TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray
ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።
በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል።
በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች ያካተቱ ሰልፈኞች ደግሞ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚነት (null and void እንዲሆን) እንዳይኖረው ፤ ጦርነት የሚፀየፉና ጅምር ሰላም እና ለውጡ እንዲቀጥል የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል።
በሰሜናዊ ምዕራብ ፣ ማእከላዊ ዞኖች መቐለ ከተማ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት ብቻ የጠራቸው ሰልፎች ሲካሄዱ ፤ በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች በደጋፊ እና ተቃዋሚ በአንድ ጊዜ የተጠሩ ሰልፎች ተከናውነዋል።
በውቅሮ ከተማ የፀጥታ አካላት በራስ ተነሳሽነት ለመውጣት በሞከሩት ላይ ለመበተን የሞከሩ ሲሆን ፤ በዓዲግራት የነበሩት የለውጥ ደጋፊዎች ላይ ግን ለመበተን የተደረገ ሙከራ እንደሌለ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዘግቧል።
ትናንት ጥር 17/2017 ዓ.ም በደቡባዊ ዞን የተለያዩ ከተሞች " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚቃወም ጦርነት የሚያወግዝ ሰላምና ለውጥ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ የተካሄደ ሲሆን ዛሬ እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት የጠራው ሰልፍ በዞኑ አልተካሄደም።
በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት በጠራው ሰልፍ የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?
- የትግራይ ሰራዊት ውሳኔ ይተግበር !!
- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በአስቸኳይ ይስተካከል !!
- የፕሪቶሪያ ውል ይተግበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የህወሓት ህጋዊነት በአስቸኳይ ይመለስ !!
- የውጭ ጣልቃ ገብነት አንቀበልም !!
- ሰራዊታችን ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ አንቀበልም !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት መተግበር ለትግራይ እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ዋስትና ነው !!
በራስ ተነሳሽነት ወጣቶች በብዛት በተሳተፉባቸው ሰልፎች የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?
- የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም !!
- የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የህዝብ አገልጋዮች እንጂ የአንድ ቡድን ከለላ አይደሉም !
- የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
- የሚቆም ትግል እና ለውጥ የለም !!
- ወጣቶች ለልማት እንጂ ለጦርነት አንሰልፍም!!
- የተረጋጋ መንግስት ለመትከል የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው !!
-ጊዚያዊ አስተዳደሩ ወደ መደበኛ መንግስት የሚያሸጋግረን በቸኛ ህጋዊ ተቋም ነው !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲፀና እንፈልጋለን !!
... ሲሉ ተደምጠዋል።
በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ ዛሬ ጥር 18/2017 ዓ.ም መቐለ ጨምሮ በመላው ትግራይ የሚካሄደው ሰልፍ መግባባት የተደረገበት እና የተሟላ ጥበቃ የሚደረገበት ነው ያለ ሲሆን ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በኩል ጥር 17/2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የተጠራ እና የተፈቀደ ሰልፍ የለም ብሎ ነበር።
የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ህወሓት ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በቂ ጥበቃ ለመስጠት በመቸገሩ ምክንያተት ቀን እንዲቀየርለት ሲጠይቅ : የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ትእዛዝ ተላልፈው ስበብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ በሚያካሂዱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ማስጠንቀቁ መዘገባችን ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ እስከ አሁን ባለው መረጃ በድጋፍ እና በተቃውሞ በኩል የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ሰላማዊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ ፓሊስ እንዲሁም የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ የሚሰጥ መረጃ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።
@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94055
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA
Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94055