TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም #የአረንጓዴ_አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
#Ethiopia🌱
የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀመረ።
በአጠቃላይ 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዟል።
በዛሬው ዕለት በወንዝ ዳርቻ ልማት አንዱ ክፍል በሆነው በእንጦጦ ዙሪያ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕረዚዳንት ካቲም ሼቲማን ጨምሮ የክልል አመራሮችና ሚኒስትሮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ የሚስማማውን ችግኝ በሚስማማው ቦታ እንዲተከል ጥሪ አቅርበዋል።
የአረንጓዴ አሻራ በቀጣይ አመት ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በስምንት ዙር የችግኝ ተከላ መርኃግብር (የአረንጓዴ አሻራ ሲጠናቀቀ) የተከለቻቸውና የምትተክላቸው ችግኞች አጠቃላይ ብዛት 50 ቢሊዮን እንደሚደርሱ ይጠበቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Tigray
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ኣለም ገ/ዋህድን በምክትል መአርግ የፕሬዜዳንት የፓለቲካዊ ጉዳዮች አማካሪ አድርጎ ሾመ።
ሹመቱ በምርጫ ቦርድ የተሻረው ህወሓት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለውን ቦታ እጅግ ከፍ አድርጎታል።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለው የተፎኳኳሪ ፓርቲዎች ቦታ ከ3 አይበልጥም።
ከሰኔ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) በምክትል ፕሬዜዳንት መአርግ የፓለቲካዊ ጉዳዮች አማካሪ ተደርገው የተሾሙት ኣለም ገ/ዋህድ ፥ ከጦርነቱ በፊት እስከ አምና 2016 ዓ.ም ነሀሴ ተካሂዶ ህገ-ወጥ ነው የተባለው የህወሓት ጉባኤ ድረስ የድርጅቱ የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል።
በተጨማሪ ከጦርነቱ በፊትና በኋላ ከ5ቱ የህወሓት የፓሊት ቢሮ አባላት አንዱ በመሆን ሰርተዋል።
በተካሄደው ጉባኤ ደግሞ ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ ወርደው የህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ 'የተገፉ' ናቸው ተብሎ ሲነገርባቸው ቆይተዋል።
ከያዝነው ወር ጀምሮ ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ማግኘታቸውን ተከትሎ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት በሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በሚመራው ካቢኔ ከፍተኛ ቁጥር የያዘ እንዲሆን አስችሎታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃ. የተ. የግ. ማኅበር
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃ. የተ. የግ. ማኅበር፣ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው ሽልማቶች ውስጥ ስድስተኛ የሆነው ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ፣ በጅማ ከተማ ለዕድለኛ ወጥቷል፡፡
በጅማ ቆጬ ሰፈር ነዋሪ የሆኑት ዕድለኛው አሸናፊ አቶ ዮሐንስ ካሳ፣ ሽልማታቸውን ሰኔ 21 ቀን 2017ዓ.ም. በጅማ ከተማ በተከናወነ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ተረክበዋል፡፡
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃ. የተ. የግ. ማኅበር፣ የፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና ሰቨን አፕ ምርቶቹን በድጋሚ ለገበያ ካቀረበ በኋላ የተለያዩ እና በርካታ አጓጊ ሽልማቶችን ለደንበኞቹ አዘጋጅቶ ዕድለኛ አሸናፊዎችን በአስገራሚና አጓጊ ሽልማቶች በማንበሽበሽ ላይ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
#ሞሐ

እንኳን ደስ አላችሁ ! Class of 2017 Commencement! በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው። ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡ ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡…
#AAU #JIGJIGA #KABRIDAHR
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ።
የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ፦
➡️ 3 ሺህ 334 የመጀመሪያ ዲግሪ፣
➡️ 2 ሺህ 859 የሁለተኛ ዲግሪ፣
➡️ 304 የሦስተኛ ዲግሪ እና 352 የስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ በአጠቃላይ 6 ሺህ 849 ተማሪዎችን አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተገኝተው ነበር።
በሌላ በኩል በዛሬው እለት የጅግጅጋ እና ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከ1,500 በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የመጡ 13 ተማሪዎች ይገኙበታል።
ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከ1,100 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።
እንኳን ደስ አላችሁ !
ፎቶ፦ AAU (FMC)