4 dynamic content features. 3 unmissable days. 1 unified platform.
Join industry leaders, policymakers and innovators at Big 5 Construct Ethiopia and the East Africa Infrastructure & Water Expo for a high-impact learning experience featuring 20+ CPD-certified sessions and an exclusive summit focused on progress, innovation and sustainability.
• Day 1
East Africa Infrastructure & Water Summit
• Day 2 & Day 3
Big 5 Talks
Infra360
Water360
Secure your seat today. Register for free: https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia
📅 26 to 28 June 2025
📍 Millennium Hall, Addis Ababa

TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " - አቶ አማኒኤል አሰፋ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙበት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል። ዛሬ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም ለሦስተኛ ቀን የተካሄደው…
#Tigray : " ከፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል ውጭ ያለው አማራጭ ተገደን እንጂ ፈቀድን የምንገባው እንዳልሆነ የዓለም ማህበረሰብ ሊገነዘበው ይገባል አሉ " የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት።
ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ዛሬ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም በትግራይ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ የተከበረው የሰማእታት ቀን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዜዳንቱ በመልእክታቸው " የትግራይ ህዝብ ምርጫ ሰላም ነው ጦርነት ተገደን እንጂ ወደን የምንገባው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ብለዋል።
" የትግሉ ሰማእታት በዓመት አንድ ጊዜ የሚታወሱ ሳይሆን የተሰውለት ዓላማ እንዲፈፀም ህዝቡ በሁሉም መስክ ተጠቃሚ በማድረግ ህያው እንዲሆኑ መስራት ይገባል " ብለዋል።
" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት እንዳይፈፀም በፌደራል መንግስት ያለው ዝቅተኛ ፍላጎት ፣ በትግራይ ፓለቲከኞች መካከል ያለው እርስ በርስ ያለመግባባት ምክንያቶች ናቸው " ሲሉ አክለዋል።
ዛሬ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም በመቐለ የሀውልት ሰማእታት በተካሄደው ስነ-ስርዓት ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ(ሌ/ጀነራል) ፣ የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ የሰማእታት ቤተሰቦችና ልሎች የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

Photo
" በተፈናቃዮች ስም የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚካሄደው እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም ተቀባይነት የለውም " - ስምረት ፓርቲ
➡️ " ከ2015 ጀምሮ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ለመመለስ የተደረገውን እንቅስቃሴ ያደናቀፈው ኋላቀሩ ቡድን ነው ! " (የነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድንን ለማለት ነው)
" የፌደራል መንግስት ከፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የተሰረዘውን የህወሓት ቡድን የሚያካሂደው ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ህግና ስርዓት ማስያዝ ይገባዋል " አለ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ።
ስምረት ፓርቲ በተፈናቃዮች ስም የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚካሄደው እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም ተቀባይነት የለውም ሲል አስታውቀዋል።
በእነ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ ይህንን ያለው በትግራይ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ የተከበረው የሰማእታት ቀን በማስመልከት ባወጣው ደርጅታዊ መግለጫ ነው።
ፓርቲው በመግለጫው ከግንቦት 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ለመመለስ የተደረገውን እንቅስቃሴ ያደናቀፈው " ኃላቀር ቡድን " ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ነው ብሏል።
ቡድኑ " ድርጅት ሳይድን የሚመለስ ተፈናቃይ የለም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች የትግራይ መሬት ሸጠዋል " የሚሉና ልሎች በሬ ወለድ ወሬዎች በማስፋፋት የፌደራል መንግስትና ነባሩ ጊዚያዊ አስተዳደር ከግንቦት 2015 ዓ.ም ጀምረው የያዙት እቅድ ሙሉ በሙሉ እንዲደናቀፍ አደርገዋል ሲል ስምረት ህወሓትን ከሷል።
ስምረት ፓርቲ " ቡድኑ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ ይቅርና ህወሓትን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ መሰረዝ መታደግ ያልቻለ አቅመ ቢስና መሰሪ " ሲል የነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓትን አጣጥሎታል።
ስምረት ፤ " ህገ-ወጥ ቡድኑ በቅርቡ ' የህዝብ ድጋፍ አለኝ ' ለማለት በማለም በተፈናቃዮች ስም ያካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የተለመደው ማጭበርበርና ማታለያ እንደሆነ ህዝቡ በሚገባ ሊገነዘበው ይገባል " ብሏል።
" ኋላቀር ቡድኑ ያለፈው ስህተት አልበቃ በሎት አሁንም ሌላ ፓለቲካዊ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል " ያለው ፓርቲው " የትግራይ መሬት በወረራ ከያዘው የኤርትራ መንግስት የጀመረው ያልተቀደሰና ህገ-ወጥ ግንኙት ሌላ ዙር ግጭትና ጦርነት ከመቀስቀስ ያለፈ ውጤት እንደሌለው ሳይታለም የተፈታ ነው " ብሏል።
" ኋላቀር ቡድኑ " ከኤርትራ መንግስት የጀመረውን ህገ-ወጥ ግንኙነት እንዲቆም የፌደራል መንግስት የሚገባውን ሃላፊነት እንዲወጣ የጠየቀው ስምረት " በአገራዊ ህጎች ከማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ የተከለከለ ቡድን ከአፍራሽ ተግባሩ በማቆም ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባል " ሲል አክሏል።
ስምረት ፓርቲ የትግራይ መሰረታዊ ችግሮች እንዲፈቱና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት እንዲተገበር ከፌደራል መንግስትና ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተቀናጅቶ እንደሚሰራ ማስታወቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የፓርቲው መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" በአደጋው በቅርቡ የተመረቀ አንድ ወጣት ሕይወት ሲያልፍ በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል " - ፖሊስ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር ከታርጫ ከተማ ወደ ዋካ በሚወስደው ዋና መንገድ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች ተጋጭተዉ የአንድ ሰዉ ሕይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የዳዉሮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር ብርሃኑ ባይከዳኝ ለቲክቪህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋዉ የተከሰተዉ ዛሬ 7 ሰዓት ገደማ ከዋካ ወደ ታርጫ እና ከታርጫ ወደ ዋካ የሚሄድ ሞተር ሳይክል ቱሪ እና ታርጫ መሃል በተለምዶ " አረቢ " ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ተጋጭተው እንደሆነ ገልጸዋል።
በአደጋው በቅርቡ የተመረቀ የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉን ተናግረዋል።
" የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እና ቅድምያ ያለመሰጣጣት ነዉ " ያሉት ኢንስፔክተር ብርሃኑ " በአደጋው አሽከርካሪውና አንዱ ተሳፋሪ እግራቸዉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ፤ አንደኛዉ ተሳፋሪ ዐይኑ ክፉኛ ተጎድቷል ፤ ተጎጂዎች በታርጫ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው " ሲሉ አስታዉቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

🤲
" በተፈጥሮአዊ ችግሮች እየተፈተንን ብንሆንም ነገር ግን በእምነታችን አንድ ሆነን ለአላህ መጸለያችን መፍትሔ ያመጣል " - ሼህ ኢብራሂም ኢማም
በድሬዳዋ እስቲስቃ ሶላት ተካሄደ።
በድሬዳዋ ከተማ የዝናብ እጥረት ተከስቷል።
ይህን አስመልክቶ ዛሬ ሰኔ 15፣ 2017 ዓ.ም በኢድ ሶላት መስገጃ ስፍራ በርካታ ሙስሊሞች የእስቲስቃ ሶላት አካሂደዋል።
መርሐ ግብሩን ያዘጋጀው የድሬዳዋ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ነው።
በምክር ቤቱ የመስጊድ እና ኡቃፍ ዘርፍ ሀላፊ ሼህ ኢብራሂም ኢማም " በተፈጥሮአዊ ችግሮች እየተፈተንን ብንሆንም ነገር ግን በእምነታችን አንድ ሆነን ለአላህ መጸለያችን መፍትሔ ያመጣል " ብለዋል።
ሼህ ኢብራሂም " እስቲስቃ ሶላት በእስልምና ሐይማኖት ውስጥ ታላቅ መንፈሳዊ ጠቀሜታ ያለው ተግባር ነው። ይህ ፀሎት ዝናብ ለመለመን ብቻ ሳይሆን፣ የማህበረሰባችንን እምነት፣ ተስፋ እና አንድነት ለማጠንከር ያለመ ነው " በማለት ለሙስሊም ማህበረሰቡ ተጨማሪ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ፀሎቱ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር እንዲሁም የእምነት አባቶች በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ተሳትፎ ተካሂዷል።
መረጃው የድሬ ቴሌቪዥን ነው።