group-telegram.com/HakimEthio/22251
Last Update:
"እሷን ማትረፍ ባልችልም ይህንን ልፅፍ ወደድኩ"
አንድ ልብ የሚነካ ክስተት ላጫውታቹ! በዚህ ገጠመኝ ለማህበረሰባችን ልጅም ፣ እህትም ፣ የትዳር አጋርም ፣ እናትም ፣ አያትም ለምትሆን አንዲት ሄዋን ጋር ይህ ልመና ጭምር የሆነ መልእክት ቢደርስ እና ቢተገበር ፋይዳው ብዙ ነውና አነብበው ቢጨርሱት ስል በትህትና እጠይቃለሁ!
ገጠመኙ ይህ ነው: ተመመላላሽ ክፍል (OPD) ቁጭ ብያለሁ... የቀጣይ ታካሚ ስም ጠራሁ ነርሷም አስተጋባች። ከደቂቃ በኋላ እድሜዋ በ20ዎቹ የሚትጠጋ ሰውነቷ የዛለ ፣ ፊቷም የገረጣ ቢመስልም ተስፋን የሰነቀ ታካሚ እያነከሰች በሰው ድጋፍ ገባች።
በዚህ ባጭር የስራ ልምድ ያወኳቸውን የበሽታ አይነቶች ሁሉ አእምሮዬ ማውጣት ማውረዱን ተያያዘው። ስሟን አመሳክሬ ባለቤቷ የያዘውን የሪፈራል እና የምርመራ ወረቀት ተቀበልኩት። ያየሁትን ማመን ተሳነኝ...
ዉጤቱ የመጨረሻ ደረጃ የማህፀን በር ጫፋ ካንሰር (Stage lVb cervical cancer) ይላል። በሚያስገርም ሁኔታ ደሞ ከተሰራጨበት የሰውነታ ክፍል አንዱ አከርካሪዋ (Thoracic vertebrae) መሆኑ ነበር። ሌላው መንፈሴን የረበሸኝ ነገር ደሞ ጥያቄ በምጠይቃት ሰአት እንኳን የእግሯን ህመም መቋቋም ስለማትችል ከ5 ደቂቃ በላይ መቀምጥ መቆምም ሆነ ካልተገላበጠች መተኛት እንደማትችል የነገረችኝ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ ልጆች እዳልወለደች ያወጋቺኝ ነበር።
ከሁሉም በላይ እዙሁ መሀል አገር አዲስ አበባ ሆና ይሄ ነገር መከሰቱ ብሎም ከልጅነቷ ጀምሮ በተማረችውን ፣ ባነበበችው እንዲሁም በሰማችው ልክ በእዝነ ልቦናዋ የሳለችው እሷነቷን እንደ ጉም በኖ እነደ ጢስ ተኖ ሲበትን ማየት ነበር።
እናም በየትኛውም የእድሜ ክልል ያላችሁ የማህበረሰባችን ዋልታ እና አሌኝታ የሆናችሁ እንስቶች የማህፀን በር ጫፋ ካንሰር በአገራችን በገዳይነቱም የአኗኗር ዘይቤንም ከሚፈታተኑ የካንሰር አይነቶች ቁጮ ላይ እደተቀመጠ ቀጥሏሏ።
ይህን ታሪክ ለማድረግ መንግሰት ፣ ፖሊሲ አውጪዎች (ነዳፊዎች) ፣ በሁሉም ደረጃ ያላችሁ የህክምና ባለሙያዎች ፣ የሚዳያ አጋሮች እና የጥበብ ቤተሰቦች የድርሻችንን እንድንወጣ ስል አሳስባለሁ።
ጥሩ ነገሩ ግን በሽታውን መከላከልም ፤ ምርመራ በማድረግ በጊዜ የሚደረስበት እና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መታከምና መዳን የሚቻል መሆኑ ነው።
Dr. Alelign Muntaz, Obgyn Resident
ቴሌግራማችን: www.group-telegram.com/sg/HakimEthio.com
BY Hakim
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/HakimEthio/22251