Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/tikvahethiopia/-94087-94088-94089-94090-94091-): Failed to open stream: No space left on device in /var/www/group-telegram/post.php on line 50
TIKVAH-ETHIOPIA | Telegram Webview: tikvahethiopia/94090 -
Telegram Group & Telegram Channel
" ተመዝግበንና ክፍያም ከፍለናቸው ትምህርት በመጀመር ሂደት ላይ ባለንበት ዩኒቨርሲቲዉ አላስተምራችሁም ብሎናል " - የሪሚዲያል ተማሪዎች

➡️ " ዉሳኔዉ የትምህርት ሚንስቴ እንጂ የዩኒቨርሲቲው አይደለም " - የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

" የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት ወራት ፊት በሣምንቱ የዕረፍት ቀናት የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ከፍለዉ መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ባወጣዉ ማስታወቂያ መሰረት የምዝገባ እና የመማሪያ ክፍያ አጠናቀን ትምህርት በመጀመር ሂደት ላይ እያለን ዩኒቨርሲቲው ሌሎች አማራጮችን መጠቀሚያ ጊዜ ባለፈብን በዚህ ወቅት አላስተምራችሁም ብሎናል " ሲሉ ተማሪዎሽ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።

ቅሬታቸዉን ካደረሱን ተማሪዎች መካከል በመደበኛው የትምህርት ሚንስቴር ምደባ ጅግጅጋ ፣ሰላሌ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ተመደብዉ እያለ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) በእረፍት ቀናት በክፍያ ለማስተማር ማስታወቂያ ማዉጣቱን ተከትሎ ከቤተሰብ ላለመራቅና በአንዳንድ አከባቢዎች ካለዉ የፀጥታ ችግር የተነሳ ከፍለዉ ለመማር በመወሰን የምዝገባና የትምህርት ክፍያ አጠናቀው የትምህርት መጀመርን ሲጠባበቁ እንደነበር ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ " ኃላፊነት በጎደለው መልኩ 'ትምህርት ሚንስቴር በግል ከፍሎ መማርን ስላልፈቀደ ማስተማር የማንችል በመሆኑ ክፍያችሁን መዉሰድ ትችላላችሁ ' ብሎ የለጠፈዉ ማስታወቂያ እጅግ አሳዝኖናል " ብለዋል።

በተመደብንባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች መሄድ በማንችልበትና ሌሎችም በግል ኮሌጆች ከፍለን የመማሪያ ጊዜዉ ካለፈብን በኋላ የተወሰነዉ ይህ ዉሳኔ ከጊዜ እና ገንዘብ ጉልበት ብክነት ባሻገር በስነልቦናም ጉዳት አድርሶብናል ብለዋል።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸዉን ለዩኒቨርሲቲዉና በግልባጭ ለትምህርት ሚንስቴርም ማቅረባቸውን ገልፀዉ የሚመለከተዉ አካል አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌን አግኝቶ በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግሯል።

ዶክተር ቅሬታዉ እንደደረሳቸዉና ዩኒቨርሲቲዉ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገዉ ሁሉ " በሣምንቱ መጨረሻ ቀናት የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ለመስጠት ማስታወቂያ ማዉጣቱንና 400 የሚሆኑ ተማሪዎች ተመዝግበው ክፍያ ላጠናቀቁ ተማሪዎች ትምህርት የመጀመር ሂደት ላይ እያለን ትምህርት ሚንስቴር በሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት ማስተማር ስለማንችል ማስታወቂያ ለጥፈናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ዩኒቨርቲዉ ለማስተማር ካለዉ ፍላጎት የተነሳ ተማሪዎችን መዝግቦ ወደ መማር ማስተማር ሂደት በመግባት ሂደት ላይ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዘረዳንቱ የተማሪዎችንና የወላጆችን ቅሬታ ተከትሎ ጉዳዩን ወደ ትምህርት ሚንስቴር በማቅረብ ሂደት ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

" በሚንስትር መስሪያ ቤቱ ምላሽ ላይ ተመስርተን ' አስተምሩ ' የሚባል ተስፋ ሰጪ ጉዳዮች የሚገኙ ከሆነ ለተማሪዎቹ ጥሪ እናቀርባለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።

ጉዳዩን ተከታትለን ተጨማሪ መረጃ የምናደርስ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94090
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94090

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

The company maintains that it cannot act against individual or group chats, which are “private amongst their participants,” but it will respond to requests in relation to sticker sets, channels and bots which are publicly available. During the invasion of Ukraine, Pavel Durov has wrestled with this issue a lot more prominently than he has before. Channels like Donbass Insider and Bellum Acta, as reported by Foreign Policy, started pumping out pro-Russian propaganda as the invasion began. So much so that the Ukrainian National Security and Defense Council issued a statement labeling which accounts are Russian-backed. Ukrainian officials, in potential violation of the Geneva Convention, have shared imagery of dead and captured Russian soldiers on the platform. Ukrainian forces have since put up a strong resistance to the Russian troops amid the war that has left hundreds of Ukrainian civilians, including children, dead, according to the United Nations. Ukrainian and international officials have accused Russia of targeting civilian populations with shelling and bombardments. Meanwhile, a completely redesigned attachment menu appears when sending multiple photos or vides. Users can tap "X selected" (X being the number of items) at the top of the panel to preview how the album will look in the chat when it's sent, as well as rearrange or remove selected media. Following this, Sebi, in an order passed in January 2022, established that the administrators of a Telegram channel having a large subscriber base enticed the subscribers to act upon recommendations that were circulated by those administrators on the channel, leading to significant price and volume impact in various scrips. The regulator said it has been undertaking several campaigns to educate the investors to be vigilant while taking investment decisions based on stock tips.
from no

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American