#Update
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት በይፋ ተመሰረተ።
ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ የመረጠ ሲሆን የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ደጀን በርሀ (ዶ/ር) በከፍተኛ ድምፅ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል።
የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት የማቋቋም ሃሳብ የክልሉ ምክር ቤት የሚያፈርሰው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋምያ ሰነድ ጥር 2015 ዓ.ም ሲፀድቅ የተነሳ ሃሳብ ነው።
ሃሳቡ በድጋፍ እና በተቃውሞ ለሁለት አመታት ያህል ሲናጥ ቆይቶ ዛሬ ጥር 25/2017 ዓ.ም በይፋ ተመስርቶ መሪዎቹ መርጠዋል።
በምስረታ ካውንስሉ መልእክት ያስተላለፉት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ የሚገኙ የኢሮብ እና ኩናማ ብሄረሰቦች የተወከሉበት ካውንስሉ ዘግይቶም ቢሆንም መመስረቱ መልካም ሆኖ አቃፊ ፣ አሳታፊ እና የሃሳብ ብዙህነት የሚንሸራሸሩበት መድረክ መሆን ይገባዋል ብለዋል።
የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተቀመጡት የትግራይ ህዝብ ጥቅሞች በተሻለ እና በአስተማማኝ እንዲመለሱ አጋዥ ሃይል ለማሰባሰብ አልሞ መቋቋሙን የጠቆሙት ፕሬዜዳንቱ " ልዩነቶቻችን በማጠበብ ለተሻለ ነገ በጋራ መስራት ወቅታዊ የትግራይ ጥያቄ ነው " ብለዋል።
የካውንስሉ እድሜ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ መሆኑ ያስረዱት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ይህንን ታሳቢ በማድረግ የትግራይ ፓለቲካዊ ምህዳር ማስፋት እና ለነገ ማመቻቸት ዋነኛ ስራው መሆን እንደሚገባ አክለዋል።
ካውንስሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች መሬት ላይ እንዲወርዱ አጋዥ ሚና ከመጫወት በተጨማሪ የትግራይ ተደማጭነት እና የመደራደር አቅም የሚያጠናክር አቅጣጫ መከተል ይገባዋል ብለዋል ፕሬዜዳንቱ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት ለመምራት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ቃለ ማህላ ፈፅሟል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት መመስረት በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት እና ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ እና ሌሎች ተቃውሞውታል
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94206
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA
Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94206