#JigjigaUniversity
“ ፈተና አልፈን ቴምፖ እየጠበቅን ባለንበት ድጋሚ በሰኔ ትፈተናላችሁ ተባልን በሰላሚዊ ሰልፍ ስንጠይቅ። የተመታ ተማሪ አለ ” - የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን
🔴 “ የኛም የመጀመሪያ ጥያቄያችን ነው። እየተከራከርን ነው ” - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት
➡️ “ ጉዳዩ ‘ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር ሆልድ ስላደረገ ነው" - የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተና አልፈው፣ ቴምፖ እየተጠባበቁ ባሉበት ወቅት ቴምፖ ተከልክለው ‘በድጋሚ ትፈተናላችሁ’ በመባላቸው ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።
ምሩቃኑ በዝርዝር ምን አሉ ?
“ ሪኤግዛም ተፈትነን አልፈናል። ሁለት ወራት ከቆዬን በኋላ ባላወቅነው ነገር ‘ቴምፗችሁ ታግዷል፤ ተሰርዟልና ድጋሚ ሪኤግዛም ትወስዳላችሁ’ ተባልን።
ሁለት ወራት ሙሉ ምላሽ አላገኘንም ነበር። ‘የተመረቃችሁ ተማሪዎች ከግቢ ውጡ’ እያሉ ጫና ሲፈጥሩብን ተሰብስበን ስንጠይቅ ‘ሪኤግዛም ነው የምትወስዱት’ አሉን። ‘ፈተና ተኮራርጃችኋል፣ ከፍተኛ ውጤት መጥቷል ' ነው ነገሩ።
ቢሮ ለመጠየቅ ስንሄድም በፓሊስ አስከብቦ ድብደባ የተፈጸመበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። የተመታ ተማሪ አለ። የሄድነው ለመጠየቅ ነው፣ ያልተገባ ነገር አልጠየቅንም።
ከኛ ግቢ የተፈተኑ ኮሌጆች ነበሩ ጥር ላይ ከኛ እኩል። እነርሱም ወስደዋል። ከሃረሚያ ዩኒቨርሲቲ መጥተውም ቴምፖ ወስደዋል እዚህ የተፈተኑት። ለግማሹ ተሰጥቶ ለግማሹ ነው የተከለከለው።
ተማሪው ተቸግሯል። ቤት ተከራይቶ፣ የቀን ሥራ እየሰራ የሚኖር አለ። ለቤተሰብ አልፈናል ብለን አውርተናል። ፈተና አልፈን ቴምፖ እየጠበቅን ባለበት ድጋሚ ሰኔ ትፈተናላችሁ ተባልን በሰላማዊ ሰልፍ ስንጠይቅ ” ብለዋል።
“ እኛ ጋር የተፈተኑ የጤና እና የኒውትሬሽን ተማሪዎች እንግዲህ ቴምፖ ወስደዋል። የተፈተነው ግን አንድ ላይ ነው። የተፈተነው አንድ ላይ ነው ‘ተኮራርጃችኋል’ የሚባል ነገር ካለ ለግማሹ ተሰጥቶ ለግማሹ ለምን ይከላከላል ? ” ብለው ቢጠይቁም አጥጋቢ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው በመግለጽ፣ አሁንም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?
ስለጉዳዩ ምንነት የጠየቅነው ማኀበሩ በሰጠን ቃል፣ “ ' ኩረጃ 'በሚል ነው። የጅግጅጋ ብቻ ሳይሆን የሦስት ዩኒቨርሺቲዎች ነው የተያዘው። የጎንደር፣ ወለጋ፣ ጅግጅጋ። የጅግጅጋው በአጠቃላይ ነው ታጥፎ የነበረው ” ብሏል።
“ የጤና ተማሪዎችን ቴምፖ አስለቅቀናል። የሌሎቹም ሂደት ላይ ነው ያለው ” ማኀበሩ፣ “ የቅሬታ ሰሚን ምርመራ እየጠበቅን ነው። ምክንያቱም እኛም የምናነሳው ጥያቄ ስላለ ” ሲልም አክሏል።
ማኀበሩ፣ “ የኮረጁ ዩኒቨርሲቲዎች ተብለው ነው የተያዙት ” ያለ ሲሆን፣ መጀመሪያ ላይ ተማሪዎቹ ተኮራርጀው ከሆነ ለምን ቅድሚያ አልተነገራቸውም? ውጤት ካዩ በኋላ ለምን ይህ ሆነ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ “ የኛም የመጀመሪያ ጥያቄያችን ነው። እየተከራከርን ነው ” ብሏል።
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን ምላሽ ሰጡ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቃቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር) በሰጡን ቃል፣ “እኔ አሁን አዲስ አበባ ነው ያለሁት። እየተከታተልሁ ነው። ጉዳዩ ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር ሆልድ ስላደረገ ነው።
ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ገብተን ተነጋግረናል ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ውጤታቸው ችግር ካለበት ይታይና የተወሰነ ልጆች ችግር ካለባቸው ተለይቶ ይለቀቅላቸው የሚል ነው የኛ ሀሳብ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ተማሪዎቹ መውጫ ፈተና እንዳለፉና ውጤታቸውን እንዳዩ፣ ቴምፖ ለመቀበል እየተጠባበቁ ባሉበት ወቅትም ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተኑ እንደተባሉ ነው ቅሬታ ያነሱትና ይህ አግባብ ነው ? የሚል ጥያቄ ለፕሬዜዳንቱን አቅርበናል።
“ እኛም ይሄን ሪፖርት ይዘን ትምህርት ሚኒስተር በማቅረብ ስብሰባ በመግባት ተነጋግረናል። ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ግን ይሄን ነገር አይተን በኋላ ውሳኔ እንሰጣለን በማለት ነው የተለያየነው ” ሲሉ መልሰዋል ፕሬዜዳንቱ።
አክለውም፣ “ ግን መጨረሻ እንደገና ‘በሰኔ ይፈተኑ’ የሚል ነው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣው። እኛም ተቃውሞ አለን። ችግር ያለባቸው ጥቂት ተማሪዎች ሊኖሩ ይችላሉ ግን ውጤታቸው መለቀቅ አለበት የሚል ሀሳብ ነው የኛም አቋም ” ነው ያሉት።
“ ጉዳዩን ከትምርት ሚኒስተር እየተነጋገርን ነው ትምህርት ሚኒስተር ኦረዲ የወሰኑት ጉዳይ አለ። እንደ ዩኒቨርስቲው ማኔጅመትም የተማሪዎቹ ውጤት በደንብ ተጣርቶ ይለቀቅላቸው የሚል ነው የኛ ሀሳብ ” ብለዋል።
ለቅሬታው ያለውን ምላሽ ለማካተት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ያደረግነው ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን፣ ምላሽ ከሰጠ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ጋዜጠኞችን ወይም የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብ ሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት አልተሰጠውም " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ማምሻውን በላከልን መግለጫ ፤ " የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ፤ ለጋዜጠኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት እና የጋዜጠኞች ምዝገባ ለማከናወን ውይይት እና እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ፤ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ፣ ጋዜጠኞች እና የሙያ ማህበራት ጉዳዩን በተመለከተ የሕጋዊነት ጥያቄ እና ስጋቶቻቸውን እያቀረቡልኝ ይገኛሉ " ብሏል።
የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤቱ ጋዜጠኞችን ወይም የሚዲያ ባለሙያዎችን የመመዝገብም ሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የመስጠት ተግባርና ኃላፊነት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንዳልተሰጠው አስገንዝቧል።
ለዚህ ተግባር እውቅና የማይሰጥ መሆኑንም አሳውቋል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ምክር ቤት ፤ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ምዝገባ፣ የሙያ ማረጋገጫ እና የብሔራዊ ሚዲያ ሽልማት እውቅና የማረጋገጫ አውደ ጥናት ማካሄዱ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቶ በነበረው ቃል ፤ የሚዲያ ባለሙያዎችን እንደ እውቀታቸው እና አስተዋጾ በመለየት ጋዜጠኞችን፣ አዘጋጆችን፣ ከፍተኛ የሚዲያ ተንታኞችን፣ አርታኢያንን፣ እና የሚዲያ ባለሙያዎችን የሚለይ አሰራር እንደሚዘረጋ ጠቆሞ ነበር።
ለጋዜጠኞች እና ለሚዲያ ባለሞያዎች ሙያዊ እውቅና ይሰጣል የተባለም ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተመዘገቡና እውቅና ለሚሰጣቸው ጋዜጠኞች ወጥ የሆነ #መታወቂያ እንዲኖር እንደሚደረግ ይህም አሁን ለሚታየው የአክቲቪዝም እና ጋዜጠኝነት መደበላለቅ መፍትሄ እንደሚሰጥ ገልጾም ነበር።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ግን ምክር ቤቱ በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንዲህ ያለውን ተግባርና ኃላፊነት እንዲፈጽም እንዳልተሰጠው አስገንዝቧል። ምንም እውቅናም እንደማይሰጥ ከወዲሁ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ሲረከቡ የፈረሙት " የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር የተልዕኮ አፈጻጸም የቃል ኪዳን ሰነድ " ምን ይላል ? 1. የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሂደት፣ በጅምር ያለው እንዲጠናቀቅ እና በቀሪ አካባቢዎችም #በፍጥነት እንዲተገበር ማድረግ፤ 2. በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት ትጥቅ የመፍታት እና የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ…
" የተሰጠኝ ኃላፊነት ከባድ የሆነ ፈተና ነው ፤ ጥሩ ከተሰራ ግን እድል ነው " - ጄነራል ታደሰ ወረደ
አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ አስተዳደራቸው የካቢኔ መዋቅር ማስተካከያ እንደሚያደረግ ገልጸዋል።
ጄነራል ታደሰ የተሰጣቸው ኃላፊነት ከባድ ፈተና እንደሆነ ተናግረዋል። " የምትመኘው ነገር አይደለም " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " ጥሩ ከተሰራ ግን እድል ነው " ብለዋል።
"ፈተና" ያሏቸውን እንደኖሩባቸውና እንደሚያውቋቸውም ጠቁመዋል።
ባለፉት ጊዜ ያልተሰሩት ስራዎች ከፕሪቶሪያ ስምምነት ጋር የተያያዙ ብቻ እንዳልሆኑ ጠቁመው " በራሳችን በውስጣች የተፈጠሩ ከፍተኛ የፀጥታ ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ቀውሶች አሉ " ብለዋል።
እነዚህን በርካታ ችግሮች ለመቅረፍ ትግራይ ማዕከላዊ ስልጣን አጥታ ነበር አሁን ግን ማዕከሉን በማጠናከር ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል።
የሰላም ስራዎች ላይ ፣ የፕሪቶሪያ ስምምነት መተግበር ላይ፣ የህዝቡ ጥያቄን መፍታት ላይ ጠንክረው እንደሚሰሩ የተናገሩት ጄነራል " አሁን ያለው ውጥረት ረግቦ ሁሉም የፖለቲካ አካሄድ ለውጥ የሚመጣበት ፤ የወጣቶችም የለውጥ ፍላጎት የሚሳካበት ሁኔታ ይፈጠራል " ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል።
በሳቸው አስተዳደር የካቢኔ ማስተካከያ እንደሚኖርም ይፋ አድርገዋል።
በፕሬዜዳንትነት ጊዜያቸው ዋናው #የትግራይ_ህዝብ ድጋፍ እንደማይለያቸው ፤ የፌዴራሉም መንግሥት እንዲሁም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍም እንዲሁ እንደማይለያቸው እምነታቸው ገልጸዋል።
" ትልቁ ነገር ደግሞ አቶ ጌታቸው ረዳ የስራ ለውጥ ቢያደርጉም ክልሉን ያውቁታል ያላቸውን እና በቀጣይ የሚኖራቸውን ሚና በደምብ እገነዘባለሁና የእሳቸው ድጋፍም እንደማይለየኛ ተስፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።

#AddisAbaba
" ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር ለማድረግ የቀረበው ጥናት ፀድቋል " - የአዲስ አበባ ካቢኔ
በዛሬዉ እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
ከነዚህም አንዱ ፥ በፕላንና ልማት ቢሮ እና በት/ት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበውን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር የማድረግ ነው።
ካቢኔው " በአካባቢው ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት ፣ የምርምር ፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ ፀድቋል " ሲል አሳውቋል።
ከዚህ ባለፈ ካቢኔው ፦
- የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና ፤የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል።
- በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶም ዉሳኔ አስተላልፏል።
- የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይም ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል።

#ችሎት
⚫️ “ እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ ” - አቶ ክርስቲያን ታደለ
🔴 “ ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሸው ተቀቷል። ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው ” - አቶ ዮሐንስ ቧያለው
የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያሌውን ጉዳይ የሚከታተሉ የቅርብ ሰዎች፣ “የመንግስት አክቲቪስት” ሲሉ የጠሯቸውና “እነ ክርስቲያን ወንጀለኛ ናቸው” ያሉትን ግለሰብ ፌደራል ፓሊስ ማግኘት እንዳልቻለ ለፍርድ ቤት መግለጹን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።
በዚህም፣ አቶ ስዩም ተሾመ የተባሉት ግለሰብ በቻናላቸው እነ አቶ ዮሐንስን ወንጀለኞች እንደሆኑ በመናገራቸው፣ እነ አቶ ዮሐንስም ክሰዋቸው ስለነበር ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዞ የነበረ ቢሆንም፣ ፌደራል ፓሊስ አቶ ስዩም ተሾመን ማግኘት አለመቻሉን ለፍርድ ቤት መግለጹን ነው ያስረዱት።
የእነ አቶ ዮሐንስ እና አቶ ክርስቲያን የቅርብ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
“ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው እና ክርስቲያን ታደለ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሰው ጉዳያቸው በመታዬት እያለ አቶ ስዩም ተሾመ መጋቢት 11/2017 ዓ/ም ባስተላለፉት ፕሮግራም ከተከሰሱበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ‘የአማራን ወጣት አስፈጅተዋል፣ ድሽቃ መሣሪያ መግዣ ጠይቀዋል’ ብለው እንደነበር አስታውሰዋል።
በዚህም፣ “በፍትህ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር፣ ሕግን የተላለፈ ፕሮግራም ስላቀረቡ፣ የፌደራል ፖሊስ ለዛሬ መጥሪያ አድርሶት ችሎት እንዲያቀርበው ቢታዘዝም፣ ‘የስዩም ተሾመ አድራሻው ስላልተገለጸልኝ ላቀርበው አልቻልኩም’ ብሎ ምላሽ ሰጥቷል ” ብለዋል።
አቶ ዮሐንስ ቧያሌው በዚሁ ጉዳይ ዛሬ ምን አሉ ?
“ ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሸው ተቀቷል። ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው። ትምህርት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው አሁንም ተመሳሳይ ድርጊት የፈጸመው።
መንግስት ቤት የሰጣቸው፣ ደሞዝ የሚከፍላቸው እና መኪና የተሰጣቸው የመንግስት አክቲቪስት ናቸው። አማራ ሲሆን የትም ይገኛል። ደብል ስታንዳርድ ነው። የፌደራል ፖሊስ የሰጠው መልስ ለእኛ አሳማኝ አይደለም ” ብለዋል።
አቶ ክርስቲያን ታደለ በዚሁ ጉዳይ ምን አሉ ?
“ ይሄ ‘ወስፌ ሲለግም ቂቤ አይወጋም’ የሚለው አባባል እውነት መሆኑን ያሳየ ነው። አቶ ስዩም ማለት የኢትዮጵያ መንግስት ጠባቂ ፖሊስ የመደበለት የመንግስት ተከፋይ ሃሜተኛ ነው።
እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ። የመንግስት ሹመኛን የሚጠብቀው የፌደራል ፖሊስ አካል ነው።
እኛን የህዝብ እንደራሴዎችን ከቤተሰባችን ፊት ደብድቦና አዋርዶ ለማምጣት ያልተቸገረው ፌዴራል ፖሊስ፣ ላገኛቸው አልቻልኩም ማለቱ ስላቅ ነው። እውነቱን ንገረኝ ካላችሁኝ አቶ ስዩም ያልታሰረው አማራ ነኝ ስላላለ ነው ” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ተብሏል።
በመጨረሻም፣ “ የተከሳሾች ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የተላለፈው ፕሮግራም ሕግን የተላለፈ በመሆኑ ፖሊስ ያለምንም ምክንያት አቶ ስዩምን እንዲያቀርብ ይደረግልን ” ማለታቸውን የቅርብ ሰዎቻቸው ተናግረዋል።
“ ፍርድ ቤቱም በድጋሚ የፌደራል ፖሊስ ስዩም ተሾመን እንዲያቀርባቸው ለሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል ” ብለዋል።
N.B፦ ፌደራል ፓሊስ ፍርድ ቤት እንዲያቀርባቸው ተብለው ነበር የተባሉት አቶ ስዩም ተሾመ፣ ከሳምንት በፊት ባሳራጩት ዩቱዩብ ቻነል ስለነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው ሲናገሩ፣ “ቧያሌው ተንኮለኛ ነው። ከኔ በላይ ማን ምስክር አለ ያረገውን፤ እሰይ ቧያሌው ታሰረ ብዬ ስላልፎከርኩ ነው? መከራዬን አይደል ያበላኝ እሱ ምን ብዬ ስላልኩት ፋኖ ትጥቅ ይፍታ ' አይፈታም' ሲል የአማራን ህዝብ ታስበላላችሁ ሆን ብላችሁ ይሄ ሴራ ነው ስላልኳቸው ነው ይሄ ችግር የተፈጠረው ፤ የተለየ ወንጀል ሰርቼ አይደለም ፤ ገዱም እሱም ጠምደው መከራዬን ሲያበሉኝ የነበረው ፋኖ ትጥቅ አይፈታም ሲሉ ይሄ የድንቁርና ሃሳብ የአማራን ህዝብ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያጋጫል ፣ የማይሆን ቅርቃር ውስጥ ያስገባዋል፣ የአማራን ህዝብ ታስበላላችሁ፣ ወጣቱን ታስፈጃላችሁ እንዳልኩ ወጣት አስፈጅተዋል። እነዚህ ሰዎች ከዛ አልፈው ታጥቀው ' መንግሥት እንግለብጣልን ' ሲሉ መንግሥት ገልብጦ እስር ቤት ከቷቸዋል ስራቸው ያውጣቸው ” ሲሉ ተደምጠዋል።

#Update " አሁን ላይ ግጭቱ ቆሟል ሕዝብ የማወያየትና የሞቱትን የመቅበር ስራ ሲሰራ ነዉ የዋለው " - የደራሼ ወረዳ ነዋሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ከመጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸዉን የአከባቢውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናግራቸው ይታወሳል። በወረዳዉ የሀይ'በረና እና ኦኖታ አከባቢ ነዋሪዎች…
#Update
" ግጭቱ ቆሞ የሕዝብ ወይይት እየተደረገ ባለበት የ18 ዓመት ወጣትን ጨምሮ ሁለት ሰዎች በማሳቸዉ ላይ ተገድለዋል " - የሟች ቤተሰቦችና የአከባቢው ነዋሪዎች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ኦኖታና ቄየማ በሚባሉ ቀበሌያት መካከል መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተከሰተ በተባለዉ ግጭት እስካሁን ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ሰዎች ሞተዋል።
ባሳለፍነዉ አርብ በአከባቢው የመከላከያ ሠራዊት በመግባቱ ግጭት መቆሙና የሕብረተሰብ ውይይት መካሄድ መጀመሩን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረው ነበር።
ዛሬ የአከባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " ወደ ልማት ስራችሁ ተመለሱ የተባልነዉን ተቀብለን ትናንት ሰኞ በማሳ ስራ ላይ የነበሩ አንድ የ18 ዓመት ታዳጊና ሌላ የ3 ልጆች አባት ተገድለዋል " ብለዋል።
የሟች ቤተሰቦች ከዐይን እማኞች ሰማን እንዳሉት ግድያው የተፈጸመው " በአካባቢው የፀጥታ ሰዎች (ፖሊሶች) " እንደሆነ ጠቁመዋል።
" ቅዳሜና እሁድን ብቻ ነዉ ሰላም የዋልነዉ " ያለን አንድ የአከባቢው ነዋሪ " ሰኞ ገና በጠዋቱ ነበር ሁለቱ ሰዎች በገዛ ማሳቸዉ እጅና እግራቸው ታስሮ በጥይት ተረሽነዉ የተገደሉት " ሲሉ ተናግረዋል።
" ጥቃቱ አሳዛኝና የአከባቢውን ነዋሪዎች እጅግ ያስቆጣ ተግባር ነዉ " ያለን ሌላኛው የሀይ'ቤና ቀበሌ ነዋሪ " የፀጥታ መዋቅሩ አከባቢዉን በተቆጣጠረበት ይህን ጥቃት የፈፀሙ አካላትን ለህብረተሰቡ በፍጥነት ግልፅ አለማድረጋቸው ሕዝቡን ቅር አሰኝቷል "ብለዋል።
በጥቃቱ ልጃቸውን ያጡ አባት ፥ " ሰባት ሴት ልጆችና አንድ ወንድ ልጅ ብቻ የወለድኩ ሲሆን አንዱ ወንድ ልጄን ነዉ አይቼ ሳልጠግበዉ ገና በለጋነቱ የተነጠኩት " ሲሉ በሀዘን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ጥቃቱን የአከባቢዉ ፖሊሶች መፈጸማቸውን ከዐይን እማኞች ስምቻለሁ ሲሉም አክለዋል።
በወረዳዉ የአይ'ቤና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑና በደቦ የማሳ ስራ ላይ የነበሩ 17 የሚሆኑ ወጣቶችም ትላንት ረፋድ በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ በርግገው ወደ ሌሎች ዞኖች መግባታቸዉን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ ወጣቶቹ በሕይወት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ አላገኘንም ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በአከባቢው ተገኝተዉ ሕብረተሰቡን ሲያወያዩ የነበሩትን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህን አግኝቶ ለማነጋገር ቢሞክርም ፈቃደኛ ባለመሆን ስልካቸውን ዘግተዋል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስከመጨረሻው የሚከታተል ይሆናል)

#AddisAbaba #EV_Charging
ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን እጅግ ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አገልግሎት በአዲስ አበባ አስጀምሯል።
ስራ የጀመረው ሁለተኛው ጣቢያ ከመገናኛ ቦሌ መንገድ አንበሳ ጋራጅ ፊት ነው የሚገኘው።
ይህ ጣቢያ የአውሮፓ ስሪት የሆኑ መኪኖችን የኤሌክትሪክ ኃይል መሙላት የሚያስችል እጅግ ፈጣን አቅም ያለው ተብሏል።
የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎቹ በ1 ሰከንድ 1 ኪሎሜትር ለመጓዝ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል በመሙላት በ15 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ (100%) የኤሌክትሪክ ኃይል የመሙላት አቅም እንዳላቸው ኩባንያው አሳውቋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ የባትሪ መስፈርቶች እና የደንበኛን ትዕዛዝ በመተንተን የባትሪውን ደህንነት እየፈተሸ የተሽከርካሪው ባትሪ በሚችለው ፍጥነት ቻርጅ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
ኩባንያው ቀደም ሲል 16 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል ጣቢያ ወደስራ ያስገባ ሲሆን ከየካቲት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ14,280 የኤሌክትሪክ መኪኖች፣ በ376,574.72 ኪሎዋት/ሰዓት ኃይል ቻርጅ ማድረግ እንደቻለ አመልክቷል።
አዲሱ የመሙያ ጣቢያ 4 እጅግ በጣም ፈጣን እና 12 በጣም ፈጣን መሙያዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም ያሉንን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች የማስተናገድ አቅም ወደ 32 ለማድረስ አስችሏል፡፡
#EthioTelecom #EcoFriendly #EV_Charging