Telegram Group & Telegram Channel
አልወጣም ከቤቴ ቁ.፪

ክፍል ፩(1) ምንጭ 👉 የእግዚአብሔር ቃል

"መስታውት ለሰው ልጅ በጣም ከሚጠቅሙ ነገሮች ውስጥ አንዱና ትልቁ ነገር ነው..... ለማየት ለውበት ሳይሆን ለማንነት.... ነገሮችን እንደ አቀባበላችን ነው የሚለውንም ቃል በተግባር ያሳየኛል ለምሳሌ መስታውቱን ሳየው ምስቅ ከሆነ በመስታውት ማያትም አብራኝ ትስቃለች ማለቅስም ከሆነ እንደዛው... ይህ ከአቀባበሌ የሚጀምር ይመስለኛል ቀና አድርጌ ከተቀበልኳት ነገር ሁሉ በጎ ይሆንልኛል መጥፎ ካደረግኩትም እንዲሁ... ሀሳቤ ተበታተነ... ? "

ዘሀራ(የፈዲላ እናት) ፡- ፈዲላ ፈዲላ.....

ፈዲላ፡- አቤት እማ

ዘሀራ፡- ብቻሽን እያወራሽ ነው ደህና ነሽ??

ፈዲላ፡- አዎ እማ ደህና ነኝ አታስቢ ዝም ብዬ ከራሴ ጋር እያወራሁ ነው

ዘሀራ፡- እሺ ልጄ መልካም ነይ ለማንኛውም ምሳ ቀርቧል

ፈዲላ፡- እሺ መጣሁ እማ ትንሽ ልቆይ

ዘሀራ፡- የለም! ይህ ሳሙኤል የሚባለው ልጅ አንቺን ከማሳመም አልፎ የምግብ ፍላጎትሽንም ዘጋው?

ፈዲላ፡- አይደለም ስለበቃኝ እኮ ነው

ዘሀራ፡- ምን በልተሽ ነው ሚበቃሽ ልጄ ትናንት ቀን ሶስት ማንኪያ ሩዝ የቀመስሽ ኮ ነሽ! ኧረ ተይ ልጄ ራስሽን አትጉጂ

ፈዲላ፡- እሺ እማ መጣሁ

አለችና እምባዋን ጠራረገች ስለ ሳሙኤል ማሰብና ማሰላሰል ማቆም ያልቻለችው ፈዲላ እስከ ዛሬ ድረስ በልቧ አስቀምጣው በሱ ፍቅር ትሰቃያለች ምክንያቱም በጣም ወዳው ነበር።

ወደ ሳሎንም ገባች

ጀማል(የፈዲላ ወንድም)፡- ይህች ልጅ እስኳሁን ሳሙኤል ላይ ነች እማ? ፊቷ ያስታውቃል

ዘሀራ፡- ተው ጀማል! ዝም በይውና ነይ ተቀመጪ ልጄ

ፈዲላ፡- እሺ እማ ትቸዋለሁ

ዘሀራ፡- ይሄው ቆንጆ አድርጌ ነው ነው የሰራሁት ብይ ልጄ

ፈዲላ፡- እሺ አመሰግናለሁ

ጀማል፡- ፈዲላ እኔ ላንቺ አስቤ እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም ..... እንድታውቂው ብዬ ነው።

ፈዲላ፡- እሺ

ጀማል፡- ደሞ ከዚህ ካፊር...

እንዳለ ዘሀራ ከአፉ ቀማችና

ዘሀራ፡- ጀማል ስርአት ይኑርህ ደህና መብላት የጀመረችውን ልጅ አትረብሻት እንደውም እስክትጨርስ መኝታ ቤትህ ሁን ተነስ

ፈዲላ፡- ተይው እማ ሁሌ እንዲህ ስለሆነ ችግር የለውም ለምጄዋለሁ

ዘሀራ፡- ምን እየጠበቅክ ነው...... ተነስ እንጂ???

ጀማል፡- እሺ እሺ ተረጋጉ...ጉድ ኮ ነው ለአንዲት ቃል ወደ መኝታ ቤት መጠለዝ ስልችት ነው ያለኝ! " በማለት እያጉረመረመ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ። ፈዲላም ምሳውን ለመብላት እየሞከረች ቢሆንም ብዙ ሊገባላት አልቻለም።

በዚህ ሁኔታ ልቧ የተሰበረው የፈዲላ እናት ሁኔታዋን እያየች እጅጉን ታዝን ነበር።

ፈዲላ፡- ይጣፍጣል እማ በቃኝ

ዘሀራ፡- እንዴ ልጄ ምኑን በላሽ

ፈዲላ፡- እያየሽኝ እማ?

ዘሀራ፡- እሺ ልጄ አልጫንሽም ግን መኝታ ቤትሽ ከመግባትሽ በፊት ስለሆነ ነገር ላናግርሽ እፈልጋለሁ

ፈዲላ፡- እሺ እማ መልካም ታጥቤ መጣሁ" አለችና ወደ መታጠቢያ ቤት ገብታ ወዲያው ታጥባ መጣች።

ዘሀራ፡- እሺ ልጄ ላናግርሽ ያሰብኩት ነገር እዚህ ቤት ላንቺ ዝም ብሎ መቀመጥ ጥሩ አይደለም ስለዚህ ስራ ነገር ፈልገሽ ቢያንስ አይምሮሽን በሆነ ነገር ላይ ብታጠምጂው መልካም ነው ብዬ አስባለሁ

ፈዲላ፡- ይሻላል እማ እኔ መስራት አልፈልግም " ይህንን ያለችበት ምክንያት ስራውን ጠልታው ሳይሆን አሁን ካለችበት ሁኔታ የተነሳ የመስራትም ሆነ ነቃ የማለት ፍላጎቱ ስላልነበራት ነው።

ዘሀራ፡- አዎን ልጄ ብትወጪ ላንቺ መልካም ነው ደህናና ጥሩ ሁኔታ ላይ እንድትሆኙ ይጠቅምሻል ብትሰሪ ጥሩ ነው ባትፈልጊም ሞክሪው

ፈዲላ፡- እሺ

ዘሀራ፡- በእውነት ልጄ...... እሺ አልሽ

ፈዲላ፡- አዎ እማ ካልሽ እሞክረዋለሁ

ወዲያው ዘሀራ ስልክ አንስታ መደወል ጀመረች

ፈዲላ፡- እ... እማ ማን ጋር ነው ምትደውይው

ዘሀራ፡- አባትሽ ጋር ነ..... ሄሎ ሄሎ

መሀመድ፡- ሄሎ

ዘሀራ፡- ፈዲላ በትላትናው ጉዳይ ተስማምታለች አሁን መፈለግ ጀምር

መሀመድ፡- በእውነት. ..? ማሽ አላህ ማሽ አላህ አሁሁ አግኝላታለሁ ኢንሻላህ

ዘሀራ፡- እሺ መልካም ሰላም ዋል

ፈዲላ፡- ይሄን ያህል አሳስቤያችሁ ነበር ማለት ነው? በጣም ይቅርታ

ዘሀራ፡- ምን ማለትሽ ነው ልጄ ቤተሰቦችሽ ነን

ፈዲላ፡- አይ እንደሱ ለማለት አይደለም ይቅርታ በድጋሚ

ዘሀራ፡- አይ የኔ ልጅ መጥፎ ነገር እንዲነካሽ አልፈልግም አንቺ ሁሉ ነገሬ ነሽ በረካ ሁኚ" አለችና የበሉበትን ሰሀን ማነሳሳት ጀመረች።

ይቀጥላል............
http://www.group-telegram.com/no/THESECRETKNOWITFIRST.com

group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST/315
Create:
Last Update:

BY THE SECRET KNOW IT FIRST

Share with your friend now:
group-telegram.com/THESECRETKNOWITFIRST/315

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

But the Ukraine Crisis Media Center's Tsekhanovska points out that communications are often down in zones most affected by the war, making this sort of cross-referencing a luxury many cannot afford. "Like the bombing of the maternity ward in Mariupol," he said, "Even before it hits the news, you see the videos on the Telegram channels." Unlike Silicon Valley giants such as Facebook and Twitter, which run very public anti-disinformation programs, Brooking said: "Telegram is famously lax or absent in its content moderation policy." On Feb. 27, however, he admitted from his Russian-language account that "Telegram channels are increasingly becoming a source of unverified information related to Ukrainian events." However, the perpetrators of such frauds are now adopting new methods and technologies to defraud the investors.
from no

Telegram THE SECRET KNOW IT FIRST
FROM American