#SafaricomEthiopia
⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ከፈተና መልስ ዘና ፈታ እንበል! 🥳
በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!
#1wedefit
#Furtheraheadtogethe

TIKVAH-ETHIOPIA
" የጉዞ ታሪክ በሌላቸው ሁለት ታዳጊዎች ላይ የMpox ምልክት መታየቱ ስጋት ፈጥሮብናል " - የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ➡️ " በኮንሶ ዞን የኤም ፖክስ(Mpox) በሽታ ምልክት በሁለት ሰዎች ላይ ታይቶ ናሙና ተወስዶባቸው ዉጤት እየተጠባበቅን ነዉ " - የዞኑ ጤና መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ስለዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) በሽታ ምልክቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች…
#Update
" በሰገን ዙሪያ ወረዳ በሁለት ሰዎች ላይ የታየዉ ምልክት የMpox በሽታ ስላልሆነ ሕብረተሰቡ ከስጋት ነፃ ሆኖ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " - የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ
ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ አማራይታ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሁለት እህታማምች ላይ የታየዉን የሰዉነት ላይ ምልክትን ተከትሎ ሕብረተሰቡ " የኤም ፖክስ በሽታ ሊሆን ይችላል " በሚል ስጋት ዉስጥ መግባቱንና የዞኑ ጤና መምሪያ በበኩሉ ከተጠረጠሩት ሁለት የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ ናሙና ወስዶ ለምርመራ መላኩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳቆ ነበር።
የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ በሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሁሉቱ እህታማሞች የተወሰደዉ ናሙና ዉጤት ከአዲስ አበባ መምጣቱንና በዉጤቱ መሰረት ምልክቱ MPox (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) አለመሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።
አቶ ግርማ ሕብረተሰቡ በሽታዉን መጠንቀቁ አግባብ ቢሆንም ልጆቹንና ቤተሰቦቻቸውን ያገለለበት መንገድ ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።
ዉጤቱን ተከትሎም ስለ በሽታው የግንዛቤ ማስፋትና የጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ልጆቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጉንም አስታውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia

" ወደ 21 የሚሆኑ ሹፈሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል " - የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ የሚከታተል አካል
➡️ " የተገደሉ ሹፌሮች እንዳሉ ሰምቻለሁ፤ በጣም ከፍተኛ ችግር ነው ያጋጠመን በአጠቃላይ በጎንደር መስመር " - የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
አማራ ክልል ከጎንደር መተማ በሚገኘው መንገድ ሹፌሮች በታጣቂዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበርና የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተል አንድ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ የሚከታተለው አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ ከጎንደር መተማ ባለው መንገድ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም " ወደ 21 ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል " ብሏል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል፣ ለጊዜው የደረሰው መረጃ ይህ እንደሆነ፣ የተገደሉት ከጂቡቲ ማዳበሪያ ጭነው የመጡ እና ሌሎች አሽከርካሪዎች መሆናቸውን፣ ጉዳዩን በተጨማሪ አጣርቶ እንደሚገልጽ ጠቁሟል።
ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ/ም አሁን ግድያ ተፈጸመ በተባለበት ቦታ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በታጣቂዎች መቃጠሉንም ገልጿል።
" ይህን ያህል ሰው እየተገደለ ጉዳዩ ትኩረት የማይሰጠው ለምንድን ነው? እኛ ዜጋ አይደለንም ወይ? ከ1500 ኪሎ ሜትር በላይ ማዳበሪያ ጭኖ የመጣን ሹፌር እልል ብሎ ይቀበሉታል እንጁ እንዴት ይገደላል ? " ሲል ይኸው የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ የሚከታተለው አካል በሀዘን ጠይቋል።
ደረሰ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅነው የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር በበኩሉ፣ ከጎንደር መተማ ባለው መንገድ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ አሽከርካሪዎች መገደላቸውን መስማቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ማኀበሩ በሰጠን ቃል፣ " የተገደሉ ሹፌሮች እንዳሉ ሰምቻለሁ። ሁኔታው በጣም አስቸግሮናል፤ ፈተታኝም ሆኖብናል፤ ምን እንደምናደርግ ግራ ገብቶናል፤ በጣም ከፍተኛ ችግር ነው ያጋጠመን በደቡብ ጎንደር፤ በአጠቃላይ በጎንደር መስመር " ሲል ገልጿል።
" በጎጃም መስመር በኩል ያለው እንቅሴቃሴ ከሌሎቹ አንጻር የተሻለ ነው " ሲል የገለጸው ማኀበሩ፣ " የሚከፈል ገንዘብ ካለ እንጂ ግድያ የለም "ብሎ፣ " የሁለቱም ደቡብ ጎንደር፣ ከወሎ ከተወጣ በኋላ ከጋይንት እስከ ሰሜን ጎንደር ድረስ ጫካማ ቦታ ነው፤ ታጣቂዎች ሁለት፣ ሦስት ሆነው ጥቃት ያደርሳሉ " ሲል አስረድቷል።
በተያያዘ ዜና በድሬዳዋ መስመር " ቦርደዴ " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽቱን አንድ አሽከርካሪ በታጣቂዎች ታግቶ እንደተወሰደ፣ ያለበትም እንዳልታወቀ ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
በተለይም የጸጥታ፣ የኬላ፣ የመንገድ ችግሮች ዘርፉን በእጅጉ እንደፈተኑት፣ ለመንግስት አካላትም እንዳሳወቀ የገለጸው ማኀበሩ፣ " ለምሳሌ ኬላ ላይ የሚጠየቅ ክፍያን በተመለከተ የትራንስፓርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አካላት የሚታገትበት ቦታ እየሄዱ በቪዲዮ ቀርጸው በፓርቲ ደረጃ ነው ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ም ባለሃብቶችን ባወያዩበት ወቅት ‘ፍተሻውን እያካሄድን ክፍያው እንዲቀር አብን እንሰራለን’ ብለዋል፤ እንግዲህ ጉዳዩን እዛ ድረስ አድርሰናል " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🚨#Alert
በትግራይ ክልል ላጋጠመ የደን ቃጠሎ የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠየቀ። በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ እንዲደረግ ነው የተጠየቀው።
የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም ለፌደራል የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ቃልአሚን ቀበሌ ሓይለ-ቡሐለ ልዩ ቦታ በሚገኘው የዱስኣ ጥብቅ ደን የእሳት ቃጠሎ አጋጥሟል።
" በዓፋር ክልል ልዩ ቦታ ገረብ ዋሕለ የጀመረው ቃጠሎ በሃይለኛ ንፋስ እየተስፋፋ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል " ብሏል።
" የአከባቢው ማህበረሰብ ቃጠሎው በባህላዊ መንገድ ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል " ያለው ኮሚሽኑ " ባለው ደረቅ የአየር ሁኔታና ሃይለኛ ንፋስ እየተባባሰ የከፋ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው " ሲል ገልጿል።
የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ከአከባቢው ማህበረሰብ አቅም በላይ በመሆኑ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርና የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠይቋል።
የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ለማዋል የፌደራል መንግስት በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ በአስቸኳይ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጠይቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#ሴጅ_ማሰልጠኛ
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)
👉ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 5-18 ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው።
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
👉ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የስልጠናዎቹ ዓይነት፦
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer
☎ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram
Tiktok
Linkedin

" የጓደኞቼ ፉገራ ለተሻለ ስራ አነሳስቶኛል፤ አሁን ላይ በአንድ ማስታወቂያ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ይከፈለኛል " - ወጣት ዳግማዊ
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀዋሳ ከተማ በብስክሌት በላይ የሚደረግ ማስታወቂዎችን ማየት የተለመደ ሆኗል።
ወጣት ዳግም ታምራት ከአምስት ወራት በፊት ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ይጠቀምባት በነበረው አንዲት ብስክሌት ላይ የተወሰኑ የፈጠራ ስራዎችን ጨምሮ የተንቀሳቃሽ የማስታወቂያ ስራ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቋሚነትና በጊዜያዊነት ለ7 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወጣት ዳግም ታምራትን በስራዉ ዙሪያ አነጋግሮታል።
" ስራዉን የጀመርኩት ለራሴ መንቀሳቀሻ እጠቀምበት በነበረዉ ብስክሌት ላይ ተቀጣይ ባለ ሁለት ጎማ ላሜራ በመስራት የራሴን ማስታወቂያ ሰዎች እንዲያነቡት በማድረግ ነበር ፤ ቀስ በቀስም የሰዎችን ትኩረት ማግኘት ሲጀምር ሌሎች ድርጅቶችንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማስታወቂያ ለማሰራት ጥሪ ማቅረብ ጀመሩ " ሲል ገልጿል።
" በአሁኑ ወቅት የብስክሌቶችን ቁጥር ከፍ በማድረግ ለ3 ቋሚና 4 ተጠባባቂ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጥሪያሁ " ያለን ወጣት ዳግም " በቀጣይም በዘርፉ የተለያዩ የማስታወቂያ ስራዎች ላይ ለመሰማራትና በLED ላይት የታገዘ ተንቀሳቃሽ የማስታወቂያ ስራ ለመጀመር ዕቅድ እንዳለዉ " ተናግሯል።
" በሞተር ሳይክል የሚንቀሳቀሱ ጓደኝቼ ' አንተ ምን አለብህ የነዳጅ ወጪ ሰልፍና ዋጋ አያስጨንቅህ፤ ለነገሩ ለጤናህም ስፖርት ነዉ ' እያሉ የሚቀልዱብኝ ቀልድና ፉገራ እንደዉም ለምን ይህን ብስክለት የገቢ ማመንጫ አላደርገዉም የሚል ቁጭት አሳድሮብኝ ብስክሌቴን ወደ ተሻለ ስራ አስገብቻለሁ አሁን ላይ በአንድ ማስታወቂያ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ይከፈለኛል " ሲል ተናግሯል።

" የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ " - ብሔራዊ ባንክ
ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጪ ባንኮች ክፍት ማድረጓን በይፋ አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ለመክፈት የሚያስችለውን መመሪያ አጽድቋል።
ባንኩ፥ መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ወይም "የባንክ ሥራ ፈቃድ፤ የእድሳት መስፈርቶች እና የውክልና ቢሮ መመሪያ " መጽደቁን ነው ያስታወቀው።
በዚህ መመሪያ መሰረትም ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባንኮችን ጨምሮ ሌሎች ስትራቴጂክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል።
ብሔራዊ ባንክ ትላንት ባወጣው መግለጫ ፥ " የኢትዮጵያ የባንክ መስክ ለውጭ ኢንቨስተሮች ተከፍቷል፤ የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ " ሲል አስታውቋል።