group-telegram.com/TIBEBnegni/2518
Last Update:
☯ኩርፊያ፣ ቂም፣ ጥላቻና ብቀላ ጊዜ ገዳይና የስኬታማ ህይወት ጠላት ናቸው። ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው። ልዩነት ሁሌም ይኖራል። በልዩነት አትበሳጭ። ከልዩነት ጋር መኖርን እወቅበት።
💜ዓለም የምትሽከረከረው፣ የምትሾረው፣ ወደፊት የምትራመደው በልዩነት ነው። ልዩነት የእድገት ምንጭ ነው። አላዋቂዎች ግን ልዩነትን የኩርፊያ ምንጭ ያደርጉታል። ያ ትልቅ ስህተት ነው!
☯ልዩነትን የምትፈታው በንግግር እንጂ በኩርፊያ አይደለም። ነገርን በልብ ይዞ ማመንዥክ ለራስም ለሌላውም አይጠቅምም። ኩርፊያ ጊዜን፣ ጤናን ሀብትን ይበላል። ኩርፊያ የቂም እናትና አባት ነው።
💜አመለካከትህ ቅንና በጎነትን የተላበሰ ይሁን። ካንተ የተለየ አመለካከት ያለው ሰው ሁሉ የተሳሳተ ነው ብለህ አትደምድም። በልዩነትም ይሁን በስምምነት ውስጥ ሁሌም የሌላውን ፍላጎት ለመረዳት ሞክር።
☮በተቻለህ ዓቅም የሌላውን ሰው ስሜት ላለማስቀየም ሞክር። እውነት ስለሆነ ብቻ ሌላውን የሚያስቀይም ንግግር አትናገር። በስሜት አትነዳ፣ ስሜትህን ተቆጣጠር።
💜ልዩነት ሁሉ በአንድ ጊዜ ካልተፈታ አትበል። ለጊዜ እድል ስጠው።
ልዩነትን በውይይት ፍታና ህይወትን ፍክት ብለህ ኑር!አለዚያም ከልዩነት ጋር በሰላም መኖርን ተለማመጂ!
✍ Toughe g.kebede
💚💚💚💚💚💚💙💙💚💙💚💙💚
ሰው ከመሆን በላይ ሌላ የሚያመሳስል ነገር የለም፡ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለክ አይደል የሚለው ። አድሮ አፈር በሚሆን ስጋች ፡ በፍቅር ኑረን ለነፍሳችን ሰላም እንስጣት፡፡
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💚💚💚💚💚💚
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
BY ሰው መሆን...
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/TIBEBnegni/2518