Telegram Group Search
🔵🛜 ያለ ዲኮደርና ዲሽ DSTVን በቤትዎ ፋይበር ማጣጣም እንደሚችሉ ሰምተዋል

የሚወዷቸውን የDSTV ቻናሎች በስማርት ቲቪዎ የዲ.ኤስ.ቲቪ ስትሪም መተግበሪያ በመረጡት ጥቅልና የዳታ ፍጥነት DSTVን በቤትዎ ፋይበር ያጣጥሙ።

🎬 #ጎጆ_ጥቅል ከ70 በላይ ተወዳጅ ቻናሎችን በወር ከ929 ብር ጀምሮ!

💁♂️ እስከ 26.5% በሚደርስ ቅናሽ የቀረቡትን የፋይበር ብሮድባንድ እና የዲ.ኤስ.ቲቪ ጥቅሎች ይግዙ፤ በአማራጭ ይዝናኑ።

ℹ️ ስማርት ላልሆኑ ቲቪዎች STB (Set-Top Box) ለማግኘትና አገልግሎቱን ለመጠቀም የአገልግሎት ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ!

👉 ለበለጠ መረጃ: https://bit.ly/የዲኤስቲቪ_ጥቅል

#DSTV
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከጎንደር መተማ በሚወስደው መንገድ በአንድ ቀን ልዩነት በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ላይና በንፁሀን ላይ " ዘግናኝ " ሲል የጠራው ጭፍጨፋ መፈጸሙን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታውቋል።

የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ለጥቃቱ " ፅንፈኛው ቅማንት " ሲል የጠራውን ታጣቂ ኃይል ተጠያቂ አድርጓል።

ዞኑ ሰኔ 19 ባወጣው መግለጫ በቀን ሰኔ 16/2017 ዓ.ም 11:00 ገደማ  ከጎንደር ገንዳ ዉሃ በሚወስደው መንገድ " መቃ " በተባለ ቦታ ጥቃቱ መፈጸሙን ገልጿል።

በቀን 16/10/2017 ዓ/ም ከቀኑ11:30 ገደማ ለአርሶ አደሩ እና በአካባቢው በእርሻ ስራ በኢንቨስትመት ለተሰማሩ የሚከፋፈፍል የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ ተሽከርካሪ እና ሌሎች የህዝብ መጓጓዣዎችን አጅበው የነበሩ  መከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስና የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት እንዲሁም አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎችን " ዘግናኝ በሆነ ጭካኔ ጨፍጭፏቸዋል " ሲል ገልጿል።

" ታጅበዉ እና ማዳበሪያ ጭነዉ ሲመጡ የነበሩ 16 ሹፌሮችን ከመኪና እያስወረደ ዘግናኝ በሆነ ጭካኔ ጨፍጭፏቸዋል። የተወሠኑትንም አግቶ በመውሠድ አድራሻቸውን አጥፍቷል " ሲል መግለጫው ይጠቅሳል።

አክሎሞ " ይህው ታጣቂ ኃይል በቀን 18/10/2017 ዓ/ም ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊታችን አመራሮችና አባላት ላይ አቅዶና ተዘጋጅቶ ድጋሜ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ግጭት አድርጓል " ብሏል።

የዞኑ አስተዳደር " ታቅዶበት የተፈፀመና ዘግናኝ " ብሎ በጠራው በዚህ ጥቃት በመጀመሪያው ቀን የሟቾች ቁጥር 16 ሹፌሮች መሆኑን ሲጠቅስ በሁለተኛው ቀን በተፈፀመው ጥቃት የሟቾችን ቁጥር ከመግለፅ ተቆጥቧል።

በመጀመሪያው ቀን በንፁሃን ላይ ደረሰ ባለው ጥቃት ቁጥራቸውን ያልገለፃቸው ሹፌሮች ታግተው መወሰዳቸውንም አክሏል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡ የአይን እማኝ ግን  ሰኔ 16፤ 2017 ዓ.ም በተፈፀመው ጥቃት የሟቾችን ቁጥር ከመቶ በላይ እንደሚደርስ ተናግረዋል።

ይህዉ የአይን እማኝ እንደሚለው " በእለቱ ከታጣቂ ሀይሉ ጋር መሬት ላይ ሲጨቃጨቁ የነበሩት አድማ ብተና ፖሊስና በFSR መኪና ተጭነው የነበሩ የፀጥታ ሀይሎችን ከጫካ እየወጡ ነው መኪና ላይ እያሉ የጨፈጨፏቸው " ብሏል።

" እነሱን ሲጨርሱ ደግሞ በየመኪናው ባሉ ሹፌሮችና ተሳፋሪዎች ላይ ጥቃቱን ፈፅመዋል" ሲል ገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር " ፅንፈኛ " ሲል የሚጠራውን የቅማንት ታጣቂ ኃይል በአካባቢው ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በንፁሀን ዜጎች ላይ ግድያና እገታ እንደሚፈፅም በመግለጫው አንስቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBD

@tikvahethiopia
#Mekelle

የመቐለ ከተማ የፀጥታ ፅህፈት ቤት የከተማው ፓሊስና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል።

በተካሄደው ውይይት ፦
- ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተገቢና አስተማሪ ባለመሆኑ ምክንያት በፀጥታ ስራ ስጋት እንደፈጠረ

- የተወሰኑ የፀጥታ አካላት የፀጥታ ስራን ከፓለቲካ ጋር የማገናኘት ፣ የመንደርተኝነት አስተሳሳብ ማንፀባረቅ ፣ ራሳቸው የፀጥታ ስጋት መሆን ፤

- ህብረተሰቡን የፀጥታው ባለቤት አለማደረግ አለማሳተፍ እንደሚታይ

- በከተማው በተደጋጋሚ በሚታዩት የግድያ ፣ ስርቆትና የማጭበርበር ወንጀሎች በመቆጣጠር ላይ መሰረታዊ ለውጥ አለማምጣት የሚሉት ተነስተዋል።

በተለይ ከጦርነቱ በኋላ በህዝብና መንግስት መሰረተ ልማቶች የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት ባልተለመደ ሁኔታ መበራከቱ ፓሊስ ገልጿል።

ባለፉት 10 ወራት በ99 የህዝብና የመንግስት መሰረተ ልማቶች ውድመትና ስርቆት መፈፀሙ በማስረጃ አስደግፎ አቅርቧል።

ሰኔ 16/2017 ዓ.ም ለመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ውሃ በሚያቀርበው የገረብ ሰገን ግድብ 2.1 ኪ.ሜ መስመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶ ከ1 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለውሃ ጥም መዳረጉንና አሁን ተጠግኖ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተጠቅሷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ የፀጥታ ስራ ከፓለቲካና ከመንደርተኝነት አስተሳሰብ በፀዳ መንገድ መከናወን እንደሚገባ አፅንኦት ተስጥቶታል።

በክልሉ ያለው የፖለቲካ ቀውስ የፀጥታ ስጋቱን እያባባሰው መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።

መረጃው ከትግራይ ቴሌቪዥን የተገኘ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia        
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ? ➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር…
#NationalExam

ዩኒቨርሲቲዎች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞችን ዛሬ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም መቀበል ጀምረዋል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በወጣው መርሐግብር መሰረት ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ይጀምራል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

Via @TikvahUniversity
" የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ መቀበል ማቆሟን በይፋ ታበስራለች " - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

የ2017 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የሃገር ውስጥ እና የውጭ ሃገራት ባለሥልጣናት በተገኙበት መጀመሩን በልዩ መርሐግብር ይፋ ተደርጓል።

ባለፉት 6 አመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች 40 ቢሊየን በላይ መድረሳቸውን በመድረኩ ተገልጿል።

በዘንድሮ ክረምት የሚተከለውን ጨምሮ እስከሚቀጥለው አመት የአረንጓዴ አሻራ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ድረስ ከ53 ቢሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ ተብሏል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መጀመሩን ያበሰሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) " በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያሳተፈ በአለም ትልቁ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይ (ዶ/ር) ፥ " የአረንጓዴ አሻራ በሚቀጥለው ዓመት 50 ቢሊየን በላይ ችግኞችን በመትከል የሚጠናቀቅ ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።

"በ2011 ዓም የጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የዘንድሮውን ጨምሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን በሚቀጥለው የስምንተኛው ዙር መርሃ ግብር ይጠናቀቃል " ነው ያሉት።

" የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ መቀበል ማቆሟን በይፋ ታበስራለች " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ የመክፈቻ መርሐግብር ላይ በይፋ ተናግረዋል።

በ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ነገ ችግኞችን መትከል በይፋ የሚጀመር ሲሆን በዘንድሮው ዓመት ከ7.5 ቢለየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ ተብሏል።።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሁሉም ዜጋ ከነገ ጀምሮ ወጥቶ ችግኝ እንዲተክል ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ባለፉት 6 ዓመታት ከተተከሉ ከ40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ውስጥ ከ 10 ቢሊየን በላይ (27.5 በመቶ) የሚሆኑት በአባይ ተፋሰስ አካባቢዎች የተተከሉ ናቸው " - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው የ2017 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትርና የአረንጓዴ አሻራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተገኙ ውጤቶችን ይፋ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያዊ በአፈር መሸርሸር ምክንያት ወንዞች በየአመቱ 1.9 ቢሊየን ቶን አፈር ወደ ጎረቤት ሃገራት ይወስዱ ነበር ያሉ ሲሆን ባለፉት ስድስት አመታት ቁጥሩን ወደ 208 ሚሊየን ቶን አፈር ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ከእርሻ መሬቶች በየዓመቱ 130 ቶን ሄክታር በዓመት ይሸረሸር የነበረውም በተመሳሳይ ወደ 54 ቶን ሄክታር በዓመት ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

የደን ሽፋንን በሚመለከትም በ 2011 ዓም ከነበረበት 17.2 በመቶ በ 2016 ዓ.ም ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት። የችግኝ ጣቢያዎችም በ2011 ዓ.ም ከነበሩበት 45 ሺ ወደ 130 ሺህ በላይ ማደጉን ተመላክቷል።

የግብርና ሚኒስትሩ፥ " ባለፉት ስድስት አመታት ከተተከሉ ከ 40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ውስጥ ከ 10 ቢሊየን በላይ ይህም 27.5 በመቶ የሚሆነው በአባይ ተፋሰስ አካባቢዎች የተተከሉ ናቸው " ብለዋል።

በዚህም በአባይ ተፋሰስ አከባቢዎች የነበረውን የደን ሽፋን ከ19 በመቶ በ2024 እ.ኤ.አ ወደ 25 በመቶ ማሳደግ መቻሉን አንስተዋል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የከርሰ ምድር ውሃ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጸዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩም ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው የተናገሩ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 63 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ 40 ቢሊዮን ችግኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል 40 ቢሊዮን ዶላር የአየር ንብረት ፋይናንስ ከሀገር ቤት (Public Finance / Domestic Climate Finance) አዋጥታለች።

ነገ በሚጀመረው የ 2017 ዓም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 7.5 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2025/06/29 17:46:07
Back to Top
HTML Embed Code: