Telegram Group Search
በአዲስ አበባ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ለሞት የሚዳርጉ 5 መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?

በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ከፍተኛ የሞት አደጋ የሚያስከትሉ 5 መንገዶች ተለይተዋል።

ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ ተብለው የተለዩት ፦
° መገናኛ፣
° ኃይሌ ጋርመንት፣
° ቦሌ ሚካኤል፣
° ጦር ኃይሎች
° ቻይና ካምፕ መንገዶች ናቸው። በአማካይ በዓመት ከ6 እስከ 13 ዜጎች በእነዚህ መንገዶች በሚደርሱ የተሽከርካሪ አደጋቸው ሕይወታቸውን ያጣሉ።

ከመንገዶቹ አንዳንዶቹ የእግረኛ መተላለፊያ የላቸውም ፤ አሽከርካሪዎች ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ከፍጥነት ወሰን በላይ እያሽከረክሩ አደጋ ያደርሳሉ።

ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በሚደርሰው የትራፊክ አደጋ፣ በአብዛኛው ሕይወታቸውን የሚያጡት ወንዶች ናቸው። መገናኛ አካባቢ አደጋ ከደረሰባቸው 13 ሰዎች አብዛኞቹ ወንዶች መሞተዋል።

አደጋ የሚደርሰው ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በተለይም ሰንበት ወይም የዕረፍት ቀናት ከመንገድ መጨናነቅ ነፃ ስለሚሆኑ፣ ተከትሎ በፍጥነት ማሽከርከር ምክንያት የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነው።

አደጋዎች የሚያሳዩት ተቆጣጣሪ ተቋማትም ሆኑ አደጋ አድራሾችና ተጎጂዎች የሚያደርጉት ጥንቃቄ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው።

ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ከሌሎች የተሽከርካሪ ዓይነቶች አብላጫውን አደጋ የሚያደርሱትም እነሱ ናቸው።

በዓለም የጤና ድርጅት የትራፊክ አደጋ ሥጋት መንስዔዎች ተብለው የተለዩት በፍጥነት ማሽከርከር፣ ጠጥቶ ማሽከረከር፣ የደኅንነት ቀበቶ አለመጠቀምና የራስ ቅል መሸፈኛ አለመጠቀም ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ።

43 በመቶ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረክራሉ። በዚህ ምክንያት ችግሩ ትኩረት ያሻዋል።

በየዓመቱ ከ400 የሚበልጡ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ። የጥናቶች የትኩረት አቅጣጫ የፍጥነት መገደቢያ መጠቀምና ሥር ነቀል የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስገልጋል።   

(የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት መረጃ)

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🚨#Alert

ከደቂቃዎች በፊት ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል።

ንዝሩት በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ተሰምቷል።

ቃላቸውን የላኩልን የቤተሰባች አባላት " ዛሬ በጣም የሚያስፈራ ነበር። ሰሞኑን ድግግሞሹ ቀንሶ ነበር። ዛሬ በድንገት በሚያስፈራ ሁኔታ ነው የተሰማን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🚨#Alert ከደቂቃዎች በፊት ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል። ንዝሩት በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ተሰምቷል። ቃላቸውን የላኩልን የቤተሰባች አባላት " ዛሬ በጣም የሚያስፈራ ነበር። ሰሞኑን ድግግሞሹ ቀንሶ ነበር። ዛሬ በድንገት በሚያስፈራ ሁኔታ ነው የተሰማን " ብለዋል። @tikvahethiopia
#Update

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት (4:38 ላይ) ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 36 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሆነ የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል ገልጿል።

መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 መመዝገቡን አሳውቋል።

በርካታ ሰዎች የዛሬው ከወትሮው የተለየ ነበር ብለዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የነበረበት አካባቢ ያሉ ወገኖች " አስፈሪ " ሲሉ ገልጸዋል።

ንዝረቱ የተሰማባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከወትሮው የተለየ እንደነበር ታውቋል።

ለአብነት አዲስ አበባ ብዙ ሰዎች ህንጻ ላይ የነበሩ ተሰምቷቸው መደናገጣቸውን ገልጸውልናል። ለተወሰኑ ሰከንዶች የቆየ ቢሆንም የህንጻ ንቅናቄ ስሜት ፣ የመንስታወት መርገፍገፍ እንደተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል " 4ኛ ፎቅ ላይ በተቀመጥኩበት መስታወቱ ፣ የቤት እቃዎች ሲነቃነቁ፣ እኔም በተቀመጥኩበት በወትሮ በተለየ ንዝረት ሲሰማኝ ነበር " ብሏል።

ሌላ 12ኛ ፎቅ ላይ የነበረ የቤተሰባችን አባል " ያስፈራ ነበር " ሲል ክስተቱን አስረድቷል።

ከዚህ ባለፈ ንዝረቱ ከተሰባቸው ቦታዎች አንዱ የጅሌ ጥሙጋ አካባቢ ሲሆን የወረዳ አስተዳደር ህንፃ ላይ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በድንጋጤ ከህንጻው መውረዳቸውን ከሰራተኞቹ ለመረዳት ተችሏል።

Photo Credit - Omer Al Faruq

@tikvahethiopa
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ከነገ ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጠጫ መንገዶች ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ ይሆናሉ።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፤ በአዲስ አበባ ከተማ በ2ኛው ዙር ከሚለሙት የኮሪደር መስመሮች መካከል የሲሚት- ጎሮ መንገድ አንደኛው መሆኑ አስታውሷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሲ ኤም ሲ- ፔፕሲ - ጎሮ - መንገድ  ልዩ ቦታው ሳፋሪ መብራት አካባቢ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት አጠገብ የመንገድ ቆረጣ እንደሚከናወን ገልጿል።

ከነገ ጥር 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጠጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆኑ አሳውቋል።

አሽከርከሪዎች ይህንኑ አውቀው አማራጭ መንገዶችን  እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
የብርሃን ቤተሰቦች በመሸለም ላይ  ናቸው!
እርሶም የብርሃን ቤተሰብ በመሆን፤ ውድድሩን ይቀላቀሉ  ተሸላሚ ይሁኑ፡፡

አርብ 4፡00 ሰዓት በቴሌግራም ገፃችን ይጠብቁን
                                      👇👇👇
Telegram Link: https://www.group-telegram.com/berhanbanksc

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Weeklyquiz #questionandanswer #stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል። በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች…
" መንግስታችን እንዳይፈርስ እስከ ሞት ድረስ እንታገላለን ፤የጦርነት ነጋዴዎች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " - አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ

ዛሬ በመቐለ  " እምቢ ለጦርነት እምቢ ለመፈንቅለ መንግስት !! " በሚል መሪ ቃል የሰሞኑን የወታደራዊ አመራሮች መግለጫ የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።

በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

በጊዚያዊ ኣስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ በሰልፉ ላይ ተገኝተው " የሰላም ዋስ የሆነው ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ አይሆንም ፥ የጦርነት ነጋዴዎች ይብቃችሁ " ብለዋል።

" የሻዕብያ ተላላኪዎች አቁሙ !" ሲሉ በምሬት የተናገሩት ከንቲባው " መንግስት ለማፍረስ የተሄደው ርቀት አይሳካም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ ህዝቡም እንዲከበሩ ያግዝ " ብለዋል።

" የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት እንዲተገበር ፣ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዲከበር እና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ  ቁርጠኛ መሆን አለበት " ያሉት ከንቲባው " የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላም ብቻ መሆኑን በማመን ወጣቱ ትግሉ አጠናክሮ ይቀጥል " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ ከመቐለ በተጨማሪ በሌሎችም ከተሞች ጊዚያዊ  አስተዳደሩን ለመደገፍ እና " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው መገለጫ እና ውሳኔና በመቃወም  ወጣቶች በበዙባቸው ሰልፎች  ተካሂደው ነበር።

በዚህም ፦
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የትግራይ ህዝብ ጥቅም በሰላም ብቻ ነው የሚረጋገጠው !
-  ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ !
- የፕሪቶሪያ ስምምነት ይከበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!

የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች ተደምጠዋል።

ትላንትና ዛሬ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የትግራይ ኃይል መኮንኖችን የሚደግፉና የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ የሚገኝ ሲሆን ሰልፎቹ የፖሊስን ክልከላ በጣሰ መንገድ ነው እየተካሄዱ ያሉት።

በህወሓት የፖለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና መከፋፈል ወደ ፀጥታ ኃይል አመራሮች መዛመቱ ህዝቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏል።

ትግራይ ከአስከፊው እና አውዳሚው ጦርነት ገና በቅጡ ሳታገግምና ችግሮች ሳይፈቱ ወደ ሌላ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ሁኔታ እየታየ መሆኑ በርካቶችን አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ አስቸጋሪ ነው። በጣም ብዙ ናቸው እናንተ አንድ ብቻ ስላያችሁ ነው እንጂ ! ” - ኢሰመኮ

የጸጥታ ኃይል ልብስ የለበሰና መሳሪያ የታጠቀ አካል እጁን ወደ ኋላ የፊጢኝ የታሰረን ወጣት ከወደጀርባው በመሆን ጭንቅላቱ ላይ ሲተኩስበት የሚያሳይ ቪዲዮ ከሰሞኑን በማኀበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ድርጊቱ ብዙዎችን ያስለቀሰና ያስቆጣ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ “ እንዲያው እንደዚህ ያጨካከነን ምን ይሆን? ” ሲሉ በሀዘን ስሜት ተውጠው ሲጠይቁ ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበከሉ፣ ድርጊቱ ደርሶት በሰብዓዊ መብት ጥሰት አኳያ ጉዳዩን ዳሶት እንደሆን በሚል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል።

ኮሚሽኑ ይህንን ግፍ የተሞላት ድርጊት ተመልክቶት ይሆን ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ “ ጉዳዩ ደርሶናል። እኛ የራሳችንን ኢንቨስቲጌሽን ስለምንሰራ በቪዲዮው ላይ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል ” የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።

ድርጊቱ የት ? መቼ ? በማን ተፈጸመ ? ለሚለው እካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የሌለ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ “ መቼ ነው የተፈጸመው ? ማነው የሞተውስ ? የሚለውን ዝርዝሩን በሙሉ እያጣራን ነው የምንገኘው ” ሲል ጠቁሟል።

“ ዲጂታሊ ሰርተን ስናበቃም እዚያው የነበሩ የአካባቢው ሰዎችን ደግሞ ማነጋገር ይኖርብናል” ነው ያለው።

ድርጊቱ የተፈጸመበት አካባቢ ታውቋል ? ለሚለው ጥያቄ ኮሚሽኑ በምላሹ፣ “ ፍንጭ አለን ግን አሁን ለሚዲያ መግለጽ አንችልም። ምክንያቱም እርግጠኛ አይደለንም። እሱን እርግጠኛ ስንሆን እንነግራችኋለን ” ብላል።

ስለዚህ አሁን ምርመራው ተጀምሯል ማለት ይቻላል? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ፣ “ ቪዲዮው ደርሶናል። ኢንቨስቲጌት እያደረግን ነው ” ሲል መልሷል ኮሚሽኑ።

እንዲህ አይነት ግልጽ የወጡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶትን በተመለከተ አስተያዬት እንዲሰጥ ጠይቀነው ባስረዳበት አውድ ደግሞ፣ “ አሁን ባለው ሁኔታ እንዲህ አይነት ቪዲዮዎች በብዛት እየወጡ ናቸው ሚዲያ ላይ። እኛ ጋም የሚደርሱ አሉ ” ሲል የድርጊቱን ሁኔታ አስረድቷል።

“ አስቸጋሪ ነው። በጣም ብዙ ናቸው እናንተ አንድ ብቻ ስላያችሁ ነው እንጂ። ስለዚህ ይሄ ቪዲዮ ላይ ብቻ አሁን ላይ ኮመንት ማድረግ አልችልም ” ነው ያለው።

“ በአጠቃላይ አገሪቱ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ለሚለው በየጊዜው የምናወጣቸው ሪፓርቶች አጠቃላይ የሚያሳዩት ገጽታ አለ እሱን መያዝ ነው ” ብሏል።

የሰሞንኛውን ቪዲዮ ምርመራ ሲያልቅ ሙሉ አስተያዬትና ማብራሪያ እንደሚሰጥ ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል የገባ ሲሆን፣ ሁነቱን ተከታትለን በቀጣይ ተጨማሪ መረጃ የምናደረሳችሁ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እስር እና ሰዎችን ወደ መጡበት አገር የመመለስ ሥራ በቁጥር ይጨምራል " - የትራምፕ የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ

በአሜሪካ ሕገወጥ ከተባሉ ስደተኞች ጋር በተያያዘ ከእሑድ ጀምሮ በተጀመረ የአሰሳ ዘመቻ እስካሁን 956 ሰዎች መታሰራቸው ተገለጸ።

ይህም ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር መሆኑን የአገሪቱ የስደተኞች እና የጉምሩክ ተቋም የሆነው ኢሚግሬሽን ኤንድ ከስተምስ ኢንፎርስምነት (አይሲኢ) አስታውቋል።

የፌደራል ተቋማት በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥልጣናቸው እንዲሰፋ መደረጉን ተከትሎ በቺካጎ፣ ኔዋርክ፣ ኒው ጀርዚ እና ማያሚ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞችን የማደኑ ዘመቻ ተካሂዷል።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወደንጀለኞች ያሏቸውን ያልተመዘገቡ ስደተኞችን በጅምላ ወደመጡባቸው አገራት እንደሚመልሱ ቃል ሲገቡ ነበር።

የትራምፕ የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ " ሰነድ አልባ ሰዎች በአሰሳ ወቅት ከተያዙ ወደመጡበት አገር ይመለሳሉ " ብለዋል።

" እስር እና ሰዎችን ወደ መጡበት አገር የመመለስ ሥራ በቁጥር ይጨምራል " ሲሉ ተናግረዋል።

" አሁን ትኩረታችን የሕዝብ ደኅንነት እና የብሔራዊ ደኅንነት ስጋትን ማስወገድ ነው " ብለዋል።

ያለፈው ሳምንት አርብ 538፣ ቅዳሜ 593 እና እሑድ 286 ሰዎች ተይዘዋል። በጆ ባይደን የአራት ዓመታት አስተዳደር ዘመን ከአሜሪካ ተባረው ወደ አገራቸው የተመለሱ 1.5 ሚሊዮን ስደተኞች ናቸው።


መረጃው የቢቢሲ እና ኤቢሲ ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
2025/01/28 07:35:01
Back to Top
HTML Embed Code: