Telegram Group Search
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዋንጫው ከሲዳማ ቡና ተነጥቋል፤ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ተሳታፊ ይሆናል " - ፌዴሬሽኑ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ባካሄደው ስብሰባ ላይ የየግባኝ ሰሚ ኮሚቴው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል።

ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው መቻል ስፖርት ክለብ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና  ህጉን ጥሰዋል ብለዋል።

ምን ውሳኔ ተላለፈ ?

- በእግድ ላይ የነበሩ ተጫዋቾች አሰልፈው የተጫወቱባቸው መርሐ ግብሮች በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆኑ

- የሲዳማ ቡና በእግድ ላይ የነበሩ ተጫዋቾችን አሰልፎ ያገኘው የ ኢትዮጵያ ዋንጫ ለወላይታ ድቻ እንዲሰጥ

- ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ተሳታፊ ይሆናል።

- በ2017 የውድድር ዘመን በፕርሚየር ሊጉ የነበሩ ክለቦች በሊጉ እንዲቆዩ (መቐለ 70 እንደርታ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፣ ስሁል ሽረ)

- የ2018 የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በሀያ ክለቦች መካከል እንዲካሄድ ውሳኔ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የንብረት ታክስ በክልሎች በሚቀጥለው በጀት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት ክልሎች የንብረት ታክስን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራሉ " አሉ።

ይህን ያሉት በህዝብ ተ/ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት ላይ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

" ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እዳ እየከፈለ የሚገኘው መንግስት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ገቢ እያገኘ መምጣቱን መጥቷል " ያሉ ሲሆን " ገቢ የማያስገኝ አገልግሎት አክሳሪ ነው " ብለዋል።

በአዲስ አበባ የንብረት ታክስ ክፍያ ተግባራዊ መደረጉን በማስታወስ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት የንብረት ታክስ በክልሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀመራል " ነው ያሉት።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ረቂቅአዋጅ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ መሬትን በሊዝ በባለቤትነት መያዝ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል። የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት " ባለቤት ' ወይም  " ባለይዞታ " የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ይህ " የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት " ወይም " ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት የሚያገኙበትን…
#Ethiopia

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጽድቋል።

በምክር ቤቱ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ " መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም " ብሏል።

የኢትዮጵያዊያንን መብት በማይነካ መልኩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖርያ ቤት ባለቤት በመሆን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ሥራዎች ይሰራሉ ሲል ገልጷል።

የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው።

የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ሲሆን በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ ይሄዳል ተብሏል። #HoPR #FMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትናንት የተሰጠውን የእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች ሌሎች ትምህርት ፈተናዎችን ከወሰዱ በኋላ ይፈተናሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ትናንት በተሰጠው የመጀመሪያ ቀን ፈተናዎች ላይ የተወሰነ የኃይል እና የሲስተም መቆራረጥ አጋጥሞ እንደነበር የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

" ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን በፍጥነት በመፍታት ፈተናውን ማስቀጠል ተችሏል " ሲሉ ተደምጠዋል።

" በሲስተምና በኃይል መቆራረጥ ችግር ትናንት የተሰጠውን የእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች ሌሎች ትምህርቶችን ከተፈተኑ በኋላ ይፈተናሉ " ብለዋል።

Via @tikvahuniversity
" የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ የአማራ ፣የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልል አካባቢዎች ላይ ከችግሩ በፊት የተተከሉ የኔትወርክ ማማዎች ላይ አንዲት እቃ አልተነካብንም "- ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአገልግሎት ፍቃዱን በተረከበ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአገሪቱ ዙሪያ ያሉት የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞቹ ቁጥር 10 ሚሊዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል።

የግል የቴሌኮም አቅራቡ ድርጅት የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት የአራተኛ ትውልድ ኔትወርክ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ከግማሽ በላይ ለሚሆነው ተደራሽ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ለዚህም ከመቶ ሃምሳ በላይ በሆኑ ከተሞች 3,141 የኔትወርከ ማማዎችን መገንባቱን ገልጿል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቺፍ ኤክስተርናል አፌርስ ኦፊሰር አቶ አንዷለም አድማስ "ሳፋሪኮም የመጠንከር የመወዳደር እና ቀና ብሎ የመጓዝ ሂደት ላይ" ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

አቶ አንዷለም አድማስ በዝርዝር በሰጡት ሃሳብም ምን አሉ ?

" 10 ሚሊየን ንቁ(Active) ደንበኞች ማለት ባለፉት ዘጠና ቀናት ውስጥ የደወለ ወይም መልእክት የተቀበለ ማለት ነው።

ባለፉት 90 ቀናት ካልደወለ ወይም ካርድ ካልሞላ ከእኛ ዳታ ቤዝ ውስጥ ይወጣል ከደወለ ወይም ካርድ ከሞላ ወደ ዳታ ቤዛችን ይገባል ስለዚህ 10 ሚሊየን ንቁ ደንበኛ ስንል ገንዘብ የምናገኝበት ትክክለኛ ደንበኛችን ማለት ነው።

3141 ታወሮች በጣራ ላይ እና ግሪን ፊልድ ላይ አሉን የተወሰኑ ሳይቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ነው የምንጠቀመው ለዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ጥሩ ገቢ ያገኛል።

ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞች አዳርሰናል ከዚህ በኋላ ወደ ሌሎች ከተሞችም እንዳረሳለን ለዚህም ከ 1.5 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ኢንቨስት እናደርጋለን።

በአሁኑ ሰአት ከኮሪደር ልማት ጋር በተገናኘ የ Fiber መቆረጥ አለ እሱ መፍትሄ በሚሰጥ መልኩ እየተሰራ ነው።

በመላ ሃጋሪቱ ነው የምንንቀሳቀሰው እቃዎች ተጭነው ነው የሚሄዱት በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ እንደማንኛውም ሰው እክል ሊገጥመን ይችላል ነገር ግን የተጋነነ ነገር አለ ብዬ አላስብም።

የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ የአማራ ፣የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልል አካባቢዎች ላይ ከችግሩ በፊት የተተከሉ የኔትወርክ ማማዎች ላይ አንዲት እቃ አልተነካብንም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ የተገደሉት አባት ለ12 ዓመት በብትውና የኖሩ ነበሩ። ቀብራቸው ተፈጽሟል። ጥቃት በተከፈተበት ዋሻ አካባቢ የነበሩ ሰባት አባቶችን ወደ ገዳሙ አምጥተናል ” - ደብረ ከዋክብት ዝቋላ ገዳም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ባለው ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም “የሸኔ ታጣቃዎች” ባህታውያን አባቶች በሚኖሩባቸው ዋሻዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገዳሙ ማሳወቁ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም፤…
" የግፍ አገዳደል ነው የተፈጸመው ፤ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ አቃጥለውታል ፤ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች ተፈናቅሏል " - የሟች የቅርብ ሰው

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የሰባት ልጆች አባት ካህን በአሰቃቂ ሁኔታ በ "ሸኔ" በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ግድያው አሰቃቂ መሆኑን፣ ሟች ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ከቤታቸው በታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ ባለቤታቸውም በተመሳሳይ ከተገደሉ አመት ከስድስት ወራት እንዳስቆጠሩ፣ የ11 ዓመት ልጃቸውም በጥይት ተመትቶ ካህኑ በጥልቅ ሀዘን አንደነበሩ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

አንድ የካህኑ የቅርብ ሰው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ፣ " ካህኑን እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ነው የገደሏቸው " ሲሉ በተሰበረ ልብ ገልጸዋል።

" አካላቸውን አፍሰን ነው ይዘን የመጣነው፤ ሰዎች በቄየው ሄደው ለቃቅመው ግማሽ አስከሬናቸው ግማሽ አካላቸው በሮቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሁድ አርፏል፤ ግማሹን ደግሞ ትላንት ለቃቅመው ነው የቀበሩት። ለመናገርም ይዘገንናል " ሲሉም አክለዋል።

" ካህኑን ' እባካችሁ ቦታውን ለቃችሁ ወደ ከተማው ኑ ብንላቸውም ' ቤተክርስቲያኑን ለቅቄ አልሄድም የሆነው ይሁን ' ብለው ሳይመጡ ቀሩ " ብለው፣ " ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ቤተ ክርስቲያን ውለው ማታ ሲገቡ ጠላት ቀድሞ ቤታቸውን ምሽግ አድርጎ ጠብቆ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ ገደላቸው " ሲሉም ተናግረዋል።

" የሟች ወንድም ደውሎ መከላከያ እንዲደርስ አደረገ፣ ካህኑ ግን ተገድለው ተገኙ፣ የግፍ አገዳደል ነው " ያሉት እኝሁ አካል፣ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ እንዳቃጠሉት፣ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች መፈናቀሉን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል እናት ፓርቲ በሰሞነኛው የአማራ ክልል መቃ የተፈጸመው ግድያ እና በኦሮሚያ አርሲ ስለተፈፀመው ግድያ መግለጫ አውጥቷል።

" ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ልዩ መቃ በታጣቂዎች እና በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች መካከል በተነሳ ግጭት መንገደኛና የእርዳታ ግብአት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ በደረሰ ድንገተኛ ተኩስ በርካታ ሹፌሮችና የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ከአካባቢው ምንጮች አረጋግጠናል " ያለው ፓርቲው " በአጠቃላይ በጥቃቱ አንድ መቶ በላይ ሰዎች እንደተገደሉና ከነዚህም ውስጥ አሥራ ስድስት የሚሆኑት ሾፌሮች መኾናቸውን ሰምተናል " ብሏል።

" ሁኔታው ከአእምሮ በላይ ነው፤ ሟቹ ከመብዛቱ የተነሳ አስከሬን በኤክስካቫተር ጭምር ሲነሳ ተመልክተናል ይላሉ እማኞች " ሲል ገልጿል።

" በሌላ በኩል ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ካህን ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ በታጣቂ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላውቸውን ከአካባቢው ምንጮች ማረጋገጥ ችለናል " ብሏል።

" ያለፉትን 7 ዓመታት ኢትዮጵያ የንጹሃን ደም ጎርፍ ሆናለች ቢባል ከእውነይ የራቀ አይደለም " ያለው ፓርቲው " በተለይ የሃይማኖት አባቶችና ሾፌሮች ግድያ የቀን ተቀን ዜና ነው " ሲል ገልጿል።

" ሞቱንም ከማለባበስ በዘለለ ከእቁብም የሚቆጥረው የለም። የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዓይነት ተቋማት እንኳን በየቀኑ የሚፈሰውን የካህናትና ቤተሰባቸውን ደም ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ድምጽ አያሰሙም " ሲል ወቅሷል።

" ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም የየቀኑ መረጃ ጠረጴዛው ላይ ደርሶት እያየ እንዳላየ ሆኗል። ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይሄ ጉዳያቸው አይደለም " ሲል ገልጿል።

" ከተወሰኑ የማኅበራዊ ሚዲያ  ተሳታፊዎች በስተቀር አጠቃላይ ሚዲያው በፍርኃት ተሸብቦ እማኝ አናግሮ ማቅረብ ዳገት ሆኖበታል፡፡ የንጹሓን ደም ግን አሁንም በየቀኑ ይጣራል" ብሏል።

ፓርቲው " ጭፍጨፋውን በጽኑ እናወግዛለን ለሞቱት እረፍተ ነፍስን፣ ለሟች ቤተሰቦችና ለየአካባቢዎቹ ማኅበረሰብ ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔ " ተገቢና ህግን ያልተከተለ ውሳኔ " ሲል ተቃወመ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ እንዲመለስ ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

ይህ ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ውሳኔውን " ተገቢነት የለሌው ውሳኔ ነው። ውሳኔው እጅግ አሳዝኖናል " ብሏል።

" ብርቅዬ የክለባችን ተጫዋቾች በጨዋታ ሜዳ የገጠሙትን ሁሉንም ከጨዋታ ብልጫ ጋር በማሸነፍ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ ማሸነፉ የአደባባይ ምስጥር ነዉ " ሲል ገልጿል።

" ይሁን እንጂ ' የሊግ ካምፓኒ ያወጣውን የፋይናንስ ደንብ አላከበራችሁም ' በሚል በክለቡና በተጫዋቾች ላይ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ቢባልም ክለቡ  ያነሳዉ ዋንጫ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ በ48 ክለቦች መካከል የተደረገው መሆኑ ዕሙን ነው " ብሏል።

" የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የታገዱ ተጫዋቾችን አሰልፎ ከሆነ በጥሎ ማለፉ ያሸነፋቸው ክለቦች በሙሉ ፎርፌ አግኝተው ጉዳያቸው እንደገና መታየት አለበት እንደ ማለትም ይሆናል " ብሏል።

" እርስ በርስ የሚጣረሱ ሀሳቦችን በማገናኘት ውጤቱን ለመቀማት መሞከር  ተገቢና ህግን የተከተለ ውሳኔ ነው ብለን አናምንም " ሲል ቦርዱ አሳውቋል።

" ፌዴሬሽኑ ዉሳኔውን ከህግጋቱ ጋር በማገናዘብ እንደገና እንዲያጠነዉ ቅሬታችንን እናሰማለን " ብሏል።

" ህዝባችን በፌደሬሽኑ ውሳኔ የተከፋ ቢሆንም የአፊኒ ባህል ያለው ታላቅ ህዝብ ስለሆነ ክስተቶችን በመረጋጋት መርምሮ በተገቢው እንዲያጠነውና  ሂደቱን  በትዕግሥት እንዲጠባበቅ በአክብሮት እየጠይቃል " ሲል ገልጿል።

" የተነፈግነው ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ጉዳዩን እስከ ፊፋ ገላጋይ ፍርድ ቤት ድረስ በይግባኝ ወስደን ለጉዳዩ  ተገቢው እልባት እስኪሰጥ ድረስ የክለቡ ቦርድ ቁርጠኛ መሆኑን እናረጋግጣለን " ሲል አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔ " ተገቢና ህግን ያልተከተለ ውሳኔ " ሲል ተቃወመ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ እንዲመለስ ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ይህ ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ውሳኔውን " ተገቢነት የለሌው ውሳኔ ነው። ውሳኔው እጅግ አሳዝኖናል…
" ተክሰናል ፤ ሕዝቡ በልዩ ልዩ መንገዶች ደስታዉን እየገለፀ ነዉ " - የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ

ዛሬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያስተላለፈዉን ዉሳኔ ተከትሎ የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ " የኢትዮጵያ ዋንጫን " ለወላይታ ዲቻ ይመልሳል ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድንም በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ #ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል።

ይህን የፌደሬሽኑን ዉሳኔ ተከትሎ የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች በአደባባይ ደስታቸዉን የገለፁ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላላ ከበደን ጨምሮ የክልሉና የወላይታ ዞን አመራሮች " የእንኳን ደስ ያላችሁ " መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገርናቸው የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ " ዉሳኔዉ በእግር ኳሱ ዘርፍ ተስፋ ሰጪና ለወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ትልቅ ደስታን የፈጠረ ተገቢ ዉሳኔ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ተክሰናል " ያሉት ስራ አስኪያጁ " የዉሳኔዉን አፈጻጸም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በሚያስቀሚጠዉ ዕቅድ መሰረት ተፈፃሚ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
2025/07/02 00:03:02
Back to Top
HTML Embed Code: