Telegram Group Search
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከፕሬዜዳንቱ እና ካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል "- አቶ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ

በትግራይ ከጊዚያዊ አስተዳደር " ከፕሬዜዳንቱ እና ከካቢኔው በላይ የሆነ የማይታዘዝ ሃይል ተፈጥሯል " ሲሉ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ ተናገሩ።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ባያውጅም መቐለ ጨምሮ በመላ ትግራይ በስሙ መጠራት ያለበት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አለ " በማለት አክለዋል።

ከህዳር 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የመቐለ ከንቲባ ሆነው በጊዚያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ የተሾሙት እና ህዳር 23/2017 ዓ.ም አንድ ጊዜ ብቻ ቢሯቸው ከገቡ በኋላ ያልተመለሱት ከንቲባው " ላዛ ትግርኛ " ለተባለ ሚድያ ሰፊ ቃለመጠየቅ ሰጥተዋል።

" ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ከመንግስት በላይ ሆኖ ከንቲባ ስራውን እንዳይሰራ ፤ ህዝብ ከከንቲባ ማግኘት ያለበት አገልግሎት እንዳያገኝ መከልከል የህግ ተጠያቂነት ከማስከተል በተጨማሪ በታሪክ ያስወቅሳል " ብለዋል።

ከ8 ወራት በፊት ሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ፤ ከ4 ወራት በፊት ማእከላዊ ዞን እንዲያስተዳድሩ በጊዚያዊ መንግስት ፕሬዜዳንት ፊርማ የተመደቡ ሃላፊዎች ተግባራቸው እንዳይፈፅሙ ስሙ ባልጠቀሱት ወታደራዊ አዛዥ የሚታዘዙ ጠበንጃ ባነገቡ ታጣቂዎች እንደተስተጓጎሉ ጠቅሰዋል።

እሳቸውም " ከፓሊሰ አቅም በላይ ያልሆነውን ጉዳይ የመቐለ አስተዳደር ዙሪያ በታጣቂዎች በማጠር ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ከሁለት ወር በላይ መከልከላቸው እጅግ አሳዛኝ እና የመንግሰት ትእዛዝ የጣሰ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ብለዋል። 

ፕሬዜዳንቱና ካቢኔው ሦስት ጊዜ ወደ ስራ ገበታቸው ገብተው ስራቸው እንዲሰሩ ቢያዝም አስተዳደሩን እንዲጠብቁ በታዘዙ ታጣቂዎች መከልከላቸው እጅግ እንዳሳዘናቸው እና እንዳበሳጫቸው ተናግረዋል።

" መንግስት መንግስት መምሰል አለበት ትእዛዝ እና ውሳኔ በማክበር እና በማስከበር ከመንግስት በላይ መሆን የሚፈልገውን አካል ማቆምን ማስታገስ  ይገባዋል " ብለዋል።

" ከፕሬዜዳንት እና ከካቢኔ በላይ በመሆን ታጣቂዎች በአስተዳደሩ ዙሪያ ያስቀመጠ አካል የወጣቶች ቁጣ እና መልእክት ተቀብሎ ያሰማራቸው ታጣቂዎች በአስቸኳይ ማንሳት አለበት " ያሉት ከንቲባው " ጉዳዩ ፓሊስን ይመለከታል ከፓሊስ አቅም በላይ ከሆነ የአድማ ብተና ሃይል ይሰማራል ፤ ከዚህ ውጭ ከአቅሜ በላይ ሆኗል የሚል ጥያቄ ባልቀረበበት ታጣቂ ሰራዊት ማስቀመጥ ከህግ በላይ መሆንን ያመለክታል " ሲሉ ስሙ ያልጠቀሱት ታጣቂዎች አሰማርተዋል ያሉትን አካል ተችተዋል።

መቐለ ካሉዋት 7 ክፍለ ከተሞች እና  33 ቀበሌዎች ዙሪያዋ የተወጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ከንቲባ ስራውን እንዲጀምር ፤ ህዝቡ መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ ፤ የጊዚያዊ አስዳደሩ ትእዛዝ እንዲከበር ድምፃቸው አስምተዋል ያሉት ከንቲባ ብርሃነ  " አሁንም መልስ ካላገኙ ከበፊት በላቀ ቁጥር ወጥተው ድምፃቸው ማሰማታቸው ይቀጥላሉ " ሲሉ ዝተዋል።

መቼ ወደ ተመደቡበት ስራ እንደሚገቡት ለቀረበላቸው ጥያቄ የተቆረጠ ቀን እንደማያወቁ  ተናግረዋል።

" ትግራይ ከገባችበት ፓለቲካዊ ቀውስ የምትወጣበት እንዱ እና ዋነኛ መንገድ መንግስት ሲኖራት የመንግስት ትእዛዝ እና ውሳኔ ሲከበሩ ነው ስለሆነም ከህግ እና መንግስት በላይ በመሆን ታጣቂ ያሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ " ሲሉ አሳስበዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እና በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደቡላት ከንቲባዎች ከስራ ውጭ ሆኖዉባት ከንቲባ ያጣቸው የትግራይ የፓለቲካ እና የኢኮኖሚ ከተማ የሆነችው መቐለ የከንቲባዋ ፅህፈት 'ታሽገዋል ' የሚል ወረቀት ተለጥፎለት   በግራና ቀኝ በቆሙ ፓሊሶች እንዲሁም ዙሪያዋ በታጣቂዎች ለ24 ሰዓት መጠበቅ ከጀመረች 64 ቀናት ተቆጥረዋል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አድርሶናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ ማስረጃ እንዳትሰጡ " - ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡ ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡ በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው…
#MoE

በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በክረምት መርሐግብር ሲከታታሉ ለቆዩ መምህራን የመውጫ ምዘና ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የምዘና ፈተናው መምህራኑ በሚኖሩባቸው አቅራቢያ ባሉ አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደተጠናቀቀ ማለትም ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ማሳሰቡ ይታወቃል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
' በጣም ከፍተኛና ልዩ ስጋት አለብን ! ' “ ኦፊሻል ስላልወጣ እንጂ ከሦስት ሳምንት በፊት ሥራ ቦታ ላይ አንድ የኮሌጁ ባለሙያ ተገድሏል በሽጉጥ ” - የኢትዮጵያ ህክምና ተማሪዎች ማኀበር የኢትዮጵያ ህክምና ተማሪዎች ማኀበር (ባሕር ዳር) “በጥይት ተገደሉ” በተባሉት በዶክተር አንዷለም ዳኘ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ “ከፍተኛና ልዩ ስጋት አለብን” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል። ማኀበሩ…
ፍትህ ! ፍትህ ! ፍትህ !

" ሀኪም ህይወት እያተረፈ ፣ህይወቱን መነጠቅ የለበትም! " - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከስራ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ በመገደሉ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ፍትህን በመጠየቅ ላይ ናቸው።

" ፍትህን እንሻለን ! " በሚል የፍትህ ጥያቄ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የዶ/ር አንዷለም ዳኜ ሐዘን በማስመልከት ፍትህ ጥያቄ በተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የቀረበበት የሀዘን ምሽት በጥበበ ግዮን ግቢ መካሄዱ ተገልጿል።

➡️ ለሃኪሞቻችን ጥበቃ ይደረግልን፤
➡️ አዳኙ ፣ አካሚው ሃኪም ለምን ተገደለ ፤
➡️ አትግደሉን፣
➡️ መድሃኒቱ ሃኪም ጥይት አይገባውም ወዘተ የሚሉ መፈክሮችና የፍትህ ጥያቄ አዘል ምልዕክቶች በስራ ባልደረቦቹ፣ በተማሪዎቹ እና በወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ቀርበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው " አንድን ትልቅ ሃኪም ቀብሮ ገብቶ ዝም ማለት እንደ ዩኒቨርሲቲ ከብዶናል " ብሏል።

" የተገደለብን፣ የተነጠቅነው፣ በርካታ የሆስፒታላችን ደንበኞች ፣ ህሙማን እንዲያድናቸው በወረፋ ቀጠሮ ይዘው የሚጠብቁትን የህዝብ ተስፋ፤ የአገር አንጡራ ሃብት ፣ ኢትዮጵያ ሃገራችን ሰፊ ሃብት ያፈሰሰችበትን ወጣት ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪም ነው፡፡ ፍትህ መጠየቃችንን እንቀጥላለን ! " ሲል አክሏል።

ሁሉም የፍትህ ጥያቄ ዘመቻውን እዲቀላቀል ጥሪ ቀርቧል።

ይኸው ከቀናት በኃላ እንኳን ዶክተር አንዷለም ዳኜን ስለገደሉ አካላት ምንም በይፋ የተነገረ ነገር የለም።

#JusticeforDrAndualemDagnie
#Healing_Hands_Should_Never_Be_Silenced_by_Guns.
#Protect_Physicians_Protect_Humanity.
#Protect_Physicians_Protect_the_Right_to_Heal.
#No_Physician_Should_be_killed_While_Saving_Others.
#Stop_the_Violence_Against_Those_Who_Heal.
#Physicians_Deserve_Safety_Not_Bullets.
#Stop_Killing_the_Healers_of_Humanity.
#Protect_the_Hands_That_Heal, #Not_the_Hands_that_Kill.
#No_Conflict_Justifies_the_Killing_of_a_Physician.
#Defend_the_defenders_of_health.
#Doctors_need_protection_not_persecution.
#Justice_for_Dr_Andualem_Dagnie

@tikvahethiopia
" ዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የምትጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ ተሳፋሩ " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (#ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎች የሚጓዙ መንገደኞች በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራቸው እንዲሳፈሩ አየር መንገዱ አሳስቧል።

ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደሚቀጥል ገልጿል።

" ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

🎁 ስድስት ወር ሙሉ ዳታ እንደልብ! ለረጅም ጊዜ የሚቆዩትን ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 1,000 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ሶሻል ሚዲያዉን ፏ ፏ እናድርግ! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም አስተማማኝ ኔትወርክ ጋር ወደፊት!⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ድልድዮች ዘላቂነት ያላቸው አይደሉም የብረት ናቸው። ወደ ኮንክሪት እንዲቀየሩ ጥያቄ እያቀረብን ነው ” - የሰሜን ወሎ ዞን መንገድ መምሪያ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የሚገኘውና ከባድ ጭነት ያየዘ ተሳቢ ሲጓዝበት ትላንት የተሰበረው ብረት ድልድይ በኮንክሪት መሰራት እንደሚገባው፣ ይህንንም ለፌደራል አካላት ማሳሰቡን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የድልድዩ መሰበር ያስከተለውን የትራንስፓርት እንቅስቃሴ መስተጓጎል ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄም፣ ለጊዜው ተለዋጭ መንገድ እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ መንገድ መምሪያ ገልጿል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፀሐይነው ሲሳይ ምን አሉ?

“ትላንት ከሰዓት በኋላ የተሰበረው መንገዱ ከወልዲያ ቆቦ አላማጣ ቆቦ የሚያዘልቅ፣ ከትግራይ ክልል የሚያገናኝ፣ ከፍተኛ ትራፊክ የሚተላለፍበት መንገድ ነው።

ከፍተኛ ጭነት የጫነ ተሳቢ መኪና ሲጓዝበት የብረት ድልድዩ ከነመኪናው ታጥፏል። የፌደራል መንገድ ስለሆነ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት አድርሰናል።

በሰዓቱም ችግር እንዳይፈጠር ተራ የሚያስጠብቁ አካላት እንዲያውቁት ተደርጎ ሥራ እየተሰራ ቆይቷል። ትላንትና ህብረተሰቡ እንዳይጉላላ በቅብብሎሽ ሰው እንዲተላለፍ ጥረት አድርገናል። 

መንገዱ አስቸኳይና ተለዋጭ መንገድ ስለሌለው ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ማሽን መድቦ በሰዓቱ ደርሷል። ሥራም ጀምሯል። ተለዋጭ መንገድ ከፈታ እየተደረገ ነው። ከፈታው አልተጠናቀቀም።

አሁን እየተሰራ ነው። የትራፊክ መጨናነቁን በከፈታው ትንሽ ማስተንፈስ ተችሏል። ሥራው እንደቀጠለ ነው። ግን ዘላቂ ነው ማለት አይቻልም። ለጊዜው ካጋጠመው ችግር አኳያ ነው ተለዋጭ መንገድ እየተሰራ ያለው”
ብለዋል።

አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ ጭኖ ነው ወይስ የድልድዩ የጥራት ችግር ነው? ስንል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄም ምላሽ ያሉትን ነግረውናል።

ምን መለሱ?

“በሚመለከታቸው ባለሙያዎች እናሳያለን። ግን ጭነቱም ክብደት እንዳለው ያሳያል። ተሽከርካሪው የድንጋይ ከሰል ነው ተጭኖ ወደ ድልድዩ የገባው የጭንት ክብደት ሊኖር እንደሚችል ያሳያል።

የሌላም ከሆነ ይታያል። በዋናነት ግን ድልድዩም ቢሆን የብረት ድልድይ ነው። ለስምንት ዓመታት አገልገልግሏል።

ይህ ብቻ ሳይሆን አካባቢው፣ በዚሁ በቀጠናችን በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ድልድዮች ዘላቂነት ያላቸው አይደሉም የብረት ናቸው። ወደ ኮንክሪት እንዲቀየሩ ጥያቄ እያቀረብን ነው። ሌሎችም የሚያሰጉን ይኖራሉ”
ነው ያሉት።

ይሄው ድልድይ በሰሜኑ ጦርነት የመሰበር አደጋ ደርሶበት ነበር እንዴ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ “ይሄኛው ሳይሆን አላውሃ ድልድይ ነበር ጉዳት የደረሰበት። እሱም የብረት ነው። ይሄም እዛው ቀጥሎ ያለ ነው” ብለዋል።

አሁን የመሰበር አደጋ የደረሰበት ድልድይ ለመጠገን ምን ያክል ወጪ እንደሚጠይቅ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ “እኛ ሥራ እንዲሰራ ነው ጥያቄ እያቀረብን ያለነው። ርዝመቱ ከ48 እስከ 50 ሜትር ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

“ቀላል ወጪ ይጠይቃል ተብሎ አይታሰብም። ምንም ቢሆን ከመሰራት ውጪ አማራጭ የለውም። ፌደራል ተለዋጭ መንገድ የለውም። መንገዱ ክልልን ከክልል፣ ወረዳዎችን ከዞን የሚያገናኝ ነው” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ " ተጠርጣሪው ተይዞ ለክልሉ ፖሊስ ተላለልፎ ተሰጥቷል " - ፖሊስ የ19 ዓመትዋን ወጣት በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ፥ ጥቅምት 19 /2017 ዓ.ም ሓበን የማነ የተባለች ፍቅረኛውን በተከራዩት የሆቴል ክፍል በጬቤ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ከቀናት ፍለጋ በኃላ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። በአሰቃቂ…
#Update

የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

ሓበን የማነ የተባለች ወጣትን በጭካኔ በመግደል ክስ የተመሰረተበት ዳዊት ዘርኡ የተባለ ወንጀለኛ ዛሬ ጥር 28/2017 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።

ፍርዱን ያሳለፈው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ነው።

አሰቃቂ ግድያው በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነበር የተፈፀመው።

ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል በቢላዋ ተገድላ መገኘቷንና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብር ስነ-ሰርዓት መከናወኑ በወቅቱ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ፓሊስ አሰቃቂ የግድያ ተግባሩ አስመልክቶ በወቅቱ በሰጠው መረጃ ፤ የነፍስሄር ወጣት ሓበን የማነ አስከሬን ከ2 ቀን በኋላ ነው በተገደለችበት የሆቴል ክፍል የተገኘው።

ገዳይ ወንጀለኛው አሰቃቂ ተግባሩ በመቐለ ከተማ ከፈፀመ በኋላ በአማራ ክልል በኩል በድብቅ ለውጣት ሲያሴር ደሴ ከተማ በአማራ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ለትግራይ ክልል ፓሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል።

በወቅቱም ለደሴ ህዝብና ለአማራ ክልል ፖሊስ ምስጋና ቀርቦ ነበር።

ፓሊስ ጉዳዩ  አጣርቶ አቃቤ ህግ ክሰ መስርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ዛሬ እሮብ ጥር 28/2017 ዓ.ም የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ባዋለው ችሎት ወንጀለኛው በዕድሜ ልክ ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
2025/02/06 00:45:22
Back to Top
HTML Embed Code: