group-telegram.com/tolehaahmed/2758
Last Update:
✨የአላህ ልዩ ሰዎች✨
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«( إِنَّ لِلَّهِ أَهْلِينَ مِنْ النَّاسِ ) قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، مَنْ هُمْ ؟ قَالَ :
( هُمْ أَهْلُ الْقُرْآنِ ، أَهْلُ اللَّهِ وَخَاصَّتُهُ )»
«ለአላህ ከሰዎች መካከል ቤተሰቦች አሉት። "እነርሱ እነማን ናቸው?» ተብለው ሲጠየቁ፤ እነርሱ የቁርኣን ባለቤቶች ናቸው። የአላህ ቤተሰቦች እና ልዩ ሰዎቹ ናቸው።»
(ኢብኑ ማጃህ: 215 ዘግበውታል። አሕመድ: 11870፣ አል-አልባኒም ሰሒሕ ብለውታል።)
وقال الشيخ ابن جبرين رحمه الله :
" الذين يقرؤون القرآن طوال عامهم ، هم أهل القرآن ، الذين هم أهل الله وخاصته
💥 ዑለማዎች በዚህ ሐዲሥ ውስጥ የቁርኣን ሰዎችን የአላህ ወዳጆች እና ልዩ ሰዎች ያሰኛቸው ምንድን ነው? ስለሚለው ሲያብራሩ ቁርኣንን መሐፈዛቸው ወይም መሸምደዳቸው፣ በእርሱ መስራታቸው፣ ጠዋት ይሁን ማታ እሱን ማንበባቸው፣ ልባቸው ከተለያዩ በሽታዎች የጠራ እንዲሁም አላህን በመታዘዝ ህይወታቸው ያሸበረቀ መሆኑ ነው ብለዋል። በተጨማሪም "የአላህ ቤተሰቦች" የሚለው የአላህ ውዴታ እና ልዩ እንከብካቤን የሚያገኙ መሆናቸውን የሚጠቁም መሆኑን ገልፀዋል።
ረመዿን ላይ ከሌላው ግዜ በበለጠ ቁርኣን ለመቅራት ትልቅ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል።
ደጋግመን ለማኽተም እንሞክር። ሌላ ወር ላይ ከሚገኘው አጅር እጥፍ ድርብ የሆነ አጅር ነውና የሚገኝበት።
✒️📖 አላህ አላማቸውን አውቀው ለዚያ ኖረው ከርሱ ዘንድ የተዘጋጀላቸው ምንዳ ከሚቋደሱ ባሮቹ ያድርገን።
ኣሚን!🤲🤲🤲
✍Toleha Ahmed
https://www.group-telegram.com/it/tolehaahmed.com
BY Tᴏʟᴇʜᴀ Aʜᴍᴇᴅ (ጦለሃ አህመድ)️
Share with your friend now:
group-telegram.com/tolehaahmed/2758