Telegram Group & Telegram Channel
🛑 ፃማ 🛑

ክፍል ስድስት

ባሰበችው ቁጥርም ይሄ ንግግሩ ይገርማት ነበር። አሁን ግን ነገሮች እየተገለጡላት መጡ። "አፍቅሮኝ ነበር ማለት ነው" እራሷን ጠየቀች። ለዚህ ነው ወደ ንቅናቄው መግባቴን የተቃወመው? የመጨረሻውን ስብሰባ እንዳትካፈል ያላደረገው ጥረት እንዳልነበር ትዝ አላት። በተኩሱ መሀል መጥቶ ጎትቶ ሲወስዳት  ዐይኑ ላይ ይነበብ የነበረው ፍቅር ከየት እንደመጣ በዛን ጊዜ ለማወቅ ተቸግራ ነበር። ግን ለምን አልነገረኝም? እኮ ለምን? ልቧ በሀዘን ደምቷል።
      ታክሲው ካዛንቺስ ደርሶ ሲቆም ወረደች። የተባለው አድራሻ ጋ ለመድረስ ብዙ ሰአት አልወሰደባትም። አልአዛር ከተባለው ሰው የጥያቄዎቿን መልስ እንደምታገኝ ስለገመተች አድራሻው ላይ የሰፈረውን ቤት ለማግኘት ተቻኮለች። መለስተኛ ሆኖ የተደላደለ ኑሮ ሊኖርበት የሚችልበት ሰፊ ቤት አጠገብ ስትደርስ 'ይሄ መሆን አለበት' አለች በሆዷ። የበሩን መጥሪያ ተጫነችው። የሷን መምጣት በመጠባበቅ ላይ የነበሩ እስከሚመስላት ድረስ በሚያስደንቅ ፍጥነት የቤቱ በር ተከፈተ።
       ከፊት ለፊቷ የቆመውን ሰው ስታይ ደነገጠች።ቁርጥ እዮብን። ልቧ በድንጋጤ ምቷን ጨመረች። እንድትገባ በሩን ወለል አድርጎ ከፈተላት። ምንም ሳታመነታ ወደ ውስጥ ዘለቀች። ጊዜ ሳይፈጅ 'አልአዛር' ብሎ እጁን ለትውውቅ ዘረጋ። 'ብሌን' አለች ነገር ግን ራሷን ማስተዋወቅ አስፈላጊ መስሎ አልታያትም። ወጣቱ ካወቃት የቆየ ይመስላልና።
     አልአዛር ገና ብሌንን እንዳየ የወንድሙ እንደዛ በፍቅር መሰቃየት ተገለጠለት። ማንስ ቢሆን ከዚች ቆንጆ የፍቅር ወጥመድ ያመልጣል ሲል አሰበ። ሰውነቷ በድካምና በዱላ የተጎዳ ስለሚመስል ዛሬ ወንድሙ በአደራ ያስቀመጠውን ወረቀት ቢሰጣት ሊጎዳት ይችላል ብሎ ስለጠረጠረ ወረቀቱን ነገ ሊያሳያት ቀጠሮውን አራዘመ።
      ቤቱ የአንድ ወንድ መኖሪያ ብቻ አይመስልም። በፅዳት ተስተካክላ የተዘጋጀችው ሳሎን የሴት እጅ የግድ ያረፈባት መሆኑን ገመተች። እንደገባች ከፊቷ የነበረው ሶፋ ላይ ተዘረረች። ድካሙና ረሀቡ ተደራርበው አቅም አሳጥተዋታል። የልቧ ሀዘን ደግሞ ይበልጥ ሰውነቷን ጎዳው። "ወንድሙ  ነው?" እንዴት ወንድም እንዳለው ለማንም ሳይናገር ኖረ? ግራ ገብቷት ራሷን ጠየቀች።
      አልአዛር ፈጠን ብሎ የሚበላ አቀረበላት። ምግቡን ከፊት ለፊቷ ቀርቦ ስታየው የረሀብ ስሜቷ ተቀሰቀሰ። በልታ እንደጨረሰች ወጣቱ በአበላል ሁኔታዋ መገረሙ አይቀርም ብላ አሰበች። እሱ ግን የተረዳት ይመስላል።
       ራሷን በድንጋይ እንደተመታ ሰው ይፈልጣታል።መቋቋም እስኪያቅታት ድረስ ህመሙ እየጨመረ ሄደ። የራስ ምታት መድኃኒት ይኖርሃል? አለች ወጣቱን እያየች። ወደ መኝታ ክፍል ሄዶ ሁለት መድኃኒቶችን ይዞ መጣ። ይኸውና የራስ ምታት መድሀኒቱ ብሎ አንዱን ወደ እጇ አቀበላት። "ይሄ ደግሞ የእንቅልፍ ኪኒን ነው።" ብዙ እረፍት ያገኘሽ አትመስዪም አላት ፊቷን እያየ። ብሌን አላንገራገረችም ሁለቱንም መድኃኒቶች ዋጠቻቸው። የእንቅልፍ መድኃኒቱ ለመስራት ጊዜም አልወሰደበትም። ጭንቅላቷን ሶፋው ላይ አስደግፋ ለመተኛት ሞከረች። አልተመቻትም። ወጣቱ ሶፋው ላይ ሙሉ ለሙሉ ወጥታ እንድትተኛ ትራስና ወፍራም ጋቢ ከመኝታ ቤት አምጥቶ ሰጣት። መድኃኒቶቹን  መኝታ ቤት አስቀምጦ እስከሚመለስ እንቅልፍ ወስዷታል።
      ከሶፋው አጠገብ ቆሞ ሶፋው ላይ የተኛችሁን ብሌንን በአድናቆት ይመለከታታል። ሁለመናዋ ልብን ይማርካል። በብዙ ነገር ራሳቸውን አስጊጠው ከሚመለከታቸው ሴቶች ይልቅ በሷ ውስጥ ከጉስቁልናዋ በላይ ጎልቶ የሚታየው አፍዝዞታል። እጁን ዘርግቶ.......
✍️✍️✍️✍️ይቀጥላል...
@yabsiratesfaye ለወዳጅ ለዘመዶ ያጋሩ

group-telegram.com/yabsiratesfaye/121
Create:
Last Update:

BY አርያም - ARYAM

❌Photos not found?❌Click here to update cache.

Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260

Share with your friend now:
group-telegram.com/yabsiratesfaye/121

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

False news often spreads via public groups, or chats, with potentially fatal effects. Recently, Durav wrote on his Telegram channel that users' right to privacy, in light of the war in Ukraine, is "sacred, now more than ever." As a result, the pandemic saw many newcomers to Telegram, including prominent anti-vaccine activists who used the app's hands-off approach to share false information on shots, a study from the Institute for Strategic Dialogue shows. Right now the digital security needs of Russians and Ukrainians are very different, and they lead to very different caveats about how to mitigate the risks associated with using Telegram. For Ukrainians in Ukraine, whose physical safety is at risk because they are in a war zone, digital security is probably not their highest priority. They may value access to news and communication with their loved ones over making sure that all of their communications are encrypted in such a manner that they are indecipherable to Telegram, its employees, or governments with court orders.
from ms

Telegram አርያም - ARYAM
FROM American