Telegram Group Search
Forwarded from Gashe Tamiru
Forwarded from Gashe Tamiru
እኔም ያምረኛል!🤭!
ማሰብ ቅንጦት በሆነበት በዚህ በዘመነ ጡዘት የማንንም ሀሳብ ሳይሆን የራሴን ሀሳብ የማስብና ሀሳቤን የምኖር ሰው በመሆኔ ታድዬ!!

"እንዲህም ያምረኛል!!
የእራሴ ቀብር ቀን ጥሩንባ ማሰማት ፣
ለቀስተኛው መሀል አብሮ ደረት መምታት ፣
ማንበብ ህይወት ታሪክ ውሸት የሌለበት ፣
ከድንኳን ውስጥ ቆሜ እድርተኛ መጥራት ፣
በእራሴ ቀብር ላይ እንዲህ ይዳዳኛል ፣
ሞቴን ቆሞ ማየት አለቅጥ ያምረኛል ፣
አልቃሽ አሽሟጣጩን ካልታዘብክ ይለኛል ፣
ያሁኑ በሽታዬ እንዲህ ያሰኘኛል ፣
የማያምር ነገር በድንገት ያምረኛል።"
ደራሲ:-አይታወቅም!!

ተመስገን!!
ዋናው መተንፈስ ነው!!
#EnvironmentFirst
#ሰው_መሆን
#ይራስን_ሀሳብማሰብ
#እራስን_የራስንና_የሌላውንማክበር
#ይሉንታናትሁትነት_ቅንነትናአገልጋይነት
#ብሩህ_ዜጋ

#አጋዥ_እረጂና_ሸክምአቅላይ
#Borderless_Volunteerisም
#UBUNTU*
#ቀርክሀ_ወርቅናሐብት_ነው
#ባሕል_ሀብትና_ቅርስነው
#PanAfricanAID-A Renewed Vision
of Connecting The Dots for Convergence, Collaboration and Global Alliances to Serve Humanity and Mother Earth, Peace & Greening Africa as Our Priority!!
*እኔ ሰው የሆንኩት በናንተ ነውና ህመማችሁና ጭንቀታችሁ ህመሜና ጭንቀቴ እንዲሁም ብትብድሉኝና ብታስከፉኝም ደስታችሁና ስኬታችሁ ደስታዬና ስኬቴ-በአፍሪቃ የባንቱ ማሕበረሰብ "I Am Because We Are” ጥበብና እሳቤ!!
አንቺ "ጨው ለራስሽ ብለሽ ጣፍጭ ካልሆነም ድንጋይ ነች ብለው ይጥሉሻል"!!
አንተ ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ ካልሆነም ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሀል!!

ትሁት ፣ ቅንና አገልጋይ ከሆንኩ ለራሴ!!
ሰውን የሚያክል
(በዓምላክ አምሳል የተፈጠረና እኔ የመሰለ እራሴን የሆነ ሰው) የማጉላላ ፣ የማመናጭቅና የምበድል ከሆንኩ ለራሴ!!
ፍትሕ የማጏድልና በሙስና ከተጨማለኩ ለራሴ!!
ዋሾና ቀጣፊ ከሆንኩ ለራሴ!!
ባሴርና ባስመስል ለራሴ!!
ክፉና ንፉግ ከሆንኩ ለራሴ!!
ቂመኛ(ካንሰርና) ተንኮለኛ ከሆንኩ ለራሴ!!
ቅንና ግልፅ ብሆን ለራሴ!!
መልካምና በጎ ከሆንኩ ለራሴ!!
በትህትና የማገለግልና የማካፍል ፣ የማግዝና የማካፍል ከሆንኩ ለራሴ!!
የውስጥ ሰላሜን ፣
ደስታዬንና ፈገግታዬን የማካፍል ከሆነ ለራሴ ፣ ለበለጠ ለውስጥ ሰላሜ ፣ ለእርካታዬና ለጤንነቴ!!

በዚች ሰው ከሆንኩ 23 ዓመታት አጭር ዕድሜዬ ውስጥ የዘራሁትን ሳጭድ አይቻለሁና!!

“ሰው የዘራዉን ያጭዳል።
በአንድ ሀገር የሚኖር ንጉስ ነበር እናም ይህ ንጉስ የአገልጋዮቹን ታማኝነት መፈተን ፈለገ ሶስት አገልጋዮችን ካስጠራ በኋላ አንድ ትዕዛዝ ያዛቸዋል

ጫካ ሄዳችሁ በዚህ ሙሉ ጣፋጭ ፍራፍሬ ለቅማችሁ ይዛችሁ እንድትመጡ እፈልጋለሁ ብሎ ለሶስቱም አንዳንድ ሻንጣ ይሰጣቸዋል።

የመጀመሪያዉ አገልጋይ በጣም ቅን እና ታማኝ ሰዉ ነበረ በደንብ ተጠንቅቆ ምርጥ ምርጥ ፍራፍሬዎችን ለጌታዉ በሻንጣዉ ሙሉ ለቅሞ ይዞ ሄደ፡፡

ሁለተኛዉ አገልጋይ እሱ ደግሞ ቸልተኛ እና ግድ የለሽ ሰዉ ነበር ዝም ብሎ መሬት ላይ ወድቆ ያገኘዉን የተበላሸዉን ያልተበላሸዉን አግበስብሶ በሻንጣዉ ሞልቶ ይዞ ሄደ፡፡

ሶስተኛዉ አገልጋይ እሱ ደግሞ ተንኮለኛ እና አጭበርባሪ ሰዉ ነበር ንጉሱ ይሄን ሻንጣ ከፍቶ አያየዉም ቢያይ እንኩዋን ሻንጣዎቹ ተመሳሳይ ናቸዉ ዬትኛዉ የእኔ እንደሆነ ማንም አያዉቅም ብሎ በሻንጣዉ ሙሉ ቅጠል ሞልቶ ሄደ።

ንጉሱ ሶስቱ አገልጋዮች እስከሚመጡ ጠበቀ እና ሶስቱም ከመጡ በሁዋላ ፖሊሶች ጠራ እና "እነዚህን ሶስት አገልጋዮች ለ አንድ ወር ያህል እስር ቤት አቆዩዋቸዉ ምግብ እንዳሰጡዋቸዉ የሰበሰቡትን እየበሉ ይቆዩ" ብሎ በትዕዛዝ ሰጠ። ፖሊሶቹም እንደታዘዙት አደረጉ።

በታሰሩበት ወቅት ጥሩ ፍራፍሬ የለቀመዉ ጣፋጭ ሲመገብ ከረመ ያግበሰበሰዉ ደግሞ ያንኑ እየበላ ታሞ ከረመ ቅጠል የሰበሰበው ደግሞ ሰዉ ያንን መመገብ ስለማይችል ሞተ።

"ሁሉም ለሰዉ የምንሰጠዉ ነገር ሁሉ ለእራሳችን ነዉ"

ዛሬ ለሰዎች ምን አይነት አገልግሎት ምን አይነት ፍቅር እና ታማኝነት እየሰጠን ነዉ የኛ ነገ እሱ ነዉ።”

ሁላችንን የምናጭደው
የዘራነውን ነውና በየእለቱ የምናስበውን ፣ የምንናገረውንና የምንዘራውን ቃልም ይሁን ተግባር
እንምረጥ!!

ዋናው መተንፈስ ነው!!
#EnvironmentFirst
#ሰው_መሆን
#እራስን_የራስንና_የሌላውንማክበር
#ይሉንታናትሁትነት_ቅንነትናአገልጋይነት
#አጋዥ_እረጂና_ሸክምአቅላይ
#ብሩሕ_ዜጋ
#Borderless_Volunteerisም
#UBUNTU*
#ቀርክሀ_ወርቅናሐብት_ነው
#የግራር_የዝግባ_የወይራ_ከተሞች
#ባሕል_ሀብትና_ቅርስነው
#PanAfricanAID-A Renewed Vision
of Connecting The Dots for Convergence, Collaboration and Global Alliances to Serve Humanity and Mother Earth, Peace & Greening Africa as Our Priority!!
*እኔ ሰው የሆንኩት በናንተ ነውና ህመማችሁና ጭንቀታችሁ ህመሜና ጭንቀቴ እንዲሁም ብትብድሉኝና ብታስከፉኝም ደስታችሁና ስኬታችሁ ደስታዬና ስኬቴ-በአፍሪቃ የባንቱ ማሕበረሰብ "I Am Because We Are” ጥበብና እሳቤ!!
Forwarded from Gashe Tamiru
2025/06/19 04:48:51
Back to Top
HTML Embed Code: