Telegram Group & Telegram Channel
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ወደ ቀን መርሃግብር ተቀይረን እንድንማር ከመግባባት ላይ ተደርሷል " - ተማሪዎች

ሰሞኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) መረሃግብር በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በግል ከፍለዉ መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት " ተመዝግበንና አስፈላጊውን ክፊያ አጠናቀን ትምህርት በመጀመር ሂደት ዉስጥ ባለንበት ዩኒቨርሲቲው ' አናስተምራችሁም ' ብሎናል " ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲዉ በበኩሉ ጉዳዩን ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በመነጋገር ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፆልን ነበር።

ቅሬታ አቅርበዉ የነበሩ ተማሪዎችና ወላጆች በዛሬው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳስታወቁት ዩኒቨርሲቲው የትምህርት መርሃግብሩን ከእረፍት ቀናት ወደ መደበኛ መርሃግብር በማዘዋወር ተማሪዎቹን ለማስተማር መወሰኑን አረጋግጠዋል።

" ዛሬ ተጠርተን ዉል ተፈራርመናል " ያሉት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) አመልካቾች " በዉሉ ላይ የተቀመጡ ጉዳዮች የመረሃግብሩ ከዕረፍት ቀናት (weekend) ወደ መደበኛ መቀየር ፣ አመልካቾች በግል ከፍለዉ የሚማሩ ስለመሆናቸው የሚገልፅ፣ ስለ ክፍያ አፈፃፀምና በዩኒቨርሲቲው እና በተማሪዎቹ መካከል ስለሚኖረዉ መብትና ግዴታ የሚደነግግ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

የተማሪ ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " ከከፍተኛ ጭንቅ ነዉ የገላገላችሁን፣ ምን እንደምናደርግ ጨንቆን ነበር ትምህርት ሚንስቴር እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም ላሳያችሁን በጎ ምላሽ እናመሰግናለን " ብለዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በግል ከፍሎ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ለሚወስዱ ተማሪዎች ያዘጋጀዉን ዉል በዚህ መረጃ ላይ ያካተትን ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት  ዶ/ር አክበር ጩፎ ስለጉዳዩ ትክክለኛነት ከመግለፅ ባለፈ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94149
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94149

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

In the past, it was noticed that through bulk SMSes, investors were induced to invest in or purchase the stocks of certain listed companies. Telegram users are able to send files of any type up to 2GB each and access them from any device, with no limit on cloud storage, which has made downloading files more popular on the platform. Asked about its stance on disinformation, Telegram spokesperson Remi Vaughn told AFP: "As noted by our CEO, the sheer volume of information being shared on channels makes it extremely difficult to verify, so it's important that users double-check what they read." Although some channels have been removed, the curation process is considered opaque and insufficient by analysts. Founder Pavel Durov says tech is meant to set you free
from sg

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American