Telegram Group Search
#Ethiopia

ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት በቅርቡ ከናይጄሪያው ባለኃብት ዳንጎቴ ጋር እንደምትፈራረም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ ሐምሌ ወር አጋማሽ የስምምነት ፊርማው እንደሚደረግ የገለጹ ሲሆን " በቀጣይ 3 ዓመታት ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ይኖራታል " ሲሉ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

ይህ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በጎዴ አከባቢ እንደሚገባ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የ3 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሆኑን መግለጻቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" የ3 ዓመት ህጻንን ጨምሮ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋድ በግምት 3 ሰዓት ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ሕጻን የሚገኝበት ሲሆን፤ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-78979 ኢት የሆነ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-04273 ኢት ከሆነ ሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ እና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ነው፡፡

አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-77970 ኦሮ ከሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስረድቷል።

ከሟቹቹ መካከል የ3 ዓመት ሕጻን ይገኝበታል።

በሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ላይ የቆመ እና በጉዞ ላይ የነበረ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
" ኃይል ተቋርጧል ! "

አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።

በዋናው የኤሌክትሪክ መስመር /ግሪድ/ ባጋጠመ ቴክኒካል ብልሽት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የተቋረጠውን የኃይል አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበኩሉ በተወሰኑ አካባቢዎች በሲስተም ላይ በተፈጠረ ችግር ከፊል የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ገልጿል።

" አዲስ አበባን ጨምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ያጋጠመውን የኃይል መቋረጥ ለመመለስ የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል፣ የኃይል ማመንጫዎች እና የማከፋፈያ ጣቢያዎች የኦፕሬሽን ሰራተኞች ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ " ነው ያለው።

ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች የተቋረጠው ኃይል እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁም ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኃይል ተቋርጧል ! " አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል። በዋናው የኤሌክትሪክ መስመር /ግሪድ/ ባጋጠመ ቴክኒካል ብልሽት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። የተቋረጠውን የኃይል አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው…
" በተወሰኑ ቦታዎች ኃይል እየተመለሰ ነው " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ በከፊል የተቋረጠው ኃይል በተወሰኑ አካባቢዎች መመለስ እንደጀመረ የኢትዮጵያ ኤሌትክሪክ ኃይል አሳውቋል።

" በተቀሩት አካባቢዎችም በየደረጃው መልሶ ኃይል የማገናኘት ስራ እየተሰራ ነው " ብሏል።

#Update : ሙሉ በሙሉ ኃይል ተመልሷል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

በሳምንታዊ ጥቅሎች ፈታ ብለን ዳታ እንጠቀም! ከጉርሻ የሳፋሪኮም ደቂቃ ጋር 🎁

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!

#1wedefit
#Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
ጦርነቱ ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ይሁን ? 🇮🇷" ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል (የሆርሙዝ መዘጋት) " - ኢራን 🇺🇸" አራን ሰርጡን ብትዘጋ መጥፊያዋ ይሆናል " - አሜሪካ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት የደኅንነት ምክር ቤቱን ውሳኔ እየጠበቀች ነው። የአለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚቀርብበትን የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲዘጋ የኢራን ፓርላማ ሲወስን የደኅንነት ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ…
#Iran #USA

ኢራን በኳታር በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ሰነዘረች።

ኢራን በኳታር አል ኡዴይድ የአየር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን የገለፀች ሲሆን ለአሜሪካ ጥቃት የተሳካ ምላሽ ሰጥቻለሁ ብላለች።

ኳታር የአየር ክልሏን ከጥቃቱ በፊት መዝጋቷን ገልፃ የነበረ ሲሆን ከጥቃቱ በፊት የኢራን ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜክሺያን ምላሽ ሳንሰጥ አንተውምም ብለው ነበር።

ኳታር ጥቃቱን ተከትሎ ሉዓላዊነቴ ተጥሷል ብላለች።

በተጨማሪ ኢራን በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ማዘዣ ላይም ጥቃት ሰንዝራለች።

ኢራን ወደ ኳታር የላከችው የሚሳኤል ቁጥርም አሜሪካ ከጣለችባት የቦምብ ቁጥር እኩል መሆኑን ገልፃለች።

በጥቃቶቹ ስለተባለ ጉዳት የተባለ ነገር የሌለ ሲሆን፤ አሜሪካም የሰጠችው ምላሽ የለም።

#AP

Via @TikvahethMagazine
" አንድ አባት በታጣቂዎች ተገድለዋል። ቤታቸውንም አቃጥለውታል። ሁለቱ ይገደሉ ይኖሩ ገና አልታወቀም " - ዝቋላ አንድነት ገዳም

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም የ " ኦነግ ሸኔ ሠራዊት" ያላቸው ታጣቂዎች፤ " ገዳሙን እናጠፋለን " በሚል እቅድ በተደጋጋሚ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

አርብ ምሽት ተከፈተ ባለው ጥቃት፣ " አንድ አባት በታጣቂዎች ተገድለዋል። ቤታቸውንም አቃጥለውታል። ሁለት አባቶች ይገደሉ ይኖሩ ገና አልታወቀም። የሟቹ ቀብር ዛሬ ከቅዳሴ በኋላ ተፈጽሟል። ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ሠራዊት ናቸው። አስከሬን ስናመጣ በአካባቢው ነበሩ " ሲል ተናግሯል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት በገዳሙ ውስጥ በሚገኝ ዋሻ የሚኖሩ ሁለት መነኮሳት ይሙቱ ይኑሩ እንደማይታወቅ አስረድቶ፤ " በሕይወት ካሉም እሰየው ከሌሉም አስከሬናቸውን እናመጣለን " ብሏል። 

በገዳሙ የተለያዩ ዋሻዎች አምስት አባቶች ከጥቃቱ ማምለጣቸውን የገለጸው ገዳሙ፣ " የታጣቂዎች እቅዳቸው ገዳሙን እናጠፋለን የሚል ነው " ብሎ፣ ሰሞኑንም ጥቃት ለመሰነዘር ያደረጉት ሙከራ ባለመሳካቱ የአሁኑን ጥቃት እንዳደረሱ አስረድቷል።

" ባለፈው ሳምንት የገዳሙን አካባቢ ህዝብ ሰብስበው ‘ወደ ገዳሙ ትመሩናላችሁ’ ብለው፤ አስገድደው ይዘዋቸው በዚህ በሂደት ላይ እያሉ መከላከያ ሠራዊት መጥቶ ከለላ አድርጎ ታጣቂዎቹ ወደ መጡበት ተመልሰው ነበር። በዚያ ቁጭት ነው ይህንን ድርጊት የፈጸሙት " ነው ያለው።

“ እናም እቅዳቸው በዚህ የሚገታ አይደለም ሁኔታው ስላልተመቻቸውና ስላልተሳካላቸው እንጂ ገዳሙን የማጥፋት እቅዳቸው ቋሚ ነው " ብሏል።

ሰሞኑን የተገደሉት አባት በደብረ ሊባኖስና በሌሎች የተለያዩ ገዳማት የኖሩ፣ ከዚያም በዝቋላ ገዳም ሲያገለግሉ ቆይተው ተፈቅዶላቸው ዋሻ የገቡ የበቁ አባት እንደነበሩ፤ በ2016 ዓ/ም አራት አባቶች በታጣቂዎች እንደተገደሉ አስታውሶ፣  "የአሁኑ ሟች ጋር በአጠቃላይ አምስት አባቶች ሰማዕትነት ተቀብለዋል” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍቅረኛዉን በቅናት ተነሳስቶ የገደላት ግለሰብ ማምለጥ እንደማይችል ሲያውቅ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል " - የኮንሶ ዞን ከና ወረዳ ፖሊስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን ከና ወረዳ የገዛ ፍቅረኛዉን በስለት በመዉጋት ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ ከሕግ እንደማያመልጥ ሲገባዉ እጁን ለፖሊስ መስጠቱን የከና ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ገዛኸኝ ካራተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ግለሰቡና…
#Update

" የመምህርት ተዋበች ገዳይ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል " - የኮንሶ ዞን ፖሊስ

በኮንሶ ዞን ኬና ወረዳ ፋሻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮቶላ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ወር በፊት የገዛ ፍቅረኛዉን መምህርት ተዋበች ኩሲያን ሌላ " የፍቅር አጋራ ይዘሻል " በሚል ጥርጣሬ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደላት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዉሎ በተመሰረተበት ከባድ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ በመባል የፍርድ ዉሳኔ እንደተላለፈበት የኮንሶ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን ካማይታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተከሳሹ ወንጀሉን የፈፀመበት ሁኔታ፣ ሰዓት እና የድርጊቱን አሰቃቂነት ዐቃቤ ህግ በሰዉና ኤግዚቢት እንዲሁም የምርመራ ማስረጃ በማቅረቡ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ኩሻቦ ኩራዎ ጥፋተኛ በማለት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የወንጀል ድርጊቱን በተፈፀመበት ወቅት የኬና ወረዳዉ ፖሊስ ምላሽ አካቶ በጉዳዩ ላይ ዘገባ ማቅረቡ አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም " - ኢራን

የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ኢራን በአሜሪካ ለተፈፀሙባት ጥቃቶች " ኃያልና ለድል የሚያበቃትን " ምላሽ መስጠት መጀመሯን ዘገበ።

በመንግሥት የሚመራው ታስኒም የዜና ማሰራጫ እንዳለው የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ በኳታር እና በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሠፈሮች ላይ የሚሳዔል ጥቃቶችን ከፍቷል።

" በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም " ብሏል አብዮታዊ ዘቡ።

ጨምሮም በጥቃቱ ኢራን ለዋይት ሐውስ እና ለአጋሮቿ ያስተላለፈችው መልዕክት " ግልጽ " ነው ብሏል።

ኢራን በሉዓላዊነቷ፣ በግዛት አንድነቷ እና በደኅንነቷ ላይ የተፈፀመባትን ጥቃት በምንም ዓይነት ሁኔታ ዝም ብላ እንደማትመለከትም ገልጿል።

ኢራን ስላጠቃችው በኳታር የአሜሪካ የጦር ሰፈር ምን ይታወቃል ?

- የአሜሪካ ጦር ሰፈር አል ኡዴይድ የሚባል ሲሆን ከዶሃ አቅራቢያ የሚገኝ ነው።

- ይህ የጦር ሰፈር ወደ ስምንት ሺህ የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች የሰፈሩበት ነው።

- በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ የአየር ኃይል ክፍል ዋና መዘዣ ነው።

- አቡ ናኽላ በሚል መጠሪያው በሚታወቀው በዚህ ጦር ሰፈር ውስጥ የብሪታኒያ ወታደሮች እየተፈራረቁ ለአገልግሎት ይቆያሉ።

- በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ረጅሙ የአውሮፕላን መንደርደሪያ ሜዳ ያለው ይህ የጦር ሰፈር በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በኢራቅ ውስጥ ለምታካሂደው ወታደራዊ ተልዕኮ ዋና ማዘዣ እና የአቅርቦት ማዕከል ነው።

- ኳታር አሜሪካ የአል ኡዴይዳ ጦር ሰፈርን እንድትጠቀምበት የፈቀደችው ከ25 ዓመት በፊት ነው።  ሁለቱ አገራት ስምምነት ተፈራርመው ጦር ሰፈሩ በአሜሪካ እጅ ከገባ በኋላ ኳታር በይፋ በግዛቷ ውስጥ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲሰፍሩ ዕውቅና ሰጥታለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ቪድዮ ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኳታር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም " - ኢራን የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ኢራን በአሜሪካ ለተፈፀሙባት ጥቃቶች " ኃያልና ለድል የሚያበቃትን " ምላሽ መስጠት መጀመሯን ዘገበ። በመንግሥት የሚመራው ታስኒም የዜና ማሰራጫ እንዳለው የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ በኳታር እና በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሠፈሮች ላይ የሚሳዔል ጥቃቶችን ከፍቷል። " በአገር ላይ ጥቃት ሲፈፀም ዝም…
" የ12ቱ ቀናት ጦርነት ማብቃቱ ይበሰራል " - ዶናልድ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውን ገለጹ።

" እስራኤል እና ኢራን አሁን የያዟቸውን የመጨረሻ ተልእኮዎች ካጠናቀቁ በኃላ በ6 ሰዓታት ውስጥ  ለ12 ሰዓታት የሚቆይ የተሟላ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል " ብለዋል።

በዚህም ጦርነቱ እንደተጠናቀቀ እንደሚቆጠር ትራምፕ ገልጸዋል።

" ኢራን በስምምነቱ መሰረት ስምምነቱን ተኩስ አቁሙን በይፋ ትጀምራለች " ያሉት ትራምፕ " እስራኤል በ12ኛው ሰዓት ትከተላለች " ብለዋል።

በ24ኛው ሰዓት " የ12 ቀናት ጦርነቱ " ማብቃቱን ለዓለም ህዝብ በይፋ እንደሚበሰር ፤ ሁለቱም ወገኖች ለስምምነቱ መከበር ተከባብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

" ይህ ጦርነት ለዓመታት ሊቆይ መላው መካከለኛውን ምስራቅ ሊያጠፋ ይችል ነበር " ያሉት ዶናልድ ትራምፕ " ግን በፍጹም አልሆነም አይሆንም " ብለዋል።

" አምላክ እስራኤልን ይባርክ፣ አምላክ ኢራንን ይባርክ፣ አምላክ መካከለኛውን ምስራቅን ይባርክ፣  አምላክ አሜሪካን ይባርክ፣ እንዲሁም አምላክ መላው ዓለምን ይባርክ " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
2025/06/27 16:04:45
Back to Top
HTML Embed Code: