Telegram Group & Telegram Channel
ዋጋን ማወቅ

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከዕለታት በአንዱ ቀን መኳንንቱና ሊቃውንቱ በተሰበሰቡበት፡

“ለመሆኑ እኔ ብሸጥ ስንተ አወጣለሁ ?” በማለት ጥያቄ አቀረቡ ። ጥያቄው ድንገተኛ ፣ ለመመለስም አስቸጋሪ ነበር ። የሚወዷቸውና የሚያከብሯቸው ነበሩና ለእርሳቸው ዋጋ ለመተመን ሕሊናቸው ተጨነቀ ። ሁሉም መልስ መመለስ አቅቶት ዝምታን በመረጠበት ጊዜ አንድ የቆሎ ተማሪ “እኔ አለሁ” በሚል ስሜት መንቆራጠጥ ጀመረ ። መልስ አለኝ ብሎም ብድግ ብሎ ቆመ።

ምኒልክም “በል ተናገር” ብለው ዕድሉን ሰጡት ። ሊቃውንቱና መኳንንቱ ያቃታቸውን መልስ ተማሪው በድፍረት መለሰ ።

“ንጉሥ ሆይ ሃያ ዘጠኝ ብር ያወጣሉ” አላቸው ።

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክም ቆጣ ብለው፡- “እንዴት እኔን በሃያ ዘጠኝ ብር ገመትከኝ?” ቢሉት ተማሪውም፡-

“የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው ክርስቶስ የተሸጠው በሠላሳ ብር ነውና ምን ደግ ቢሆኑ ከክርስቶስ አይበልጡም ብዬ ነው በሃያ ዘጠኝ ብር የገመትክዎት” አላቸው ።

በተማሪውም መልስ ንጉሡና በዙሪያቸው የነበሩ መኳንንቱና ሊቃውንቱ ተደንቀው ሳቁ ።

በዚህ ዓለም ላይ የራሳችንን ዋጋ ማወቅ የምፈልግበት ቀን አለ ። ንጉሥም ሆነ ሎሌ “እኔ ስንት አወጣለሁ ?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል ፤ ዙሪያውንም መልስ ፍለጋ ያማትራል ። ምን ያህል ሕዝብ ይወደኛል ? ብሞት ማንን አጎዳለሁ ? ብኖርስ ማንን እጠቅማለሁ ? የሚሉ ጥያቄዎች በውስጣችን ተረግዘው ይወለዳሉ ። እነዚህ ጥያቄዎች ከጽንሰት እስከ ልደት ድረስ አስጨናቂ ናቸው ። አንዳንድ ሰው ራሱ በራሱ ፊት ዋጋው እያነሰበት “መኖር ትርጉም የለውም” ብሎ ይደመድማል ። ምክንያቱ ካለቀበት አንድ እርምጃ መጓዝ ሁሉም ሰው ሊከብደው ይችላል ። ወደ እግዚአብሔር “አቤት” ብሎ “ጌታዬ ሆይ ዋጋ ሁነኝ” ካላለ ውስጡን መገሠጽ ፣ ማዕበሉን መቅዘፍ ይቸገራል ።

“እኔ ብሞት ምን ትላላችሁ ?” ብለን ልጆቻችንን እንጠይቃለን ። የምትሄደው ወይም የምትሄጅው ክርስቶስ ጋ ነውና ጥሩ ነው ካሉን ፣ “የዛሬ ልጅ ጨካኝ ነው” እንላለን ። የጠየቅነው የምንፈልገውን መልስ ለመስማት ነው ። ራሳችን ጠይቀን ራሳችን እንታዘባለን ። የዚህ ሁሉ አሰሳ ምክንያቱ ዋጋችንን ለማወቅ ነው ። ጓደኞቻችንን “ፎቶዬን ላሳድግ ፎቶ ቤት እየሄድኩ ነው” እንላለን ። ለምን ? ሲሉን “ብሞት እንኳ ማስለቀሻ ይሆናል” በማለት እንመልሳለን ። ሲደነግጡና “አይባልም” ሲሉን ደስ ይለናል ። ምክንያቱም በእነርሱ ዘንድ ያለንን ዋጋ አውቀናልና ። የአገር መሪዎች ሰልፍ የሚያስወጡት ዋጋቸውን ለማወቅም ነው ። ይጠፉና ታመሙ የሚባል ወሬ ያስወሩና ሁሉም ለፍልፎ ሲደክመው ብቅ ይላሉ ። የፎከረና ዙፋን ያማረው ያፍራል ። ያዘነና ያለቀሰም ይደሰታል ። አመመኝ የሚሉ ሚስቶች ፣ የሚያጉረመርሙ ባሎች አንዱ ችግራቸው ዋጋቸውን ስንት መሆኑን ማወቅ ስለሚፈልጉ ነው ። ኑሮ በዘዴ እንጂ በጉልበት አይደለም ። ዘዴውን ያወቁ መንገዱ ጥርጊያ ሲሆንላቸው ፣ ያላወቁት ደግሞ ፊት ለፊት ከሚጋረጥ ተራራ ጋር ይጋጠማሉ ።

ሕፃናትም ዋጋቸውን ማወቅ ይፈልጋሉ ። በድንገት ውድቅ በማለት “ልጄን” ሲባሉ ይደሰታሉ ፣ ይስቃሉ ። የሚደነግጥላቸው ፣ በአካል ሲወድቁ በአሳብ አብሮ የሚወድቅላቸውን ማወቅ ይሻሉ ። ወንድም በወንድሙ ዘንድ ያለውን ዋጋ ለማወቅ “እንዲህ ያለ ወንጀል ሠርቼ ልታሰር ነው” ይለዋል ። ወንድሙም ሐሰተኛ ዜና መሆኑን ሳያውቅ ይደነግጥና መላ ማቅረብ ይጀምራል ። ያን ቀን ጠያቂው ወንድም ፣ ተጠያቂ ወንድሙን በወርቅ ቀለም ይጽፈዋል ። መምህራን ዋጋቸውን ለማወቅ፡- “ጉባዔውን በትኜ አንድ ገዳም እገባለሁ” ይላሉ ። ተማሪውና ሕዝቡም፡- “ምን በደልን ይቅር ይበሉን” ሲላቸው ዋጋቸውን ያገኙትና ደስ ይላቸዋል ።

ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ነው ። ምንም ትሑት ብንሆን ከእርሱ አንበልጥም ። እርሱ ሊያጠፋን አቅም እያለው ችሎናል ። ምክንያቱም ትሑት ነውና ። እኛ ግን አቅም ስላነሰን ዝቅ ማለታችን ትሕትና ተብሎ ይጠራል ።

እርሱ ቢገድለንም ቢያድነንም ሁሉም በፊቱ ነው ። ትዕግሥተኛ ነውና ለመግደል በቂ ምክንያት እያለው ያድነናል ። ጥፋታችንን ሳይሆን ራሱን እያየ ይጋርደናል ። ምንም ትዕግሥተኛ ብንሆን የእርሱን ያህል ታጋሽ አይደለንም ። ምንም መከረኛ ብንሆን የእርሱን ያህል መከራ አልተቀበልንም ። እርሱ በጌትነቱ ብቻ ሳይሆን አርአያ ገብርን በመንሣቱም ልክ የለም ፣ አይደረስበትም ።

እርሱ በበረት ተወልዷል ። ከበረት ያነሰ ቦታ መፈለግ ይገባናል ። እርሱ እኛን ሀብታም ሊያደርግ እንደ ደኸየ ከማሰብ እርሱ በመንፈስ ሊያበለጥገን ምንም የሌለው ምስኪን እንደሆነ ማመን የተሻለ ነው ። እርሱ በግብጽ በረሃ ተሰድዷል ። እኛ ግን ተሰደድን የምንለው ከእርሱ ስደት ጋር የማይነጻጸር ነው ። እርሱ ቤት የለሽ ሁኖ ኑሯል ። እኛ ግን በኪራይ ቤት ስለምንኖር እንበሳጫለን ። በኪራይ ዓለም ተቀምጠን ፣ በኮንትራት ዕድሜ እየኖርን ቋሚ ቤት እንፈልጋለን ። እርሱ በተውሶ ጀልባ ተንቀሳቅሷል ፣ እኛ ግን የራሳችን መኪና ስለሌለን ፣ በታክሲ ስለምንንቀሳቀስ እንበሳጫለን ። እርሱ በባሪያው እጅ ተጠምቋል ፣ እኛ በዕድሜም በጸጋም በክህነትም ለሚበልጡን አባቶች ዝቅ ማለት አንሻም ። እርሱ ጋኔን አለበት ተብሏል ። እኛ ግን ባነሰ ስድብ ደንብረናል ። እርሱ እብድ ነው ተብሏል ። እኛ ግን መናፍቅ መባል ያሰጋናል ። እርሱ አናጢነትን ሙያው አድርጓል ። እኛ ግን ሥራ እናማርጣለን ፣ በምንሠራው ሥራም ትልቅነት አይሰማንም ። እርሱ በጲላጦስ አደባባይ ያለ ወንጀሉ ተከስሷል ። እኛ ግን በገዛ ወንጀላችን ስንከሰስ ይከፋናል ። እርሱ በጴጥሮስ ተክዷል ። እኛ ግን በልባችን የከዳናቸው በአካል ሲከዱን ተቀደምኩ ብለን እናዝናለን ። እርሱ በይሁዳ ተሽጧል ። እኛ ግን ብዙዎችን ሸጠን ፣ አንድ ጊዜ ስንሸጥ ይቆረቁረናል ።

በጣም ትሑት ሆነን ዝቅተኛውን ስፍራ በረትን ከመረጥን እርሱንም ክርስቶስ ይዞብናል ። በሲና በረሃ መንከራተትን ብንመርጥ እርሱ ተሰዶበታል ። ቤት የለሽ መሆንን ብንፈልግ እርሱ በተራራ ያድር ነበረ ። የገዛ ወንድሞቻችን ስለናቁን ትልቅ ማዕረግ እንዳለን ከቆጠርን እርሱ ይበልጥ በእናቱ ዘመዶች ተንቋል ። ከበረት ያነሰውን ቦታ ፣ ከባሪያ ያነሰውን አገልጋይ ፣ ከሲና በረሃ የባሰውን መንገድ ፣ ከሠላሳ ብር ያነሰውን ዋጋ መፈለግ አለብን ። እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ይህን ካገኘ እኛማ ገና ይቀረናል ።

ስለ መከራችን ለማውራት መከራው ይገሥጸናል ። ስለ ስደታችን ለመተረክ ስደቱ ገና ነው ይለናል ። የሚሊየን ብር ዋጋ ለራሳችን ስናወጣ ክርስቶስ የተሸጠበት ሠላሳ ብሩ ተዉ ይለናል ። በመከራው ፊት መከራችን ፣ በአገልግሎቱ ፊት አገልግሎታችን ፣ በመሥዋዕትነቱ ፊት የከፈልነው ዋጋ ትንሽ ነው ።

ጌታ ሆይ ዋጋችንን ካንተ ዋጋ እንዳናስበልጥ እርዳን ።@THESECRETKNOWITFIRST
@THESECRETKNOEITFIRST

group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST/269
Create:
Last Update:

BY THE SECRET KNOW IT FIRST

Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260

Share with your friend now:
group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST/269

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

'Wild West' Now safely in France with his spouse and three of his children, Kliuchnikov scrolls through Telegram to learn about the devastation happening in his home country. Telegram, which does little policing of its content, has also became a hub for Russian propaganda and misinformation. Many pro-Kremlin channels have become popular, alongside accounts of journalists and other independent observers. Again, in contrast to Facebook, Google and Twitter, Telegram's founder Pavel Durov runs his company in relative secrecy from Dubai. On Feb. 27, however, he admitted from his Russian-language account that "Telegram channels are increasingly becoming a source of unverified information related to Ukrainian events."
from no

Telegram THE SECRET KNOW IT FIRST
FROM American