Telegram Group Search
#Iran Vs #Israel

እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ሥፍራዎች እና የጦር አዛዦቿ ላይ ያነጣጠረ ከፍተኛ ጥቃት መፈጸሟን የእስራኤል መከላከያ ኃይል አስታውቋል።

በዚህ ከባድ በተባለው ጥቃት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃላፊ ሆሴይን ሳላሚ መገደላቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

እስራኤል " ኢላማ ያደረግኩት ወታደራዊ ይዞታዎችን ነው " ብትልም፤ የኢራን መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው በቴህራን የመኖሪያ ቤቶች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው እና ከተገደሉትም መካከል ሲቪሊያን ይገኙበታል ብለዋል።

የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው በኢራን የፈጸመችው ጥቃት 'ኦፕሬሽን ራይዚንግ ላየን' (የሚያንሰራራ አንበሳ ዘመቻ) ሲሉ የጠሩት አካል ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ኢራን ለእስራኤል የህልውና ስጋት መሆኗን ተናግረዋል።

ኢራን በምላሹ በቅርቡ አጸፋዊ የመልሶ ማጥቃት ልታደርስ እንደምትችል የገለጸችው እስራኤል የአስቸኳይ ጊዜ አውጃለች።

የኢራን መንግሥታዊ ቴሌቪዥን እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸውን ዘግቧል።

በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት እነማን ናቸው ?

➡️ ሆሴይን ሳላሚ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃላፊ ተገድለዋል።

➡️ የአገሪቱ የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ኃላፊ የነበሩት የኒውክሌር ሳይንቲስቱ ፍሬይዱን አባሲ ተገድለዋል። ፍሬይዱን አባሲ ለኢራን የኒውክሌር ማበልጸግ የአንበሳውን ድርሻ እንደተጫወቱ ይነገርላቸዋል። ሳይንቲስቱ ከዚህ ቀደም በአውሮፓውያኑ 2010 በቴህራን ጎዳና ላይ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ተርፈው ነበር።

➡️ የኒውክሌር ሳይንቲስት በቴህራን የሚገኘው የእስላሚክ አዛድ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መህዲ ቴህራንቺም ተገድለዋል።

አሜሪካ ተሳታፊ ነበረች ?

ኢራን " አሜሪካ የእስራኤልን ጥቃት ደግፋለች " ስትል የከሰሰች ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው አገራቸው እንዳልተሳተፈች ተናግረዋል።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቃቶቹ እንደሚፈጸሙ እንደሚያውቁ፤ ነገር ግን አገራቸው እንዳልተሳተፈች ለፎክስ ኒውስ ገልጸዋል።

እስራኤል ለፈፀመችው ጥቃት ከፍተኛ አፀፋ ከኢራን ይጠብቃታል ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው ከቢቢሲ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጨመረ።

እስራኤል ኢራን ላይ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ከ2020 በኋላ በቀን ውስጥ በዚህ ደረጃ ሲጨምር ከፍተኛው ነው ተብሏል።

የአንድ በርሜል የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 78 ዶላር ገብቷል።

አሁን ያለው ውጥረት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ መቆራረጥ እንዳይፈጥር ተሰግቷል።

ተንታኞች ውጥረቱ ተባብሶ በዚሁ ከቀጠለ ሁኔታው ​​የዓለምን የኃይል ገበያ የበለጠ ሊያናጋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ኢራን በቀን እስከ 3.3 ሚሊዮን በርሜል ታወጣለች፣ ይህም ከዓለም አቀፍ አቅርቦት 3 በመቶውን ይሸፍናል።

መረጀው የሲኤንቢሲ እና ቢቢሲ ነው።

Via @TikvahethMagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ምንድነው ያሉት ? 🔴 ፕሬዝዳንቱ አብዛኛው ንግግራቸው ስለ ሀገራቸው ኤርትራ የውስጥ ጉዳይ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ሀገራት ጉዳይ ነበር ! ኤርትራ ትላንት ቅዳሜ 34ኛ ዓመት የነፃነት በዓሏን አክብራለች። ለ34 ዓመታት አገሪቷን በብቸኝነት እያስተዳደሩ ያሉት ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለ34ኛ ጊዜ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዜዳንቱ 20 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው ንግግራቸው…
#Ethiopia🇪🇹

" አሁን ኩርፊያ መጥቷል ፤ መወራጨትም አለ " - የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?

" ለመተባበር ብዙዎችን ጋብዘናል ኤርትራን ሳይቀር ጋብዘናል ፤ አብረን እንስራ ብለናል ፤ ባህር ለሁላችን ይሁን ብለናል ፤ የ20 ዓመት ፍጥጫ ይቁም ብሎ መንግሥታችን የነበረውን ቁርሾ በመፍታት ወደ ልማት ፣ ወደ ኢንተግሬሽን፣ ወደ ጋራ ተጠቃሚነት ፣ ወደ አብሮ መበልፀግ እንድንገባ ኤርትራውያንም የሚጠቀሙት ጥቅም ካለ ከኢትዮጵያ እንዲጠቀሙ ኢትዮጵያም ከኤርትራ እንድትጠቀም በጣም ሰፊ ስራ ተሰርቷል ፤ ተልፍቷል።

በጣም ባልተለመደ መንገድ የኤርትራንና የኢትዮጵያን ግንኙነት ለመፍታት መንግሥታችን ረጅም ርቀት ሄዷል፤ ግን አልተሳካም።

አብረን እንጠቀም ነው እንጂ የባህር በር ይዤ እናተን እንደፈለኩ ላድርጋችሁ የሚል አስተሳሰብ ስላለ አይ እንደዛ ሳይሆን በጋራ ተጠቃሚነት ፣ በእኩልነት ነው ፤ የሆነ ቁልፍ መሳሪያ ይዘህ በቁልፍ መሳሪያ ይሄን ሁሉ ማህበረሰብ ለማሽከርከር መሞከር ልክ አይደለም የሚል ነገር ሲመጣ አሁን ኩርፊያ መጥቷል መወራጨትም አለ። "

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiotelecom

🆕🎁 የ100 ብር አየር ሰዓት ሲሞሉ 30 ብር እንደሚመረቅልዎ ሰምተዋል

በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp የ100 ብር ካርድ ሲሞሉ ተጨማሪ የ30 ብር የአየር ሰዓት ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡

👉 በዕለቱ በድጋሚ ካርድ ከሞሉ 25% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ!

💥 የአየር ሰዓትዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ ይሙሉ፤ በየዕለቱ ተጨማሪ ስጦታ ያግኙ!

🗓 እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2017 ዓ.ም


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
50ሺህ ብር ሊሸለሙ ነው!

ሰኔ 29 የሚወጣው ቶምቦላ ሎተሪ ገበያ ላይ ነው!

ዛሬ ከታች ባለው ሊንክ የቶምቦላ ሎተሪ ለሚቆርጡ 5 እድለኞች ለእያንዳንዳቸው የ10ሺህ ብር ሽልማት አዘጋጅቷል.

የቶምቦላን ሎተሪን https://www.ethiolottery.et/am?affiliate=684c3f42ba9392adbfc0f689 እዚህ ባለው ሊንክ በመጫን ተመዝግበው ይቁረጡ!

በ1ኛ እና በ2ኛ ዕጣ ባለሶስት እንዲሁም ባለሁለት መኝታ መኖሪያ የቤት ባለቤት ይሆናሉ፡፡
ከቤቶቹ በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ!

በ3ኛ እና በ4ኛ ዕጣ ደግሞ SUV ID-6 ጨምሮ ዘመናዊ የኤሌትሪክ የመኪና ባለቤት ይሆናሉ፡፡
ከመኪናዎቹ በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ!

ከወዳጅዎ ጋር ይጋሩ!  ቶምቦላን ስጦታ ይላኩ!

ለተጨማሪ መረጃ በ +251977717272 ይደውሉ!

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!
#ትግራይ

" የፕሬዜዳንቱ ትእዛዞች ይጣሳሉ ፤ የመኪና መንገዶች በዘፈቀደ ይዘጋሉ ህገ-ወጥነት እየተስፋፋ ነው " ሲሉ የትግራ ክልል ነዋሪዎች አማረሩ።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል ) ግንቦት 25/2017 ዓ.ም የፃፉት ደብዳቤ ከጉምሩክ እውቅና ውጪ ኬላ ሰርቶ መኪኖች መፈተሽ እንዲቆም ያዛል።

ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው በየደረጃው ያሉ የፀጥታ ሃላፊዎች ትእዛዙ እንዲያስፈፅሙ በአፅንኦት አሳስበው ነበር ፤ ሆኖም የትእዛዝ ደብዳቤው ከተፃፈ ከ11 ቀናት በላይ ቢቆጠሩም የተነሳ ኬላ የለም።

በተያያዘ በዋና መኪና አስፋልት አጠገብ በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎች በአከባቢያቸው የሚፈጠር የመልካም አስተዳደር እጦት ትኩረት እንዲያገኝ የመኪና መንገድ ይዘጋሉ።

ትናንት ሰኔ 5/2017 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ተምቤን በሚወስደው ዋና የአስፋልት መንገድ በደጉዓ ተምቤን ወረዳ ማርያም ቆራር ተብሎ በሚጠራ ቦታ የመኪና መንገድ ለሰዓታት ተዘግቶ በርካታ አሽከርካሪዎችና ተጓዦች ለእንግልት ተዳርገዋል።

" የተሰጠን መሬት የለውጥ ደጋፊ በመሆናችን ምክንያት ልንቀማ ነው " ያሉ ወጣቶች ናቸው መንገዱ ለሰዓታት የዘጉት።

ፓሊስ ወጣቶቹ መንገዱ እንዲከፍቱ የሰጠው ማሳሰብያ ባለመከበሩ ምክንያት ጥይቶች ከመተኮስ አልፎ ህገ-ወጥ ተግባሩ አስተባብረዋል ያላቸውን አስሯል።

በትግራይ በየቀኑ የሚታያዩ ያልተለመዱ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚገታ ከላይ እስከታች ጠንካራ መዋቅር ያለው መንግስትና አስተዳደር ያስፈልጋል ብለዋል ሁኔታዎች ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአማራ ክልል ከስራ ተባረው የነበሩት 5 የጤና ባለሙያዎች ወደ ስራ ተመልሰዋል ፤ የታሰሩትም በሙሉ ተለቀዋል " - የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ማህበር በአማራ ክልል ከሰሞኑ የሀኪሞች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከስራ ተባረው የነበሩ 5 የጤና ባለሙያዎች ወደ ስራ ሲመለሱ ታስረው የነበሩ 32 ቱ ደግሞ መለቀቃቸውን የአማራ ክልል ጤና ባለሙያዎች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፀ። በማህበሩ የአባላት…
" በአጠቃላይ ባለሙያዎች በሀሰተኛ ሽብር ክስ ተከሰው ቢሆንም የተያዙት እየተለቀቁ ነው። ያልተለቀቁም እንዲለቀቁ መልዕታችን ነው " - ጤና ባለሙያዎች

ከጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ጋር ከተያያዘ በርከታ ባለሙያዎች መታሰራቸው ይታወሳል።

ጉዳዩን የሚከታተሉና ስማቸውን እንዲገለጽ ያልፈለጉ ባለሙያዎች ለቲክቫህ አትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ አሁን ላይ ጤና ባለሙያዎቹ ከእስር እየተለቀቁ እንደሆነ ፤ የሚቀሩም እንዳሉ ፤ አብዛኛዎቹ ከትላንት በስቲያ ማታ ድረስ ወደቤታቸው እንደገቡ ተናግረዋል።

" በአጠቃላይ ባለሙያዎች በሀሰተኛ ሽብር ክስ ተከሰው ቢሆንም የተያዙት እየተለቀቁ ነው። ያልተለቀቁም እንዲለቀቁ መልዕታችን ነው። የባለሙያዎች መፈታታቸው ደስ ቢለንም መጀመሪያውንም መታሰር አልነበረባቸውም " ብለዋል።

" መደራጀትና ጥያቄ መጠየቅ ሰብዓዊ መብት ነው። አሁንም ጥያቄ እስካላቸው ድረስ በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ይችላሉ ፤ የሚመለከታቸው አካላትም ከቃላት የዘለለ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው እናምናለን " ሲሉ አክለዋል።

ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተጀምሮ የነበረው ውይይት ከምን ደረሰ ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ " ከሚኒስቴሩ ጋር ለተጀመረው ውይይት ሁለተኛ ጥሪ ነበር ፤ ግን ይፋ ያልሆነና በቃላት ብቻ የተደገፈ ስለነበር ቀጥሮ አክብረው የሄዱ ለደርድር የተወከሉ ባለሙያዎች ‘የምን ስብሰባ’ ተብለው ተመልሰዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሁንም የጤና ባለሙያዎች የመብት ጥያቄዎቻቸው እንዲመለሱ አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" 20 ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተይዘው በጤና ጣቢያው ግቢ ድንኳን ውስጥ ላይ ነው ያሉት " - የጤና ጣቢያ ባለሙያ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ጎልጎታ ቀበሌ ውስጥ 20 ሰዎች በኮሌራ በሽታ መያዛቸውን የአካባቢው ጤና ባለሙያዎችና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።

በሜርቲ ወረዳ ጎልጎታ ጤና ጣቢያ የህክምና ባለሙያ የሆኑትና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት በጤና ጣቢያው 20 ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተይዘው መግባታቸውንና በግቢው ውስጥ ድንኴን ተዘጋጅቶላቸው ለብቻቸው ህክምና ሲደረግላቸው መቆየቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ሌላው ስማቸውን በሚስጥር እንድንይዝ የጠየቁን የቀበሌው ነዋሪ ፥ ልጃቸው በበሽታው መያዙ ተነግሯቸው በድንኳኑ ውስጥ ህክምና እየተሰጠው እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አቶ ዋርዮ ቱሬ የተባሉ የጎልጎታ ቀበሌ ነዋሪ ደግሞ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በመርቲ ወረዳ ጤና ጣቢያ ውስጥ ተለይተው ህክምና ሲደረግላቸው መመልከታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በወረዳው ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት በመኖሩ ንፅህናው ያልተጠበቀ የዝናብና የወንዝ ውሃ እንደሚጠቀሙ ገልፀዋል።

ስሜ አይጠቀስ ያሉት የህክምና ባለሙያው በኮሌራ ከተያዙት ሀያዎቹ ሰዎች ሶስቱ ሰዎች አገግመው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን ተናግረዋል።

ባለፈው አመት በተመሳሳይ ወቅት በሽታ ተክስቶ እንደነበር የገለፁት ባለሙያው በርካታ ሰዎች ተይዘው አገግመዋል ብለዋል።

በወረዳው ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት በመኖሩ
ምክንያት ነዋሪዎቹ ለበሽታው በተደጋጋሚ እንደሚጋለጡ ጠቅሰው በሽታውን ለመግታት ህብረተሰቡ የግል እና የአከባቢ ንፅህና እንዲጠብቁ ትምህርት እየተሰጠ ነው ብለዋል።

የመርቲ ወረዳ ነዋሪዎች እና የጤና ባለሙያው የውሃ እጥረት ምክንያት ነው የኮሌራ በሽታ የተከሰተው ብለው ላነሱት ቅሬታ ከወረዳው ውሃ ሀብት ጽህፈት ቤት መረጃ ለማግኝነት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamliyNekemte

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እንዲህ አይነት አቅጣጫ ስታስቀምጥ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት፣ የቴሌኮም አገልግሎት መስፋፋትን፣ የሞባይል ስልክ ስርጭትን፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማደግን ማየት አለብህ " - የባንክ ባለሙያ  

የገንዘብ ሚኒስቴር በግብይት ወቅት ከ 10,000 ብር በላይ ጥሬ ገንዘብን መጠቀም የሚከለክል ህግ ሊያወጣ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

በሒደት ላይ የሚገኘው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ሲፀድቅ ከ10,000 ብር በላይ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መፈፀምም እንደሚያስቀጣ ተዘግቧል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ውይይት እንደተደረገና አዋጁ ያስፈለገው በጥሬ ገንዘብ የሚፈፀም ግብይትን ለመገደብ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የጠየቃቸው አንድ ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ አሰራሩ ተገቢና ከረዥመም ጊዜ በፊት ጀምሮ ሲነሳ የነበረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህን አቅጣጫ የመስጠት ስልጣን የብሔራዊ ባንክ ነው ትግበራውም በአንዴ ሳይሆን ጊዜ ይፈልጋል ሲሉ ስሜ እንዳይጠቀስ ያሉት ባለሙያ ገልፀዋል፡፡

ባለሙያው በዝርዝር ምን አሉ ?

" የዚህ ዓይነቱ አሰራር እንዲተገበር ምክረ ሀሳብ የቀረበው የዛሬ አስራ አምስት አመት ነበር፡፡ ከያኔው ጀምሮ ከወረቀት/ ከብር ኖት ጋር የማይያያዝ/ፔፐርለስ አገልግሎት መስጠት አለብን የሚል ሀሳብ ሲቀርብ ነበር፡፡

ህዝቡ ብር በጆንያ እና በአይሱዙ እያጓጓዘ መኖር የለበትም፡፡ እንዲህ ዓይነት አሰራር በሌላውም አለም በአውሮፓም በአሜሪካም የተለመደ ነው፡፡ ለግብይት በጥሬ ገንዘብ ይዘህ የምትንቀሳቀሰው መጠን ገደብ አለው፡፡

በጀርመን ከሁለት ሺህ ዩሮ/ማርክ በላይ ይዘህ መንቀሳቀስ አትችልም ከያዝክ ደግሞ ይወረሳል፡፡ ይህ ደግሞ ጥቅም አለው፡፡
በዚህ አይነቱ አሰራር ህዝብረተሰቡን ወደ ዲጂታላዊ የፋይናንስ አገልግሎት ታመጣዋለህ፡፡

ሌላው ደግሞ ለብር ማተሚያ የሚወጣ ለማጓጓዣና የተበላሸ ብር/Mutilated currency (የተቀደደ፣ የተጣጠፈ፣ የተጎዳ) ብር ለማስወገድ የምታወጣውን በቢሊዮን የሚገመትን ወጪ ታድናለህ፡፡

መንግስት በዚህ አሰራር የሚያድነውን ወጪ ለህዝቡ ትራክተርና ማዳበሪያ ሊገዛለት፣ ትምህርት ቤትና ሆስፒታል ሊገነባለት ይችላል፡፡

ህዝቡ ጥሬ ገንዘብ ይዞ ሲዘዋወር ወይም እቤቱ በማስቀመጥ የሚገጥመውን የዘረፋ ወንጀልም ትቀንሳለህ፡፡ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ትቆጣጠራለህ፡፡

ይህ አሰራር ግን በአንድ ሌሊት ይተግበር መባል የለበትም፡፡ የቴሌኮም ኔትወርክ ካደገ በኋላ ፣ የባንክ አገልግሎት ተስፋፍቶ፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ሲጠናከርና ብሔራዊ ባንክም ተዘጋጅቶበት፣ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ትምህርት ሰጥቶ ነው እንዲህ ዓይነት ውሳኔ መተላለፍ ያለበት፡፡ ብሔራዊ ባንክ አቅጣጫ አስቀምጦ ነው መደረግ ያለበት፡፡

አሁን በገንዘብ ሚኒስቴር የተቀመጠውን አቅጣጫ ብሔራዊ ባንክ ተቀብሎታል ወይ ? ነው፡፡ ይህን አቅጣጫ ማስቀመጥ ያለበት እሱ ነው ገንዘብ ሚኒስቴር አይደለም፡፡

የገንዘብ ማስተላለፍን ስርዓት የሚወስነው ብሄራዊ ባንክ ነው ገንዘቡን የሚያትመው እሱ ስለሆነ፡፡ ስለ ገንዘብ ዝውውርና ልውውጥ ገደብ ማውጣት ያለበት እሱ ነው፡፡

ለአምጪው እንዲከፈል ህግ ያስገድዳል የሚለውን የባንኩን ህግ ጥሰህ በዲጂታል ካልሆነ በቀር ብርን አልቀበልም ማለት እንዴት ይቻላል ? የብሩ ባለቤት እኮ ብሔራዊ ባንክ ነው፡፡ አሁን ይህን አቅጣጫ ሲቀይሱ ብሔራዊ ባንክን አማክረዋል ወይ ? የሚለው ሊታይ ይገባል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ትንሽ ቆዩ መጀመሪያ ህዝቡን ላስተምር ሊላቸው ይችላል፡፡

ገንዘብ ነክ ጉዳይ ሁሉ በብሔራዊ ባንክ ነው የሚከናወነው፡፡ የገንዘብ ዝውውርን፣ ፍሰትን፣ ልውውጥን የሚመለከቱ መመሪያዎች፣ ህጎችና ደንቦች በዚህ ነፃ ተቋም ነው መውጣትና መመራት ያለባቸው፡፡

ዲጂታላይዜሽን መጣ ሲባል የክፍያ ሁኔታም እንደዚሁ ዲጂታላይዝ እንደሚደረግ ስለሚታወቅ ይህን አሰራር ማስተዋወቅ የሚገባው ብሔራዊ ባነክ ነው፡፡ ብሔራዊ ባንክስ ምን ይላል ?    

ሌላው ደግሞ እንዲህ አይነት አቅጣጫ ስታስቀምጥ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት፣ የቴሌኮም አገልግሎት መስፋፋትን፣ የሞባይል ስልክ ስርጭትን፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማደግን ማየት አለብህ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ አለ ወይ ? ብለን መጠየቅ ይገባል፡፡

አብዛኛው የገጠሩ ህብረተሰብ የባንክ ተጠቃሚ አይደለም የባንክ ሒሳብ የለውም ፣ ስልክ አይጠቀምም፣ ሞባይል ስልክም የለውም፡፡ በሬውን ሲሸጥ እንዴት ነው ገንዘቡን የምትሰጠው፡፡ ነጋዴውስ እንዴት ነው ከገበሬው ለገዛው ሸቀጥ ክፍያ የሚፈፅመው፡፡ ገበሬው በዚህ ምክንያት ሸቀጥ መሸጥ ቢያቆም በከተማም እኮ የሸቀጥ እጥረት ሊፈጠር ይችላል፡፡

ስለዚህ አሰራሩን በየደረጃው የሚተገብሩት ነው የሚመስለኝ፡፡ እንደ ቦታው ርቀትና እንደ ቴክኖሎጂው መስፋፋት እየታየ በአንዴ ሳይሆን በሒደት መተግበር ያለበት ነገር ነው የሚመስለኝ፡፡ እንደዛ ካልሆነ ግን ገበሬው መልሶ የደላሎች መጫወቻ ሊሆን ነው፡፡ በእኔ ሞባይል ላስገባልህ ይህን ያህል ክፈለኝ ይላል ደላላው፡፡ በኮሚሽን ማለት ነው፡፡ ሌላ የማጭበርበሪያ መንገድም ሊሆን ይችላል፡፡ ስሜታዊ ሆነህ ከገጠር እስከ ከተማ ከመሀል እስከ ጫፍ በአንዴ ላስፈፅም ብትል አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የአቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ ያለመከሰስ መብት ተነሳ። " በሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር እና በከፍተኛ የኮንትሮባንድ እና አደንዛዥ ዕፆች ንግድ ተሰማተዋል " የተባሉት ባለስልጣን በቁጥጥር ስር ውለው ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ። የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስን ያለመከሰስ…
" አቶ አለማየው ጢሞቴዎስ ለ2 ዓመታት በጥብቅ ዲሲፕሊን ተገምግመው በማስጠንቀቂያ እና በሂስ እንዲታለፉ ተደርገዋል " - በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት

ያለ መከሰስ መብታቸው የተነሳው የቀድሞው የሲዳማ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየው ጢሞቴዎስ በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ዛሬ ባሰራጨው መረጃ ፥ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ በተከታታይ 2 ዓመታት በጥብቅ ዲሲፕሊን ተገምግመው በማስጠንቀቂያ እና በሂስ እንዲታለፉ መደረጋቸውን ጠቁሟል።

በዚህም በራሳቸው ላይ ማሻሻሎችን በማምጣት በፀጥታ ተቋማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ መቻላቸው ፤ ከጥፋታቸው ተምረው እና ታርመው እየሰሩ እንደነበርም ገልጿል።

ይህ ባለበት ሁኔታ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፓርቲ መርህ ባፈነገጠ መልኩ የክልሉ መንግስት ላይ በተቃራኒው ሲሰሩ እና ከህገወጥ አካላት ጋር ሲገናኙ እንደነበር ጠቁሟል።

በዚህም ምክንያትና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ከነበራቸው የስልጣን ገደብ በላይ በመጠቀማቸው ፓርቲው የእርምት እርምጃን በመውሰዱ ምክንያት ከስራ ገበታቸው ላይ በመቅረት ፓርቲው በስም በግልጽ ጠቅሶ ካልጠራቸውና " የሽብር አካላት " ካላቸው አካላት ጋር ግኑኝነት ሲያካሂዱ እንደተደረሰባቸው አመልክቷል።

በዚህም የተነሳ ሲመሩት የቆየው ተቋም መጥራት ስላለበት በፓርቲ ማዕከል ሰነድ ተዘጋጅቶ ከፀጥታ አመራሮች ጋር በመነጋጋር ሰፊ ወንጅሎች ሲፈፅሙ እንደቆዩ ማወቅ እንደተቻለ ፤ በቀጣይም የማጥራት ሂደቱ በፓርቲው የአሰራር መሰረት እየተካሄደ የሚዘልቅ እንደሆነ ገልጿል።

አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ምንም እንኳን ምክር እና ተግሳፅ ቢሰጣቸውም የግል ጥቅማቸውን ለማግኘት ሲሉ ፦
- በኮንትሮባንድ ንግድ፣
- በህገወጥ መሣሪያ ዝውውር፣
- ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም፣
- የስርዓት ግልበጣና በሌሎች መሠል ወንጀሎች በመጠርጠራቸው ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አሳውቋል።

ቀጣይ ሂደቱ የፍርድ ቤት እንደሆነም ጠቁሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የ2026 - 2027 የሁበርት ኤች. ሀምፍሬይ ፌሎሺፕ ፕሮግራም ክፍት ተደርጓል ፤ እርሶም ያመልክቱ።

በአሜሪካ መንግሥት ፈንድ የሚደረገው ይኸው ፕሮግራም በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን (እድሜያቸው ከ32- 46) የሚመለከት ሲሆን አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ለአንድ የአካዳሚክ አመት (በnon-degree program) ብቃትን ለማሳደግ እድል የሚሰጥ ነው።

ማነው ማመልከት የሚችለው ?

- እድሜያቸው ከ32 እስከ 45 ዓመት
- በምትሰሩበት የስራ ዘርፍ በትንሹ 5 ዓመት የሙሉ ሰዓት ስራ ልምድ ካላችሁ
- የመጀመሪያ ዲግሪ ካላችሁ
- ጥሩ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ከሆናችሁ (የTOFEL ፈተና ሊኖር ይችላል)
- የኢትዮጵያ ዜግነት ያላችሁ ወይም በቋሚነት በህጋዊ መልኩ በኢትዮጵያ የምትኖሩና ፓስፖርት ማግኘት የምትችሉ
- ፕሮግራሙ በሚሰጥበት ጊዜ ከመ/ቤቱ የስራ እረፍት ሊያፅፍ የሚችል

መስኮቹ ምን ምን ናቸው ?

1. ሂማውን ኤንድ ኢንስቲቱሽናል ካፓሲቲ
ለምሳሌ ፦
° ኢኮኖሚክ ፖሊሲ ኤንድ ፋይናንስ፣
° ፐብሊክ ፖሊሲ አናለሲስ ኤንድ አድሚኒስትሬሽን፣
° ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ኤንድ ማኔጅመንት፣

2. ራይትስ ኤንድ ፍሪደም
ለምሳሌ ፦
° ጆርናሊዝም/ጋዜጠኝነት ኤንድ ኮሚኒኬሽን፣
° ሂውማን ራይትስ ኤንድ ሎው/ህግ

3. ሰስቲነብል ላንድስ
ለምሳሌ ፦
° አግሪካልቸር/ግብርና ኤንድ ሩላር ዴቨሎፕመንት፣
° ኢንቫይሮመንታል ፖሊስ እና ናቹራል ሪሶርስ ፣ አርባን ኤንድ ሪጅናል ፕላኒንግ

4. ትራቪንግ ኮሚዩኒቲስ
ለምሳሌ ፦
° ፐብሊክ ሄልዝ ኤንድ ፖሊሲ ኤንድ ማኔጅመንት
° ሰብስታንስ አብዩዝ ኢዱኬሽን ኤንድ ፖሊሲ
° ኢዱኬሽን አድሚኒስቴርሽን፣ ፕላኒንግ ኤንድ ፖሊሲ

ለማመልከት ምን ያስፈልጋል ?

CV
የፕሮግራም ፕላን (ለማሳካት ተስፋ የምታደርጉት)
2 የድጋፍ ደብዳቤ (አንዱ ከአሁን አሰሪ)
ኮፒ ትራንስክሪፕት (አመልክታችሁ ለኢንተርቪው ካለፋችሁ ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት ያስፈልጋል)

ማመልከቻችሁን በኦንላይን በዚህ ድረገጽ ብቻ፦ https://apply.iie.org/huberthhumphrey አስገቡ።

ከጁላይ 31,2025 በፊት ብቻ ነው ማመልከቻ ማስገባት የሚቻለው።

ስታመለክቱ ግልጽ ያልሆነላችሁ ጥያቄ ካለ በ [email protected] ላይ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲን ማነጋገር ይቻላል።

NB. በፕሮግራሙ ወቅት ማንኛውም የቤተሰብ አባል አብሮ መሄድ አይችልም።

(ተጨማሪ ዝርዝር ማብራሪያዎች ከላይ በሁለት ገጽ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
2025/06/14 01:22:25
Back to Top
HTML Embed Code: