"ዳግም የመሬት ናዳ ተከስቶ የሰዉ ሕይወት ጠፍቷል ! " - የዞኑ አደጋ ስጋት
➡️ " ባለፈዉ ዓመት ከ5 ሺ በላይ ዘጎች በመሬት ናዳዉ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን የመልሶ ማቋቋሙ ስራ እየተሰራ ቆይቷል! "
የወላይታ ዞን አደጋ ስጋት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ባሳለፍነዉ ዓመት በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ የመሬት ናዳ ተከስቶ ለሰዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ከሆነ በኋላ ስጋት ዉስጥ ናቸዉ ተብለዉ ከተለዩ አከባቢዎች ነዋሪዎች እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በተከለከሉ አከባቢዎች የተወሰኑ ሰዎች ሲንቀሳቀሱ ዳግም ናዳ ተከስቶ የአንድ ሰዉ ሕይወት ማለፉን አስታዉቀዋል።
የካዎ ኮይሻ ወረዳ 12 ቀበሌዎች ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው በመሆኑ ነዋሪዎችን በማስነሳት አባላ አባያ በተባለ ሜዳማ አከባቢ የማስፈር ስራ እየተሰራ መሆኑንና በመጀመሪያው ዙር ለ8 መቶ አባዎራዎች ቤት ተሰርቶ መጠናቀቁን ገልፀዋል።
የወላይታ ዞን አብዛኞቹ ደጋማ አከባቢዎች ለመሬት መንሸራተትና ናዳ ተጋላጭ መሆናቸዉን የሚገልፁት አቶ ዳዊት አምና ሰፋ ያለ ናዳ ያስተናገደው የካዎ ኮይሻ ወረዳ ሙሉ አከባቢዎችን ጨምሮ ፦
- ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ፣
- ኦፋ ወረዳ ፣
- ቦሎሶ ሶሬ እና ቦሎሶ ቦንቤ ወረዳዎች ከፍተኛ ስጋት ካለባቸዉ ቦታዎች የክረምቱን ወቅት ከፍተኛ ስጋት በማያስተናግዱ አከባቢዎች ባሉ የትምህርት፣ የጤናና ሃይማኖታዊ ተቋማት እንዲያሳልፉ የማድረጉ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።
ባሳለፋነዉ ዓመት በተከሰተዉ ናዳ 2,347 አባዎራዎች በአጠቃላይ ከ5 ሺ በላይ ዘጎችች መፈናቀላቸዉን የሚገልፁት የዞኑ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኋላፊ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን ሃብት በማሰባሰብ ዘላቂ መፍትሔ የማሰባሰቡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡፡ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፤ " ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው " የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡…
" በኢ-መደበኛ መንገድ ከሚሰሩት ውጪ 860 የተመዘገቡ የፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች አሉ ይህም ጥቅል ካፒታላቸው 58.8 ቢሊዮን ብር ይገመታል " - ፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ማህበር
ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው " የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ " በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል።
አዋጁ በረቂቅ ሂደት ላይ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በተጠቃሚውም ሆነ በአምራች ማህበረሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱበት ነበር።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ጎማና ፕላስቲክ አምራቾች ማህበር አባሉ በረከት ገ/ህይወት አዋጁን " ጭካኔ የተሞላበት ውሳኔ " ሲሉ ገልጸውታል።
ማህበሩ በራሱ እና በገለልተኛ ቡድን አማካኝነት አሰራሁት ባለው ጥናትም ኢንዱስትሪው በአመት 441 ሺ 228.8 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ኢንዱስትሪ መሆኑን አስረድተዋል።
ማህበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ዝርዝር ሃሳብ ምን አለ ?
" ከአዋጁ ረቀቅ ሂደት ጀምሮ ቅሬታ አለን አንድ አዋጅ ሲረቅ ሊያሳትፋቸው የሚገቡ ባለድርሻ አካላት አሉ በረቂቅ ሂደቱ የፕላስቲክ ውጤት አምራቾችም ሆኑ ማህበራችን እንደማህበር አድሬስ አልተደረገም የአሳታፊነት ውስንነት ችግር ነበረበት።
አዋጁ ካስቀመጣቸው ድንጋጌዎች ውስጥ ሁሉንም ሳይሆን አንዳንድ ድንጋጌዎች በስጋት እና በጥርጣሬ የምንመለከታቸው አሉ።
አዋጁን በንድፈ ሃሳብ ደረጃ አያስፈልግም የቀድሞው አዋጅም መሻሻል የለበትም ነበር የሚል አቋም የለንም ነገር ግን ይህ አዋጅ ከረቂቁ ጀምሮ ባለው ሂደት ውስጥ የሳታቸው መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ።
የመጀመሪያው ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ከግንዛቤ ያላስገባ ነው የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት ከሰላሣ አመት ባልበለጠ ታሪኩ ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ለምርት ይጠቀምባቸው የነበሩ ጥሬ እቃዎች በሙሉ ያስመጣ የነበረው ከውጭ ነው።
አሁን ላይ 90 በመቶ የሚሆነው የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) የሚሰራው በአካባቢያችን ከሚገኙ እና ሌሎች ኢንዱስትሪዎች ከሚያመነጯቸው እንደ የዘይት ጀሪካን እና የኮስሞቲክስ እቃዎች ከመሳሰሉት ደረቅ ቆሻሻዎች ነው።
በዚህ አሰራር መሰረት ፌስታል ከውጭ ይገባ ከነበረበት አሰራር ከማስቀረቱ በተጨማሪ ጥሬ እቃውንም በሃገር ውስጥ መተካት ተችሏል።
በየአካባቢው በርካታ ወጣቶች በመዳበሪያ ላስቲክ እና ጀሪካን እየለቀሙ ለፋብሪካዎች ግብአትነት ያቀርባሉ ይህ አሰራር የላስቲክ ፋብሪካዎች የሚጠቀሙት በሌሎች ፋብሪካዎች ከወጡ ተረፈ ምርቶች በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃ ያበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ሊሰጠው ይገባ ነበር።
በሁለተኛ ደረጃ ተያያዥ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው በአግባቡ ሊጤን ይገባው ነበር።
እኛ ባለን መረጃ እና ገለልተኛ የጥናት ቡድን በሰራው ጥናት መሰረት የፌስታል ምርት ጥቅል ሃገራዊ ኢኮኖሚ ላይ የ 51.6 ቢሊዮን ብር አስተዋጽኦ የሚያደርግ ኢንዱስትሪ ነው።
ከውጭ ይገባ የነበረ ጥሬ እቃንም በመተካት 350 ሚሊየን ዶላር ማዳን ተችሏል።
በሦስተኛነት እዚህ እንዱስትሪ ላይ የተሰማሩ ዜጎች እንዴት ነው እየሰሩ ያሉት ከማይክሮ ፋይናንስ አበዳሪ ድርጅቶች ጋር ያላቸው ትስስርስ እንዴት ነው የሚለው በአግባቡ ሊጤን ይገባው ነበር።
አዋጁ ከጸደቀ በኋላ በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይገልጿል ይሄ አንድን ትልቅ ኢንዱስትሪ አይደለም ማንኛውንም ትንሽ ኢንዱስትሪ ለመዝጋት የሽግግር ጊዜ ያስፈልጋል።
ይህንን አዋጅ በማርቀቅ ሂደት ውስጥ የጎረቤት ሃገራት ልምድ ወስደናል ተብሏል ነገር ግን ይህ ህግ ተግባራዊ ያደረጉ ሃገሮች ከሦስት እስከ አምስት አመት የሽግግር ጊዜ ሰጥተዋል በዛ ኢንዱስትሪ ላይ ለተሰማሩ አካላት ደግሞ ወደፈለጉት ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ ድጋፍ አድርገዋል።
ወደ እኛ ስንመጣ ስድስት ወር የሚባለው ነገር በብዙ መልኩ እኛን የሚያጠፋ ነው።
በስራችን ከ 168 ሺ በላይ ሰራተኞች አሉ እነዚህን ሰራተኞች የስራ ዋስትና የሚያሳጣ ነው።
አዋጁ አንድ ድርጅት ሲዘጋ ሰራተኞቹን በምን ሁኔታ ነው የሚያሰናብተው የሚለውን አላስቀመጠም።
ዛሬ ድረስ ማሽን እየተከሉ ያሉ አምራቾች አሉ በመንገድ ላይ እየመጣ ያለ ማሽነሪ አለ ይህ ሁሉ ከጥቅም ውጪ ይሁን ማለት ፍጹም ጭካኔ የተሞላው ውሳኔ ነው።
ወደ ሃገር ውስጥ በሚገባ የጥሬ እቃ ላይ በሚከፈል ታክስም የፕላስቲክ ኢንዱስትሪው 10 ቢሊዮን የቀጥታ ታክስ አስተዋጽኦ እንዳለው ይታወቃል።
በኢ-መደበኛ መንገድ ከሚሰሩት ውጪ 860 የተመዘገቡ የፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች አሉ ይህም ጥቅል ካፒታላቸው 58.8 ቢሊዮን ብር ይገመታል።
ይህን የሚያህል ሴክተር ከኢኮኖሚው በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ውጣ ስትለው ባለሃብቱን ከፋብሪካ ባለቤትነት በነጋታው ወደ ተመጽዋችነት እንዲሁም በስሩ ያቀፋቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ ስራ አጥነት ማሸጋገር ነው።
በየሰፈሩ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶችን እየለቀሙ ወደ ፋብሪካ የሚያቀርቡ እና ትራንስፖርት የሚሰጡ አሉ ይሄ ጥሬ እቃን መልሶ የመጠቀም ሂደት ላይ አብዛኛውን የምንጠቀመው እኛ ነን በዚህ ሂደትም በአመት 441 ሺ 228.8 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ኢንዱስትሪ ነው።
ስለዚህ በረቂቅ ሂዱቱ ላይ እነዚህን አንኳር ነጥቦች እንዴት አድርጎ ሊመለከታቸው እንደተዘጋጀ ሳያስቀምጥ ለምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ አምራቹንም ሆነ ማህበራችንን እጅግ ያሳዘነ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

ወጋገን ባንክ !
በ4% ጉርሻ ይመንዝሩ! ይቀበሉ!
ከውጭ ሀገር በሃዋላ ድርጅቶች በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከወጋገን ባንክ ሲቀበሉ እና የውጭ ሀገር ገንዘብ ሲመነዝሩ ከዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ ላይ የ4 በመቶ ጉርሻ በማከል ገንዘብዎን በፍጥነት እናስረክብዎታለን፡፡
🔶 ይፍጠኑ የጉርሻው ተቋዳሽ ይሁኑ 🔶
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ ወጋገን ባንክ የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል በ 866 ነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ!
ከስር የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) በመጫን የማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይቀላቀሉ!
𝖩𝗈𝗂𝗇 ➥ Telegram 📲 Facebook
🌍 https://linktr.ee/WegagenBank
📩 [email protected]

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!
አንድ ሲገዙ አንድ ቦነስ!
ዛሬ የቶምቦላን ሎተሪ ቀድመው ለሚገዙ 1000 እድለኞች 1000 የቶምቦላ ሎተሪ በስጦታ ይበረከታል!
በአንድ የቶምቦላ ሎተሪ ትኬት - ህይወት ቀያሪ ዕድሎች በእጅዎ ናቸው!
በ100 ብር ብቻ ቶምቦላ ባለ3 ወይም ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት የግልዎ ይሆናል። ከተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ጋር።
ID-6 እና BYD -SUV የኤሌክትሪክ መኪናዎችም እርስዎን እየጠበቁ ነው። ከተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ጋር።
ቶምቦላ ሎተሪን በ https://www.ethiolottery.et እና በቴሌብር ሱፕር አፕ ላይ ይግዙ፡፡
ለበለጠ መረጃ በ +251977717272 ይደውሉ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቴል አቪቭ ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ቴል አቪቭ የሚደረጉ በረራዎችን እስከ ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማቋረጡን አስታውቋል።
አየር መንገዱ ደንበኞቹ በበረራው መቋረጥ ለሚደርስባቸው እንግልት ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን በጉዳዩ ሰለባ የሆኑ መንገደኞች በአየር መንገዱ የትኬት ቢሮ ወይም በ+251116179900 በመደወል ተጨማሪ እገዛ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል።
በእስራኤል እና ኢራን መካከል ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ሃገራቱ የአየር ክልሎቻቸውን የዘጉ ሲሆን በርካታ አየር መንገዶችም በረራዎችን እየሰረዙ ነው።
Via @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል ” - ጤና ሳይንስ ኮሌጁ
ከተላላፊዎቹ ይልቅ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ህዝቡን ለሞት እያጋለጡት መሆኑን እና በህፃናት የሚስተዋለው የስኳር በሽታ አሳሳቢ ስለመሆኑ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኮሌጁ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር አለሙ ጫሚሶ በገለጹት መሠረት፣ “ድሮ ተላላፊ በሽታዎች ነበሩ፤ አሁን ግን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ናቸው ህዝቡን ለሞትና ለጤና ችግር እያጋለጡት ያሉት”።
ክትባትን ጨምሮ የተለያየ ሥራዎች በመሰራቸው በተላላፊ በሽታዎች የሚያጋጥሙ ሞቶች መቀነስ ትችሎ እንደነበር አስታውሰው፣ “በብዙ ምክንያቶች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል” ብለዋል።
በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተጓዳኝ በሽታ በማምጣት፣ በጤናና በፋይናንስ ጉዳይ በህዝቡ ላይ ጫና መፍጠሩን ገልጸው፣ “ድሮ ታይፎድ፣ ታይፈስ ነበር፤ አሁን ግን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ነው የምናክመው” ነው ያሉት።
“ህፃናት ላይ ስኳርና ካንሰር በጣም በዝቷል። እዛ አካባቢ ያለው ህክምናም ወጪው በጣም ከባድ ነው” ሲሉ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
መንስኤው ምንድን ነው?
ዩኒቨርሲቲው ጥናት አጥንቶ እንደነበር የገለጹት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፣ “በእኛ የተለዩ ነገሮች አሉ፤ የበሽታው ስርጭት ሲዳማ በስድስት ወረዳዎች የግፊትና ስኳር በሽታ ከሌሎቹ ይሰፋል። ለምን? የሚለውን ስናጠና አፈር፣ ውሃ ላይ በተለየ ሁኔታ መጥናት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ” መረዳታቸውን ገልጸዋል።
ከግኝቱ በመነሳት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በጥናቱ መሰረት “32% ደርሷል፤ የግፊት ፕሬቫለንሲ፤ የስኳር ደግሞ 12% ደርሷል። አንዱ በሽታ አንዱን ያመጣል። ግፊትና ስኳር እየበዛ በሄደ ቁጥር የኩላሊት በሽታም እየበዛ ነው” ብለዋል።
ብዙዎች ሳያውቁት ተጠቅተው እየተገኙ በመሆኑ በተለይ የስኳር በሽታን በተመለከተ በየወቅቱ የጤና ምርመራ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሻምፒዮን ሆነ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክን በማሸነፍ የ2017 ዓ.ም የባንኮች የእግር ኳስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ፡፡
ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተደረገውን የፍጻሜ ጨዋታ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አሸንፏል፡፡
መደበኛ ጨዋታው 1 ለ 1 በመጠናቀቁ ግሎባል ባንክ በመለያ ምት አሸንፏል።
በውድድሩ ከ10 በላይ ባንኮች የተወዳደሩ ሲሆን የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ፣ ዘምዘም ባንክ እና ዳሽን ባንክ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን በመከተል ከ2 እስከ 4 ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
የውድድር ዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች የግሎባል ባንክ ተጨዋች ማርቆስ ወልዴ ሲሆን የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪውንም በድጋሚ ማርቆስ ወልዴ ከሌላ ባንክ ተጨዋች ጋር እኩል ጎል በመጋራት ግሎባል ባንክ ድርብ ድል ተቀናጅቷል ።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለመላው የእግር ኳስ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታውን ይገልጻል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

" የኢነርጂ ስርቆት መፈጸሙን ለጠቆመ አካል ጥቆማው ትክከለኛ መሆነና ከተረጋገጠ በኋላ የቅጣት ገንዘቡ ላይ 25 በመቶ ማበረታቻ ክፍያ እንዲከፈለው ይደረጋል " - የኤሌክትሪክ አገልግሎት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 11 ወራት ደንብን በማስከበር ስራዎች የተገኙ ግኝቶች እና አዲሱን የኢነርጂ አጠቃቀም ፣ቆጣሪና ተያያዥ ዕቃዎች ምርመራ መመሪያ ይፋ አድርጓል።
አገልግሎቱ ባለፉት 11 ወራት ብቻ 9,369 ከሃይል ስርቆት፣ ያልተፈቀደ የሃይል ጭነት እንዲሁም ብሬከር መቀየር ጋር የተያያዘ ግኝቶች መመዝገባቸውን ገልጾ ይህም 259 ሚሊየን 608 ሺ 455 ብር ኪሳራ በተቋሙ ላይ እንዳደረሰ ገልጿል።
ይህንን ለመከላከል ያግዛል ያለውን በየደረጃው የሚወሰዱ የቅጣት እርምጃዎች የያዘ መመሪያም ይፋ አድርጓል።
መመሪያው ያስቀመጣቸው የቅጣት እርከኖች ምን ይመስላሉ ?
የኤሌክትሪክ ኃይል ሥርቆት መፈጸሙ ለተረጋገጠበት ደንበኛ
ለመጀመሪያ ጊዜ አስተዳደራዊ ቅጣት:-
ሀ) ለመኖሪያ ቤት ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ ብር 20.000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
ለ) ለጠቅላላ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ, ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
ሐ) ለዝቀተኛ ኢንደስትሪ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)
መ) ለመካከለኛ ኢንደስትሪ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር) የሚቀጣ ይሆናል።
- የኤሌክትሪክ ኃይል ሥርቆት በድጋሚ መፈጸሙ ለተረጋገጠ ደንበኛ በመጀመሪያ ደረጃ እርከን የተገለጹ የቅጣት እርከኖች እንደተጠበቀ ሆኖ አስተዳደራዊ ቅጣቱ ሁለት እጥፍ እንዲከፍል ይደረጋል ተብሏል።
- ከዚህ በተጨማሪ ከመኖሪያ ቤት ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ በቀር ለጠቅላላ ታሪፍ ደንበኛ 1 ሚሊየን ብር፣ ለዝቅተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ታሪፍ ደንበኞች ደግሞ 2 ሚሊየን ብር ተቀማጭ (Security Deposit) ለተቋሙ እንዲያስይዝ ይደረጋል፡፡
የተቋሙ የሽያጭ እና የደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይሄይስ ስዩም " ተቋሙ ተቀማጭ ገንዘብ ማስያዝ ወደ ሚል አሰራር የገፋው ተደጋጋሚ ስርቆት የሚፈጽሙ ደንበኞቹ ታማኝ አይደሉም ተብሎ ስለሚታሰብ ነው " ብለዋል።
- የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት ሲፈጸም አቅርቦቱ በጊዜያዊነት ከምሰሶ ወይም ከአቅርቦት መነሻ ላይ የሚቋረጥ ሆኖ የድርጅቱ የህግ አገልግሎት ፖሊስ ወይም የህግ አካል የምርመራ ሂደቱን ማጠናቀቁን በጹሁፍ እስኪያሳዉቅ እንዲሁም ደንበኛዉ የሚጠበቅበትን ክፍያ እስኪፈፅም እና መተማመኛ የዉል ሰነድ ላይ እስኪፈርም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- እንዲሁም ሲስተም ላይ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የሚቆይ ሆኖ ዉሳኔ ካገኘ በኋለ ቀጣይ እርምጃ ይወሰዳል።
- ከሁለተኛ ጊዜ በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት ለሚፈጽሙ ደንበኞች ደግሞ የተቀመጡት ቅጣቶች እንደተጠበቁ ሆነው አስተዳደራዊ ቅጣቱና ተቀማጩ (Security Deposit) ቀደም ሲል ከከፈለው እጥፍ እየሆነ እንዲሄድ እንደሚደረግ ተቋሙ አሳውቋል።
- ተቀማጭ እንዲሆን የተደረገው ገንዘብ በተመለከተም የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት ፈጽሞና በአሰራር ስርዐቱ መሰረት ተገቢውን መስፈርት አሟልቶ ኃይል የተገናኘለት ደንበኛ ለሁለት አመት በህጋዊ አግባብ መጠቀሙ ሲረጋገጥ ያስያዘው ተቀማጭ(Security Deposit) ገንዘብ እንዲመለስለት ይደረጋል፡፡
- የኢነርጂ ስርቆት መፈጸሙን ለጠቆመ አካል ጥቆማው ትክከለኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ስርቆቱን ከፈፀመው አካል ላይ ያልተከፈለ ኢነርጂ ፍጆታ እና ቅጣት ተሰልቶ የቅጣት ገንዘቡ ላይ 25 በመቶ ማበረታቻ ክፍያ እንዲከፈለው ይደረጋል።
መመሪያው መጽደቁን አገልግሎት በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን ስለ መመሪያው ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቀጣይነት የሚከናወኑ መሆኑን አሳውቋል።

በጋምቤላ ክልል እሁድ ዕለት በታጣቂዎች ግድያ ተፈጽሟል።
በጋምቤላ ክልል አኙዋ ዞን ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለው፣ ከ20 በላይ እንስሳት ደግሞ መዘረፋቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
በአቦቦ ወረዳ፣ ቼቦ መንደር ዘጠኝ በሚባል ቀበሌ፣ እሁድ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ከብቶች ሲጠብቁ የነበሩ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ስማችን አይጠቀስ ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ አራት አስተያየት ሰጪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ተናግረዋል፡፡
ማንነቴ አይጠቀስ ያሉ አንድ የአካባቢው አስተዳደር አመራር አባል የሆኑ ባለስልጣንም ይህን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡
ዘረፋውና ግድያው ሲፈፀም አይተናል ያሉ ሁለት አስተያየት ሰጭዎች፣ የሚሊሻ ልብስ የለበሱና የጊኒወርም ቦርሳ ያነገቱ 8 ታጣቂዎች ከጫካ ወጥተው ከብቶች ሲጠብቁ በነበሩት ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ገልፀዋል፡፡
እነዚሁ ታጣቂዎች ከብቶች ሲጠብቁ የነበሩ ሁለት ሰዎችን ገድለው 20 ከብቶችን ነድተው መውሰዳቸውንም ተናግረዋል፡፡ የሟቾቹ ስም መለሰ ላራጎ እና ዘለቀ ጋቦሬ የሚባል ሲሆን እድሜያቸውም ከ 45 እስከ 50 ባለው ይሆናል ብለዋል፡፡ ጥቃቱ እንደተፈፀመ ወድያውኑ የቀበሌ ምሊሻዎች አካባቢውን መቆጣጠራቸውን ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ባለፈው ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ከብቶችን ለመዝረፍ ጥቃት ፈፅመዋል፣ ከ 100 በላይ ከብቶችንም ወስደዋል ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡ “ከብቶቻችንን ለማስጣል ጥረት አደረግን፣ ተከትለንም ስንሔድ ነበር፣ ሆኖም የታጠቁ ስለሆኑና ወደ እኛ ሲተኩሱ ስለነበር አልተሳካልንም” ሲሉም አክለዋል፡፡ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ችግር ግን አልነበረም ሲሉም ገልፀዋ፡፡
ከዚህ በፊትም እንደዚሁ በአቦቦ ወረዳ መንደር 17 በሚባል ቀበሌ 4 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም፣ የህዝቡ አቤቱታ ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ጥቃቶቹ ሊቆሙ አልቻሉም፣ በየጊዜው የሰው ህይወት እየጠፋ ነው፣ እንስሳትም በብዛት እየተዘረፉ ናቸው ብለዋል፡፡
ጥቃቱን የሚፈፅሙት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ቢሆኑም፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ግን ከደቡብ ሱዳን የመጡ ሀይሎች ናቸው ይሉናል፣ ይህ ግን ልክ አይደለም ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት ጥቃቶች ሲፈፀሙ ለወረዳ፣ ለዞንና ለክልሉ ባለስልጣናት አሳውቀናል፣ ነገር ግን የተወሰደ እረርምጃ የለም፣ ከብቶቻችንንም አላስመለሱልንም ብለዋል፡፡
“ በ1977 ዓ.ም በሰፈራ የመጣን ነዋሪዎች ነን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ እየተፈፀመብን ባለው ተደጋጋሚ ጥቃት ግን ሞት አፋፍ ላይ ቆመን ለመኖር ተገደናል” ብለዋል፡፡ ዕድሜ ልካችንን ያመረትነውን ሀብትና ንብረት በአንድ ቀን ሰብስበው ሲወስዱት ምን ህይወት አለን ? ሲሉም አማርረዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ መኖር ስለምንቸገር፣ መንግስት እንዲደርስልን እንማፀናለን፣ ካልሆነ ግን አካባቢውን ለቀን እንወጣለን በማለትም ገልፀዋል፡፡ ለህይወታችን እየሰጋን ነው የምንኖረው ያሉት ነዋሪዎቹ የጋምቤላ ክልል መንግስት የፀጥታ አካላትና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥበቃ እንዲያደርጉላቸውም ጠይቀዋል፡፡

10% ጉርሻ!
ዛሬ የቶምቦላ ሎተሪ ለሚገዙ እድለኞች 10% ጉርሻ ይበረከታል!
በአዲስ አበባ ባለ 3 ወይም ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የቮልስዋገን ID 6 እና የBYD -SUV የኤሌትሪክ መኪናዎችን እርስዎን እየጠበቁ ነው።
ቶምቦላ ሎተሪን www.ethiolottery.et ፣ በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ ወይም በወረቀት መግዛት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በ+251977717272