Telegram Group Search
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መልካም ጥርጣሬ
.....

ልጅቷ በኹለት እጆቿ ቱፋሕ ይዛለች። እናት ከኹለቱ ቱፋሖች አንዱን ትሰጣት ዘንድ ጠየቀቻት።

ልጅቱም አሰብ አድርጋ በቀኝ እጇ የያዘችውን ቱፋሕ ግምጥ አድርጋ ማለመጥ ጀመረች።

እናት በግራ እጇ የያዘችውን ትሰጠኛለች ብላ ስትጠብቅ፣ልጂቱ ቀጥላ በግራ እጇ የያዘችውን ደግሞ ገምጣ ማላመጥ ጀመረች።

ይህን ያየች እናት በልጇ ተግባር ተናዳ፣ "ለእኔ ለእናትሽ አንዱን መስጠት እንዴት ከበደሽ? አንቺ ከመች ጀምሮ ነው በዚህ ልክ ስስታም የኾንሽው?..." ብላ ኃይለ- ቃል ጨማምራላት እየተመናጨቀች ጥላት ከክፍሉ ወጣች።

ብዙም ሳይቆይ ልጅቱ " እናቴ ይህንን እንኪ" እያለች ከኋላ ትከተላት ጀመር።

እናቲቱ የበለጠ ንድድ ብላ "የበላሽለትን ነው እንዴ የምትሰጭኝ? ትንሽ አይከብድሽም?..." ብላ አጉረጠረጠችባት።

ልጂቱም " የትኛው እንደሚጣፍጥ ስላላወቅኹ ነው እንደጠየቅሽኝ ልሰጥሽ ያልፈለኩት፤ ይኽኛው የበለጠ ስለሚጣፍጥ ይህንን ውሰጂ" ስትላት፣ እናት በራሷ እፍር ብላ በልጇ አስተሳሰብ ተደንቃ ተቀበለቻት።

እናም ወዳጄ አንድ ሰው በተመኩሮውም ኾነ በዕውቀቱ የትም ይድረስ በመልካም ጥርጣሬ ካላጌጠ ሲከፍቱት ተልባ መኾኑ አይቀርምና ይታሰብበት።

ፈረንጆቹ "Don't judge a book by its cover _ የመጽሐፉን ሽፋን ዓይተህ ስለመጻፉ አትፍረድ" ይላሉ።

መረሳት የሌለበት አላህ በቃሉ እጅግ በጣም ተጠንቀቁ ያለን ክፉ ጥርጣሬን ነው፦

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِنَ الظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ الظَّنِّ إِثْمٌ وَلَا تَجَسَّسُوا وَلَا يَغْتَبْ بَعْضُكُمْ بَعْضًا...

https://www.group-telegram.com/boost/E_M_ahmoud.com
ኺንፊሻር
....

በዐረቦች ተረተ አንድ ኹሉን ዓዋቂ መሐል ጠሊቅ ነኝ የሚል ሰው ነበር አሉ።

ይህ ሰው ስለተጠየቀው ነገር ኹሉ ዐውቃለኹ እያለ ከጥንት ስነ-ግጥምም ከስነ-ቃልም ጭምር ምሳሌ እያደረገ ይመልስ ነበር።

አንድ ቀን የአካባቢው ሰዎች እርስ በርስ " ይህ ሰው እንዴት ይህንን ኹሉ ነገር ሊያውቅ ቻለ? ትላንት ከኛ ዘንድ ሲመላለስ የነበረና በዕድሜም ታናሻችን የኾነ የምናውቀው አይደለምን?" ተባባሉ።

ቀጠሉናም " ዕውነተኛ መኾኑን ለማወቅ አንድ የኾነ ቃል እንፍጠርና ይህ ምንድን ነው ብለን እንጠይቀው፤ ዐውቃለኹ ብሎ ከመለሰ ውሸታም መኾኑን እናውቃለን። እናጋልጠዋለንም።" ተባባሉ። ተስማሙም።

ከዚያም ሰውየው የሚያስተምርበት ቀን ላይ ሄደው ከፊቱ ተኮለኮሉ። ለጥቀውም "ኺንፊሻር" ምንድነው ብለው አዲስ የፈጠሩትን ቃል ጠየቁት።

ሰውየው አሰብ አደረገና " ኺንፊሻር ማለት የእጽዋት ዓይነት ነው። ቅጠሉ የዚህ ዓይነት ነው። ግንዱ ደግሞ ...ወዘተ" እያለ አናቶሚውን ዘረዘረው።

አስከተለናም ከጃሂሊያ ግጥሞች ማሰረጃ ለማድረግ የራሱን ስንኝ ፈጠረ፦

لقد عَقَدَت محبتُكم فؤادي

كما عقد الحليبَ الخنفشار

"ኺንፊሻር ወተትን እንደሚያረጋ
የናንተም ፍቅር ልቤን አረጋጋ"

ካለ በኋላ ከሐዲስም ጭምር ማስረጃ ለማምጣት ሲያኮበኩብ " በሌላው ላይ የዋሸኸው ይበቃል፤ በመልክተኛው ላይ ስትዋሽ መስማት አንፈልግም" ብለው ጮኸው ተነሱ። ሰውየውም ውሸታም መኾኑ ታወቀ።

ከዚያ ቅጽበት በኋላ ሰውዬው ከልቡ ውሸታም እንደኾነና በዙሪያውም ያሉ ከዕውቀት የተጣሉ የሰሙትን በጥሬው አምነው የሚቀበሉ መኾናቸው ይፋ ኾነ።

ወዳጄ ይህንን ምሳሌ ከዛሬዎቹ ኹሉን እናውቃለኖች ጋር አገናኙት።

ለኛ ትምህርት ይኾነን ዘንድ ደግሞ፦

"وَلا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْؤُولًا"

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ሶስት ነገራትህን ሸሸግ አድርግ
....

ኢብኑል ጀውዚ ስስት ነጋራትኽን ሸሸግ አድርግ ይላል።

፩ኛ) ንብረትኽን

ይህን ያህል ገንዘብ አለኝ፤ይህን ያህል እነገሌ ዘንድ ደግሞ በብድር የተወሰደ አለኝ ወዘተ...ማለት ታይታን ወይም ምቀኝነት ስለሚያስከትል የንብረትኽን መጠን አታውራ ይላል።

፪ኛ) ዕቅድኽን

ዕቅድ በሰውዬውና በአላህ መካከል መሸሸግ ያለበት ነገር ነው።

ምናልባት እዚህ ጋር የጋራ ዕቅድ፣ ወይም የመስራ-ቤት ራዕይ እንዳልኾነ ይሰመርበት።

ኢብኑል ጀውዚ ሊነግረን የፈለገው ኹሉም መድረስ የሚፈልግበት የሕይወት ግብና መዳረሻ ነጥብ አለው፤ ያንን ነጥብ ለራሱና ለአላህ ይተወው የሚል ነው።

አንድ ሰው የሕይወት ግቦቹን የባቄላ ወፍጮ አድርጎ በየደረሰበት መበተኑ በአላፊ አግዳሚው አፍ እንዲገባ ከማድረግ በዘለለ የሚያተርፈው ሒስድን ወይም ተጠግቼ ልብላ የሚሉ ስግብግብ አፎችን ብቻ ነው።

፫ኛ) የሕይወት መርሆዎችኽን
....

ከኢስላማዊ ርዕዮት በዘለለ አንድ ሰው ከራሱ ተሞክሮ የሚከተላቸው የሕይወት ፍልስፍናዎች / አካሄዶች ሊኖሩት ይችላል።

ፍልስፍናው ለራሱ ሰርቶለት ለሌላው ግን ላይሰራ ስለሚችል ርዕዮቱን ቢደብቅ ይሻላል።

ማንም ሰው በግል ሕይወቱ ምከረኝ ካላለኽ በስተቀር ልምከረው ብለኽ አትጣደፍ።

ስለ ራስኽም ቢኾን ብዙ ከማውራት ተቆጠብ።

አንዳንዶች ሰዎች ስለነርሱ መስማት እጅጉን የሚጓጉ፣ ከልብ የሚያስደስታቸው የልጅነታቸው የእናታቸው የእሹሩሩ እንጉርጉሮ ይመስላቸዋል?

ወዳጄ ጉዳዩ ወዲህ ነው! ስለ አንተ ኹሉንም ነገር መስማት የምትወደው ብቸኛዋ ሰው እናትኽ ብቻ ናት።

ትላንት ከነምናምናችን ስማ ያጎረሰችንና ጀርባዋን እንዳይኾን ያደረግናት በሕይወት እስካለች ድረስ ስለ እኛ ምኑንም ሳትጠየፍ ኹሉንም ማወቅና መስማት ትወዳለች።

ከእናትህ ውጪ ያለ የትኛውም ሰው ራሱን የሚያዳምጥበት እንኳ በቂ ጊዜ ሳይኖረው ያንተን የጨረባ "ዘፈን" ሰለምን እንዲያዳምጥ ትፈርድበታለኽ?!

ወዳጄ ተቸገርኽ ከኾነ መቸገርኽ ለራስኽ ነው ! የኾነ ነገር መስራት ፈለግኽ እንደኾነ ለራስኽ ነው! ...በጥቅሉ አፍህን ከፍተኽ ላውራኽ የምትለው ኹሉ የኋላ ኋላ ቢታዘብኽ እንጂ ዘንጋዳ ዘግኖ አይሰጥኽም። ለአንተ ከሚሰጥኽ ይልቅ ቢበትነው እጅግ ይወዳል።

ወዳጄ ይህችን "ኹሉም ለራሱ ነው!!" የምትለውን የዱንያም የአኺራም መርሆን ልብ ይበሉ።

ዱንያ ላይ ኹሉም ለራሱ ብቻ ነው!!!! አኺራ ላይም ኹሉም ስለ ነፍሱ ብቻ ተሟጋች ነው።

لكل امرئ منهم يومئذ شأن يغنيه

ኢብኑል ጀውዚን (ዐለይሂ ረሕመቱላህ) ይህችን ውድ ነገር ስለነገረን አመሰገንን፦

اكتم عن الناس ذهبك وذهابك ومذهبك
....
ማብራሪያዎቹ የግሌ ናቸው
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ነብይ ለመኾን
….

ነብይነት በአላህ የሚሰጥ የምርጫ ጉዳይ ያልኾነ በረከት ነው፡፡ በአንጻሩ እዝች ሐገር ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮ የቆለመመው ኹሉ እየተነሳ ነብይ ነኝ ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

በአዲስ ሃይማኖት ስም ብቅ ብሎም ነብይ ነኝ ያለና እምብዛም ያልተሳካለት ሰው እንዳለ ድፍን ሐበሻ ያውቃል፡፡

ግለሰቡ ዛሬ ላይ ጭራሽ በሚዲያ ገብቶ ሲዘላብደው የቆየው “ሕልምና” የከፊል ደመናማ “ትንቢት” እንዳላዋጠው ይልቁነም ንብረቱን ኹሉ በዛ ምክንያት እንዳጣ እያወራ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ ሜዳ ላይ ለየት ባለ ማሊያ የተሰለፉ የዛ ሰፈር ወጠምሻዎች ደግሞ ከአፍሪቃ ወንድሞቻቸው ቀድተው ሕዝቤን በአጓጉል ተስፋ እየሞሉ ሲዘርፉ ተው የሚል ሕግ አለመኖሩ እጅግ ያስተዛዝባል፡፡

ይዘገያል እንጂ አንድ ቀን በአደባባይ የሕግ እራት መኾናቸው በፍጹም አይቀርም፡፡ ለዚህ ትልቁ ማሳያችን አርኣያዎቻቸው ጆሹዋና ቡሽሪ ናቸው፡፡

ጆሹዋ ባዕድ /ሰይጣን አምላኪ የነበረና በራሱ ተከታዮች በስተመጨረሻ የተጋለጠ በበጎች መሐል የሚመላለስ ተኩላ ነበር፡፡ ቡሽሪ ደግሞ ጭራሽ በአየር ላይ እሄዳለኹ ይል የነበረ- መሄዱ ምን ትርጉም እንዳለው ግልጽ ባይኾንም- ከሰማይ እሳት አዛለኹም ብሎ በተራ ግለሰቦች እንዴት ነገራትን እንዲቀጣጠሉ ያደርግ እንደነበር የተጋለጠ ፍልጥ ጅል ነበር፡፡

ቡሽሪ ከደቡብ አፍሪቃ ለቆ አኹን ላይ ማላዊ እንደሚገኝና በዘረፈው ገንዘብ ትላላቅ ቢዝነሶችን እንደጀመረ ይነገራል፡፡

ነብይነት ወይም ነቡዋ (النبوة) የሚለው ቃል ነብእ (النبأ) ከሚለው ስረወ-ቃል የተፈለቀቀ ነው፡፡ ትርጉሙም ዜና ማለት ሲኾን በተጨማሪም ከፍ ማለት ወይም መላቅ የሚልም ትርጉም አለው፡፡

ነብይም ኾነ ረሱል ኹለቱም ከአላህ የተወረደላቸውን መልዕኮታዊ ራዕይ የሚያስተምሩ ሲኾኑ ብዙዎቹ የኢስላም ልሒቃን እንደሚስማሙበት ልዩነታቸው ነብይ የቀደመውን ስርዓተ-መለኮት (ሸሪዓ) የሚያሰተምር ሲኾን ረሱል ደግሞ በአዲስ ስርዓተ-መለኮት የሚነሳ ነው፡፡

ለመኾኑ አንድ ግለሰብ ነብይ ለመኾኑ ማስረጃዎቹ ምንድን ናቸው? እንደ አላህ ፈቃድ ቀጣይ የምንመለከተው ርዕስ ይኹን!
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
አወወ ይህንን ቻናል እናስተዋውቅልኽ ያላችኹኝ ሰዎች በመጀመሪያ አላህ ምንዳችኹን ይክፈል እላለሁ።

ቀጥዬ ቻናሉ ለዛ በቂ ነው ካላችኹ አስተዋውቁት ግን የኔ ግፊት አይኹን።

የተከታዬ ቁጥር ጨመረም ቀነሰም ማለት የፈለግኹትን የምልበት ቤቴ ስለኾነ ከመጻፍ አልቦዝንም።

ላለፉት ስምንት ዓመታት የዚህ ቤት እድርተኛ ከአንድ ሺህ ከምናምን ዘሎ አያውቅም።

ግን ማስታወቂያም ኾነ እዚህ እናድርሰው የሚል ቻሌንጅ ከትቤ አላውቅም። አለከትብምም።

የሻ ሰው ሐሳቤ ተስማማውም አልተስማማውም አብሮኝ ይዝለቅ። የኮሰኮሰው ደግሞ ሊሰናበተኝ መብቱ ነው።

ለማንኛውም ወዳጄ የማስተዋወቅና የማዳረሱን ምርጫ ለእርሶ ትቻለኹ።

🙏አመሰግናለሁ 🙏

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የምስራች ከቁርአን ቀጥሎ ትልቁን ኪታብ ሶሂሁ አልቡኻሪን መቅራት ለምትፈልጉ ሁሉ

ለመመዝገብ


አኅት ዘሃራ ሙስጠፍን፦ https://www.group-telegram.com/Zhara_mustefa
እኅት ዝሃራ ኢማምን ፦ @Zehar678
ያናግሩ
Eliyah Mahmoud
راقـ ـصات حول مجسم الكعبة وشيخ سعودي يبكي على انتهاك حرمات الله في موسم ... https://youtube.com/watch?v=YjA1kGMy1V8&feature=shared
በዚህ ተንቀሳቃሽ እንደሚደመጠው በሪያድ የታየውን ትርዒት አስመልክቶ የስዑዲ ሼኽ አንብቷል።

የካዕባን ምስል በአስመሳስሎሽ (አኒሜሽን) መድረክ ላይ አዘጋጅተው የተራቆቱ እንስቶች ፋሽን ሾው ሲያደርጉ ይታያል።

ይሕ ምን ማለት እንደኾነ ለማንም ግልጽ ነው። በዚህ ልክ ሙስሊም ነን በሚሉ አካላት ኢስላም ሲረክስ ማየት ብናኝ ኢማን ላለው እጅግ የሚሰቀጥጥ ነው።

ወዳጄ በግሌ በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ መጻፍ ፈልጌ ሳይኾን ጉዳይ እንደ ሙስሊም ኹላችንንም የሚመለከት ስለኾነ ብቻ ነው።

ካዕባ ለኹሉም ሙስሊም ቂብላ ነው። በዚህ ልክ በማንም ቅጥረኛ ሲፌዝበት ማየት አግባብ ነው ብዬ አላምንም።

ተው ይሉ የነበሩ ዱዓት ታስረዋል። ዛሬ ላይ እነዛ የታሰሩትን ደግፎ ለምን ታሰሩ? ያለ ስም ይሰጠዋል።

ቢን ሰልማንን ያልደገፈ ኹሉ በኾነ ስልቻ ውስጥ ተጨምሮ ይወቀጣል።

ወዳጄ ኢስላም ግለሰቦች ሳይኾኑ ኢስላም ኪታብና ሱና ነው። የትኛውም አካል በኪታብና ሱና ይለካል። ካለፈ ያልፋል ከወደቀም እንዲኹ!!!

እነዚህ ኹለት ዋቢዎቻችን ላይ ቆመን የቢን ሰልማን መንግሰትን እንመዝነው ወይም የሚመዝኑ ዑለሞችን እናዳምጥ።

እየኾነ ያለው ነገር የኢስላምን ቅዱስ ምድር በምዕራባዊው ሰይጣናዊ ርዕዮተ መበከል ብቻ ነው።

እንደው ስለ ዕውነት እናውራና ከሰለፎች አንዱ ቢኖር ይሕንን መረንነት ያደንቀው ነበርን ወይስ እስከ ሕልፈቱ ድረስ ያወግዘው ነበር?!

اللهم دمِّر المعتدين، أعداءك وأعداء الدين


https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
2024/11/18 08:37:35
Back to Top
HTML Embed Code: