Telegram Group Search
ሥነ-ኪን መቼና የት ተጀመረ?

ሥነ-ኪንን ወይም የኪነትን መቸት በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም የሰው ልጆች በማኅበራዊ የሕይወት መስተጋብር ምክንያት በጣም በቆየ ዘመን በተለይም በቤተ አምልኮዎች እንደተጀመረ ይታመናል፡፡ ሥነ-ኪን (ኪነት) ለምንና እንዴት ተጀመረ፡-

1. ሰዎች የወደዱትን ነገር መውደዳቸውን በተሻለ መንገድ ለመግለጽ በሚጥሩበት ጊዜ፡፡
2. በጥንት ዘመን በተለያዩ የአምልኮ ቦታዎች ያሉ ምእመናን ወይም አማኞች ማለት ማድረግ የሚፈልጉትን (ጸሎታቸውንና አገልግሎታቸውን) በውበትና በተመስጦ ለማቅረብ በሚሞክሩበት ጊዜ፡፡
3. የሰው ልጆች ሕይወትን በተሻለ መንገድ ለመኖር ለማስቀጠል ብሎም ለማሳመር በሚያደረጉት ጥረት፡፡
4. አማልክቶቻችን የሚሏቸውን በሚታዩ በሚጨበጡና በሚዳሰሱ ምስሎች ለመወከል ከመነጨ ፍላጎት፡፡
5. አማልክቶቻችን ናቸው ከሚሏቸው ማግኘት የፈለጉትን ነገር ለማግኘት ጸሎታቸውና ሌላው አገልግሎታቸው በተዋቡ ሥራዎችና በጥዑመ ዜማ ማታጀቡ የአማልክቶቻችንን ልብ ያባብልልናል፣ ያስደስትልናል፣ ፈቃዳችንንም ያስፈጽምልናል፣ ዋጋን ያሰጠናል ከሚል የጸና እምነት ሥነ-ኪንን ወይም ኪነትን ጀመሯት፡፡

ተግባረ ኪን (ኪነት) ምን ምን ጥቅሞች አሏት፡-
1. ሥልጣኔን ትከስታለች፡፡
2. ደስታና ኀዘንን አይረሴ በሆነ መንገድ ትገልጻለች፡፡
3. ባሕልን ትፈጥራለች ትቀርጻለች ከነ እሴቱም ጠብቃ ታቆያለች፡፡
4. ታሪክን በተለያየ መንገድ መዝግባ ለተከታታይ ትውልዶች ታሻግራለች፡፡
5. ለተፈለገው ዓላማ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማለትም ሕዝብን ለማስተማር፣ ለመቀስቀስ፣ ለማነሣሣት የማይተካ ሚናን ትጫዋታለች፡፡
6. መሠላል በመሆን አማኞችን ከአምላክ ጋር ታገናኛለች፡፡
7. የግለሰቦችን ወይም የሕዝብን ሕይወት እራሷን በመግለጥ አዎንታዊ በሆነ መንገድ ትለውጣለች ማለትም ታሳድጋለች ታንጻለች ትገነባለች፡፡
8. መፍትሔንና አቅጣጫን ትጠቁማለች፡፡
9. ጤናማ እና የተረጋጋ ሰብእናን ትገነባለች፡፡
10. በሥራ የደከመን አእምሮ ዘና ታደርጋለች አዲስ ጉልበትንም ትሰጣለች፡፡
11. ኀዘንንና ጭንቀትን ታስረሳለች ታጽናናለች ታረጋጋለች መንፈስን ታድሳለች፡፡
12. ከተለያየ ዓይነት በሽታ ትፈውሳለች፡፡
13. ፍቅርን ትፈጥራለች ታሰማምራለች ታበጃጃለች ታቆነጃጃለች፡፡
14. ጸብንና ክርክርን አርቃ ታስታርቃለች ሰላምን የማስፈን ትልቅ ጉልበት አላት፡፡
15. ቀቢጸ ተስፋን አርቃ በተስፋ ትሞላለች።
16. እንደ ማቅረቢያ መነጽር (Telescope) እና እንደ ማጉያ መነጽር (microscope) ሩቁን አቅርባ፣ ሥውርና ረቂቁን አጉልታና ገልጣ ታሳያለች፡፡
17. በማኅበራዊና እምነተ አሥተዳደራዊ (ፖለቲካዊ) ጉዳዮች ያሉ ጉድፎችን እንደ መስታውት ቁልጭ አድርጋ ታሳያለች፡፡
18. ብሶት መተንፈሻና እንዲደርሰው ለተፈለገው አካል በታማኝነት በሚገባ ታደርሳለች።

በሠዓሊ - አምሳሉ ገ/ኪዳን
Forwarded from Mama Femi
Little try
My drawing
One year's ago
Dear members i think this the best chance for you,just send me your HD photo within 5 minutes and i sketch it🎨
Send it up to 11:30 AM @agezagn
Stay home
Pointer
For the Artist, It is something that Drives him/her to Create & Express an Idea with an Emotional effects to their Audience or themselves.
& For the Audience, It doesn't only Entertain but also gives a lesson, Emotional/psychological satisfaction...
Pen
By Adane
drawn by me
Cartooned by #Adane
2024/10/02 11:15:16
Back to Top
HTML Embed Code: