠቃሚ አይሆንም፣ በ50 ኪ.ሜ. ራድየስ ዉስጥ ያሉት ከተሞችም ጥቂት ስለሆኑ፣ ቢያንስ ከድምበር እስከ 300 ኪሎሜትር አካታች እንዲሆን ስንጠይቅ ቆይተናል።

ሁለተኛዉ ደግሞ በዚህ ንግድ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑት ሰዎች ቁጥር ማነስ ነዉ። ሶስተኛዉ ለ አንድ ነጋዴ የተፈቀደዉ የሸቀጦች ጅምላ ድምር ጣርያም በቂ አለመሆንና አራተኛ ላይ የሸቀቶቹ አይነቶችም እስካሁን በጥያቄ ዉስጥ ያሉ ናቸው " ሲሉ አብራርተዋል።

ለንግድ ስምምነቱ ትግበራ በኬንያ በኩል የሀገሩ መንግስት ና ነጋዴዎች በቂ እንቅስቃሴ ላይ ናቸዉ ያሉት አቶ አዲሱ፥ በኢትዮጵያ በኩል ያለዉን ሁኔታ ግን በመተቸት " ኃሳቡ ለሀገር ጥቅምን የሚያስገኝ ቢሆንም፣ ነጋዴዎች እያነሱት ያሉት ነጥቦች ከትግበራዉ በፊት መስተካከል አለበት " ብለዋል።

የቦረና ዞን አስተዳደር ንግድ ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ምን አለ ?

የቦረና ዞን አስተዳአደር ንግድ ፅህፈት ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

አቶ ቀራርሳ ዴራ የፅህፈት ቤቱ ገበያ ጥናት ባለሞያ ሲሆኑ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝደንቱ ያነሱትን ቅሬታ በትክክልም እንዳለ ገልጸዋል።

" የዞኑ ነዋሪ ከዚህ ስምምነት ተጠቃሚ ለመሆን ለዓመታት ሲጠይቀው የነበረ ጥያቄ ነዉ ካሉ በኋላ፣ ጥያቄዉም ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነዉ " ብለዋል።

የሞያሌ ከተማ ንግድ ፅህፈት ቤት፣ የተሳታፊ ነጋዴዎች አኃዝን በተመለከተ፣ በነጋዴዎች በኩል የሚነሳ ቅሬታን መስማቱን ገልፆ ነገር ግን የስምምነቱ ትግበራ መመርያ እስካሁን ስላልደረሰ በሁኔታዉ ላይ ምላሽ መስጠት እንደማይችል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የቦረና ዞን አስተዳአደር ንግድ ፅህፈት ገበያ ጥናት ባለሞያ አቶ ቀራርሳ አክለውም፥ መመርያዎች እየተዘጋጁ መሆናቸዉን ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዳማ
#TikvahEthiopiaFamilyAdama

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!

ጥሮ ግሮ መብላት ለሰው ልጅ ወጉ ነውና በስራዎ ዘወትር ይበርቱ ዕድል ግን መምጫው አይታወቅምና 
በአንድ ትኬት ፡- የቤትና የመኪና ባለቤትነት ፤ ከተጨማሪ የብር ሽልማት ጋር ተሞሸሮ  በቶምቦላ ቀርቦልዎታል፡፡

በ100 ብር ብቻ  ዕድልዎን ሲሞክሩ
ባለ 3 መኝታ መኖሪያ ቤት የግልዎ ያደርጋሉ፡፡ ቤትዎን ሲረከቡም ለ3 ዓመታት በየወሩ የ60 ሺህ ብር ሽልማት አለዎት፡፡

ፍላጎትዎ ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት ከሆነም ፤ ከቶምቦላ የሽልማት ማዕድ ያገኙታል፡፡ ለ2 ዓመታት በየወሩ 40 ሺህ ብር ሽልማት ታክሎበት፡፡

መኪናስ ያስፈልግዎታል? ቮልስዋገን ID-6 ባለቤት ይሁኑ፡፡ በተረከቡት ቁልፍ ላይ ለ2 ዓመታት የሚቀጥል ወርሃዊ የ20 ሺህ ብር ሽልማትም  አለዎት፡፡  

ቶምቦላ በዚህ ሳያበቃ የቢ.ዋይ.ዲ- ኤስ.ዩ.ቪ  ኤሌትሪክ መኪና፤ ለ2 ዓመታት ከሚቀጥል ወርሃዊ የ15 ሺ ብር ሽልማት አጠቃሎ ቀረቦልዎታል ፡፡

ቶምቦላ ሎተሪን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ አሁኑኑ ይግዙ! በዲጂታል ethiolottery.et ላይ መግዛት ይችላሉ፡፡
በወረቀት ከፈለጉም ከዕድል አድራሾች ያገኙታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በ +251977717272፣ +251950189808 እና +251950199808 ይደውሉ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
🆕

ካለፈው ከአርብ ጀምሮ ለሦስተኛ ቀን የቀጠለው የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት እየተባባሰ ነው።

ዛሬ በሁለቱም ወገኖች ጥቃቶች እየተፈጸሙ ናቸው።

በእስራኤል የተፈጸሙ ጥቃቶች

- እስራኤል በኢራን ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎችን መምታቷን ቀጥላለች፤ የእስራኤል የመከላከያ ኃይል እንዳለው በዛሬው ዕለት 250 ዒላማዎችን መትቷል።

-  የኢራን የመገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አስከ ቅዳሜ ዕኩለ ቀን ድረስ 128 ሰዎች ሲገደሉ 900 የሚደርሱት ደግሞ ተጎድተዋል። ከሟቾች መካከል በርካታ ህጻናት ይገኙበታል።

በኢራን የተፈጸሙ ጥቃቶች ፦

° ኢራን ሌሊት ላይ በእስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃቶችን የፈጸመች ሲሆን፣ በዚህም 6 ሰዎች ከቴል አቪቭ በስተደቡብ በምትገኘው ባት ያም በምትባል ቦታ እንዲሁም 4ቱ በሰሜናዊቷ ታምራ ከተማ አጠቃላይ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የእስራኤል ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

° ዛሬ እሁድ ከሰዓት በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል በማስወንጨፍ ጥቃት ሰንዝራለች። የእስራኤል ጦር ሠራዊት እንዳለው አብዛኞቹ ሚሳዔሎች የከሸፉ ሲሆን፣ ጉዳት ስለመድረሱ የወጣ ዘገባ የለም።

በሌላ በኩል ፤ እስራኤል እየወሰድች ባለው ጥቃት  በኢራን በዋና ከተማ ቴህራን የሚገኘው የሳህራን ነዳጅ ማከማቻ መመታቱን የኢራን ነዳጅ ሚኒስቴር ገልጿል። የነዳጅ ማቀነባበሪያው በጥቃቱ የእሳት አደጋ ቢደርስበትም አሁን በስራ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

መረጃው ከቢቢሲ ሲሆን ቪድዮው ከማህበራዊ ሚዲያዎች የተገኘ ነው።

ቪድዮ፦ ሀይፋ ዛሬ ምሽት (እስራኤል)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" እንዲህ አይነት አቅጣጫ ስታስቀምጥ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት፣ የቴሌኮም አገልግሎት መስፋፋትን፣ የሞባይል ስልክ ስርጭትን፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማደግን ማየት አለብህ " - የባንክ ባለሙያ   የገንዘብ ሚኒስቴር በግብይት ወቅት ከ 10,000 ብር በላይ ጥሬ ገንዘብን መጠቀም የሚከለክል ህግ ሊያወጣ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በሒደት ላይ የሚገኘው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ሲፀድቅ ከ10,000…
" የገንዘብ ሚኒስቴር ያስቀመጠው አቅጣጫ የብሔራዊ ባንክን ስልጣን የሚገዳደር አይደለም፡፡ ይህን አካሔድ በአዎንታዊነቱ ነው የምናየው፡፡ የተቀመጠው አቅጣጫ፣ ብሔራዊ ባንክ የሚደግፈው ነው " - የብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ባለሙያ

የገንዘብ ሚኒስቴር በካሽ የሚደረጉ ግብይቶችን ለመገደብ የያዘውን አቅጣጫ፣ ብሔራዊ ባንክ የሚደግፈውና የባንኩን ስልጣን የማይገዳደር እንደሆነ አንድ ባለሙያ ተናገሩ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር በግብይት ወቅት ከ 10,000 ብር በላይ ጥሬ ገንዘብን መጠቀም የሚከለክል ህግ ሊያወጣ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡በሒደት ላይ የሚገኘው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ሲፀድቅ ከ10,000 ብር በላይ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መፈፀም እንደሚያስቀጣ ተዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አንድ ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ በበኩላቸው የዚህ አይነት ህግም ሆነ መመሪያ ማውጣት የብሔራዊ ባንክ ስልጣን ነው ብለው ነበር፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ባለሙያን በጉዳዩ ዙርያ አስተያየት እንዲሰጡት ጠይቋል፡፡ ባለሙያውም፤ አንድ መስሪያ ቤት ለግብር አላማ ሲባል ከዚህ በላይ የሆነ ገንዘብ በካሽ መክፈል አትችልም ቢል፣ ከግብር አከፋፈል ግልፀኝነት ጋር የተያያዘ ስለሆነ መብቱ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ካየነው የገንዘብ ሚኒስቴርን አካሔድ የብርን ህጋዊነት የሚገዳደር ሆኖ አላገኘሁትም ብለዋል፡፡

ሆኖም፣ የባንክ ሒሳብ ተደራሽነት በሀገሪቱ ውስጥ ገና 45 በመቶ ላይ እንዳለ አውስተው፣ የዲጂታል የክፍያ መንገድ ባልተስፋፋባቸው የገጠር አካባቢዎች ይህን መተግበር ስለሚያስቸግር አካሔዱ ጥንቃቄ ያስፈልጓል ይላሉ፡፡

የብሔራዊ ባንክ ባለሙያው በዝርዝር ምን አሉ ?

" ለግብር አላማ ሲባል አንድ ግብር ከፋይ በካሽ እንዳትከፍል ሊባል ይችላል፡፡ ለብሔራዊ ደህንነት ሲባልም እንደዛ ሊደረግ ይችላል፡፡ ምክንያቱም በካሽ የሚደረግ ግብይት የገንዘብ ምንጩን ለማወቅ ያስቸግራል፡፡

አንተ ዛሬ በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ግብይት ብትፈፅም፣ አንተ ማነህ የሚለውን ለማወቅ አያስችልም/ትራክ አይደረግም፡፡ ከዚህ አኳያ ይህ አለምአቀፍ አሰራር ነው፡፡ አብዛኞቹ ሀገራት በካሽ የሚደረገውን ግብይት በደህንነት መስሪያ ቤቶች ወይም በግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቶች በኩል ይደነግጋሉ፡፡ ያ ማለት ግን ገንዘቡን የሚያትመውን አካል ስልጣን የመገዳደር ነገር አይደለም፡፡የአከፋፈል መንገዱ/ቅርፁ/አይነቱ ነው የሚለው እንጂ አሁንም ብር ነው የሚከፈለው፡፡

የወረቀት ገንዘብ ነበር አሁን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ሆነ ማለት ነው፡፡ የኤሌክትሮኒክ ብር የሚተዳደርበትን አሰራር ደግሞ ብሔራዊ ባንክ ነው የሚያወጣው፡፡

የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ/ብር የሚተላለፍበትን ስርዓት  የሚቆጣጠረውና የሚከታተለውም ብሔራዊ ባንክ ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ እቃ ገዝተህ በቴሌ ብር ስትከፍል፣ በብር ነው እየከፈልክ ያለኸው፡፡ ግን እኔ ቴሌብር አልቀበልም ልትል ትችላለህ መብትህ ነው፡፡ በብር አልቀበልም ማለት ግን አትችልም፣ መብትህ አይደለም እሱ፡፡ ህጋዊነቱ እሱ ላይ ነው፡፡

ስለዚህ ከታክስ አኳያ መንግስት ወይም ከብሔራዊ ባንክ ውጭ ያለ ሌላ መስሪያ ቤት ያንን የማድረግ መብት አለው፡፡ ከብሔራዊ ባንክ አኳያ አካሔዱን በአዎንታዊነቱ ነው የምናየው፡፡ ክፍያዎች ዲጂታል እንዲሆኑ ስንጠይቅ ነበር፡፡ በተለይ በከተሞች የሚደረጉ ግብይቶች በካሽ እንዳይደረጉ መገደብ አለባቸው ስንል ነበር፡፡

እኛም እኮ ከቅርንጫፍ ባንክ በካሽ የሚወጣን ብር ከ 50ሺህ እንዳያልፍ ገድበናል፡፡ ከአንድ ቅርንጫፍ ባንክ ከ 50 ሺህ ብር በላይ በካሽ ማውጣት አትችልም፡፡ ከ 50ሺህ ብር በላይ ንግድን በካሽ ማከናወን አትችልም የሚል መመሪያም ማውጣት ይቻል ነበር፡፡ ግን እሱ የብሔራዊ ባንኩ ስልጣን አይደለም፡፡

ከዚህ በኋላ ብሔራዊ ባንክ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽነት ከማስፋት አኳያ ሊሰራ ይችላል፣ ድጋፍም ያደርጋል፡፡ የዲጂታል ክፍያ የሚፈፅሙ አካላትን ከማብዛትና ከመከታተል አኳያም ብሔራዊ ባንክ ሚና ይኖረዋል፡፡ ቁጥጥርም ያደርጋል፣ ስርዓቱ ጤናማ እንዲሆን፡፡    
                
ይህ አካሔድ ሰዎች ወደ ዲጂታል አጠቃቀም እንዲመጡ ያደርጋል፡፡ የገንዘብ ምንጩን ለይቶ ለማወቅ ያግዛል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነቶቹን የክፍያ አማራጮች ያልገቡባቸውን አካባቢዎች ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል፡፡ ገጠር አካባቢ ሰንጋ/በሬ የሚሸጥ አንድ ሰው፣ ከ 10ሺህ ብር በላይ በካሽ ስትገበያይ ከተገኘህ ትቀጣለህ ካልከው አስቸጋሪ ነው፡፡ እንደዚህ እየተባለ ያለው ሰው፣ በግብር ማእቀፉ ውስጥ ያለ አካል ነው ወይስ ማንኛውም ሰው ነው የሚለው ግልፅ መሆን አለበት፡፡ ማንኛውንም ሰው ከሆነ አስቸጋሪ ነው፣ የተመዘገበ ግብር ከፋይን ከሆነ ግን መብቱ ነው መስሪያ ቤቱ፡፡

ግብር ከፋይም ሆኖ፣ በገጠር አካባቢ የዲጂታል አገልግሎቱ ተደራሽ ስላልሆነ፣ በእንስሳት ንግድና በእህል ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ሊከፍሉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ይህን ሁኔታ በየፈርጁ ነው እያየህ የምትተገብረው፡፡ እንደዛ ካልሆነ ለስራው አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

አገልግሎቱ ተደራሽ ያልሆነባቸው አካባቢዎች አሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ያለው የባንክ ሒሳብ ተደራሽነት/access to account 45 በመቶ ነው፡፡ የባንክ ሒሳብ ማውጣት ካለበት አዋቂ ሰው መካከል፣ የባንክ ሒሳብ ያለው ተብሎ የሚታሰበው 45 በመቶ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአብዛኛው በከተሞች ያለው ሰው ነው፣ በገጠር አካባቢ ተደራሽነቱ የለም፡፡ ይህንን ተሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከቴክኖሎጂው ጋር ተያይዞ ያለውም ነገር ገዳቢ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🤙🏽ማንኛውንም የድምጽ ወይም የዳታ ጥቅል እየገዛን በጉርሻ ደቂቃዎች እንንበሽበሽ! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
"ዳግም የመሬት ናዳ ተከስቶ የሰዉ ሕይወት ጠፍቷል ! " - የዞኑ አደጋ ስጋት

➡️ " ባለፈዉ ዓመት ከ5 ሺ በላይ ዘጎች በመሬት ናዳዉ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን የመልሶ ማቋቋሙ ስራ እየተሰራ ቆይቷል! "

የወላይታ ዞን አደጋ ስጋት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ባሳለፍነዉ ዓመት በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ የመሬት ናዳ ተከስቶ ለሰዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ከሆነ በኋላ ስጋት ዉስጥ ናቸዉ ተብለዉ ከተለዩ አከባቢዎች ነዋሪዎች እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በተከለከሉ አከባቢዎች የተወሰኑ ሰዎች ሲንቀሳቀሱ ዳግም ናዳ ተከስቶ የአንድ ሰዉ ሕይወት ማለፉን አስታዉቀዋል።

የካዎ ኮይሻ ወረዳ 12 ቀበሌዎች ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው በመሆኑ ነዋሪዎችን በማስነሳት አባላ አባያ በተባለ ሜዳማ አከባቢ የማስፈር ስራ እየተሰራ መሆኑንና በመጀመሪያው ዙር ለ8 መቶ አባዎራዎች ቤት ተሰርቶ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

የወላይታ ዞን አብዛኞቹ ደጋማ አከባቢዎች ለመሬት መንሸራተትና ናዳ ተጋላጭ መሆናቸዉን የሚገልፁት አቶ ዳዊት አምና ሰፋ ያለ ናዳ ያስተናገደው የካዎ ኮይሻ ወረዳ ሙሉ አከባቢዎችን ጨምሮ ፦
- ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ፣
- ኦፋ ወረዳ ፣
- ቦሎሶ ሶሬ እና ቦሎሶ ቦንቤ ወረዳዎች ከፍተኛ ስጋት ካለባቸዉ ቦታዎች የክረምቱን ወቅት ከፍተኛ ስጋት በማያስተናግዱ አከባቢዎች ባሉ የትምህርት፣ የጤናና ሃይማኖታዊ ተቋማት እንዲያሳልፉ የማድረጉ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።

ባሳለፋነዉ ዓመት በተከሰተዉ ናዳ 2,347 አባዎራዎች በአጠቃላይ ከ5 ሺ በላይ ዘጎችች መፈናቀላቸዉን የሚገልፁት የዞኑ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኋላፊ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን ሃብት በማሰባሰብ ዘላቂ መፍትሔ የማሰባሰቡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡፡ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፤ " ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው " የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡…
" በኢ-መደበኛ መንገድ ከሚሰሩት ውጪ 860 የተመዘገቡ የፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች አሉ ይህም ጥቅል ካፒታላቸው 58.8 ቢሊዮን ብር ይገመታል " - ፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ማህበር

ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው " የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ " በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል።

አዋጁ በረቂቅ ሂደት ላይ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በተጠቃሚውም ሆነ በአምራች ማህበረሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱበት ነበር።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ጎማና ፕላስቲክ አምራቾች ማህበር አባሉ በረከት ገ/ህይወት አዋጁን " ጭካኔ የተሞላበት ውሳኔ " ሲሉ ገልጸውታል።

ማህበሩ በራሱ እና በገለልተኛ ቡድን አማካኝነት አሰራሁት ባለው ጥናትም ኢንዱስትሪው በአመት 441 ሺ 228.8 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ኢንዱስትሪ መሆኑን አስረድተዋል።

ማህበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ዝርዝር ሃሳብ ምን አለ ?

" ከአዋጁ ረቀቅ ሂደት ጀምሮ ቅሬታ አለን አንድ አዋጅ ሲረቅ ሊያሳትፋቸው የሚገቡ ባለድርሻ አካላት አሉ በረቂቅ ሂደቱ የፕላስቲክ ውጤት አምራቾችም ሆኑ ማህበራችን እንደማህበር አድሬስ አልተደረገም የአሳታፊነት ውስንነት ችግር ነበረበት።

አዋጁ ካስቀመጣቸው ድንጋጌዎች ውስጥ ሁሉንም ሳይሆን አንዳንድ ድንጋጌዎች በስጋት እና በጥርጣሬ የምንመለከታቸው አሉ።

አዋጁን በንድፈ ሃሳብ ደረጃ አያስፈልግም የቀድሞው አዋጅም መሻሻል የለበትም ነበር የሚል አቋም የለንም ነገር ግን ይህ አዋጅ ከረቂቁ ጀምሮ ባለው ሂደት ውስጥ የሳታቸው መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ።

የመጀመሪያው ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ከግንዛቤ ያላስገባ ነው የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት ከሰላሣ አመት ባልበለጠ ታሪኩ ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ለምርት ይጠቀምባቸው የነበሩ ጥሬ እቃዎች በሙሉ ያስመጣ የነበረው ከውጭ ነው።

አሁን ላይ 90 በመቶ የሚሆነው የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) የሚሰራው በአካባቢያችን ከሚገኙ እና ሌሎች ኢንዱስትሪዎች ከሚያመነጯቸው እንደ የዘይት ጀሪካን እና የኮስሞቲክስ እቃዎች ከመሳሰሉት ደረቅ ቆሻሻዎች ነው።

በዚህ አሰራር መሰረት ፌስታል ከውጭ ይገባ ከነበረበት አሰራር ከማስቀረቱ በተጨማሪ ጥሬ እቃውንም በሃገር ውስጥ መተካት ተችሏል።

በየአካባቢው በርካታ ወጣቶች በመዳበሪያ ላስቲክ እና ጀሪካን እየለቀሙ ለፋብሪካዎች ግብአትነት ያቀርባሉ ይህ አሰራር የላስቲክ ፋብሪካዎች የሚጠቀሙት በሌሎች ፋብሪካዎች ከወጡ ተረፈ ምርቶች በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃ ያበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ሊሰጠው ይገባ ነበር።

በሁለተኛ ደረጃ ተያያዥ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው በአግባቡ ሊጤን ይገባው ነበር።

እኛ ባለን መረጃ እና ገለልተኛ የጥናት ቡድን በሰራው ጥናት መሰረት የፌስታል ምርት ጥቅል ሃገራዊ ኢኮኖሚ ላይ የ 51.6 ቢሊዮን ብር አስተዋጽኦ የሚያደርግ ኢንዱስትሪ ነው።

ከውጭ ይገባ የነበረ ጥሬ እቃንም በመተካት 350 ሚሊየን ዶላር ማዳን ተችሏል።

በሦስተኛነት እዚህ እንዱስትሪ ላይ የተሰማሩ ዜጎች እንዴት ነው እየሰሩ ያሉት ከማይክሮ ፋይናንስ አበዳሪ ድርጅቶች ጋር ያላቸው ትስስርስ እንዴት ነው የሚለው በአግባቡ ሊጤን ይገባው ነበር።

አዋጁ ከጸደቀ በኋላ በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይገልጿል ይሄ አንድን ትልቅ ኢንዱስትሪ አይደለም ማንኛውንም ትንሽ ኢንዱስትሪ ለመዝጋት የሽግግር ጊዜ ያስፈልጋል።

ይህንን አዋጅ በማርቀቅ ሂደት ውስጥ የጎረቤት ሃገራት ልምድ ወስደናል ተብሏል ነገር ግን ይህ ህግ ተግባራዊ ያደረጉ ሃገሮች ከሦስት እስከ አምስት አመት የሽግግር ጊዜ ሰጥተዋል በዛ ኢንዱስትሪ ላይ ለተሰማሩ አካላት ደግሞ ወደፈለጉት ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ ድጋፍ አድርገዋል።

ወደ እኛ ስንመጣ ስድስት ወር የሚባለው ነገር በብዙ መልኩ እኛን የሚያጠፋ ነው።

በስራችን ከ 168 ሺ በላይ ሰራተኞች አሉ እነዚህን ሰራተኞች የስራ ዋስትና የሚያሳጣ ነው።

አዋጁ አንድ ድርጅት ሲዘጋ ሰራተኞቹን በምን ሁኔታ ነው የሚያሰናብተው የሚለውን አላስቀመጠም።

ዛሬ ድረስ ማሽን እየተከሉ ያሉ አምራቾች አሉ በመንገድ ላይ እየመጣ ያለ ማሽነሪ አለ ይህ ሁሉ ከጥቅም ውጪ ይሁን ማለት ፍጹም ጭካኔ የተሞላው ውሳኔ ነው።

ወደ ሃገር ውስጥ በሚገባ የጥሬ እቃ ላይ በሚከፈል ታክስም የፕላስቲክ ኢንዱስትሪው 10 ቢሊዮን የቀጥታ ታክስ አስተዋጽኦ እንዳለው ይታወቃል።

በኢ-መደበኛ መንገድ ከሚሰሩት ውጪ 860 የተመዘገቡ የፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች አሉ ይህም ጥቅል ካፒታላቸው 58.8 ቢሊዮን ብር ይገመታል።

ይህን የሚያህል ሴክተር ከኢኮኖሚው በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ውጣ ስትለው ባለሃብቱን ከፋብሪካ ባለቤትነት በነጋታው ወደ ተመጽዋችነት እንዲሁም በስሩ ያቀፋቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ ስራ አጥነት ማሸጋገር ነው።

በየሰፈሩ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶችን እየለቀሙ ወደ ፋብሪካ የሚያቀርቡ እና ትራንስፖርት የሚሰጡ አሉ ይሄ ጥሬ እቃን መልሶ የመጠቀም ሂደት ላይ አብዛኛውን የምንጠቀመው እኛ ነን በዚህ ሂደትም በአመት 441 ሺ 228.8 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ኢንዱስትሪ ነው።

ስለዚህ በረቂቅ ሂዱቱ ላይ እነዚህን አንኳር ነጥቦች እንዴት አድርጎ ሊመለከታቸው እንደተዘጋጀ ሳያስቀምጥ ለምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ አምራቹንም ሆነ ማህበራችንን እጅግ ያሳዘነ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2025/06/16 16:18:03
Back to Top
HTML Embed Code: