Telegram Group Search
#ዘመን_ገበያ ምን ጠፍቶ 🤷‍♂️

🛒 ያሻዎትን ያለድካም ባሉበት ይዘዙ፤ በአስተማማኝ የዴሊቨሪ አገልግሎታችን ይዘን ከተፍ እንላለን፡፡

💁‍♂️ ቴሌብር ሱፐርአፕዎ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ላይ ያገኙታል!

📍በክልል ዋና ዋና ከተሞች ጭምር ያገኙናል!

በዘመን ገበያ ግብይትዎን ያዘምኑ!

አጠቃቀም ላይ እገዛ ካሻዎት፡ https://youtu.be/Q0udbA8-o1g


#ZemenGEBEYA
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
" በተመዘገቡበት ቁጥር ቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት ወደሚያገኙበት የ 904 አሰራር ይገባሉ " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደንበኞች የአገልግሎት ጥሪ ማዕከል 905 ከሚሰጠው አገልግሎት በተለየ ቁልፍ ደንበኞች ብሎ ለለያቸው ተጠቃሚዎች 904 የተሰኘ የደንበኞች ጥሪ መቀበያ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አሳውቋል።

የአገልግሎት የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ሃላፊ ወ/ሮ ስምረት በለጠ ይህ አሰራር በሚቀጥለው የ 2018 ዓም የመጀመሪያው ሩብ አመት ወደ ስራ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አዲሱ አሰራር ወደ ስራ ሲገባ በተለመደው የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ከሚያገኙት ደንበኞች በተለየ ቅሬታ በሚያቀርቡበት ወቅት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሚያገኙ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ስምረት ይጀምራል ስላሉት የ 904 አሰራር በዝርዝር ምን አሉ?

" የቁልፍ ደንበኞች መመሪያ አለን አሰራሩም ይፈቅድልናል።

ደንበኞቻችንን ስንከፋፍል የታሪፍ ልዩነት እንዳለን ሁሉ በሚሰጡት አገልግሎት እና የሃይል መጠን እንዲሁም በሚከፍሉት የታሪፍ ክፍያ የተቋማችን ቁልፍ ደንበኞች ብለን እንወስዳቸዋለን።

ቁልፍ ደንበኞች ብለን ለመለየት መስፈርቱ ደንበኛው የሚጠቀመው የሃይል መጠን እና የገዛውን ኤሌክትሪክ ለምንድነው የሚጠቀመው የሚለው ነው።

እነዚህ ደንበኞች ስልክ እና ኢሜላቸው ተመዝግቦ ተቀምጠዋል ቋሚ ቁጥር የለውም ዛሬ አዲስ ቁልፍ ደንበኛ ሲመዘገብ በየቀኑ ቁጥሩ እየጨመረ ይሄዳል።

አገልግሎቱ ሲጀምር በተመዘገቡበት ቁጥር ቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት ወደ ሚያገኘበት የ904 አሰራር ይገባሉ።

የሚሰጡት አገልግሎት ሰፋ ያለ በመሆኑ የእምነት ተቋማት እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት አሰራር ተጠቃሚ ይሆናሉ። 

ትልልቅ ፋብሪካዎች እና ኢንዱስትሪዎችም የእዚህ አሰራር ተጠቃሚ ናቸው።

ይህ አሰራር ሲስተም ይፈልጋል ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየሰራን ነው በ2018 ዓም የመጀመሪያ ሩብ አመት ወደ ስራ እንገባለን ብለን እናስባለን " ብለዋል።

በ905 እየተሰጠ የሚገኘው የደንበኞች የጥሪ ማዕከል አገልግሎት በአሁኑ ሰአት አገልግሎት እየሰጠ ያለው ለአዲስ አበባ ደንበኞች ብቻ ሲሆን የጥሪ ማዕከሉን ሰራተኞች ቁጥር በመጨመር በመላው ሃገሪቱ ለማዳረስ እየተሰራ ነው ተብሏል።

የጥሪ ማዕከሉ በቀን በአማካይ ከ 11 ሺ እስከ 13 ሺ የስልክ ጥሪዎችን ይቀበላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" የአስራ ሁለት አመት ልጄን ነው በወባ በሽታ ያጣሁት " - አቶ ኦስማ አባመረሀባ

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ቆንዳላ ወረዳ ውስጥ ሁለት ህፃናትና አንድ አዋቂ በቱዋምቢ፣ ዲቾ እና ሹራ የተባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በወባ በሽታ ህይወታቸው ማለፉን ነዋሪዎች እና የቤተሰብ አባላት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

የቱዋምቢ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኦስማን አባመረሀባ የ12 ዓመት ልጃቸውን በወባ በሽታ ሰኔ 1ቀን 2017 ዓ.ም ማጣታቸውን ይናገራሉ።

የሚኖሩበት አካባቢ፥ " ቱዋምቢ " ከወረዳው ከተማ  በጣም ሩቅ በመሆኑና መንገዱ አስቸጋሪ በመሆኑ ልጃቸውን በሽታው ሳይጠናበት ቶሎ ወደ ጤና ጣቢያ ባለመውሰዳቸው ህይዎቷ ማለፉን በሀዘን አስረድተዋል።

ሌላው የሹራ አካባቢ ነዋሪ አቶ ስራጅ አሜ በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ የበሽታ ስርጭት ከወትሮው በተለየ ጨምሯል ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይ ከወረዳው ከተማ ርቀት ላይ የምገኙ ቀበሌዎች መንገዱ አስቸጋሪ በመሆኑ ህብረተሰቡ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መድረስ አልቻለም ብለዋል።

በቆንዳላ ወረዳ በወባ በሽታ የሰው ህይወት አልፏል ብለው ነዋሪዎች እና ቤተሰቦች ባነሱት ቅሬታ ላይ ከወረዳው አስተደደር፣ የጤና ፅህፍት ቤት እና ከጤና ተቀማት መረጃውን ለማጣራት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ነገር ግን የቆንዳላ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ካሳሁን ለዶቸበሌ እንደተናገሩት በወረዳው ሹራ እና ሌሎች አካባቢዎች የወባ ስርጭት መጨመሩን ከየአካባቢው ጥቆማ መሰጠቱን ተከትለው የተከሰተው በሽታ ወባ ይሁን ሌላ በሽታ የሚለውን ለመለየት ባለሙያዎች ወደ ቦታ መላካቸውን ተናግረው ነበር።

በተጨማሪም የምዕራብ ወለጋ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ መሰፍን ጣሰው የወባ በሽታ ከክረምት መግባትጋር በተገናኘ ከጤና ጣቢያዎች እየመጡ ያሉ መረጃዎች በበሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ስለመሆኑ አንስተዋል።

በአንድ ሳምንት ውስጥ ከአንድ መቶ እስከ ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰውች  ለበሽታው ተጋልጠው ብለዋል። ነገር ግን በሰዉ ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት መደረሱን በተመለከተ ያሉት ነገር አልነበረም።

ነዋሪዎቹ የጤና ባለሙያዎች ወደ ህብረተሰቡ ተጠግተው አግልግሎት እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
#TikvahEthiopiaFamliyNekemte

@tikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል 8,384 ብር እንዲሆን ተጠይቋል። ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ፡፡ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፥ " ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ተቀጣሪ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ…
" በፔይሮል የሚያገኘውን ብቻ በማሳደድ ሀገር ማሳደግ አይቻልም ! "

የገንዘብ ሚኒስቴር ከሠራተኛ የሚቀነስ ግብርን ጨምሮ ሌሎች የገቢ ጉዳዮችን የሚመለከተውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል ባስደረገው ጥናት በየወሩ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው የትኛው የደሞዝ መጠን ላይ ነው ለሚለው ሦስት አማራጮችን አቅርቧል።

እነዚህም 1,200፣ 1,600፣ ወይስ 2,000 ብር ከሚከፈላቸው ላይ ይሁን የሚሉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ግን ዝቅተኛው ከግብር ነፃ መሆን ያለበት የደሞዝ መጠን 8,300 ብር ነው ብሏል።

የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ " ይህን የገንዘብ መጠን መነሻ ያደረግነው ኢትዮጵያን ጨምሮ ታዳጊ በሚባሉ ሃገራት አንድ ሰው በቀን ከ2.15 የአሜሪካ ዶላር በታች የሚያገኝ ከሆነ ድሃ የሚባል ስለመሆኑ ዓለም አቀፍ ትንተና ያለ በመሆኑን ነው " ብለዋል።

ኮንፌደሬሽኑ መንግሥት ያጠናውና ያቀረበው አማራጭ የደሞዝ ወለል እጅግ ዝቅተኛ ነው የሚል መከራከሪያ አቅርቧል።

ምክንያት ያለውም " ከኑሮ ውድነት እና ከገንዘብ የመግዛት አቅም " አንፃር ነው።

" ለምሳሌ ኬንያ እስከ 24,000 ወርሃዊ ደሞዝ ብር ግብር የማይከፈልበት ነው። ስለዚህ እኛ ደግሞ 24 ሺህውን ትተን እንደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ፣ እንደ ኑሯችን ሁኔታ አገናዝበን በሦስት እጥፍ ወርደን 8,324 ቢሆን የተሻለ ነው የሚል አስተያየት አቅርበናል ለገንዘብ ሚኒስቴር " ብለዋል አቶ ካሣሁን ፌሎ።

በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙላይ ወልዱ ምን አሉ ?

" ይህ የማሻሻያ እርምጃ መንግሥትን በቢሊዮን የሚቆጠር ከፍተኛ ገቢ የሚያሳጣው ነው። ከግብር ነፃ የሚለው መነሻ 2,000 ብር በሚለው አማራጭ ቢፀና እንኳን የሀገሪቱን 0.6 በመቶ ገቢ ይወስዳል " ብለዋል።

ለ2018 ዓ.ም 1.93 ትሪሊዮን ብር የፌዴራል በጀት ተደግፎ መቅረቡን ከሳምንት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ " የልማት ፍላጎታችንን ለማሳካት የሀገር ውስጥ ገቢ ማሳደግ ላይ በከፍተኛ ደረጃ መሥራት ይኖርብናል " ብለው ነበር።

አቶ ካሣሁን ግን ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሠራተኞችን ከግብር ነፃ ማድረግ " ገቢ ያሳጣል " የሚለው ብቻ ሳይሆን " የሠራተኛው ኑሮው መታየት አለበት " በሚል ያቀረቡት አማራጭ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይከራከራሉ።

" ግብር ማስፋት ማለት ግብር መክፈል የሚገባው፣ አቅም ያለውን እሱን ትቶ በፔይሮል የሚያገኘውን ብቻ በማሳደድ ሀገር ማሳደግ አይቻልም " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
" ሁለት ጊዜ በተከፈተ ጥቃት 18 ሰዎች ተገድለዋል " -ነዋሪዎች

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በሱቡ ሶሬ እና ጉቶ ጊዳ ወረዳዎች፣ " የሸኔ ታጣቂዎች ፈጸሙት " በተባለ ጥቃት ቢያንስ 18 ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎችና የሟች ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ ነዋሪ በሰጡን ቃል፣ ሰኔ 9/2017 ዓ/ም እና ግንቦት 27/2017 ዓ/ም " በሸኔ ታጣቂዎች 18 ሰዎች ተገድለዋል። ሟቾቹ የአማራም የኦሮሞም ተወላጆች ናቸው " ብለዋል።

"ጊዮርጊስ የሚባል አንድ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል። በሁለቱም ብሔር ሰዎች ተሰውተዋል" ያሉት እኝሁ አካል፣ "እርሻ ትተናል። ርጭትም ትተናል። መኖር አልቻልንም " ሲሉ አማረዋል።

" ሰሚ ጠፍቶ እንጂ በየቀኑ የሚገደለው እና የሚፈናቀለው ብዙ ነው " ብለው፣ " የሰሞኑን ጥቃት ለየት የሚያደርገው ወደ አርሶአደሩ ከባድ መሳሪያ ነው ሲተኮስ የነበረው። የኦሮሚያ ተወላጆችም አርጆ ከሚባል ቀበሌ ወደ ውኬ ተፈናቅለዋል። ለምን እንደወጡ ስንጠይቃቸው ‘ ወረዳውና ዞኑ ውጡ ’ ብለው ነው " እንዳሏቸው አስረድተዋል።

ሌላኛው ነዋሪም፣ የሟቾች ቁጥር 18 መሆኑን ተናግረው፣ " በሰሞኑ ተጎጂ አንዱ እኔ ነኝ። ያጣሁትም ወንድሜን ነው። ሸኔ ነው መጥቶ ጥቃቱን የፈጸመብን። ብዙ ሰዎች በጥይት ተመትተው ቆስለዋል " ብለዋል።

ከሟቾች ባሻገር አራት ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ፤ የሟች ወንድማቸው የቀብር ሥርዓተ ጃርቶ ቶሌራ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደተፈጸመ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ፣ ከሟቾች ባሻገር ከብቶች እንደተወሰዱባቸው፣ መከላከያ በአካባቢው ደርሶ እንደተመለሰ፣ ታጣቂዎቹ ግን በአካባቢው እንዳሉ፣ አሁንም ስጋት እንዳለባቸው ገልጸው፣ " ለማን አቤት እንበል? እንዴት ሆነንስ ነው የምንኖረው? " ሲሉ ጠይቀዋል።

ታጣቂዎቹ ጎራ ቀበሌ " ሐሙሲት " ፤ " ቦሎ " በሚባል ቦታ ያሉ እንደሆነ ጠቁመዋል።

እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ በወረዳዎቹ የንጹሐን ግድያ መፈጸሙን፣ ከሁለት ሳምንት በፊትም 8 ንጹሓን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን፣ አራቱ የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ ገልጾ፣ " አሁን ላይ በጉቶ ጊዳ ወርዳ ጃርቶ ቶሌራ፣ ፈይሳ፣ አርጆ፣ ሎኮ፣ ሊጎና ወጤ ቀበሌዎች፤ በሱቦ ሱሬ ወረዳም በተለይ ደንገጆ ጉዮ ቀበሌ ዋነኛ የእልቂትና የጥቃት አካባቢዎች ናቸው " ብሏል። 

በአካባቢዎቹ ሰኞ ሰኔ 9/2017 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውንና ቀብራቸውን መፈጸምም ሳይቻል ቀርቶ እንደነበር፣ ግድያውን የተፈጸመው ' ሸኔ ' እንደሆነ፣ በርካታ ንብረትም እንደተዘረፈ ገልጿል።

ፓርቲው በመግለጫው ግድያውን አውግዞ፣ " በሁለቱ ወረዳ ያለው ሕዝብ ከማለቁ በፊት መከላከያው ወደቦታው ይሰማራ፤ ሕዝቡም በሕጋዊ አግባብ ራሱን የሚከላከልበት አማራጭ እንዳይነፈገው ብሎም በዞንና ወረዳ አመራሮች እየተደረገ ያለው ተስማምቶ በኖረ ማኅበረሰብ መሐል በመግባት ማንነትን ማዕከል ያደረገው የእልቂት ጠመቃና ሚዲያ ጭምር በመጠቀም የሚደረጉ መሰል የፍጅት ቅስቀሳዎች ያቁሙ " ሲል አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ 
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ጸደቀ፡፡ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡…
አዋጅ ቁጥር 1387/2017

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ‘ን ለማሻሻል የወጣው ሰሞኑም የፀደቀውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን  በተመለከተ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ምን አለ ?

" ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር ተቋም ያቋቋመችው በ2002 ዓ.ም ነው።

በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቋቁሟል፤ ተልዕኮው ደግሞ ሀገራችን የአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል የሚባለው ምከረሃሳብን መተግበር ከሚጠበቅባቸው ከ200 በላይ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ነው።

የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል 40 ቀጥታ አባል አገራት አሉት፡፡ እንዲሁም ደግሞ  ዘጠኝ  ቀጠናዊ አባል ሀገሮች አሉ።

ከአፍሪካም ሶስት የምስራቅ እና ደቡቡን የሚያካትተው 21 አባል ሀገሮችን የያዘው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካን የያዘው ኢስተርን ኤንድ ሶውዘርን አፍሪካ አንቲ ላውንድሪ ግሩፕ (eastern and southern africa anti money laundry group) ይባላል፡፡

ኢትዮጵያም ከ21 አባል ሀገራት አንዷ ናት።

እነዚህ አባል ሀገራት የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት  ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ 40 ምክረ ሃሳቦችን ይተገብራሉ፤ በየአምስት ዓመቱም የእርስ በእርስ ግምገማ ያካሂዳሉ ያሉት ሶስተኛውም ገምገማ በመጪው ዓመት ይካሄዳል።

እነዚህን ምከረ ሃሳቦች ተግበባራዊ ከምናደርግባቸው ህጎች አንዱ ባለፈው የተሸሻለው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ነው።

የተሸሻለው አዋጅ ኢትዮጵያ ለ12 ዓመታት ስተገለገልበት ቆይታለች። የተሸሻለበት ምክንያት ደግሞ አለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ምክረሃ ሃሰቦቹን እያሻሻለ በመሄዱ ነው።

በዚህም የተሸሻሉ ምከረ ሃሳቦች ስላሉ እነሱን ሊመልስ የሚችል ህግ በማስፈለጉ እና ግብረ ሃይሉም ወንጀሎች እየተለዋወጡ ስለመጡ ሀገራት እነሱን ለመከላከል የሚመጥን የህግ ማዕቀፍ  እንዲኖራቸው ስለሚያዝ ነዉ።

የቀድሞው አዋጅ አመንጪ ወንጀሎችን በዝርዝር አያስቀምጥም ይህም አንዱ የአዋጁ ችግር ነበር " ብሏል።

#MinistryofJustice #FinancialIntelligenceService #ShegerFM

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዋጅ ቁጥር 1387/2017 በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ‘ን ለማሻሻል የወጣው ሰሞኑም የፀደቀውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን  በተመለከተ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ምን አለ ? " ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን…
#UndercoverInvestigation

" ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን አዋጁ አይፈቅድም " - የፍትሕ ሚኒስቴር

የፍትሕ ሚኒስቴር ፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ሰሞኑን በፓላማው የፀደቀውን የተሻሻለ አዋጅ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም " አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም " ብሏል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ምን አለ ?

" አዲሱ አዋጅ ከመደበኛ የወንጀል መርመራ ሂደት የወጣ መንገድን የሚከተል እንደሆነ ሰው ሊረዳው ይገባል።

አዲሱ አዋጅ ልክ በመደበኛው የምርመራ ሂደት እንደሚደረገው ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት መያዣ መያዝ ፣ ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ምስከሮችን መስማት እና መሰል ሂደቶችን አይከተልም።

አዋጁ ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው።

ለምሳሌም፦ መርማሪው አካል ወንጀለኞችን መስሎ ተቀላቅሎ ወይንም አብሮ በመስራት፣ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ በማደር፣ ሲሸጡ ገዢ መስሎ ፣ ሲገዙ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል።

ምርመራውን የሚየካሂደው አካል ምረመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ካገኘ ብቻ ነው።

ፍርድ ቤት በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ ተግባራዊ እንዲደረግ በአሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድ ምርመራው የሚፈጸምበትን ዘዴ ፣ የአተገባበር ሁኔታ ፣ የሚከናወንበትን ጊዜ በትዕዛዙ ላይ በግልጽ ማስቀመጥ እንዳለበት አዋጁ ደንግጓል።

እንደሚባለው አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ እያሰቃዩ አይመረምርም ይህም  ፍጹም ስህተት ነው። በማስገደድ ማስረጃ የሚሰበሰብበትም አይደለም።

መርማሪው ፍርድ ቤት አሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድለት በሽፋን ስር የሚደረግ ልዩ የምርመራ ዘዴን ይተገብራል ሲባል በተጠርጣሪዎች ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ወንጀል ሊፈጽምባቸው ይችላል፤ ወንጀሉን ከፈጸመባቸው በኋላ በወንጀል አይጠየቅም የሚል አይደለም።

ከተጠርጣሪዎች ጋር የወንጀል ተካፋይ ወይም ግብረ-አበር በመሆን በራሱ ፈቃድ አስቦና ፈቅዶ ሳይሆን ፦
- ያለፈቃዱ፣
- ተገዶ፣
- በተጽእኖ፣
- በተጠርጣሪዎች ሕገ ወጥ ትዕዛዝ ወይም ከአቅሙ በላይ በሆነ ማንኛውንም ምክንያት ሌላ ከባድ ጉዳትን ለማስቀረት ወይም የተሰጠውን ሕጋዊ ተልእኮ ለማሳካት ሲል ወንጀል የሚፈጽምበት ሁኔታ ሲኖር ከወንጀል ክስ #ነጻ የሚደረግበትን ሁኔታ ለማመላከት የተደነገገ ድንጋጌ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። " ብሏል።

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ከሰሞኑ መፅደቁ ይታወሳል፡፡

ይህም መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈፅሙ በር ይከፍታል በሚል ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ነበር።

#MinistryofJustice #FinancialIntelligenceService #ShegerFM

@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)

የፎቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ፣ ግራፊክ ዲዛይን እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Photography, Videography, Cinematography, Graphic Design እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ በአንድ ላይ
👉 ፕሮጀክቶችን በስቱዲዮ እና በመስክ በመስራት የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.group-telegram.com/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የ2017 ዓ/ም የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች እየተላከ ይገኛል። ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ውጤት ለተቋማት እየላከ እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋማቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል። ውጤቱ የደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸው ውጤታቸውን በሬጅስትራር በኩል እንዲያዩ መልዕክት እያስተላለፉ ናቸው። ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከልም ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን…
እንኳን ደስ አላችሁ !
Class of 2017 Commencement!

በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።

ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡

ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ!

ምስል፦ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ደምቢ ዶሎ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የመምህራን ጥቅም ባልተከበረበት ሁኔታ ውስጥ ለዚህ በቅተናል። የመምህራን የ17 ወራት ደሞዝ ሳይከፈል ለዛሬዋ ቀን ደርሰናል " - መቐለ ዩኒቨርሲቲ

መቐለ ዩኒቨርስቲ 31ኛ ዙር የምረቃ ስነ ስርዓቱን ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ/ም በሰማዕታት ሀውልት አካሂዷል።

ዩኒቨርስቲው በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፋና ሀጎስ (ዶ/ር)፣ " የመምህራን ጥቅም ባልተከበረበት ሁኔታ ለዚህ በቅተናል " ብለዋል።

" የመምህራን የ17 ወራት ደሞዝ ሳይከፈል ለዛሬዋ ቀን ደርሰናል " ሲሉም አክለዋል።

በመክፈቻ ንግግራቸው፣ " መቐለ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ቢኖርበትም፤ ከመንግስት የተሰጠው ተልዕኮ በላቀ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት በመፈፀም ላይ ይገኛል " ሲሉም ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንቷ፣ " ከጦርነት ወቅት ጠባሳ ያን ሁሉ ተግዳሮት አልፋችሁ ለዚህ የደስታችሁ ቀን ያደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

መቐለ ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች እና ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 2,385 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል በመጀመሪያ የዲግሪ መርሃ ግብር 1,859፣ በሁለተኛ ዲግሪ 509 ተማሪዎች፣ በሦስተኛ ድግሪ ደግሞ 17 ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ከተመራቂዎቹ ውስጥ 600 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው የተባለ ሲሆን፣ በምረቃ መርሃ ግብሩ ከፍተኛ የክልል ባለሥልጣናትና የዩኒቨርስቲው አመራሮች ተገኝተዋል።

በትግራይ ክልል መምህራን የ17 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው በተደጋጋሚ ሲገልጹ የነበረ ሲሆን፣ ይህንኑ ጉዳይ ዩኒቨርሲቲውም በዛሬው የምረቃ መርሃ ግብር ወቅት አንስቶታል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ከአንድ አመት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " በትግራይ ክልል የ17 ወራት የመምህራን ደመወዝ አልተከፈለም። የአምስት ወሩን ክልሉ እከፍላለሁ ብሎ ነበር እስካሁን አልከፈለም " ማለቱ አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2025/06/28 15:55:55
Back to Top
HTML Embed Code: