group-telegram.com/ETH724/12
Last Update:
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት 30 ከመቶ በውጪ ሙሁራን 70 ከመቶ ደግሞ በሀገር ውስጥ ሙሁራን ተዘጋጅቷል።
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት 30 ከመቶ በተለያዩ ሀገራት ሙሁራን 70 ከመቶ ደግሞ በሀገር ውስጥ ሙሁራን ጥራቱ ተረጋገጦ የተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት እንደሆነ ትምህርት ሚኒስተር የስርዓተ ትምሀርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዛፍ አብርሃ ገለጹ።
ከነሀሴ 5-7/2013 ዓ.ም ድረስ በአርባ ምንጭ ማዕከል የመማሪያ ማስተማሪያ መጽሓፍት ዝግጅት ላይ ሲሰጥ በነበረው ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዳይሬክተሯ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአለም አቀፍ ጨረታ የካብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተወዳድሮ በማሸነፍ የአዲሱን ስርዓተ ትምህርት ጥራት ያረጋገጠ ጥናት አካሂዶ ሰነድ ሰጥቶናል ሲሉም ነው በዚህ ወቅት የገለጹት።
ይህ ስርዓተ ትምህርት እንደባለፉት ጊዜያት ቀጥታ ከውጭ ሀገራት የተቀዳ ሳይሆን የሀገር በቀል እውቀቶች አካቶ የተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት ነው ሲሉ ወ/ሮ ዛፍ አብርሃ ጠቅሰዋል።
የደቡብ ክልል ትምሀርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማሄ ቦዳ በበኩላቸው በክልሉ ወደ 7,773 አዘጋጆች ስልጠና መውሰዳቸውንና 2,700 መጽሐፍትም እንደሚዘጋጅ ጠቅሰዋል። አክለውም ክልሉ በርካታ ህብረ ብሔራዊነት ያለበት ክልል በመሆኑ ይህን ታሳብ ባደረገ መልኩ ዝግጅት የሚደረግ ይሆናል ብለዋል።
መረጃው የደቡብ ክልል ት/ቢሮ ነው።
@ETH724
@ETH724
BY ኢትዮ 7/24 መረጃ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/ETH724/12