TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም " - ኢራን
የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ኢራን በአሜሪካ ለተፈፀሙባት ጥቃቶች " ኃያልና ለድል የሚያበቃትን " ምላሽ መስጠት መጀመሯን ዘገበ።
በመንግሥት የሚመራው ታስኒም የዜና ማሰራጫ እንዳለው የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ በኳታር እና በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሠፈሮች ላይ የሚሳዔል ጥቃቶችን ከፍቷል።
" በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም " ብሏል አብዮታዊ ዘቡ።
ጨምሮም በጥቃቱ ኢራን ለዋይት ሐውስ እና ለአጋሮቿ ያስተላለፈችው መልዕክት " ግልጽ " ነው ብሏል።
ኢራን በሉዓላዊነቷ፣ በግዛት አንድነቷ እና በደኅንነቷ ላይ የተፈፀመባትን ጥቃት በምንም ዓይነት ሁኔታ ዝም ብላ እንደማትመለከትም ገልጿል።
ኢራን ስላጠቃችው በኳታር የአሜሪካ የጦር ሰፈር ምን ይታወቃል ?
- የአሜሪካ ጦር ሰፈር አል ኡዴይድ የሚባል ሲሆን ከዶሃ አቅራቢያ የሚገኝ ነው።
- ይህ የጦር ሰፈር ወደ ስምንት ሺህ የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች የሰፈሩበት ነው።
- በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ የአየር ኃይል ክፍል ዋና መዘዣ ነው።
- አቡ ናኽላ በሚል መጠሪያው በሚታወቀው በዚህ ጦር ሰፈር ውስጥ የብሪታኒያ ወታደሮች እየተፈራረቁ ለአገልግሎት ይቆያሉ።
- በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ረጅሙ የአውሮፕላን መንደርደሪያ ሜዳ ያለው ይህ የጦር ሰፈር በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በኢራቅ ውስጥ ለምታካሂደው ወታደራዊ ተልዕኮ ዋና ማዘዣ እና የአቅርቦት ማዕከል ነው።
- ኳታር አሜሪካ የአል ኡዴይዳ ጦር ሰፈርን እንድትጠቀምበት የፈቀደችው ከ25 ዓመት በፊት ነው። ሁለቱ አገራት ስምምነት ተፈራርመው ጦር ሰፈሩ በአሜሪካ እጅ ከገባ በኋላ ኳታር በይፋ በግዛቷ ውስጥ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲሰፍሩ ዕውቅና ሰጥታለች።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ቪድዮ ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኳታር
@tikvahethiopia

" በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም " - ኢራን የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ኢራን በአሜሪካ ለተፈፀሙባት ጥቃቶች " ኃያልና ለድል የሚያበቃትን " ምላሽ መስጠት መጀመሯን ዘገበ። በመንግሥት የሚመራው ታስኒም የዜና ማሰራጫ እንዳለው የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ በኳታር እና በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሠፈሮች ላይ የሚሳዔል ጥቃቶችን ከፍቷል። " በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም…
" የ12ቱ ቀናት ጦርነት ማብቃቱ ይበሰራል " - ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውን ገለጹ።
" እስራኤል እና ኢራን አሁን የያዟቸውን የመጨረሻ ተልእኮዎች ካጠናቀቁ በኃላ በ6 ሰዓታት ውስጥ ለ12 ሰዓታት የሚቆይ የተሟላ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል " ብለዋል።
በዚህም ጦርነቱ እንደተጠናቀቀ እንደሚቆጠር ትራምፕ ገልጸዋል።
" ኢራን በስምምነቱ መሰረት ስምምነቱን ተኩስ አቁሙን በይፋ ትጀምራለች " ያሉት ትራምፕ " እስራኤል በ12ኛው ሰዓት ትከተላለች " ብለዋል።
በ24ኛው ሰዓት " የ12 ቀናት ጦርነቱ " ማብቃቱን ለዓለም ህዝብ በይፋ እንደሚበሰር ፤ ሁለቱም ወገኖች ለስምምነቱ መከበር ተከባብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
" ይህ ጦርነት ለዓመታት ሊቆይ መላው መካከለኛውን ምስራቅ ሊያጠፋ ይችል ነበር " ያሉት ዶናልድ ትራምፕ " ግን በፍጹም አልሆነም አይሆንም " ብለዋል።
" አምላክ እስራኤልን ይባርክ፣ አምላክ ኢራንን ይባርክ፣ አምላክ መካከለኛውን ምስራቅን ይባርክ፣ አምላክ አሜሪካን ይባርክ፣ እንዲሁም አምላክ መላው ዓለምን ይባርክ " ሲሉ ገልጸዋል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ZemenGEBEYA
🌟📦 በዘመን ገበያ እንዴት በቀላሉ እንገበያያለን?
ቴሌብር ሱፐርአፕዎ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ላይ ያገኙታል!
በዘመን ገበያ ግብይትዎን ያዘምኑ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalEthiopian #RealizingDigitalEthiopia

ቶምቦላ ሎተሪ ስለቆረጡ ብቻ እየተሸለሙ ነው !
ቶምቦላ ሎተሪ በመቁረጥ እህትና ወንድም የIPhone 15 Pro Max ሲያሸንፉ የሽያጭ ባለሞያው ደግሞ የሳምሰንግ S-24 Ultra ሽልማቱን ተረክበዋል፡፡
ሰኔ 29 የሚወጣው የቶምቦላ ሎተሪ በ1ኛ እና 2ኛ ዕጣ ፤ የባለ 3 እና የባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤቶችን ከተጨማሪ የገንዘብ ሽልማቶች ጋር አቅርቧል፡፡
በ3ኛ እና በ4ኛ ዕጣ ደግሞ ቮልስዋገን ID-6 እንዲሁም የቢ.ዋይ.ዲ SUV መኪናዎችን ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር አዘጋጅቷል።
የቤት እና የመኪናው ዕጣ የፊታችን ሰኔ 29 ከመውጣቱ በፊት የመንደርደሪያ ሽልማቶች እየወጡ ነው።
ቶምቦላ ሎተሪን በዲጂታል የቆረጡ ዕድለኞች “ስለቆረጡ ብቻ” በተዘጋጁ እድሎች ተሸላሚ እየሆኑ ነው ።
ሰኔ 12 የዲጂታል ሎተሪ ለቆረጡ የተዘጋጀው የሳምሰንግ S-24 Ultra ሽልማት አቶ ናሆም ይትባረክን ዕድለኛ አድርጓል።
የሽያጭ ባለሞያ መሆኑን የነገረን አቶ ናሆም በዲጂታል መንገድ ሎተሪ ሲቆርጥ የመጀመሪያው እንደሆነ ይናገራል። የሳምሰንግ S-24 Ultra ማሸነፉ ሲነገረው እንዳላመነ በመጥቀስ በአካል ተገኝቶ ሸልማቱን መረከቡ ቀጣይ የቤትና የመኪና ሽልማቱን ለማግኘት በተደጋጋሚ ሎተሪ እንዲቆርጥ ምክንያት ሆኖኛል ብሏል።
በታናሽ እህቱ ሀና ጌታነህ ውትወታ ሰኔ 13/2017 በዲጂታል መንገድ ሎተሪ የቆረጠው ጌዲዮን ጌታነህ ደግሞ ከእህቱ ጋር የIphone 15 Pro Max ተሸላሚ ሆነዋል።
Ethiolottery.et ላይ በመግባት በ100 ብር ብቻ የቆረጡት ቶምቦላ ሎተሪ የIphone 15 Pro Max ተሸላሚ ያደረጋቸው እህትና ወንድም ከስልኩ በላይ ቤቱና የመኪናው ሽልማት እንዳጓጓቸው ተናግረዋል።
የስልክ ዕድለኞች በዛሬው ዕለት ሸልማቶቻቸውን በአካል ተገኝተው ተረክበዋል።
ከስልክ በላይ የቤት እና የመኪና ሽልማት ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር ይዞ የመጣውን የቶምቦላ ሎተሪ ባለ ዕድል ለመሆንም፣ እነሱ ቆርጠው ባለ እድል በሆኑበት፤ በዲጂታል https://www.ethiolottery.et ላይ እና በቴሌ ብር ሱፐር አፕ አሁኑ ይግዙ ብለዋል!
ስለገዙ ብቻ ይሸለማሉ
ቶምቦላ በሽልማት የተሞላ!
ለበለጠ መረጃ በ +251977717272፣
+251950189808 እና
+251950199808 ይደውሉ!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!

#Update
የኢራን መገናኛ ብዙኃን በሰሜናዊ ኢራን ፍንዳታዎች በመሰማታቸው " ተኩስ አቁሙ ተጥሷል " አሉ።
በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም መደረጉ ቢነገርም በሰሜናዊ ኢራን ማዛንዳራን ግዛት ውስጥ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ለኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ ቅርብ የሆነው 'ፋርስ' የተባለው የዜና ወኪል እንዳለው ከዋና ከተማዋ ቴህራን በስተሰሜን ማዛንዳራን ግዛት ውስጥ በምትገኘው ባቦልሳር ከተማ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፊል መንግሥታዊ የሆኑት 'መህር' እና 'ኢስና' የተባሉት የዜና ወኪሎች በሰሜናዊ ግዛት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች ፍንዳታዎች መከሰታቸውን እና የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ተኩስ መሳማቱን በመጥቀስ የተኩስ አቁሙ “ተጥሷል” ብለዋል።
በተጨማሪም የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ፍንዳታዎች መከሰታቸውን እና የግዛቲቱን አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ ክስተቱን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች ገና አለመታወቃቸውን መናጋራቸው ገልጿል።
በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ " እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም የለባትም " በማለት ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ " እስራኤል፤ እነዚያን ቦምቦች አትጣይ። በጥቃቱ የምትቀጥይ ከሆነ ከፍተኛ ጥሰት ነው። የጦር አውሮፕላን አብራሪዎችሽን አሁኑኑ ወደ ቤታቸው መልሺ! " ብለዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ የመጣው ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የተኩስ አቁም በኢራን እና በእስራኤል መካከል መደረጉን ካስታወቁ በኋላ ነው።
እስራኤል በትራምፕ ሃሳብ መስማማቷን ስታሳውቅ፣ ኢራን ደግሞ ጥቃቱን የምታቆመው እስራኤል ካቆመች ብቻ ነው ብላለች።
ምንጭ ፦ ቢቢሲ

" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result ላይ መመልከት ይችላሉ " - ቢሮው
በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 88.8 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
በመዲናዋ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።
በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 70,525 ተማሪዎች መካከል 88.8 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን ይፋ አድርጓል።
ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች መካከል 13 የሚሆኑት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሩ መሆናቸው ተገልጿል።
የዘንድሮው ውጤት በ2016 ዓ.ም ከነበረው የ78.9% ወደ 88.8% ማደጉን በመግለጽ መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ቢሮው ምስጋና አቅርቧል።
ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
ውጤት መመልከቻ ፦ https://aa.ministry.et/#/result

" ከኢሶዴፓ 9 የስራ አስፈፃሚ አባላት 6ቱ ተሰብስበው፣ ምክትል ሊቀመንበሯን ዶ/ር ራሔልን እና ነባሩን ማህተም አግደዋል "- የኢሶዴፓ ጊዜያዊ ሊቀመንበር ነኝ ያሉት አቶ አጫሞ ቦቄ
የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ/ሶዴፓ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ማለትም ሰኔ 8/2017 ዓ.ም የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ራሔል ባፌን ማገዱን የሚያትት መግለጫ ተሰራጭቶ ነበር፡፡
የፓርቲው መሪ ዶ/ር ራሔል ባፌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል መግለጫው ቀደም ሲል በማዕከላዊ ኮሚቴ በታገዱ 4 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የተፃፈና በህገወጥ ማህተም የተዘጋጀ ነው ብለውታል፡፡
የእግድ መግለጫውን አዘጋጅተዋል ከተባሉት ሰዎች መካከል የሆኑትና በዚሁ መግለጫ ላይ በጊዜያዊ ሊቀመንበርነት መሾማቸው የተገለፀ አንድ አባል በበኩላቸው የዶ/ር ራሔል የመታገድ ውሳኔ በፓርቲው ህገደንብ መሰረት በስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ አባላት በአብላጫ ድምፅ መተላለፉን ተናግረዋል፡፡
የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሐላፊ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ አጫሞ ቦቄ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " ዶ/ር ራሔል ከተሰጣቸው ሐላፊነት ውጭ እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸውና ማህተሙንም ላልተገባ ተግባር እየተጠቀሙበት ስለሆነ " ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የእግድ ውሳኔውን አሳልፏል፣ አዲስ ማህተምም አስቀርፆዋል " ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አቶ አጫሞ ቦቄ በዝርዝር ምን አሉ ?
" እኔ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ/ሶዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሐላፊ ነኝ፡፡ ቢያንስ 30 አመታት ለሚሆን ጊዜ ከፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ጋር በፓርቲው ውስጥ ሰርቻለሁ፡፡
ፓርቲውን ከብሔር ፓርቲነት ወደ ሀገርአቀፍ ፓርቲነት በማሸጋገሩ ሒደት ሚናዬን ተወጥቻለሁ፡፡ አንድ ፓርቲ የሚመራው በህገደንቡ መሰረት ነው፡፡ አደረጃጀቱንና ውሳኔ አሰጣጡን የሚወስነው ህገደንቡ ነው፡፡ እኛም የምንመራውና የምንሰራው በዚሁ ህገደንብ መሰረት ነው፡፡
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አሁን 9 ብቻ ነን፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከማለፋቸው በፊትም 10 ነው የነበርነው፡፡ የአባላቱ ቁጥር 11 እንዲሆኑ ዶ/ር አወል አለማየሁ የሚባል ሰው ነሐሴ 20/ 2015 በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ ተመርጦ ነበር፡፡ ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች አልተቀላቀለንም፡፡
ፕሮፌሰር በየነ በሞት ከተለዩንም በኋላ መንግስቱ እና ወንድሙ የሚባሉ ሁለት ሰዎች እንዲቀላቀሉን ተጠቁመው ነበር፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች አልተቀላቀሉንም፡፡ ስለዚህ፣ ፕሮፌሰር እያሉ 10 ነበርን ከዛ በኋላ ግን እስከዛሬ ድረስ በፓርቲው 9 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ነን ያለነው፡፡
መስከረም 28/2017 ዘጠኛችንም ዶ/ር ራሔል ሊቀመንበር እንድትሆን ተስማምተን ቃለጉባኤ ፈርመን ለምርጫ ቦርድ ልከናል፡፡ ነገር ግን ምርጫ ቦርድ አልተቀበለውም ውሳኔያችንን፡፡ ሽግሽግ አይቻልም አለን፡፡ በማዕከላዊ ምክር ቤት ምርጫ አድርጋችሁ ነው ሊቀመንበር የምትመርጡት አለን፡፡ ከዛ በኋላ በቃ በምክትል ሊቀመንበርነት ፓርቲውን ምሪ ብለን ተስማማን፡፡
9ኙ የስራ አስፈፃሚ አባላት ከፕሮፌሰር ህልፈት በኋላ አንዴ ብቻ ነው የተሰበሰብነው፡፡ ከዛ በኋላ ዶ/ር ራሔል ልትሰበስበን አልፈለገችም፡፡ ነገር ግን ስራ አስፈፃሚውን ሳትሰበስብ የተናጠል ውሳኔ ማሳለፍ ጀመረች፡፡ ለምሳሌ የስራ አስፈፃሚው ሳይነጋገር ፣ በጀት ሳያፀድቅ አጀንዳ ሳይዝ፣ የስብሰባ ቦታም ሳይመርጥ፣ በራሷ ውሳኔ ወላይታ ሶዶ ከተማ ላይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጠራች፡፡
በህገደንቡ መሰረት ግን ስራ አስፈፃሚው ስለስብሰባው ተወያይቶ መወሰን ነበረበት፡፡ ህገደንቡ ተጥሶ ስብሰባ ተጠርቷል ብለን አቤቱታ አቀረብን ለምርጫ ቦርድ፡፡
ከዘጠኝ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ስድስታችን ነን አቤቱታ ያቀረብነው፡፡ ሁለቱ አባላት በሀሳቡ ያልተስማሙ ናቸው የተባለው ትክክል አይደለም፡፡ ሁለቱ ሰዎች ራሳቸው መፈረማቸውን ለምርጫ ቦርድ አረጋግጠዋል፡፡ በህይወት ያሉ ናቸው ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ ከራሳቸው አንደበትም መስማት ይቻላል፡፡ ከሀሰት ፊርማ ጋር ተያይዞ በፖሊስ ሲፈለግ የነበረም ሆነ የተደበቀ ሰው የለም፡፡ እኔንም ያሳደደኝ ፖሊስ የለም፡፡
ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማገድ አልችልም በማለቱ ስብሰባው ተጠራ፡፡ እኛም ወደ ስብሰባው ገብተን፣ ህገወጥ እንደሆነ ገልፀን ፖሊስ ጠርተን አስበተነው፡፡ ከተበተነ በኋላ ስድስት ሽማግሌዎች ተመርጠው አነጋገሩን፣ ስብሰባው ሌላ ቀን ይሁን ብለን ተስማምተን ወደቤታችን ገባን፡፡
ከዛ ዶ/ር ራሔል የተወሰኑትን አባላት አግባብታ በመሰብሰብ ማታ ላይ ቃለጉባኤ እንዲዘጋጅ አደረገች፡፡ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በአራቱ ሰዎች ላይ እግድ አስተላልፏል ብላ የእገዳ ደብዳቤ ሰጠችን፡፡ ይህ ትክክል አልነበረም፡፡ማዕከላዊ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ አባላትን የሚያግድባቸው በህገደንቡ ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎች አሉ፡፡ እነሱን ያሟላ አይደለም እግዱ፡፡ እኛ የሰራነው ስህተት የለም፣ የአካሔድ ክፍተት ተፈጥሯል፣ የህገደንብ ጥሰት ተፈፅሟል ነው ያልነው፡፡
ከታገድን በኋላ ደግሞ አሁንም ስድስታችን ለሁለተኛ ጊዜ ለምርጫ ቦርድ አመለከትን፣ የተጣለብን እግድ ህገወጥ ነው ብለን ማለት ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም ውሳኔ ሰጠ፡፡
ወላይታ ሶዶ ላይ የተደረገው ስብሰባ ህገደንቡን የተከተለ አይደለም፣ የአባላት እግዱም ህገወጥ ነው ብሎ አነሳው፡፡ በፓርቲው አሰራር መሰረት ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለስ አለ፡፡ ችግራችሁን በስራ አስፈፃሚ ውይይት ፍቱ አለን፡፡ እኛ ደግሞ ሰብስቢን ብለን ጠየቅን ዶ/ር ራሔልን፡፡ አሁንም ፈቃደኛ አልሆችም፡፡
ዶ/ር ራሔል ባፌ ከፓርቲው ህገደንብ በላይ ስላልሆነች ሰኔ 8/2017 ዓ.ም ከዘጠኙ ስራ አስፈፃሚ አባላት ስድስቱ ተሰብስበን የእግድ ውሳኔውን አሳልፈናል፡፡ ወደፊት ማዕከላዊ ኮሚቴው ተሰብስቦ በህገደንቡ መሰረት ሊቀመንበሩን እስኪመርጥ ድረስ እኔን ጊዜያዊ ሊቀመንበር አድርጎ መርጦኛል ስራ አስፈፃሚው፡፡ በስድስቱም ስራ አስስፃሚ አባላት ተመርጫለሁ፡፡
ማህተሙንም ዶ/ር ራሔል ለህገወጥ ተግባር ስትጠቀምበት ስለነበረ ቀይረነዋል፡፡ ነባሩን ማህተም በመጠቀም የተላለፉ ውሳኔዎች አሉ ወደፊት በህግ የሚያስጠይቁ ናቸው፡፡ ዶ/ር ራሔል ከታገደች በኋላ የፓርቲው ህልውና መቀጠል ስላለበት ስራ አስፈፃሚው አዲስ ማህተም እንዲቀረፅ አድርጓል፡፡
ይህን የእግድ ውሳኔ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቀናል፡፡ ለሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትም አሳውቀናል፡፡ ምርጫ ቦርድ፣ የመተዳደሪያ ደንባችንን መርምሮና ፈትሾ ውሳኔያችንን ይቀበላል ብለን እንጠብቃለን፡፡ ቦርዱ የሚሰጠን ውሳኔ የማያረካ ከሆነ የመተዳደሪያ ደንባችንንና ሰነዶቻችንን ሰብስበን ወደ ፍርድ ቤት እንሔዳለን፡፡
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሐላፊዎችን የማገድ፣ የመሾምና የመሻር ስልጣን አልተሰጠውም የሚለው ትክክል አይደለም፡፡ በህገደንቡ አንቀፅ 14/6 ላይ ይህ ስልጣን በግልፅ ተቀምጧል። በዚህ አንቀፅ መሰረት ስራ አስፈፃሚው ሐላፊዎችን ማገድ ይችላል፡፡
ከዚህ በፊት የውስጥ ችግራችንን በውይይት ለመፍታት ሞክረናል በዶ/ር ራሔል እምቢተኝነት ሁሉም ጥረቶች አልተሳኩም፡፡ አሁንም ጉዳዩን በውይይት ለመፍታት ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥላለን፣ ግን ደግሞ የሚሳኩ አይመስለኝም፡፡ ወደ ውይይት የምንመጣ ከሆነ ግን መጀመሪያ እኛንም፣ ሽማግሌዎችንም ይቅርታ መጠየቅ ይኖርባታል፣ ዶ/ር ራሔል ባፌ "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

" አንድ አባት በታጣቂዎች ተገድለዋል። ቤታቸውንም አቃጥለውታል። ሁለቱ ይገደሉ ይኖሩ ገና አልታወቀም " - ዝቋላ አንድነት ገዳም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም የ " ኦነግ ሸኔ ሠራዊት" ያላቸው ታጣቂዎች፤ " ገዳሙን እናጠፋለን " በሚል እቅድ በተደጋጋሚ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። አርብ ምሽት ተከፈተ ባለው ጥቃት፣…
“ የተገደሉት አባት ለ12 ዓመት በብትውና የኖሩ ነበሩ። ቀብራቸው ተፈጽሟል። ጥቃት በተከፈተበት ዋሻ አካባቢ የነበሩ ሰባት አባቶችን ወደ ገዳሙ አምጥተናል ” - ደብረ ከዋክብት ዝቋላ ገዳም
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ባለው ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም “የሸኔ ታጣቃዎች” ባህታውያን አባቶች በሚኖሩባቸው ዋሻዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገዳሙ ማሳወቁ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም፤ “ ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ ግን በርካታ አባቶች ተገደሉ፤ ታግተው ተወሰዱ ” የሚል መረጃ በማህበራዊ ሚዲያው በሰፊው የተዘዋወረ ሲሆን በርካቶችን አሳዝኗል አስቆጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ በሰሞንኛው የታጣቂዎች ጥቃት የተገደሉት ምን ያህል አባቶች ናቸው ? ታግተው የተወሰዱስ አሉ እንዴ ? “ ይገደሉ ይኖሩ ገና አልታወቀም ” የተባለላቸው አባቶች ጉዳይስ ከምን ደረሰ ? ሲል ዛሬ ገደሙን ጠይቋል።
" 'ሁለት አባቶች ተገድለዋል' የሚል መረጃ ተሰራጭቶ ነበር፤ ይህን ያሉን አባቶች አንዱን አባት ከዋሻው ሲገድላቸው ሲያዩ ተደብቀው ቆይተው ሸኔዎቹ ሲሄዱላቸው ተኩስ ወደ ከተከፈተበት ዋሻ ሲመለሱ አንዱን አባት ሞተው አገኟቸው፤ ወደ ሁለተኛው አባት ዋሻ ሲሄዱ ግን አጧቸውና በተከታታይ ጥይት ተተኩሶ ስለነበር እሳቸውንም ገድለዋቸዋል በሚል 'ሁለት አባቶች ሞተዋል' ብለው ነገሩን " ሲል መልሷል።
" ነገር ግን ትላንት ዋሻው ድረስ ሂደን አይተን ስናረጋግጥ የሞቱት አንድ አባት ብቻ ናቸው። ሌላኛው 'ተገደሉ ተብለው የነበሩት አባት ደግሞ ሸኔዎቹን ሲያዩ ከዋሻቸው ወጥተው ተሰውረው ስለነበር በፍለጋ አግኝተናቸዋል" ሲል ገዳሙ ገልጷል።
የጥቃት ቀጠና በነበሩት የገዳሙ ዋሻዎች የነበሩ ሌሎች ሰባት አባቶችን ወደ ዋናው ገዳም አምጥተው ቦታ እንደሰጧቸው፣ የሞቱት አባት ደግሞ አምና ከተገደሉት አራት አባቶች አጠገብ የቀብር ሥርዓታቸው እንደፈጸመ ገዳሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ሟቹ ባህታዊ አባ ኃይለሚካኤል በመጀመሪያ ገዳማቸው ማኀበረ ስላሴ፣ ዲሙ የሚባል በርሃ፣ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እንዳገለገሉ፣ በኋላም በዝቋላ ገዳም ብዙ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ወደ ዋሻ ሂደው 12 ዓመት በብትህውና እንደኖሩ፣ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ/ም በጥቃቱ ሰማዕትነት እንደተቀበሉ ተመላክቷል።
" የታገቱ አባቶች አሉ " ለሚለው መረጃስ እውነተኛ ነው ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ታግተዋል ተብሎ የነበረው በአቅራቢያቸው የነበሩ አባቶች ከተኩስ በኋላ በዋሻቸው ሲያጧቸው ጊዜ የተናገሩት እንጂ የታገተ ሰው የለም " ሲል ገዳሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥቷል።
ሆኖም ግን አሁንም በዋሻ ያሉ አባቶችን፣ ታጣቂዎቹ፣ " 'እዚህ ሸኔ መጥቷል ብላችሁ ብትናገሩ ሙሉ ለሙሉ እንጨርሳችኋለን' በሚል ዝተውቸዋል" ብሎ፣ መንግስትና ህዝቡ ከለላ እንዲያደርግለት ዝቋላ ገዳም በአጽንኦት ጠይቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" ከሟቾቹ አንዱ የሊስትሮ ስራ የሚሰራ ታዳጊ ነው " - ፖሊስ
በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ3 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋዉ የደረሰዉ በሶዶ ከተማ በተለምዶ አጂፕ ከሚባል አከባቢ የተነሳዉ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ - 3 - 63419 ኢት የሆነ የፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪ ከቁጥጥር ዉጪ በመሆን እስከ ማርያም ቤተክርስቲያን አጥር ድረስ በፍጥነት በመምጣት በመንገድ ላይ በነበሩ እግረኞች፣ በስራ ላይ የነበረ ሊስትሮ እንዲሁም ከቆሙ ተሽከርካሪዎች ጋር በመጋጨቱ ነው ብለዋል።
በአደጋዉ አንድ የሃይላክስ ሚኒባስ ረዳት፣ አንድ እግረኛ እና መንገድ ዳር ሊስትሮ ይሰራ የነበረ ወጣት በአጠቃላይ 3 ሰዎች ወዲያዉኑ ሕይወታቸዉ ሲያልፍ 3 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዉ በጤና ተቋም የህክምና ክትትል እየተደረገላቸዉ መሆኑን ተናግርዋል።
የተሽከርካሪዉ የቴክንክ ብልሽት የአደጋዉ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል የገለፁት ፖሊስ አዛዡ አሽከርካሪውም ጉዳት ከደረሰባቸዉ 3 ሰዎች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa