group-telegram.com/theonlytruth1/34
Last Update:
በየ እምነቱ ይፀልይ
ዓለምን እያስጨነቃት ባለው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙ ሰዎች እንደ መፍትሄ ሲናገሩት ከሰማውት መካከል አንዱ #በየእምነታችን #እንፀልይ የሚል ነው ።
ይህን በየ እምነት መፀለይ የሚለውን ሳስብ #እንፀልይ የሚለው በጣም አስፈላጊ ነው ። ነገር ግን መነሳት ያለባቸው ወሳኝ ጥያቄዎችን አግኝቻለሁ ፦
#1ኛ/ በየ እምነታችን የሚለው በዓለም ውስጥ ስንት ዓይነት እምነት አለ ? ስንት እሚታመንስ አለ?
#2ኛ/ እንፀልይ የሚለው ከሠዎች ዘንድ መፍትሄ እንደጠፋ በመረዳት
ከእኛ ውጭ የሆነ ማንነት መፍትሄ እንዲሰጠን እንለምን እንጠይቅ የሚለው በጣም መልካም ነው።
ነገር ግን መነሳት ያለበት ጥያቄ ? ዓለም በሙሉ መፍትሄ ላጣችለት የስልጣኔ ማማ ላይ ያሉትን ሀገሮች ያንበረከከውን ኮሮናን ሊያስወግድ #የሚችል ማን ነው ? የምንፀልየው ወደ ማን ነው?
በየ እምነታችንእንፀልይ ሲባል እውነተኛው አምላክ ፀሎትን ሰምቶ ሊመልስ የሚችለው
አምላክ (elohim) አንድ እርሱም እግዚአብሔር ብቻ ነው?
የፀሎት አድራሻ ወደ ማን ነው ? ስንል
ቃሉ እንዲህ ይላል ፦
(መዝሙረ ዳዊት 65 )
------------
1 … ለአንተም ጸሎት ይቀርባል።
2 #ሥጋ #ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል።
ይህ ቃል ፥በየ እምነታችን እንፀልይ የሚለውን የሰዎች መረዳት ሁሉ ከንቱ የሚያደርግ ነው ። የስጋ ለባሽን ሁሉ (የሰውን ሁሉ) ፀሎት ብቻ ሳይሆን #የፍጥረትን ሁሉ ፀሎት የሚሰማው
" ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፥ የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ መብልን የሚሰጠው …
(መጽሐፈ ኢዮብ 38: 41)
ሁሉን የፈጠረው አምላክ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ያስረዳል ።
(ትንቢተ ኤርምያስ 32 )
------------
16 ……እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦
17 አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም።
ፀሎትን የሚሰማው ጆሯችንን የፈጠረው አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው ፦
(መዝሙረ ዳዊት 94 )
------------
8 የሕዝብ ደንቆሮች ሆይ፥ አስተውሉ፤ ሰነፎችማ መቼ ይጠበባሉ?
9 #ጆሮን የተከለው #አይሰማምን? ዓይንን የሠራው አያይምን?
" #የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን #ጆሮቹም ወደ #ጩኸታቸው ናቸውና።"
(መዝሙረ ዳዊት 34: 15)
ሁሉንም የፈጠረ አምላክ (ELohim) እግዚአብሔር ነው ፦
(ትንቢተ ኢሳይያስ 40 )
------------
28 አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።
29 ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
የፀሎት አድራሻ ወደ እግዚአብሔር ሲሆን ፦
" ……በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።"
(የሐዋርያት ሥራ 12: 5)
የምንፀልየውም በኢየሱስ ስም ነው ፦
" …… አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 16: 23)
ከእግዚአብሔር ውጭ ወደ ማንምና ወደ ምንም አድራሻቸውን ያደረጉ ፀሎቶች ሁሉ ሰሚም መላሽም የላቸው ።
(ትንቢተ ኢሳይያስ 45 )
------------
20 ……… ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
21 …… ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም።
22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
ዳዊት እንዲህ አለ ፦
" በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን #ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም #ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን #ሰማኝ፥ #ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው #ገባ።"
(መዝሙረ ዳዊት 18: 6)
ወዳጀ አንተስ የምትጠራው የምትጮኸው ወደማን ነው?
ሸር በማድረግ በየ እምነታችን ለሚሉት ተክክለኛውን አድራሻ እንናገር ።
የናተው channel @theonlytruth1
@theonlytruth1
BY እዉነት ብቻ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/theonlytruth1/34